February 13, 2020
9 mins read

በግርግር አገር ስትመዘበር – ከአባዊርቱ 

ወገኖች ተረጋጉ፣ ቆም ብላችሁ አስተውሉ። በዚህ ፈታኝ ወቅት ቀጥ ያለ የሚመስለው ጠማማ፣ ላይ ላዩን ሲያዩት አገር ወደ ሞት አፋፍ እየከነፈች ያለ ነው የሚመስለው። ይህ ደሞ የሆነው ሆን ተብሎ ነው። እንደዛ እንድናስብ ሌት ተቀን እየተሰራብን ስለሆነ። የኢትዮጵያ ጠላቶች ብዙ ናቸው። እየተናበቡ ነው የሚሰሩት። እየተመካከሩም።  በገንዘብም ፣ በጉልበትም በደንብ እየተደጋገፉ ነው። ይህ የጥፋትና የጽልመት ሀይል ከባድ ጥፋት እያደረሰ ለመሆኑ የሞቱት ወገኖቻችን፣ የወደሙት ንብረቶቻችን፣ የታገቱት ልጆቻችን ህያው ምስክር ናቸው። ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው የአቢይን አስተዳደር ሆን ብሎ ለመስበርና በዚህ ግርግር አገርን ዳግም ለመመዝበር ነው። የዚህ ሁሉ ጥፋት ዘዋሪዎች ደግሞ ያው በዚህ ጉዳይ ለአመታት የተካኑትና የስራ ልምድ ያካበቱት ወያኔዎች ናቸው። አዎ ይዘውሩታል እንጂ በስራቸውና በሚመሩት የጽልመት ብርጌድ ብዙ አማሮች፣ ዖሮሞዎች፣ ሲዳማዎችና ሌሎች አሉበት። ባብላጫው ለዚህ መርዝ ተልእኮ ያልተመቹት ሱማሌዎች፣ ጋሞዎችና ሌሎች የደቡብ ወገኖቻችን ናቸው።
ውድ ኢትዮጵያውያንና ውያት!
ቆም በሉ፣ ሰከን በሉ፣ ለመፈረጅ አትቻኮሉ። ዶር አቢይ ገና መቶ ፐርሰንት ማንዴቱ የላቸውም ለአመታት የጎበጠውን ለማቅናት። ውስጣቸው ያሉት ሰዎች ባብላጫው በደመነፍስ ያሉ ፣ አጥር ላይ ተንጠልጥለው ወዴት እንደሚዘለል እያሰለሰሉ ያሉ ሀሞተቢሶች ናቸው። ድንገት ህውሀት በሚመጣው ምርጫ ይሁን  የጉልበት ቅርጫ በለስ ከቀናው ተሽቀዳድመው እጅ ለመንሳት አሰፍስፈው እየጠበቁ ያሉ ናቸው የሚመስለኝ። ለዚህም ነው መንግስት ስለመኖሩ እስክንጠራጠር ድረስ ላይታቹ እየታመሰ ያለው። ግን ግን ሆን ብሎ ላየው፣ እንደቁጥራችንና እንዳሳለፍነው መከራ ጥልቀት አገሪቱ ጠላቶችዋ እንደጠበቁት አልፈራረሰችም፣ የፈራረሰች ያህል ግን ከፍተኛ የሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደባት ነው። ወገኖቼ ስራ እየተሰራ ነው። አገሪቱ አለምአቀፍ ቢዝነሶችን እያካሄደች በህይወት ያለች፣ ወደፊትም የምትኖር የዋዛ ያይደለች ናት። ዝም ብዬ አስተዋልኩት። አቢይና ጥቂት ደፋር ከየጎሳው የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን መልካም ስራቸውን እየሰሩ ነው። የነዚህን ጥቂት ሰዎች መልካም ስራ ለማጠልሸት ከውስጣቸው ለሆዳቸው ያደሩ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይሰማኛል። የታገቱት ልጆች የዚህ ስራ ውጤት ይመስለኛል። በአቢይ ላይ ከባድ ድራማ እየሰሩባቸው ያለ ይመስለኛል። ለምን? አቢይ እራሳቸው መግለጽ እስኪቸግራቸው ድረስ ልጆቹን ሳይወዱ በግድ እነዛ  ክፉ ዘዋሪዎች ወይም አክራሪዎች የተረከቡዋቸው ይመስለኛል። በቃ ከባድ ጥርጣሬ በሰውዬው ላይ ለመፍጠር የታቀደች ስልት ናት።ወያኔዎቹና አክራሪዎች ይህ ስልት ብቻ ይመስላል የቀራቸው። ፖሊሶችና ምንደኛ መለዮ ለባሾች የጥቅም ተባባሪዎች ብዙ ናቸው። ሰውዬው አላስር፣ አልገድል፣ አላሰቃይ አሏቸዋ። ምን ያድርጉ?  ጓዳቸው ገብተው፣ በገንዘብና ጥቅማጥቅም ደልለው የቅርብ የሚሏቸውን ድረስ ያስኮበለሉ ይመስላል ። አቢይ እንዲህ እንደዋዛ የሚረቱላቸው አልሆኑም እንጅ ። ከባድ ስልተኛ ናቸው። ክፋቱ ባብላጫው አገር ወዳድ የተባለ ሁሉ ስሜታዊ ነው። ላይላዩን ነው የሚጋልበው። ሰከን ብሎ ለምን ይህ ሆነ የሚል የለም። ለመሾምና መሻር መቻኮል ብቻ። አሳዛኝ ዘመን። ታድያ ምን ይሆን መፍትሄው? እንዴት አገራችንን ከጥፋት እንታደጋለን? እስቲ የምክሬን ያህል በነጥብ ላስቀምጥ። ቢረዳም ባይረዳም፣
፩) አስሩ ቦታ እየገባችሁ ወሬ አትቀላውጡ። ካነበባችሁ ወይም ከሰማችሁ በሁዋላ ደግም የወሬውን መሰረትና ፍሬ ነገር ገምግሙ። ስሜታችሁን ከነካው ነገር አለና ሼር ከማድረጋችሁ በፊት በደንብ መርምሩ። ጁዋር የተባለው ምንደኛ በወያኔ ዘመን የፈዘዙና የነፈዙ ልጆቻችንን አይምሮ በስሜት እየነካካ ነው ጉድ እያደረገን ያለው።
፪) ሌላው እጅግ የሚደንቀኝ እንደምን አድርገው አቢይ አህመድ የ መቶ ሚሊዮን ህዝብ በነፍስ ወከፍ እምባ አባሽ እንደሚሆኑ ነው። ሰውዬው ጓዳም እራሳችሁን እያስገባችሁ ተረዱላቸው እንጅ። ባለፈውም ደቡብ ላይ ይህንኑም ብለዋል።
፫) ከዚህ ቀደምም ብያለሁ፣ አሁንም ልድገመው። ይህን ምርጫ ስጋ እንዳየች ቀበሮ አድፍጠው የሚጠብቁት ወያኔዎቹና በስራቸው የሚዘወሩት አክራርያን ናቸው። ይህን ምርጫ “በሞተ ” ህገመንግስት አሳቦ ቀኑን ማስተላለፍ አይቻልም የሚሉት ጫወታ አይገባኝም በበኩሌ። በቅርብ አቶ ልደቱና ዶር ኦባንግም ይተላለፍ እያሉ ነው። መፍትሄው እነ ኢዜማን ሌሎችንም ጨምሮ ፔቲሺን ማድረግ ነው ምርጫ ቦርድን።ማንን ለመጥቀም ነው ምርጫው?ደሞስ ምን ፖሊሲ ሰማንና ነው ምርጫው? እነብልጽግናን እንዲወስኑ ተጠብቆ እንደሆነ ህዝቡ ገና ምን እንደሚፈልግም የገባው አይመስልም ።
፬) የፖለቲካ ድለላን መና ማስቀረት። እንዴት? የነ መረራ፣ በቀለን ከጁዋር ጥምረት ዎንኛ ምክንያት ማጋለጥ። እዚህ ላይ ብልጽግናዎች ብዙ ይቀራችሁዎል። በቅርብ ጀግናው ታዬ ደንደአ እንዳደረገው ሌሎችም በብርቱ ታገሉ እንጅ ። አንድ ታዬ ብቻ እንዴት ብቻውን ይፍጨረጨራል? ሌሎችም በብልጽግናው የታቀፋችሁ እህትና ወንድማማቾች ዝም አትበሉ እንጅ ። ይህ ጁዋር የተባለው ጠንቅነቱ ለኦፒዲ ብቻ መስሏችሁ ከሆነ ተሸውዳችሁዋል።ምንም እንኳ ምኞቱ አማሮችንና ዖሮሞዎችን ለማባላት ቢሆንም ዳፋው ለአገር ነውና በህብረት ይሁን በተናጠል አጥብቃችሁ መታገያ ጊዜው አሁን ነው። ሁዋላ መቆምያው ይቸግራል ይህ ጉዳይ በጊዜ ካልተመከተ።
ፈጣሪ በቃችሁ ብሎ አገራችንና ህዝባችንን ከክፉ ይጠብቅልን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop