“በሣዑዲ ዐረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመዉ ዘግናኝ እና አረመኔአዊ ተግባር የወያኔ የግፍ አገዛዝ ውጤት ነዉ” – ሞረሽ
ወደአረቡ ዓለም በስደት በሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ እና በ21ኛው ክፍለ-ዘመን ይፈፀማሉ ተብለው የማይታሰቡ ግፎች መፈፀም ከጀመሩ ከሃያ ዓመታት የማያንስ ጊዜ አስቆጥረዋል። በተለይ ግን ሰሞኑን በሣዑዲ ዐረቢያ በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እህት ወንድሞቻችን ላይ