አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ አንድ – ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም /ጥቅምት 2006

ወያኔና የነፖሊቲካ አጋሮቹ የሚያደርጉትን ለእነሱ የሚመች አከፋፈል ትተን አበሻን ለሁለት እንክፈለው፤ ሆድ ያለውና ሆድ የሌለው፤ ወይም የሚበላና የማይበላ፤ ዛሬ የምናገረው ሆድ ስላለው ወይም ስለሚበላው አበሻ ነው፤ አታውቁት እንደሆነ ተዋወቁት፤ በአጠቃላይ ስንመለከተው ግን የአበሻ ፍቅርም ሆነ ጠብ ለሆድ ነው፤ አበሻን የሚያጣላው፣ የሚያነታርከው፣ የሚያቧጭቀው የሆድ ነገር ነው፤ ለመብላት ነው፤ አንዳንዴም ሎሌውን ለማብላት ነው፤ ግብር ለማግባት ነው።

አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል፤ እስቲ በመጀመሪያ ስለምግብ እንነጋገር።

በሌላው ነገር ሁሉ ኋላ-ቀር ቢሆንም በምግብ ጉዳይ አበሻን የመበልጠው ያለ አይመስለኝም፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምግብ ውድድር ቢያደርጉ በምግብ ዓይነት፣ በጣዕም፣ በአሠራሩ ጥበብ አበሻ በቀላሉ እንደሚያሸንፍ በፍጹም አልጠራጠርም፤ የቱ አገር ነው ወዝ ያለውና ለስላሳ እንጀራ ያለው? በነጭ ጤፍ በሠርገኛው፣ በጥቁር ጤፍ፣ በስንዴውና በገብሱ፣ በማሽላውና በዘንጋዳው፣ በበቆሎው በእጅ ለመጠቅለል፣ በጉሮሮ ለማውረድ እንደአበሻ አመቻችቶ የሚሠራ የቱ ሕዝብ ነው? እንጀራው ሲፈለግ ቃተኛ፣ ሲፈለግ አነባበሮ እየሆነ በቅቤና በአዋዜ ርሶ ሆድ የሚያርስ ምግብ ማን ይሠራል፣ ከአበሻ በቀር?

የዳቦው ዓይነትስ ቢሆን ብዛቱና ጣዕሙ! ድፎው፣ የዶሮ ዳቦው፣ አምባሻው፣ ሙልሙሉ፣ ቂጣውስ ቢሆን ስንት ዓይነት ነው?

አበሻ ከጥንትም ጀምሮ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ ስለዚህም ይጾማል፤ ለእግዚአብሔር ሲል፣ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ሲል ከወዳጁ ከምግብ፣ በተለይም ከሥጋና ከቅቤ ይለያል፤ መጾም ዓላማው ለነፍስ ቢሆንም ለሥጋም ትልቅ ጠቀሜታ አለው፤ በአካል ውስጥ የተጠራቀመውን ጮማና ሞራ ለማራገፍ ይረዳል፤ አበሻ ግን ምኑ ሞኝ ነው፤ በሆድ ቀልድ የለም! የጾም ምግብ የሚባል ነገር ፈጥሮ ሆዱን ያስደስተዋል፤ ሥጋና ቅቤ ቀረብኝ ብሎ እንዳይጠወልግ ተቆጥሮ ብዛቱ የማይታወቅ ዓይነት የጾም ወጥ አለው፤ ስንት ዓይነት የአትክልት ምግብ፣ በዚያ ላይ ሹሮው፣ ክኩ፣ ስልጆው፣ ተልባው፣ ሱፉ፣ የሽምብራ ዓሣው፣ አዚፋው፣ ስንቱ ይቆጠራል!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጉዞአችን ወዴት ነው?( ሉሉ ከበደ)

ጾሙ ያልፍና ፍስኩ ሲመጣ አበሻ ፊቱን ከአትክልት ዓለም ወደእንስሳት ዓለም ያዞራል፤ ከዶሮ ጀምሮ እስከበሬው ኡኡ እያለ ለእርድ ይሰለፋል፤ የዶሮው ወጥ፣ የበጉ ወጥና አልጫው፣ ቅቅሉ፣ ምንቸት አብሹ፣ ክትፎው፣ ጥብሱ፣ ዱለቱ፣ ጥሬ ሥጋው፣ ምኑ ቅጡ!

የአበሻ ምግብ በዚህ ብቻ አይቆምም፤ አንዳንድ አበሻን የማያውቁ ሰዎች አበሻ ፍቅር አያውቅም ይላሉ፤ አበሻ ሌላ ቀርቶ በምግብም ፍቅሩን ይገልጻል፤ የመዝናኛና የፍቅር ምግብም አለ፤ እነቅንጬ፣ እነጨጨብሳ፣ እነግፍልፍል እዚህ ውስጥ የሚመደቡ ናቸው።

አበሻ የመንገድ ምግብም አለው፤ አገልግሉ፣ ቋንጣው፣ በሶው፣ ጭኮው፣ ጭኮው፣ የቡና ቁርስ እያለ ቆሎውን፣ ንፍሮውን፣ በቅቤና በአዋዜ የራሰ ቂጣውን፣ አነባበሮውን፣ አሹቁን ይከሰክሳል፤ አበሻ ከተመቸው መቼ ነው ከመብላት የሚያርፈው? የቱ አገር ነው በዚህ ሁሉ ምግብ ተወዳድሮ አበሻን ማሸነፍ የሚችለው?

አበሻ ምግብ ስለሚወድ የሚያስበላው ነገርም ይወዳል፤ ቃሪያን መብላት ልዩ ጥበብ ያደረገው ለዚህ ነው፤ ቂሉ ፈረንጅ አፐረቲቭ እያለ (ከሣቴ ከርስ መሆኑ ነው፤) አንጀቱን የሚጠብሰውን አረቄ ይጠጣል፤ በቅመማቅመምና በድልህ የተቁላላውን ወጥ በእንጀራ እየጠቀለለ ቢጎርስ እያላበው ይበላ ነበር!

የአበሻ ምግብ የሚበላው ወገን በፈረንጅ አገር ሲኖር አገሬ የሚለውና የሚናፍቀው የአበሻ ምግብ ነው! ስለዚህም በሄደበት የአበሻ ምግብ አይለየውም! አበሻ ሆዱን ትቶ አይሰደድም! እንዴት ብሎ!

17 Comments

  1. yEH PROFESSER YESHALAL FELSEFENAW BAYREBAM KENEZA BERGER EYEBELU tAXI EYENEDU NERSING HOM EYETEREGU yE eTHIOPIAN HIZB WEDE GEDEL YEMIMERUT pROF MESFIN JEGNA NEW EYETASERE EYETEFETA YETAGELAL

  2. algebagnem meliktu!?
    Mendin new addisu neger?
    Abesha abesha abesha yemiut neger gin betam annoying new. Abezut!!!!

  3. ምናልባት እኔ እንደገባኝ ለማለት የፈለጉት በማይሆን ነገር ላይ ለሆዱ ሲል ሞራሉ ን ይሸጣል ነዉ። በዚህ ጉዳይ ላይ እንኩዋን ባህሪው ከሌሎች አገሮች የተለየ አይለይም።
    የኛ ባህሪ፣ወይ በደንብ እንጠግባለን ወይ በደንብ እንራባለን ወይ በፍጥነት እንሮጣለን ወይ ቁጭ እንላለን፣ ወይ በትምህርት ጎበዝ ን ወይ ሰነፍ ነን።
    ለምግብ ከብደት የምንሰጠውን ያህል ለሽንት ቤት አንሰጥም ወይም ለአካባቢ ንፅህና ወይ ለመናፈሻ ቦታ።
    ከድህነት የተነሳ በትንሽ ጥቅም ብዙ ሀገር የሚጎዳ ነገር ሊፈፀም ይችላል።
    የህዝባችንን የስራ ሞራል የገደለው ግን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው።ወደ ድህነት ከመራ በሁዋላ የምግ ጥገኛ በማድረግ የፓለቲካ ተፅእኖ ለማሳደር የታለመ ነው።

  4. አይ ፕሮፌሰር አሁን የኛ ህዝብ ይበላል ነው ያሉት? ለነገሩ ነጩ ህዝብን በደንብ ያውቁታል ብዬ አስባለሁ። እነርሱ አፋቸው ከእህል ተለያይቶ ይውላል እንዴ! እኛ ምግብን እንበላለን አዎ ግና እነርሱ ደግሞ ይበሉታል የሚለው ቃል አይመጥናቸውም ፤ ይጠጡታል እንጂ!

  5. It is a creative and entertaining article. I read it with interest. It is not an insult on Habesha. Don’t take it at face value.

  6. For some reason the professor seems angry at all Ethiopians.
    I respectfully disagree with his thinking on this one.

  7. Very true.
    All politician leaders are doing their best for better food. What they speak is their mask. They always go apart to hunt for food.

  8. Hodam nachihu alun migib betefabet
    hode ader binibal ahun min alebet
    demoz tekebilen sileminbelanet.

  9. Ewenet belewal….lehod yelemedewen le’chenkelatu demo adis eweqeten beyaregew eseyew neber…gen yezot yetesededew hod be’sew hager ye’Zombie honebenen techegeren…gashey!!! Because of insecurity I have been using public domain and the desk top is short of Amharic Fonts to install.
    Qetayun eskeyasenebebun tena yesetelen!!!

  10. Yes. He spoke out the truth.
    Mainly the politicians are exposed to this critique. Political elites speak too much; but, their deeds speak and sound more.
    I respect & like Pro. Mesfin from the bottom of my heart. He is the first born Ethiopian man. Either authority or wealth can’t change his mind. He is always telling us the truth.
    Dear sir, I was and am defendng Lidetu for I believe that his contribution to the failure of the struggle was silly. I was rather accusing Engineer Hailu and Dr Birhanu for the destruction of CUD.
    Professor, can you say something about this?
    Would you please tell us about Lidetu Ayalew?
    Is he a man as he is understood at the moment?
    What wrong had he made during the time of Kinijit?
    Was he really a Woyane agent who infiltrated in Kinjit?
    Tell us the truth. I will then accept what you tell us.

  11. ይህች ሆድ ስንት አይነት አመል ታፈራለች። ጉደኛ ሆድ ስንቱን ስንቱን አሳየችን። ቴዲ አፍሮ “አስገምቼው ራሴን አለሞላውም ኪሴን” ብሎ የዘፈነው ሰለሞን ተካልኝ “ሆድ ተቅደም አቆርቛዧ ይውደም” ብሎ ለኢህአደግ ባደረ ማግስት መሆኑ የጊዜ ግጥጥሞሽ ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም። አረ ስንቱ? ብቻ መታዘብ ነው። ንዋይ ደበበስ “ከሆዴ ሌላስ ማን አለኝ” ብሎ አንጀት በሚበላ ድምጥ ዘፈነ አይደል የተባለው፤፡ እንግዲህ ለቴዲ አፍሮ ፈጠጥ ያለ መልስ መሆኑ ነው። የእያንዳንዱ እንቅስቃሴ በሆድ ስሌት እየሆነ አልትቸገርንም እንዴ? አብርሀም ያየህ በቅርቡ “ካንተ ጋር ታየሁ አይደል ወይኔ በቃ ጉዴ ፈላ” ብሎ እንደ አስቴር አወቀ በቀጭኑ ዘፍኖ ሮጠ የሸሸው ኢትየጲያዊ እንዳጋጠመው በአግራሞት ነግሮናል። ታማኝ በየነን “እባክህ ጌትዬ ፡ ይህች ኮተቤ የጀመርኩዋት ዶሮ ማርቢያ እስክታልቅ እንደው ከናንተ ጋር ባልታይ እባክህ በድጋሚ ተባበረኝ። ለማንኛውም ከናንተው ጋር ነኝ…እና መቼም ሞት ለወያኔ ቀጥሉ ፤ ትግላቸሁን ግፉበት” እያለ የሚያሹፍበት ስንተ ደንደሳም እንዳለ አልተናገረም እንዴ? በአደባባይ እንደ ውሻ ጭራ የሚቆላው፡ ማንም ሳይቆነጥጠው ኢህአደግ ጌታ ነው እያለ ነጠላ ዜማ የሚለቀው፡ ኮሽታ ሳያሰማ አኔ ምን ቸገረኝ ብሎ ዝም ብሎ አድፍጦ የሚበላው። የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ በሚል ፈሊጥ ሀገርን በቅርጫ የሚዘርፈው። አረ ስንቱ። ፕሮፌሰር መስፍን እንደው ከሆድ ቢፌው ትንሽ ቆንጠር አድረገው እንካችሁ አሉ እንጅ ጭራሽ መች ተነገረንና?

  12. The professor did not come up with anything new I have not heard of before. Perhaps, I am as old a git as he is. In any case I put myself in the other category of habesha he created, whatever that means. Where does he put himself?
    I could not agree more with dagnachew’s rebuttal.

Comments are closed.

Share