ንጉሠ ነገሥት አብርሃም ያዬህ ሆይ! መፍትሔው ይሄው ነው በቃ?

ይሄይስ አእምሮ

“የአፄ አብርሃም ያዬህን ጽሑፍ አንብበን ስንጨረስ ነገር ማብላላታችንን ትተን ዝም ብለን መጋደም አልቻልንም፡፡ ዘመናችን ብዙ የሚሠራበት ሣይሆን ብዙ የሚወራበትና የሚጻፍበት መሆኑን እናውቃለንና አግራሞታችን ወሰን አልነበረውም፡፡ ጥሎብን ‘ሌላ ሥራ የላቸውም ወይ?’ እስክንባል ድረስ በዬቀኑ ብዙ እናነ(ብ)ባለን፤ ይህም ሲሆን በምንታዘበው ሁሉ እናነባለን፡፡ ሕዝባችንን የሚጠቅም ነገር ለማከናወን የዛሬ አሥራ ሁለት ዓመት ገደማ ብዙ ብንጥርም የአማራ ኤሊቶች እያወኩን ጥረታችን ስንዝር ሳይራመድ ተኮላሽቶ እንዲቀር አደረጉብን፡፡ ያዘጋጀነው በመቶ ሺዎች የሚገመት ዘመናዊ ጦርም ሳይዋጋ ወደየመጣበት ተበተነብን፡፡ አሁን ደግሞ እነሙሉጌታ ሉሌ ትናንት እንዳልሰደቡን አሁን ደግሞ እኛን ተመሳሰሉና ለነአንትና እየሰገዱ አስደሰቱን፤ በሣቅም ፈጁን፡፡ አማርኛችን በጣም መሻሻሉን ወዳጆቻችን ስለጠቆሙን በጣም ተኩራርተናል፤ ከእሥራቷ እንደተለቀቀች ጥጃም ፈንጥዘናል፡፡ እነዚህ የአማራ ሙንጣዦች ግን ቢመከሩ ይመከሩ፤ አለበለዚያ ዋጋቸውን እንደምንሰጣቸው ለሕዝባችን ቃል እንገባለን፡፡ እነዚህ የትግራይ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች የሆኑ የአማራ ልሂቃን “ትግሬ ነገሰ” ብለው በምቀኝነት ሊያብዱ ደርሰውልናል፡፡ በፊት ብንመክራቸው እምቢ ብለዋል፤ አሁን ደግሞ እንገስጻቸዋለን ወይ እንቆነጥጣቸዋለን፡፡ አለበለዚያም ብትር ቢጤ እናቀምሳቸዋለን፡፡ ….”

ባይቆጭ ያንገበግብ፡፡ይሄ አማራ እሚባል ‹ፍጡር› ፈረደበት፡፡ ስደተኛውም፣ የፖለቲካ ጥገኛውም፣ የኢኮኖሚ ጥገኛውም፣ የስኳር ሌባውም፣ የጨው ሌባውም፣ የወርቅ ሌባውም፣ ሁሉም ይረባረብበታል – አሃ፣ አሸሞርኩ መሰለኝ፤ ይቅርታ፡፡ ምን ይደረጋል – ጥላሸት ሲቀቡህ መቼም ቅቤ አትቀባ ነገር ሆነብኝ እኮ – ስለዚህ  የሀሰትም ልትሆን ብትችል ጠባብ ቀዳዳ እየፈጠርህ መሸሟሞር ጉደኛው ዘመናዊ ባህላችን የሚጠብቅብን አነስተኛው መሥፈርት ነው፡፡

አብርሃም ያዬህ የአማራ ልሂቃንንና አማሮችን በጅምላው ምን አድርጉ እያላቸው እንደሆነ አልገባህ አለኝ – የሞተ ፈረስ ጋላቢ ሆነብኝ፡፡ እግር እጁ በማይጨበጠውና ከቁም ነገሩ ይልቅ አትርሱኝ ባይነቱ በሚያሳብቅበት በዚህ የተውገረገረ ዘባዘቦው የአማራ ልሂቃን የሚላቸውን ወገኖች እንደምን አድርጎ በአግቦና የስድብ ቾኬ እንደጠረባቸው ስመለከት እንኳንስ ልሂቅ አልሆንኩ ብዬ የጨዋነት ዕድሌን አመሰገንኩ፡፡ እውነቴን ነው፡፡ ብሆን ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር? ገመድ ቢጤ ይዤ ወደሚቀርበኝ ዛፍ እሮጥ እንደነበር አሁን ሳስበው በልጆቼ ዕድል ቀናሁ፡፡ ግን እኮ የማንሰማው ጅላጅልና ብሶት ወለድ ነገር እንዳይኖረን እየሆን ነው ጃል! ምን ዓይነት ዘመን ነው፡፡ በነገራችን ላይ የላይኛው አንቀጽ ጌታው አብርሃም ያዬህን እንዳቅሚቲ ለመተረብ በርሱ አነጋገር ማለትም የአጻጻፍ ሥልት ብዕሬን ማናገሬ ነው፡፡ ሰውዬው ግን እዬለየለት መጣ ልበል? ምነው ዐርፎ ቢቀመጥ? አሽሙርና አግቦስ ባይሆን ‹እኛ ወጣቶቹ› ጽሑፍና ንግግራችንን እናሳምርበት እንጂ በርሱ ያምራል እንዴ? በአሽሙር ዕድሜን መጨረስስ እግዜር ይወደዋል? ኧረ አቅል ጀባ! መካሪ ማጣት እንጂ እንዲህ ከሁሉም ጋር መናጀስ ማንን ይጠቅማል? ይህን ስል ግን ሃሳቡን በነጻነት የመግለጹን ያልተሸራረፈ መብት ከማክበር ጭምር ነው፡፡ ያንን መብቱን በአግባቡ እንዲጠቀምበት ግን እጠቁማለሁ፡፡

ትልቁ የአብርሃም ችግር የሚጀምረው የጽሑፉ የትርክት አቅጣጫ (point of view) ላይ ነው፡፡ የመረጠው የትርክት አቅጣጫ ሥልጣን ወዳድነቱን የሚያሳይ ነው – አብርሃም ከመጠን ያለፈ ሥልጣን አፍቃሪ ነው፡፡ ያን ፍላጎቱን የሚያጨናግፍበት የመሰለውን ግለሰብም ሆነ ቡድን በዛቻና በነገር ውርጅብኝ ለማደባየት ደግሞ በምንም ዓይነት መንገድ ወደኋላ እንደማይመለስ ከአጻጸፍ ሥልቱ መገንዘብ ይቻላል፤ የሠለጠነበት ይመስላል፡፡ በዚህ ‹ጥንቆላየ› ትክክል መሆኔን የአቶ ያዬህ ልጅ አብርሃም ራሱ ይመሰክርልኛል፡፡

የመረጠው  የትርክት አቅጣጫ ንጉሣዊ ነው – ልክ እንደቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዓይነት፡፡ አብርሃም ንጉሥ አይሁን እያልኩኝ አይደለሁኝም፤ አሁን ግን ስደተኛ እንጂ ንጉሥ አይደለምና እንዲያ መናገሩ ትርጉመቢስ ነው ለማለት እደፍራለሁ፡፡ በነገራችን ላይ የትርክት አቅጣጫ ስል “የጽሑፉን ታሪክ ማን ነው የሚነግረን?” የሚለውን ጥያቄ የሚመልስልን ነው፡፡ አብርሃም የተጠቀመው የአንደኛ መደብን ብዙ ቁጥር ነው – በንጉሣዊ የአነጋገር ሥልትነት የሚታወቀውን መጠቀሙ ነው፡፡ እንግዲህ ለመንገሥ እያሰበም ሊሆን ይችላልና ይቅናው፡፡ አብርሃም ያዬህ “የምንወድህና የምትወደን ሕዝባችን…” ለማለት የቀረው ጊዜ ምናልባት ቀጣዩ ጽሑፉ እስኪወጣ ነው፡፡

አብርሃም ጥቂት ማሰብ ቢችልና ነባራዊ የትርክት አቅጣጫ ቢጠቀም ኖሮ ከእንደኔ ዓይነቱ ሥራ-ፈት አቃቂረኛ ትችት ይድን ነበር፡፡ ከራሱ ጽሑፍ ምሳሌ ልውሰድና እንዳመጣብኝ ራሴው በመረጥኩት አንድ መንገድ ላሻሽልለት – ሌላም ዘዴ ይኖራልና፡፡

 

ከቅርብ ቀናት በፊት ያስተላለፍነው ማስታወቂያ መሰረት በማድረግ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ የለቀቀናቸውን ሁለት ኣበይት ጉዳዮች ያዘሉ ፅሑፎቻችንን በጥሞና ኣጢናችሁ ምስጋና ለለገሳችሁንና ላበረታታችሁን እጅግ በርካታ ወገኖቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። ለወደፊቱም ምክራችሁና ድጋፋችሁ፥ ጉድለት ሲኖርም ተግሳፃችሁ፥ እንዳይለየን በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።ከሁሉም በላይ ያስደሰተንና ያስፈነደቀን ግን የኣማርኛ ቋንቋ ኣቅማችን መዝናችሁ ከፍተኛውን የማለፊያ ቁጥር/ማርክ ሰጥታችሁ ያበሰራችሁን ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ያደረጋችሁት መልካም ተሳትፎ ነው።

 

ከቅርብ ቀናት በፊት የተላለፈውን ማስታወቂያ መሠረት በማድረግ ባለፉት ሁለት ሣምንታት በተከታታይ የተለቀቁትን ሁለት ጉዳዮች ያዘሉ ጽሑፎችን በጥሞና አጢናችሁ ምሥጋና ለለገሳችሁኝና ላበረታታችሁኝ እጅግ በርካታ ወገኖቼ ከልብ የመነጨ ምሥጋናየ ይድረሳችሁ፡፡ ለወደፊቱም ምክራችሁና ድጋፋችሁ፣ ጉድለት ሲኖርም ተግሣጻችሁ እንዳይለየኝ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ያስደሰተኝና ያስፈነደቀኝ ግን የአማርኛ ቋንቋ አቅሜን መዝናችሁ ከፍተኛውን የማለፊያ ቁጥር/ማርክ የሰጣችሁኝ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ያደረጋችሁት ተጨማሪ ጥረት ነው፡፡

 

በመሠረቱ አብርሃምን በአማርኛ ችሎታው ማማት የሚቻለው የለም – ጎበዝ ነው፤ በዚያ በደርግ የመጨረሻ ዘመን በሚያምር ንግግሩ ያላማለለው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቲቪ ተከታታይ አልነበረም፡፡ ይህም ችሎታው የዛሬውን አያድርገውና እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ ያገኘው የጋራ ሀብት እንጂ ለ‹ወደር ለሌለው ጀግንነት ኒሻን› ወይም ለ‹ኖቤል የሥነ ልሣን ለመዳ› ሽልማት የሚያሳጭ ታላቅ ጀብድ አልነበረም፤ አይደለምም፡፡ አማርኛን ከአማሮች በላይም እንኳን አሣምሮ መናገር መቻል ብርቅ አይደለም/ሊሆንም አይችልም፤ በ”ቋንቋችሁን ዐወቅሁላችሁ”ም የሚያንቀባርር አይደለም – እነአሉላ ፓንክረስት ምን ይበሉ ታዲያ፡፡ በመሠረቱ እኮ አንድን ቋንቋ አጣርቶ ለማወቅና ለመጠቀም በአማካይ ስድስት ወራትን ብቻ እንደሚፈጅ ባለሙያዎቹ የሚናገሩት ጉዳይ ነው – በዚያም ላይ ማንኛውም ቋንቋ የሰው ልጅ ጠቅላላ ሀብት እንጂ ‹የኔ የብቻየ አንጡራ ሀብት ነው› ሊባል የሚገባው አይደለም – እንደዚያ የሚሉ ጅሎችና የቋንቋን ሥነ ተፈጥሮ የማይረዱ ናቸው፡፡ እንግሊዝኛን ከእንግሊዞች በላይ የሰለጠኑበት የዓለም ዜጎች ሞልተዋል ይባላል፡፡ አማርኛን በሚመለከት ግን እነበዓሉ ግርማ፣ እነሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን፣ እነጥላሁን ገሠሠ፣ እነማህሙድ አህመድ፣ … እና ሌሎቹም ሚሊዮናት የኢትዮጵያ ፈርጦች ምን ሊባሉ እንደሚችሉ አብርሃም ያዬህ ብቻ ነው ሊነግረን የሚችል – ደግሞም እኮ አማርኛና ትግርኛ ተለያይተው ሞተው – ፒ! በዚህም አለ በዚያ እሱ በቀጥታ ሳይናገረው በሾርኒ እንደተናገረው ቆጥሬ እንደምረዳው  እሱን መሰል ትግሬዎች ለአማርኛና ለአማሮች ባላቸው ቀረቤታና ታሪካዊ ዝምድና ሲሉ አማርኛ ቋንቋን አጥርተው መናገራቸው እንዳለ ሆኖ በታሪካዊ ኹነቶች መገጣጠም ምክንያት እንግሊዝኛ የዓለም ቋንቋ ሊሆን እንደተቃረበ ሁሉ ከ80 ቋንቋዎች በላይ በሚነገሩባት ኢትዮጵያም በሆነ ታሪካዊ አጋጣሚ ይህ የጭቁኖች ቋንቋ ለሀገሪቱ ሕዝብ እንደጋራ የመግባቢያ ድልድይ ሆኖ ቢያገለግል ያሸልመው እንደሆነ እንጂ አያስኮንነውም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ወርቅ ላበደረ ጠጠር መመለስ እንደባህል እየተቆጠረ ስለመጣ አማርኛ አለአበሳው እንደክርስቶስ እየተወገረ ያለበት ሁኔታ ነው ተፈጥሮ ያለ፡፡ በውጤቱም ኢትዮጵያ ነጻ ስትወጣ በቀላሉ ወደማትወጣው ሥነ ልሣናዊ ውጥንቅጥ ውስጥ እየገባች እንደሆነ መገመት የሚቻልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነው ያለ፡፡ በሃፂሩ ዘይተፈጥረ ኹኔታ የለን ምባል ይኸሸና አኅዋተይ፡፡ “ዝዛረቦን ዝፅህፈሎን ኣምሃርኛ ፅቡቕ ተባሂሎለይ፤ እንኳዕ ቃህ በለኩም፤ አነ ቃህ ኢሉኒ ” ኢልካስ ከምዚ ምርጓድ? ቧይ! አታ አብርሃም፣ እንታይ’ሞ ኮይንኻ? …

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዛሬ ወሬዎችና መጪው ጊዜ - መሳይ መኮነን

እባካችሁን እያልኩ ያለሁት ግልጽ ይሁንልኝ፡፡ አማርኛ በግድ የጋራ ቋንቋ ይሁን የሚል ሥነ ልሣናዊ ህልምም በሉት ቅዠት የለኝም፡፡ የማምንበት ጉዳይ ግን ኢትዮጵያውያን በአንድ የግዛት አንድነት ሥር ለመኖር እስከፈለጉ ድረስ ከ80 በላይ በሚገመቱ ቋንቋዎች በሁሉም መግባባት ይቸገራሉና ቢያንስ አንድ ኦፊሴል የሥራ ቋንቋ የሚያስልጋቸው መሆኑን ነው፡፡ ያም ቋንቋ ሲፈልግ ኑዌርኛ ሲፈልግ ደግሞ ዳዋሮኛ ይሁን፡፡ ችግሩ እሱ አይደለም፡፡  በ80 ቋንቋ ቲቪ ፕሮግራም መክፈት፣ በ80 ቋንቋ ዐዋጅ ማርቀቅ፣ በ80 ቋንቋ ጋዜጣና መጽሔት ማተም፣ በ80 ቋንቋ የትምህርት ሥርዓት መንደፍ … ይህን እንኳንስ እኛ ያደጉ አገሮችም አይችሉትም፤ እስካሁን የሠራነውም የጅሎች ሥራ ነው፡፡ ስለዚህ ውድ አብርሃም እንዲያውቀው የሚገባው ነገር አማርኛን የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ለአማርኛ ባለውለታ ናቸው እንጂ አማርኛ ተገልብጦ ውለታ ከፋይ ሊሆን የሚገባው አለመሆኑን ነው፡፡ ቋንቋን ከመሣሪያነቱ በላይ አዝልሎ የሚመለከት በሽተኛ እንጂ ጤናማ ሰው ሊባል አይችልም፡፡ ላወቀው ቋንቋ ልክ እንደሸሚዝና ከናቴራ ሊጠለቅና ሊወልቅ የሚችል በጣም ተራ ነገር ነው፤ ሰዎችን የሚያባላውስ የግል ወይም የቡድን እንስሳዊ ጥቅምና ፍላጎት ነው፡፡ ቋንቋ ልባስ ናት – ጭምብል፡፡ በዛሬ ዘመን ደግሞ የአንዲት እናት ልጆች እንኳን እርስ በርስ ይባላሉ – ይቅርና የአንድ በሄረሰብ አባላት፡፡ ሶማሌን ተመልከቱ፡፡ በሁሉም ነገር አንድ ሆነው ሲያበቁ ከኛ በበለጠ መንግሥት አልባ ሆነው በዓለም ዙሪያ ተበትነዋል፡፡ የበተናቸው በቋንቋ ያለመስማማት ጣጣ አይደለም፡፡ ሆድ እንጂ የቋንቋ ልዩነት አያፋጅም፡፡ ዐመል እንጂ በምትናገረው ቋንቋ ምክንያት አትጨራረስም፡፡ እውነቱ ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡

አማርኛን በሚመለከት እንዲያውም በአሁኑ ወቅት በገዢው የወያኔ ቡድን ምክንያት የኢትዮጵያውያን የጋራ መግባቢያ ድልድይ እየተሰባበረ በመሆኑና የሚተካውም ባለመዘጋጀቱ ብዙ ዜጎች እየተጎዱ እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ባሏን የጎዳች መስሏት የገዛ ሰውነቷን በጋሬጣ መለጎጠች እንደተባለችው ቂል ሴት፣ ወያኔም አማራ እሚባሉትን ዜጎች ከጨዋታ ውጪ ያወጣ መስሎት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ በተለይ የገጠራማይቱ ኢትዮጵያ ዜጎችን ከሁለት ያጣ ጎመን አድርጓቸው መቅረቱን መገንዘብ አይከብድም፡፡ በስመ ብሔር/ብሔረሰብ የማላገጫ “ፌዴራል” ተብዬ የፖለቲካ ቁማር ሰበብ ጆሮውን ቢቆርጡት አማርኛን መናገር የማይችል ኢትዮጵያዊ ዜጋ አምርቶ ወደመናገሻ ከተማ ለሥራ ፍለጋ ሲመጣ ከቢጤዎቹ በተለዬ ባይተዋር እንዲሆን ማድረግ ዛሬም ባይሆን ከነጻነት በኋላ ዳፋውን የምናየው ይሆናል፡፡ ከደምቢዶሎ በእንግሊዝኛ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቶ አዲስ አበባ ለሥራ ፍለጋ የመጣና ኦሮሚፋ በስተቀር እንግሊዝኛም አማርኛም መናገር ባለመቻሉ ገና በኢንተርቪው ያለማለፉን መርዶ እየሰማ ይሰቃይ የነበረ ወጣት በቅርብ አውቃለሁ፡፡ ወያኔዎች በቂም በቀልና በድንቁርና ተነሳስተው የኢትዮጵያን ወጣት በዚህ መልክ ቢጫወቱበትም ታሪክ ፍርዱን ሲሰጥ የሚገባቸውን ምንዳ እንደሚያገኙ አይጠረጠርም፡፡ የነሱን ልጆች ግን እንዴትና እጅግ ውድ በሆ ክፍያ የት እንደሚያስተምሩም እናውቃለን፡፡ ሌላው ቀርቶ በውቅሮው ወንድሜ በሐጎስ ገ/ማርያም ግምባር ላይ የምትገኘዋ ያቺ 11 ቁጥር መለያ እንኳን በነሱ ልጆች ግምባር እንዳታርፍና የባህል ተከታይ እንዳይባሉባቸው ያደርጋሉ፤ አቸፈርና ወይንማ የገጠር ትምህርት ቤት “የተማረው” የስንሻው አገሩአደመ ልጅ “ኧሯ!” ሲል በአማርኛው ጎጃሜ መሆኑን ተረድተህ ስታፌዝበት የወያኔዎችን ልጆች ግን በምንም መንገድ አትለያቸውም – “ሥልጡናን” ናቸው፡፡ አነሳሴ ሌላ ሆነ እንጂ በዚህ ዙሪያ ብዙ የሚያሳዝኑ ገጠመኞችን መናገር በቻልኩ፡፡

አብርሃም ያዬህ በተለይ የአማራ ልሂቃን የሚላቸውን በጅምላ ለምን እንደጠላቸውና በዴሞክራሲያዊ ልቅ ብዕሩ ለምን በስድብ እንደሚሞልጫቸው ገርሞኝ ባነሳሁት ብዕር ስላልተነሳሁበት ነገር ከፍ ሲል ጥቂት ዘባረቅሁ መሰለኝ፡፡ ምን እንዲያው – የዚህች አገር ነገር እኮ ሳይጠጡ እያሰከረን ብዙዎች ተቸገርነ፡፡ ምን ይብቃነ? ሁሉም እየተነሣ የስድብና የአቃቂር መለማመጃ አደረገነ፡፡ በቁም ሞትነ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶክቶር ብርሃኑ ነጋ ና አውራምባ ታይምስ - ከግርማ ካሣ

አንድ የኔ አገር ሰው ነው አሉ፡፡ አንድ ጓደኛው “እናንት ጎንደሬዎች ስትባሉ – በየቃሉ መጨረሻ ‹ነ› ታበዛላችሁ ይባላል፤ መጣነ፤ ገደሉነ፤ በላነ… ነው አሉ እምትሉት፤ ለምንድነው?” ብሎ ቢጠይቀው “ለምዶብነ!” አለው ይባላል፡፡ ዘና በሉና አንብቡ፡፡ ሊያልፍ ዓለም የምን መጨነቅ ነው፡፡ ጠላታችሁ ይጨነቅ፡፡

አብርሃም ያዬህ ጥላቻህን በቅጡ ያዘው ወንድማለም፡፡ ከአንተ እንዲህ ያለ “ኮምፕሌክስ” አይጠበቅም፡፡ የአማራ ልሂቃን፣ የትግሬ ልሂቃን፣ የኦሮሞ ልሂቃን፣ የኮንሶ ልሂቃን፣ የወላይታ ልሂቃን፣ የሶዶ ልሂቃን፣ የወለንጪቲ ልሂቃን፣ የቡታጅራ ልሂቃን፣ የጨቦና ጉራጌ ልሂቃን …  ይህ የዘረኝነትና የጎጠኝነት ልክፍት ለካንስ ማቆሚያ የለውም …  እንዴት የሚያስጠላ አነጋገር መሰላችሁ፤ አንድ የተማረ ሰው ዜጎችን እንዲህ በመሰለ አጸያፊ መነጣጠያ እንዴት ይከፋፍላል? ለዚህ ለዚህማ ከወያኔ በምን እንሻላለን? ዋጮን ቢገለብጡት ያው ዋጮ ነው እንደሚሉት መሆኑ እኮ ነው፡፡ ልዩነቱ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት በመግባትና ባለመግባት ሆነ እንጂ አንዳንድ በቤተ መንግሥት ውስጥና ከቤተ መንግሥት ውጪ ያሉ ወገኖቼ አነጋገራቸው እዬተመሳሰለብኝ መጥቷል፡፡ “መንግሥቱን፣ መንግሥቱን መሰልከኝ!” ነበር አይደል ያሉት ዶር. ነጋሦ? አበጁ! ልኩን ነግረውት ሄደ፡፡ እንኳንም የነገሩት፤ እሱም እንኳንም ጥርግ ያለ፤ ሐምሌና ነሐሴም ነጉደዋል፡፡

አብርሃም ተመለስ፡፡ የማትመለስ ከሆነ ግዴለህም ዝም ብለህ ስደትህን ብቻ አሰላስል፤ ከ14ሺህ ማይል ማዶ ሆነህ ያልበላንን ለማከክ አትሞክር፡፡ ያውጡብሽ እምቢ ያግቡብሽ እምቢ አትሁን፡፡ የዱሮውንም ተቃውመህ፣ የአሁኑንም ተቃውመህ፣ ያንንም ጠልተህ፣ ይህንንም ጠልተህ… ደግሞ የምትዘልቀው አትመስለኝም፡፡ ለመሆኑ ትግሬ ነገሠብኝ ብሎ ያኮረፈው የአማራ ልሂቅ የትኛው ይሆን? አለ ካልክና ካጋጠመህ በጅምላ አማራውን የአገም ጠቀም አዘኔታ ባጀበው መርዛማ አነጋገርህ ከምትወርፍ ስሙን ጠቅሰህ ለምን አትወቅሰውም? ምን ዓይነት የጠብ ስንጥቃት እየፈጠርህ ነው? የነበሩን ቅራኔዎች አነሱንና ነው በትግሬና በአማራ መሃከል ሌላ ሽብልቅ እያበጀህ ልትቀበቅብብን የምትዳዳው? እንደውነቱ አማርኛን ማወቅ አማሮችን በማይፈለግ ቅራኔ ውስጥ እየከተቱ በስቃይ ለማዳከር ጥቅም ላይ መዋል አልነበረበትም – ኩነኔ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ደግሞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጥርሱን ከነቀለ ሰው በፍጹም አይጠበቅም፡፡ ከአንተ የሚጠበቀው የአስታራቂነት ሚና እንጂ እንደቀድሞ የትግል አጋርህ እንደመለስ ዜናዊ ዜጎችን በማጋጨት የመርካት ፍላጎት ልታዳብር አይገባህም ነበር፡፡ አጋጫቸው፣አፋጫቸው የሚል ስሜት የሚፈታተንህ ከሆነ – መቼም አይታወቅም – ወደሚቀርብህ ጠበል ሂድና አንድ ሦስት ሰባት ያህል ተጠመቅ – በአጠገብህ ካገኘኸው ያን ተስፋዬ ገብረአብ የሚባለውን ሰውዬም አብረህ ይዘኸው ሂድና አብራችሁ ተጠመቁ – የያዟችሁ ፀረ-ሕዝብ አጋንንት ውልቅ ይሉላችሁ ይሆናል፡፡ ስለኢትዮጵያ ነጻነት የዐዞ ዕንባ እያነቡ አንድ የነጻነቱ ትልቅ ኃይል ሊሆን የሚገባውን የአማራ ብሔር በቀጥታም ባይሆን በተዛዋሪ እንደእባብ መቀጥቀጥ ከሞራልም ሆነ ከሃይማኖት አንጻር አግባብነት የለውም፡፡ የሚቀጠቅጠንና የሚያቀጣቅጠን አላጣንምና አንተ እንኳን እባክህን ማረን፤ በሞቱ ዘመዶችህ አጥንት ይሁንብህ፡፡

አማሮች እኮ ዘራቸው እንኳን እንዳይራባ በመርፌና በበሽታ እንዲያልቁ ሤራ የተሸረበባቸው የዘመናችን ምንዱባን ናቸው – በዚህ ላይ ዛሬ አንተ ተነስተህ በጭቃ ጅራፍህ ብትሸነቁጣቸው ላንተስ ግፍ አይሆንብህምን? ታውቃለህ አብርሃም ያዬህ – መለስ ዜናዊ በተላላፊ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎች ከየቦታው በመብራት እየተፈለጉ ወደአማራው አካባቢ እንዲሄዱና በዚህ ምሥኪን ሕዝብ ላይ የተኩስ ድምፅ የሌለበት ዳግማዊ የክተት ዘመቻ ታውጆባቸው ብዙዎች እንዲያልቁ ማድረጉን ሳትሰማ አልቀረህም – እሱ ሺህ ዓመታትን ሊኖር፡፡ ይህች ቆሻሻ ዘመን ያላሳየችንና ያላሰማችን ነገር የለም፤ እናም እባክህን በድጋሚ ልማጸንህና ልጆች ካሉህ በልጆችህ ይሁንብህ አማሮችን ተዋቸው፤ ነጻ ልታወጣን አስበህ እየታገልክልን ከሆነም እንደኔ እንደኔ ይቅርብን – ከዕብሪት አነጋገርህ ነጻ መሆናችን ራሱ ትልቅ እገዛ ነው፡፡ የፈጠረን አይረሳንምና እርሱ ራሱ እንደፍጥርጥሩ ያድርገን፡፡ ይልቁንስ ላንተው ተጨነቅ፡፡ ደግሞም አታስፈራራን፡፡ ፈርቶ የጨረሰን ለማስፈራራት መሞከር ትርፉ ትዝብት ነው አባት ዓለምዬ፡፡ በዚያ ላይ እንኳን ከፎከረ ከተወረወረም የሚያድን አምላክ አለንና በወያኔ ኃያልነት እያሳበብህ በልጆች አማርኛ ‹አታስቦካን›፡፡ እስኪ ይህን ልብ በል፡- እሳት ውስጥ ገብቶ እየተቃጠለ ያለን ሰው “መጪው ዕድልህ ከዚህ የባሰ መሆኑ ያሳዝነኛልና ዐርፈህ ብትቃጠል ይሻልሃል! ዋልህ አንት ዋልጌ! ለዚህ ያበቁህ አስተምረህ ለወግ ለማዕረግ ያበቃሃቸው ልጆችህ ናቸው፡፡ …” እያልክ ቲሪሪም ቲሪሪምህን ብትነፋበት ምን ያህል የሞራል ልዕልናና የመንፈስ እርካታ ታገኝበታለህ? ታዲያ ከመጡበት ዘጠኝ ሞቶች አንዱን ግባ ብሎ በወያኔ እየተቃጠለ የሚገኝን ማኅበረሰብ የግፍ ግፍ አሁን ላይ ሆነህ ስለወደፊቱ ማስፈራራት ምን ትርጉም አለው? ጉደኛ ነህ ጃል!

መመጻደቅህንም ቀነስ ብታደርገው አንተው ነህ ከተጨማሪ ትዝብት የምትድነው፡፡ ኤዲያ – ምነው ይሄን ኢንተርኔት የሚባል ነገር የሚያጠፋልኝ ባገኘሁ! ስንቱን እንቶፈንቶ ዝግንትል መሰላችሁ የሚያስነብብ፡፡ ጥቂት የአብርሃምን ዕንቁ ንግግሮች ከምዝስዕብ ከቕርብለኩም እየ’ሞ ቕሩብ ምዕንቲ ክትዘናግዑ የኽትት፡፡ ብዚ አገጣሚ አብርሃም ያዬህ ብፍላይ ንክልቴኦም ብሔራት ዝአዳለዎ ድግምቲ መስተፃልዕ ክሠርኽ ከምዘይክእል አፀቢቐ ከርገግጸልኩም እደሊ፡፡ ኳርት ቀየርኩ ልበል? ሆን ብዬ ነው – አማርኛና ትግርኛ ምን ያህል “አራምባና ቆቦ የሆኑ”ና በምንም ዓይነት መንገድ “የማይቀራረቡ ቋንቋዎች” መሆናቸውን በጨረፍታ ለመጠቆም ፈልጌ ነው፡፡ ለማንኛውም ወደአብርሃም ጽሑፍ በቀጥታ እናምራ፡፡ ከ12 ገጾች ጽሑፍ የሚከተሉትን ብቻ ነው ለአብነት ያህል የጠቀስኩት፡፡ በክፍል በክፍል ተመድቦ የቀረበውን ዋናውን ቅራቅንቦ በየድረገጹ ተለጥፎ ታገኙታላችሁና ማወቅ አይከፋም ተዝናኑበት -በበኩሌ እስኪገባኝ እየደጋገምኩ ሣይቀር ‹ተላጥኩበት›፡

ኧረረረረረረረረረረረረረረ ….

የኣማራ ኤሊቶች በሽታ ኢትዮጵያ ከኛ በላይ የሚቆረቆርላትና የሚያስብላት ሌላ ሰው የለም ብለው ስለሚያስቡ (እንዲያውም “ኢትዮጵያን የሰራት ኣማራ ነው” የሚሉንም ኣልጠፉም)፥ ከኣማራ ውጭ ሌላ ሰው ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ቢያስረዳቸውም እንኳ ሃሳቡን ኣዳምጠው መመርመርና ማስላት የማይፈቅዱ መሆናቸው ነው። እኛ ደግሞ ከፋም በጀ የትግራይ ህዝብ ስትራተጂካዊ ወገን የኣማራ ህዝብ ነው ብለን ስለምናምንና ትክክልም ስለሆነ፥ የነዚህ ወገኖቻችን ኣጉል መተራመስና ትጥቅ/ዝግጅት የለሽ ባዶ ፉከራና ሽለላ ለደጉና መከረኛው የኣማራ ህዝባችንም ሆነ ለምንቆረቆርላት ኣገር የማይበጅ በመሆኑ የኣማራ ሊሂቃን ወገኖቻችንን ኣበክረን ስንወቅሳቸው ኖረናል። ለወደፊቱም ሸውራራ ኣመለካከታቸውና ባዶ ፉከራቸው እስከሚገታና ሰከን ብለው የተቆርቋሪ ወገኖቻቸው ተግሳፅና ምክር ምን ይዘት እንዳለው ተረድተው ኣደብ እስኪገዙ ድረስ ወቀሳችን ከመሰንዘርና ኣቤቱታችንን ጥፋት በላዩ ላይ ላንዣበበው የኣማራ ብሄር ህዝባችን ከማቅረብ ኣንቦዝንም። ይቺን ኣጋጣሚ በመጠቀም፥ የኣማራ ሊሂቃን ወገኖቻችንን ለመውቀስና በተሳሳተ መንገድ ሲነግዱ ከዚያ የተሳሳተ መንገድ እንዲታቀቡ የምንወተውትበት ምክንያት ባጭሩ ጠቅሰን እናልፋለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢቲቪ ሽርፍራፊዎች (በሃብታሙ አያሌው)

ኧሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮ ….

ስለሆነም፥ ከኣማራ ሊሂቃን ወገኖቻችን ጋር የምንዳረቀው፥ በኢትዮጵያ ምድር የበቀሉት ሁሉም ህዝቦች ወገኖቻችን ቢሆኑም፥ በተለየ ታሪካዊና ተፈጥሮኣዊ ምክንያት የትግራይና የኣማራ ህዝብ ኢትዮጵያን በወረፋ እየተቀባበለ ለመግዛት ሲል በስልጣን ከሚሻኮት በቀር መጥፊያውም መዳኛውም መንገድ ኣንድ ስለሆነ፥ የትግራይ ኤሊቶች ሲያጠፉ እንደምንቃወማቸውና እንደምንዋጋቸው ሁሉ ኣማራ ነን የሚሉ ፍጥረቶች ሲያጠፉም እነሱንና ኣገራችንን ከጥፋት ለማስጣል ካለን ቁጭት ተነስተን ያለ ምንም ምህረት እንወቅሳቸዋለን፤ እንገስፃቸዋለን። ከዚህ ውጭ፥ በማጠያይቅ ሆኔታ፥ ኢትዮጵያዊያን ነን ብለን በፅናት የምናምን እኛ የትግራይ ተወላጅ ዜጎች እንደ ህወሓት መሪዎች በኣማራ ጥላቻ በሽታ የተለከፍን ሆነን ሳይሆን፥ ከኣማራ ኤሊቶች ጋር ያለን ግብግብ “ላም እሳት ወለደች፤ እንዳትልሰው ነደደች፥ እንዳትተወው ደግሞ ወለደች” ከሚል ኣገራዊ ብሂል የሚመነጭ ለመሆኑ በሚገባ መታወቅ ያለበት መሆኑን ከታላቅ ትህትና ጋር ባጭሩ ጠቁመን እናልፋለን።

ኧረረረረረረረረረረረረረረረረ …..

ባለፉት ሃያ ዓመታት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን (ባብዛኛው የኣማራ ሊሂቃን) በትግራይ ህዝብ ላይ ከረጩት መጠነ ሰፊ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ኣንፃር የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ውድቀት በኋላ የሚኖረው ዋስትና በምንና በማን ይረጋገጣል? ሌትና ቀን ሳይሉ የሚታገሉና በራሳቸውና ኣገርቤት በሚኖሩ ዘመዶቻቸው ላይ ብዙ መከራ እየተቀበሉ ያሉ እውቅ የትግራይ ህዝብ ታጋይ ልጆች ላይ (እነ ስየ ኣብርሃና እነ ገብሩ ኣስራት፤ ዛሬ ደግሞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምንም ወንጀል ያልፈፀሙትና የወያነ መንግስት ሰለባ ከመሆን ኣምልጠው በስደት የተቀላቀሉን ወንድሞቻችን እነ ወጣት ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ሳይቀሩ)፥ በዘረኛ ኣማሮች የሚወረወርባቸው ጦርና የሚመዘዝባቸው ሰይፍ እያየ፥ እየሰማ፥ እያነበበና፥ እየታዘበ ያለው የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ጠልቶ የልጆቹን ኣሳዳጆች የሚመርጥበት ምን ምክንያት ኣለው?

 

ኧሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮ …

 

የ”ትግሮች ነገሱብን” ኣባዜያቸው የሚጋለጠው ደግሞ ኣገር የሚያጠፋውን የወያነ ኣመራር በመቃወም ሳይሆን፥ “ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ኣብረህ ተወቀጥ” እንዲሉ፥ ኣብርሃም ያየህን ጨምሮ ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የሆነውን ሁሉ በማቀላቀል ጠላት ነው በሚል ፈሊጥ የተጨማለቀ ነው። ይህ ፈሊጥ ደግሞ ኢትዮጵያን ከሚበትን በቀር ሌላ ፋይዳ የለውም። ለነገሩ ኢትዮጵያ ብትበተን ምን ገዷቸው! ጉዳቱ ለኛ ይተርፈን እንደሆነ እንጂ እነሱማ የፈረንጅ ኣገርና ዜግነት ኣዘጋጅተው የለ! እኛ በእግዚኣብሔር ድጋፍ ብዙ ደክመንና ጥረን ያስገኘነው ጠቃሚ ግኝት የተስተጓጎለውም ከዚህ የመከነና ኣፍራሽ ፈሊጥ የመነጨ ነው። እኛ የሰራነው ታላቅ ስራ ያመከኑት ያማራ ኤሊቶችም “ኤርትራን ያስወሰዱ ኣፄ ምኒልክ ናቸው ብለው የሚከሱን ትግሮች ኤርትራን ከሚያመጡልን ትቅርብን፤ ወይም ደግሞ ትግሮቹ ያስወስዷትን ኤርትራ የምትመለስ ከሆነም በኛ ባማራዎቹ ብቻ መሆን ኣለበት” ያሉትም ያንን ኣፍራሽ የእብዶች ፈሊጣቸው የወለደው ኣባዜ ነበር።

ኧረረረረረረረረረረረረረረረረረረረረረ….

ዛሬ በሞተ ሰዓት ላይ ግንቦት ሰባቶች በኤርትራ በኩል ተኣምር ይሰሩልናል ብለው የሚያሽካኩት ፍጥረቶችና እንደነ ሙሉጌታ ሉሌ ያሉ “ኣንጋፋ ጋዜጠኛ” ተብየዎች ትናንት እኛ በትክክለኛው ጊዜና መንገድ ልንሰራው ያቀድነውን ኣንገባቢ ስራ ሲያደናቅፉና ሲያበላሹ የነበሩቱ መሆናቸውን ስንመለከት ባንበሳጭም በመገረም እንደመማለን። እየተገረምናና እየተደመምን ደግሞ ደግነቱ የማያልቅበት ፈጣሪያችን ዕድሜ ሰጥቶን የትናንቱ ኣውጋዦቻችንና ኣደናቃፊዎቻችን ጭቃ ውስጥ ተዘፍቀው የኢሳያስ ኣፈወርቂ ኣሞጋሾችና ተነጣፊዎች ሆነው መገኘታታቸው ስናይ በእጅጉ እንደሰታለን። እንኮራለንም!

 

ኧሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮሮ…..

ይህንን መጣጣፍ የምንቋጨው ኣጭር መልእክት በማስተላለፍ ነው። ግንቦት ሰባቶች በጉራና በፉከራ ከየዋህ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብር መዛቅ ይችላሉ። ይህ ቀላል ነው። በዚያ ብር ልክ ግን ፈተና ይጠብቃቸዋል። ይህንን የሚያፍሱት ብር በተላለፉት የግንቦት ሰባቶች ዲስኩሮች መሰረት በመሬቱ ላይ ባጭር ጊዜ ተጨባጭ ቁምነገር ካላስገኘ ብሩ እሳት ሆኖ እንደሚለበልባቸው ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። እኛ ይህ እንዲሆን ባንፈልግም ውጤቱ ግን ይህ እንደሚሆን ኣንጠራጠርም። ስለዚህ፥ ይህ ከመሆኑ በፊትና ኋላ ደብቁኝ ሰዉሩኝ ማለት ሳይመጣ፥ ከኤርትራ መንግስትና ህዝብ የሚደረግ ማንኛውም ግኑኝነትም ሆነ ትብብር ፋይዳ የሚኖረው ከሆነ፥ ግንቦት ሰባት ትህዴን በተባለ የትግራይ ፈረስ ተፈናጦ በመጋለብና የሻዕቢያ ጎራዴ ኣንግቶ ኣካኪ ዘራፍ በማለት ሳይሆን፥ ካገር ሽማግሌዎችና ወሳኝ ሚና ካላቸው የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በመመካከር፥ በተለይ ደግሞ የቀድሞ የህወሓት መሪዎች የነበሩትን በማማከርና በማሳተፍ ብቻ መሆን እንደሚገባው ኣስታውሰን ኣንባቢዎቻችን በትህትና እንሰናበታለን።

መዘምዘሚያ፡- ይህ የፖለቲካ ጎምቱ ሰውዬ ምን ማለት እንደፈለገ የገባችሁ ሰዎች እኔም ይገባኝ ዘንድ እባካችሁን
አስረዱኝ፡፡ ጠላታችን ግራ ይግባውና ግራ ግብት ነው ያለኝ፡፡ ምን አባቴን ልሁን? አብርሃም
እውነቱን ይሆን እንዴ ወያኔ በሽምግልና ሥልጣን ይለቃል የሚለን ያለ – ሊያውም አሥሮ ጢባጢቤ
በተጫወተባቸው የትግል ጓደኞቹ ሽምግልና? ወይንስ እያሾፈብን  ነው ያለ?

 

9 Comments

  1. Abrham Yahweh has always been right the so called Amhara Elites are stupid and ignorants who thinks only for themselves other than their society. Amhara elites and historians chose to mute and do nothing to challenge ignorant OLF, TPLF and ELF so called evil and hate driven Historians rewrite false and fabricated History to encite hate and violence for the imminent genocide and conflict they dreaming
    When it comes to politics the so called AMHARA elites are the once who are making the anti woyane struggle as they have no clear ajenda to work with Tigrians and Oromos due to this you see them working hand in hand with people like JAWAR and TESFAYE IBAB while pushing aside Tigrians who want to work with them
    You are one of those morons who is good for nothing came out to attack Abrhams personality rather than attacking his ideas and you even went to attack his Amharic what a low life person you are
    The way I see you you like ye Mender set who is good at gossip

  2. በጣም የረከሰ እና ያው ዘላለም እንደ አሲድ ሲበላቸው የሚኖረውን የበታችነት ስሚቱን መጠን በለለው ጥላቻ የሚያንጸባርቅበት ፍሪፈርስኪ ፁሁፍ ነው ያስነበበን። ሰውየው ጢናማ ቢሆን እንዴት ነው አንተ አንድን ሕዝብ ሙሉጭ አድርገህ እየሰድብክ እና እያዋረድክ አብረን እንስራ በልህ የምትጠይቀው። በመጀመሪያ በዚህ የድም ፍላትህ በፍጹም ሽማግሌ ሆነህ ሰማስታረቅ ቀርቶ ከራስህ ጋር የሚያስታርቅ ስብእና የለለህ አጋርንት ነህ። በመሰረቱ አንተ በዚህ አነጋገርህ በምንም አይነት ከንሰሳ የሚለይ ፀባይ የለለህ ባይውሎጂካል ኒኩለር ነህ አንተ ፈንድተህ ሌሎችን ለማበላሽት የተዘጋጀህ ነብስ ያለው ተንቀሳቃሽ መሳርያ ሆነሃል። እሲኪ በፍጠረህ ከገብረመድህን አርያ ትንሽ ተማር እሱ ባሁኑ ጊዜ ምን ያክል የሞራል እና የመንፈስ እረፍት እንዳደረግ በሚያደርጋቸው ቃለ መጠይቆች እና በሚጽፋቸው ጦማሮች ተረድተናል ። በመሰረቱ ሰዎችን እንደሰዎች ከእንሰሳት ልዩ ያደረጋቸው ተፈጥሮዋዊ ስጦታ ላጠፉት ጥፋት ይቅርታ መጠየቅ እና እራሳቸውን ከዓለማዊ እና ከሰማያዊ ጥያቄ ነጻ ማድረግ ነው። ይሄን እንኮዋን በሚገባ ያላጢንክ ለጥላቻና ለዚረኝነት እራስህን ተገዥ ያደረክ ሱሰኛ ነህ። በጣም ትንሹን ነገር ማገናዘብ ያቃተህ ደካማ እንደሆንክ ከጹሁፉ መረዳት ይቻላል ሽማግሌ ለመሆን መስፈርቶች እንዳሉት እንኮዋን ልብ አላልክም ያንተ ስነልቦና በፍጹም ለዚህ ስራ ዝግጁ እንዳልሆነ ከፃፍከው መረዳት ያቻላል። እሩጠህ እንደገባህበት እሩጠህ የወጣህበትን የወያኔ የፖለቲካ መድረክ እንዳይመስልህ። ፈጣሪን የምታውቅ ከሆንክ ፈጣሪ ይቅር ይበልህ ሃገራችንንም ከእንዳተ አይነት ሸረኛ ይጠብቃት። ( ዘ ሐበሻዎች እባካችሁ መልክቴ ሳይቆራረጥ እንዲደርስ አድርጉልኝ ) አመሰግናለሁ!!!

  3. I didn’t read much about your childish article. you can carry Tigre on your back after this we care less. But The guy who couldn’t get a job though he graduated in English and fluent in Afaan oromo. He is refused to get job in Finfinee. I understood why Finfine with 360 degree circled in Afaan oromo land, but only 20% residence are from this people. not only that these 20% live in extreme poverty even less than their immediate farmers in shanti towns. If Oromo are not colonized then there must be different definition of colonization. In Johannesburg also there was a similar story about 20 years ago. I am very sad to find people like Gidada telling me we are not colonized. What a shame.

  4. ተስፍየ ገብረኣብ የኢትዮጵያ ተስፋ!
    በነጻ የመጻፍ መብት ላይ ሁላችን እንስማማለን። ችግሩ የሚመጣው እናንተ ኣትጻፉ እኛ የጻፍንላቹሁ ብቻ ተቀብላቹሁ ንሩ ነው ወይም በኛ ሳጥን ግቡና እኛን መስላቹሁ ኑሩ ኣለበላዝያ ኢትዮጵያውያን ኣይደላችሁም እንድያውም የኢትዮጵያ ጠላቶች፣ ኣፍራሶች፣ በታኞች፣ ጠባቦች፣ ተገንጣዮች፣ ወዘተ ናቹሁ ነው። ኣድበስብሰው ያለፉት በኣረም ይመለሱት!
    በተስፋየ ኣጠቃላይ ድብደባው ከኣንድ ኣካባቢ ብቻ ነው፣ ከተወሰኑ የኣማራ ተወላጆች። ተስፋየ በጻፈው ድርጊት የሚክዱ ኣይመስለኝም፣ ማንሳቱን ላይ ይመስለኛል። ከዛ የባሰ በኣጼ ምንሊክ፣ በሃይለስላሰ፣ በደርግ እንደተፈጸመ እንዴት ይካዳል። በኦሮሞ፣ በትግራይ፣ በኤርትራ፣ በወሎ፣ በራያ፣ በቤጌምድር፣ በጎጃም፣ ወዘተ መፈጸሙ እንዴት ይካዳል። ኣታንሱት ደብቁት እና ወያኔ ብቻ እንደመሰረተው ይታወቅ፣ ይጻፍ ብቻ ነው ምኞታቸው። ወያኔ ንጽሁ ነው ማሌቴ ኣይደለም ቀደምት የጀመሩት ቀጠሉበት እንጂ ስለዚህ ሁሉም መንግስታት ይመዘኑ።
    የሚገርመው ደግሞ በኣማርኛ የኣጻጻፍ ችሎታው ያደንቁታል፣ እና በርታ እንደማለት። ኣማራ/ ኣማርኛ ኣትንካ ከሆነ የማይነካበት ምንም ምክንያት የለም። እንድያውም ወደ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሌሆችም ቃንቃችን ተተርጉመው ተውያይተንበት ተምረንበት ተመኩሮ እንድናገኝበት መደረግ ኣለበት፣ ለዚህም በግሌ እንቀሳቀስበታለሁ ምክንያቱም ልንተዎው ልንረሳው ብንፈልግ፣ እምየ እያላቹሁ እምየ የፈጸሙት ድርጊት ግን መግላጽ ኣትፈልጉም፣ የሚመቻች ሁ ብቻ ቀንጭባቹሁ ለማቅረብና ለመቀባት ስለምትመኙ ብቻ ነው።
    ኣሁን ወዳለንበት መከፋፈል ዋናው ምክንያት ኣጼ ምንሊክ፣ ሃይለስላሰ፣ ድርግ ብቻ ናቸው፣ ይህ ደግሞ ባብዛኛው የኣማራ ህዝብ ሳይሆን የኣማራ ባለስልጣናት የፈጸሙት ድርጊት ነው። ኣፓርታይድ የሳውዝ ኣፍሪካ ነጮች፣ ለጥቁር ኣመሪካውያን ነጮች፣ ለሳውዝ ሱዳን የሰሜን እስላሞች፣ የፈጸሙት ድርጊት ነው። ኢህወዴግ እድል ኣግኝቶ ስልጣን ያዘ ያን ሁሉ የእናንተው ክፋት፣ ብሶት፣ ኢሰብ ኣዊ ድርጊቶች ተጠቀመበት። ኢህወዴግን ተቃውመን ብነነሳ ኣንተማ ትግሪ ወያኔ፣ ኣንተማ ኣሮሞ ኦነግ፣ ኣንተማ ኤርትራዊ ሻእብያ እያላቸሁ የከፋፈላች ሁት እናተ የኣማር ሙሁራን ፕ/ር ለማ፣ ዶ/ር ጌታቸው፣ የሆላንዱ ዶ/ር ኣይደላችሁም እንዴ? የራሳችሁ ቤት ሳታጸዱ ምን ነው ወደ ተስፋየ?
    በቤተ ክርስትያን ስር ተሁኖ ኣሰራሮችን እንዳይስተካከል፣ ምእመናኑ እንዳይበተንና ለውጭም ተጠቂዎች እንዳንሆን ሳታስቡ የግላቹሁ ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ ኣቡነ መርቆርዮስ ወደ ውጭ ስባቹሁ ቤተ ክርስትያን ለሁለት ከፈላቹ ሁ፣ በዘር፣ በቃንቃ መሰባሰብ ኣራመዳቹሁ፣ ኢህአዴግም ኣራመደው ኣቀጣጠለው፣ ሌሎችም ለህልውናቸው ሲሉ፣ የእናንተ ስድብ ከመስማት፣ መሰባሰብ ተጀመረ።
    ኣብራሃም ያየህም ከተሞክሮው ከሱዳን ጀምሮ እስከ ኣዲስ ኣበባ ከዛም ወዳ ኣፍሪካ እንዲሁም ኤርትራ ያየው የሰማው የታዘበው ውስብስብ ሁኔታዎችን በማጤን ለማንም ሳይፈራ በግልጽ የመሰለውን ይሻላል ያለውን መፍትሄ https://zehabesha.info/archives/8786 በማቅረቡ ጥቃታችሁን እንደ ተስፍየ ወረዳችሁበት። ችግራችሁ የሌሎችን ብሶት ምሪት መገናዘብ ኣለመፈለጋችሁ ነው። እናንተ ብቻ የምትሉትን እንዲፈጸም እንጂ ተመካክራችሁ ማእከላይ መፍሄ መሻት ከምታስቀድሙ ኢትዮጵያ ብትከፋፈል ደንታች ሁ ኣይደለም፤ ለዚህ ኣይደለምን ኣቡነ መርቆርዮስን ወደ ገዳም ሳይሆን ወደ ስደት በኬንያ ኣድርገው እንዲሰደዱ ያደረጋችሁት።
    ጃዋር መሓመድም ቢሆን በቃለ መጠይቅ እንደገለጸው በተለይ በዲሲ ኣከባቢ ኣብሮ ለመስራት መኩሮ ግን ማህበራዊ እንቅስቃሴው የኣንድ ብሄር ብቻ ሁኖ እንዳገኘው ተከባብረህ መስራትም እንዳላየ ተናግሮ ሲያበቃ እናንተ ግን ኦሮሞኖቱ ኣስቀደመ ብላችሁ ወረዳችሁበት፣ መነሻውን መግለጽ ኣልፈለጋችሁም፣ ሌሎች ቅሪታዎች ላይ መጻፍ ኣልፈለጋችሁም፣ ብልህ ስለሆነ ለማቃለል ተነሳሳችሁ፣ ለተስፈየም ለኣብርሃምም ለሌሎችም እንደዛ ናችሁ።
    እንድያውም የተስፈየን ጽሁፍ በድራማ ተሰርቶ ቢቀርብ ምን ኣዲስ ነገር ኣለው። የደረሰብን የተፈጸመብን ትውልድ እኮ ኣለን። በደርግ ወላጆቻችን ተረሽነውብን ያደግን ኣለን። በሀይለስላሰ የራያ ድብደባ የመቱብን ትውልድ እኮ ኣለን። የዓድዋ በጣልያን ድል እንደምን ኣስታውሰው፣ ኣጼ ምንሊክ መረብ ምላሽ ለጣልያን መሸጣቸው እኩል እናስታውሰዋለን፣ እናንተ ግን የመረብ ምላሽ እንዲነሳም ኣትፈልጉም፣ ታድያ እንዴት ብለን እንስማማለንና።
    እናንተ ሌላውን ደብቃችሁ ያሰኛችሁን እንደምትጽፉ ተስፋየም የተፈጸመ ድርጊት የመጻፍ ሙሉ መብት ኣለው። እናትተ በዛን ግዜ እንደተፈጸ መኮንናችሁ መግለጽ ነው፣ ያኔ እኛም ይቅር ብለን ኣብረን ለምስራት እንችላለን። ወደ ኣባቱ ኤርትራ ዘመተ እያላችሁ እነ ጉንበት 7 ከኢሳያስ ጋር መተባበር ትደግፋላችሁ። በዚህም በዝያም የናንተ ግዜ ኣብቅተዋል ስለዚህ ተከባብረን እንኑር። ተከባብረን ስርዓት እንመስርት። ለህግ የበላይነት እንቁም። ሌላው እንደ ታሪኩ ይገለጻል, ይጻፈል, ይደረሳል, እናውቀዋልን እንማርበታለን እንዳይደገም ይኮነናል ይረጋገጥበታል።
    ገሪ ወዲ ሃገር.
    11/30/2013

  5. it seems like somebody is treatened by the wit and cleverness of smart politician. Mr Abrham Yayeh. Mr. Abrham cares….. he is the first ETHIOPIAN patriot to educate us about shabiya and woyaness grand plan…..so i would razr listen his reasons than your nonesense comment.
    truz is to stand strong,evenif you r alone.

  6. @dh what are you talking about? Where do you bring that colonisation from? Your OLF dirty politics has failed miserably for over the last five decades which is ridiculous and will continue to fail in the years to come whether you like it or not. By the way forget Finfine and can you tell me the legitimate boundary of your Oromia? TPLF created ambitious and imaginary map of Oromia is total fake. Do you think south nation and nationalities whose territories are included in the contemporary oromia will give you their concession to take their land. What about the future destiny of kemissie-Oromos in the Amhara province of Wollo. Do you also try to think about the reaction of Somalis towards Oromos if the Bale and Harer Oromos decide to separate themsves from the rest of Ethiopia I am quite sure they will be invaded by somalies the same day you declared independence and flocking back to the rest of Ethiopia as refugee. So when you think of separation prepare for any eventualities from within and neighbouring notorious somalies. One thing I can assure you is that no one in Ethiopia except Woyanes and OLF embraces territorial demarcation of fake regions. We need to claim our historical provincial boundaries back soon after we remove TPLF gov.

    • The kids are ready when the oldies are done which you transformed to amharanized oromo by keeping them in darkness and ignorance, you will see the real heat. Born freeman or die seeking it. You are also not free by the way because as long as there are people subjugated in that country you will never be free. We will free you from your miserable life too.

    • The main thing is to know where to shoot. I am sure many don’t have any problem with Somalia. They have ambition and they tried it when your people kept us in darkness out of the interaction, education and power with the world Today it is different with Qubbe generation, I know but that can be dealt. The other thing is my main enemy starts from the north and Somalia is at the end of the list. You will see Yougosalivia or USSR kind of civil war once the defeated unitary system come back. This is if? Don’t worry about the south. Remember this time south, oromo and tigre (Except Mr. Abraham Yayeh lol) can not be a foot soldiers for you and they all shoot at u

  7. To avoid ethnic bash is to respect all ethnics and to have a law that protects and treats everyone equal. Anything less, everyone will carry a gun and Ethiopia will become a house mess. We need enlightened people who can do that. It is wrong to target any group based on elites. The amhra elites playing negative roles because they are chasing everyone whom they do not like. For example, they chased Jawar because he said he is Oromo first? They become mad. They must learn how to accommodate other people indentity. You can force anyone to think the way you think. Ethiopia is made of ethnics and if there are no ethnics, there will never be Ethiopia. And indentifiying people their ethnics must not be considered as a taboo and crime. Elites are destroying either inside or outside. The curse of Ethiopian the Ethiopians elites and the worst are the amhara elites because they do not know how to communicate with other Ethiopians because they think they are the only who give and take Ethiopianism and this is driving people away from Ethiopianism. We need people who believe in equality than in bullying and chasing people because they do not like them. you can bring peace by criminalzing and demonizing others. Time to think broader and rationally than being driven by narrowism.

Comments are closed.

Share