“በሣዑዲ ዐረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመዉ ዘግናኝ እና አረመኔአዊ ተግባር የወያኔ የግፍ አገዛዝ ውጤት ነዉ” – ሞረሽ

ወደአረቡ ዓለም በስደት በሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ እና በ21ኛው ክፍለ-ዘመን ይፈፀማሉ ተብለው የማይታሰቡ ግፎች መፈፀም ከጀመሩ ከሃያ ዓመታት የማያንስ ጊዜ አስቆጥረዋል። በተለይ ግን ሰሞኑን በሣዑዲ ዐረቢያ በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እህት ወንድሞቻችን ላይ በመፈፀም ላይ ያለው ዘግናኝ እና አረመኔአዊ ተግባር ከዚህ በፊት ከተፈፀሙትም እጅግ ይብሣል። ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያውያን ይህንን ድርጊት ያየነው እና የሰማነው እጅግ መሪር በሆነ የሐዘን እና የቁጭት ስሜት ነው።
የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ብቻ ሳይሆን ፣ ከኢትዮጵያ የበቀለን ማናቸውንም ነገር ሁሉ ሳያጠፋ እንደማይመለስ መናገር ነብይነትን አይጠይቅም። ለዚህም ዕቅዱ ተግባራዊነት አገር ተረካቢ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ወጣት ትውልድ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት የተለያዩ የጥፋት መረቦችን ዘርግቷል። ከእነዚህ የጥፋት ድሮች አንዱ ተግባሩ ወጣት ኢትዮጵያውያንን በአገራቸው ሠርተው እንዳይኖሩ በማድረግ በኑሮ አማርሮ ከአገር ማሰደድ ነው። ከአገር ለሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን ዋና አስተላላፊዎች ወያኔዎች እንደሆኑ አገር ያወቀው ፣ ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። በዚህ ረገድ በዘመናዊ ባርያ ፍንገላ ወደአረቡ ዓለም ለሚሸጡት ኢትዮጵያውያን ደላላ እና ባርያ ፈንጋይ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ እንደሆነ ይታወቃል። ባለፈው ዓመትም የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ወደ ሣውዲ ዐረቢያ ብቻ በወር 40 ሺህ ኢትዮጵያውያት ልጃገረዶችን በባርነት ለመሸጥ ተስማምቷል። የተሸጡት ኢትዮጵያውያን በአረቡ ዓለም ከሰውነት ተራ ወጥተው ፣ ለኅሊና የሚከብድ የግፍ ጽዋ እየተጎነጩ ፣ ለድሃ ቤተሰቦቻቸው የዕለት ጉርስ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለመላክ ይጣጣራሉ። ሆኖም በዘመናዊ የባርነት ሠንሰለት መታሰራቸው አልበቃ ብሎ ፣ እንዲህ ዓይነቶቹ አሰቃቂ እና ዘግናኝ ወንጀሎች “በጌቶቻቸው“ በአረቦች እጅ ሲፈጸም ማየቱ ከኅሊና የማይጠፋ ብሔራዊ ስብራትን ይፈጥራል።
የድርጊቱን ሁኔታ ለተገነዘበው ፣ ኢትዮጵያውያን አገር እና ወገን የሌለን ፣ ማንም እንደፈለገ የሚያደርገን ፣ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ ተለይተን ባይተዋሮች የሆንን ፣ የበደሎች ሁሉ በደሎች ተሸካሚዎች እንድንሆን ዓለም በሙሉ የፈረደብን ይመስላል። የሌላው ዓለም ሕዝብ አድማ እና ቸልተኛነት ሣያንስ እኛም መከራውን ለመቋቋም አንድነቱ እና ኅብረቱ የሌለን ነን። ምናልባት «አምላክም ይህን ዓይነቱን መከራ እና ስቃይ እንድንቀበል ያደረገን በእኛ አማካይነት የሰውን ልጅ ሁሉ ሊያስተምርበት የሚሻው ተዓምር ኖሮት ይሆን?» ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን። «እንዲህ ዓይነቱ ግፍ ለምንድን ነው ተደጋግሞ የሚደርስብን?» የሚል ቁጭት እና ንዴት የቀላቀለ ስሜት ያጣነው ለምን ይሆን? ምን እስክንሆን ነው የምንጠብቀው?
ሠሞኑን የምናየው ድርጊት በትግሬ-ወያኔ የአገዛዝ ዘመን ሲፈፀም የመጀመሪያው አይደለም። እንዲያውም ዘረኛው ወያኔ በአገር ውስጥም በተለያዩ ሥፍራዎች ኢትዮጵያውያንን በግፍ ሲጨፈጭፍ መኖሩን እናውቃለን። ስለዚህ ሠሞኑን በሣዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ ሲፈፀም ለምናየውም ሆነ ከዚህ በፊት በወገኖቻችን ላይ ለደረሰው እልቂት እና መከራ መበራከት ዋናው ተጠያቂ ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን ልንዘነጋው አይገባም። በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነን ፣ ይህንን አገር ፣ ትውልድ እና ታሪክ አጥፊ የአገዛዝ ቡድን ከጫንቃችን ላይ መንጭቀን መጣል እስካልቻልን ድረስ መከራችን እና አሣዛኝ አሟሟታችን ፈጽሞ አይቆምም። ስለዚህ እያንዳንዳችን የተሸከምነውን ብሔራዊ ውርደት በመጣል፤ የመከራው እና የሥቃዩ ገፈት ቀማሽ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ወገናችንን ደም የምናፍሰው እና እንባውን የምናብሰው ይህን ዘረኛ ቡድን ከሥልጣን መንበሩ አሽቀንጥረን ስንጥል ብቻ ነው። ስለዚህ ደጋግሞ ማልቅስና መበሳጨት ብቻውን መፍትሔ አይሆንም። ይልቁንስ ተገቢው መፍትሔ እልክን ቋጥሮ ፣ ኃይልን አሰባስቦ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ላይ በአንድነት መዝመት ብቻ ነው።
የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በትግሬ-ወያኔ ደላላነት እና ሻጭነት ፣ ወደ ሣውዲ ዐረቢያ በዘመናዊ ባርነት ተፈንግለው ፣ በአሠሪዎቻቸው በሣውዲ ዜጎች ግድያን ጨምሮ አሰቃቂ ግፍ የተፈፀመባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ጉዳይ የሚመለከተው በኢትዮጵያውያን ላይ በአጠቃላይ ሆን ተብሎ እንደተፈጸመ ብሔራዊ ጥቃት ነው። የሣውዲ መንግሥት እና ሕዝብ ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ፣ በኢትዮጵያውያን ላይ ለሚፈፅሙት ወንጀል ዛሬም ሆነ ለወደፊት ተጠያቂ እንደሆኑ ሊገነዘቡት ይገባል። በተለይም የዓለም ማኅበረሰብ ድርጊቱን በዝምታ ቸል እንዳይለው ፣ በዓለም ዙሪያ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በአንድነት ድምፁን ሊያሠማ ይገባል። ይህንን በማድረግ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ እና በሣዑዲ ዐረቢያ መንግስት ላይ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ እንዲቀጣጠል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በተጎጂ ወገኖቻችን ስም ጥሪውን ያቀርባል። በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ወገኖቻችንን ለመታደግ ከሚንቀሣቀሱ ኃይሎች ጎን በመቆም አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በአፅንዖት ይገልፃል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
የእህት ወንድሞቻችን ደም የውሻ ደም ሆኖ አይቀርም!
ሥቃይና መከራን ከሕዝባችን ጫንቃ ለማውረድ በአንድነት እንነሣ!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስብሰባ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

 

[gview file=”https://zehabesha.info/wp-content/uploads/2013/11/MWAO_V2No3_ረቡዕ-ኅዳር-፬-ቀን-፪ሺህ፮-ዓም_Wed-13Nov2013_በሣዑዲ-ዐረቢያ-በሚኖሩ-ኢትዮጵያውያን-ላይ-የሚፈጸመዉ-ዘግናኝ-እና-አረመኔአዊ-ተግባር-1.pdf”]

2 Comments

  1. Realy the curunt amara dem ara oposition trying to preach about freedom and peace but twenty years ago the amara were killing the oromo, tigray,sidama and gurage people for no resone, just for asking basic right….and forcing the victum family to pay for the bulet $50 birr and to take the body. more than $500 birr(one year salery) for each body most familise loose more 3 ppl.now they were a peace maks to fool the ethiopian ppl.all of this crime dune not by the durg but by the amara ppl 100 % of the generals were amaras….

    • @freeoromia PPL like u cannot fool us. u r either dedeb woyane or bloodthirsty, never_able_to_learn OLF. u can never represent the decent oromo ppl.

Comments are closed.

Share