ስለእግራቸው ውጤት (የስንኝ ቋጠሮ ለብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች) – ከፋሲል ተካልኝ አደሬ
ያልከውን አላልኩም..ሰማህ ወይ ወዳጄ? እንዴት እበላለሁ?..እጄን በገዛ እጄ:: ክብሬን አላቀልም..እንደምን አድርጌ? እንደሌለ አውቃለሁ.. የቁሳቁስ እንጂ..የጀግና አሮጌ:: መቼም..መቼም..መቼም አልዘነጋ የናቤን..የማሞን..ክብርና ዋጋ:: እንዳልከው በእግራቸው..በዓለም የነገሱ ሁሌም የሚኖሩ..በታሪክ ሲወሱ ሕያው ጀግኖቻችን..መቼም አይረሱ!!! ሰማህ ወይ ወዳጄ?