በአውሮፓ የተባበሩት ኢትዮጵያውያን የተግባር ቡድን(እንቅስቃሴ) መግለጫ

በአውሮፓ የተባበሩት ኢትዮጵያውያን የተግባር ቡድን(እንቅስቃሴ)
United Ethiopians Action group in Europe

በአመስተርዳም ከተማ የአውሮፓ አቀፍ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ዝግጅትን(ፌስቲቫል)በተመለከተ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ጥሪና መግለጫ

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓም(17-07-2023)

ለሰላምና ለአንድነት ብሎም ለዴሞክራሲ ሥርዓት መስፈን የበኩሉን ለማበርከት ከላይ በተገለጸው ስያሜ በቅርቡ ከተለያዩ ያውሮፓ አገሮች በተውጣጡ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ስብስብ በአገራችን ውስጥ የሚካሄደው ጎሳ ተኮር መንግሥታዊ የፖለቲካ ምስቅልቅል ሁኔታ በአገራችንና በሕዝቧ ላይ የሚያደርሰውን በደልና ጥፋት በሚችለው አቅሙ በአውሮፓ ውስጥ ለሚገኙት ልዩልዩ መንግሥታዊና ሕዝባዊ ተቋማት ለማሳወቅ እንቅስቃሴ መጀመሩን በአክብሮት እንገልጻለን።ይህንን በተመለከተም በያለንበት አገር መንግሥታትና ተቋማት በአገራችን ውስጥ ስላለው ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ቀውስና በከባቢው ሊያስከትል የሚችለውን ቀጠናዊ ቀውስ የሚያብራራና በአካል ተገናኝቶም ሁኔታውን ለማስረዳት ቀጠሮ የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፏል።

በቅርቡ በአሜሪካ መንግሥት የተወሰደውን የፖሊሲ ለውጥን ተከትሎ በኦነግ ብልጽግናና በወያኔ ቡድኖች ላይ ጥሎት የነበረውን እቀባ በማንሳት የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀሎችን እንዳልፈጸሙ አድርጎ ከተጠያቂነት መሰረዙን በመቃወም ፖሊሲውን እንደገና እንዲመረምረው፣በኢትዮጵያም ላይ በተደጋጋሚ ያደረገውን ክህደት ከታሪክ ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ አሁንም ከዚያ አድራጎቱ እንዲቆጠብ፤በተጨማሪም አሜሪካኖችና አውሮፓውያን በቀጠናው ይኑረን የሚሉት ሚናና ተሰሚነት በመዳከሙና በቻይናዎች እዬተነጠቁ በምምጣታቸው ኢሳያስ አፈወርቂን አሶግዶ አጎብዳጅ ታዛዥ አመራር በማስቀመጥ የበላይነትን መልሶ ለመያዝ በሚያደርጉት ግብግብ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን የአሰብ ወደብን ምክንያት በማድረግ የመስዋእት በግ አድርገው ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ጦርነት እንዲገጥም የጠነሰሱትን የተንኮል ሴራ በማውገዝ ደብዳቤ በያገሩ በሚገኙት ኤምባሲዎች በኩል እንዲደርስ ወስኗል። የተግባር ቡድኑ በተቋቋመ በጥቂት ዕድሜው እነዚህን የመሰሉ ድፍረትና ወኔ የተሞላባቸውን እርምጃዎች የወሰደ ሲሆን ለወደፊቱም የሚያስፈልገውን ለማበርከት በቁርጠኛነት መዘጋጀቱን ለማሳወቅ ይወዳል።

በተጨማሪም በውጭ አገር በስደተኛ ስም እዬኖሩ ሆኖም ግን አሰደደን ከሚሉት መንግሥት ጋር በጥቅም በመተሳሰር ጸረ አገርና ጸረ ሕዝብ እንቅስቃሴ የሚያካሂዱትን ግለሰቦችና ቡድኖች እዬተከታተለ በማጋለጥ ሌላው አገር ወዳድ በነዚህ ባንዳና ጥቅመኞች ተታሎ ከመረባቸው ውስጥ እንዳይገባ ለማድረግ እንደሚንቀሳቀስ ለመግለጽ እንወዳለን።

እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ውስጥ የሰፈነው የጎሰኞች ስርዓት አገር ለመበታተንና ትናንሽ አገራት በጎሳ ተዋረድ ለምፍጠር የሚሠራ መሆኑን የማይረዳ አገር ወዳድ ይኖራል ብለን አናምንም።አገር የማፍረስ ዓላማውን ለማሳካት እንቅፋት የሚሆንበትን አገር ወዳድ የማጥፋት ፍላጎቱ ከፍተኛ በመሆኑ ለዚያ ሰለባ የሆነው ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት ዋልታና ማገር የሆነው የአማራውና ሌላው አገር ወዳድ በመሆኑ በነዚህ ላይ በግልጽ ከሚያደርገው እብሪተኛ ተግባር፣ጭፍጨፋና ማሳደድ በተጨማሪ አገር ወዳድ መስሎ አገር ወዳዱን ለመከፋፈል የተሰማራ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎች ያሳያሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጥብቅ ማሳሳቢያ ለወልቃይት ጠለምትና ጠገዴ! - ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (ዐሕድ)

አማራውን ለመከፋፈል በአማራው ስም የተለያዩ ድርጅቶችን መፍጠር ዋናው ሲሆን ሌላው ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ነውረኛ አገር አጥፊ ድርጊቱን ሽፋን የሚሰጥ ድግስና ዝግጅት ማካሄድ ሌላው ስልት ነው።ዘፈንና እስፖርት ከሚጠቀሱት ማዘናጊያዎች ዋናዎቹ ናቸው።

ምንም እንኳን እስፖርትና ሙዚቃ ለሰው ልጆች ጤናና መንፈሳዊ እድገት የማይናቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ባይካድም የሚደረጉበት ጊዜና ቦታ ከግምት ውስጥ ሊገባ የሚገባው ነው።ከዚያም በላይ በነማን እንደሚዘጋጅ ማወቁ ከጸጸትና ከጉዳት ያድናል።

በቅርቡ በአሜሪካ በዳላስ ከተማ የተደረገው የእስፖርት ዝግጅት ለአገራችን ሕዝብ በተለይም ለለውጥ ፈላጊው ያበረከተው ጥቅም ባይታወቅም ብዙ ወጣት ብቻም ሳይሆን አዛውንቱም የተዝናኑበት እንደነበር የወጡት ምስሎች ያረጋግጣሉ።በኢትዮጵያ ውስጥ የተናቀውና እንደነውር የሚቆጠረው፣ የሚያስቀጣውም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ፣አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሜዳውን ሞልቶት ሲውለበለብ ማዬቱም አንዱ መልካም ገጽ ነው።እንዲያ ባለው ብዙ ወጣት በተገኘበት አጋጣሚ ስለኢትዮጵያ ሁኔታ፣ስለትግሉና መደረግ ስላለበት ተሳትፎ ወጣቱ ምን ያህል ግንዛቤ አግኝቷል የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።በእኛ ግምት ግን ኢትዮጵያውያን ከመገናኘታቸው ጋር የተያያዘው የጥቅም ዘመቻ ማለትም የነጋዴዎችና የዝግጅቱ ገቢ ተቀራማቾች የዘመቱበት ሜዳ እንደሚሆን ካለፈው ታሪክና ከአዘገጃጀቱ ልንረዳ እንችላለን።በኢትዮጵያውያን ስም በእስፖርት ዝግጅት ጀርባ የሚደረግ የንግድና የዘረፋ እንቅስቃሴ ከመሆን እንደማያልፍም አስረግጠን ለመናገር እንደፍራለን።

በተመሳሳይ በአውሮፓም ውስጥ ላለፉት 17 ጊዜ ተመሳሳይ የእስፖርትና የባሕል ዝግጅት ተከናውኗል። ዝግጅቱን ከያገሩ በክበብ ስም የተውጣጡ ግለሰቦች የሚመሩት ሲሆን በተደረጉት ዝግጅቶች ያዘጋጁ አገር ተጠሪዎች በገንዘብ ዘረፋ የተጠመዱ በመሆናቸው ብዙ ውዝግብና ጭቅጭቅ እንደተፈጠረ ማንም አይክደውም።በአሁኑም ዓመት የዚያ ዘረፋ አካል የሆኑ ግለሰቦች በአመስተርዳም ከተማ የዘንድሮውን በዓል ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያሉ ነው።በአመስተርዳም ሲዘጋጅ ይህ የመጀመሪያው ሳይሆን ቀደም ባሉትም ጊዜ በዚችው ልማደኛ ከተማ ተዘጋጅቶ ዘራፊዎች በፈጸሙት ወንጀል ከኑዋሪው ማህበረሰብ ጋር በተፈጠረ ጭቅጭቅ ለረጅም ዓመት የኖረውን የኢትዮጵያውያውያኑን ማህበር ቅርንጫፍ እስከማፍረስ የደረሰ እንደነበር ለማስታወስ እንወዳለን።የዘንድሮውን ካለፉት ለዬት የሚያደርገው ቢኖር አዘጋጆቹ ከጎሰኛው የብልግና ስርዓት ጋር የተሳሰሩና ስምሪቱ ከዚያው መሆኑ ነው።ከሁለት ዓመት በፊት ኮሮና ባይመጣ ኖሮ የአውሮፓን የእስፖርት ዝግጅት በኢትዮጵያ ውስጥ እናደርጋለን የሚል ሃሳብ ነበራቸው።ለዚያም በልማደኛው ሌባ በክንፉ አሰፋ በኩል ያገር ውስጥ ባለሃብቶችን በመቅረብ ገንዘብ ለመቦጨቅ ያልተደረገ ሙከራ የለም።ለአሁኑም ዝግጅት ባለሃብቶቹ ድጎማ ሳያደርጉ የሚቀሩ አይመስለንም።ይኽው ሌባበአገር ውስጥ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ በመነሳት ከኦነግ የእስፖርትና ባሕል ሚኒስትሩ ከቀጀላ መድረሳና ከሌሎቹ ጋር ሳይማክረ እንደማይቀር ጥርጣሬያችን ከፍተኛ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዐማራ የህልውና ትግል መርህ የትግል ጥሪ

2

አገራችንና ሕዝቧ ባሉበት የሞት የሽረት ወቅት ላይ አስረሽ ምችው ድግስ ማካሄዱ ከባድና አላስፈላጊ መሆኑ ባይካድም ፣ብዙሃኑ አገር ወዳድ በንጹህ ልቦና ለአገሩ ያለውን ፍቅር ለመግለጽና ፣ከተለያዬው ወዳጅ ዘመዱ ጋር ተገናኝቶ መልካም ጊዜ ለማሳለፍ በማሰብ የሚያደርገው ተሳትፎ የስርዓቱና የጥቂት ሌቦች መጠቀሚያ እንዳይሆን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

1 ለዝግጅቱ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከዬት ተገኘ?መጠኑስ ምን ያህል ነው? ከሚዘጋጅበት አገር የከተማ አስተዳደሩ በኩል የተጠዬቀና የተገኘ የገንዘብ ድጎማ አለ ወይ?ስንት?ይህንን ያነሳንበት በቀደመው ዝግጅት የአመስተርዳም ከተማ አስተዳደር ለአናሳ ማህበረሰቦች ለባሕላዊ እንቅስቃሴ ተብሎ የተመደበ ባጀት በመኖሩ በዚያ ሰበብ የተጠዬቀ ገንዘብ በአንድ ግለሰብ በልማደኛው ሌባ ክንፉ አሰፋ ኪስ ገብቶ በጭቅጭቅ ማህበሩ ከወለዱ ጋር እንዲከፍል መገደዱ ስለሚታወቅ ነው፤ማስረጃውም ይገኛል።የዚህ ሌባ ጉድ በዚህ ብቻ አያበቃም ።ለዝግጅቱ ማካሄጃ ለሁለት ቀናት ላበደረው 10,000 ኤሮ ሶስት ሽህ ኤሮ ወለድ መብላቱ ነው።በከፍተኛ የወለድ ሂሳብ በዓመት 20 %ቢከፈል እንኳን 10 000ኤሮ በዓመት የሁለት ሽህ ወለድ ሲኖረው ወለዱ በቀን ሲሰላ 5,48 ኤሮ፣በሁለት ቀን 10,96 ኤሮ ብቻ ይሆን ነበር።ይታያችሁ በጠራራ ጸሃይ 2,989 ኤሮ ሙልጭ አድርጎ በልቷል ማለት ነው።የዚህ ሌባ የወንጀል ተባባሪዎች ናቸው የአመስተርዳሙን የአውሮፓ እስፖርት ዝግጅት ግንባር ቀደም በመሆን የሚራወጡት።

ከዝግጅቱ ምን ያህል ገንዘብ ገባ?ገቢና ወጩ ምን ያህል ነው?ለምንስ ተግባር ዋለ?በየትኛውስ የሂሳብ ተቆጣጣሪ ተረጋገጠ?የሚሉት ጥያቄዎች ከዝግጅቱ ፍጻሜ በዃላ የሚነሱ ቢሆኑም እንቅስቃሴው ሁሉ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ስም ስለሆነ ሁሉም በባለቤትነት ሊጠይቅ ይገባዋል።አለበለዚያ በዝምታ ሌቦችን እያበዙና እያበረታቱ መሄድ ይሆናል።ከዝግጅቱ የሚገባው ገንዘብ የት እንደሚገባ የመጠዬቅና የመከታተል መብቱን እንዳይዘነጋ ለማሳሰብ እንወዳለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

3 አገራችንና ህዝቧ በጎሰኞች ስርዓት የሚደርስባቸውን በደል፣ጭፍጨፋ፣መፈናቀልና የአገር የመፍረስ አደጋ ላይ መሆኗን በመቃወም የእስፖርት ተቋሙ ያለውን አቋም በግልጽ በበዓሉ መክፈቻ እለት ማሳወቅ አለበት።ታዳሚው ማህበረሰብ በስልጣን ላይ ባለው አገር አጥፊ ቡድን ላይ በአጠቃላይ በጎሳ ፖለቲካ ላይ እንደ ተቋም የሚከተለው ፖሊሲ ወይም መመሪያ ምን እንደሆነ መጠዬቅ እንዳለበት ለማሳሰብ እንወዳለን።እንደማንኛውም ጊዜ እስፖርትና ፖለቲካ የተለያዬ ነው በሚል ሽፋን ማደናገር እንደማይገባ ተረድቶ ሕዝብ እያለቀና ሰላም ሳይኖር እስፖርቱ ለማን ነው? ብሎ መጠዬቅ ተገቢ ነው እንላለን።እዬዬም ሲደላ ነው! የእምነት ተቋማት ሳይቀሩ በሚታመሱበት ዘመንና ስርዓት እስፖርት ነጻ ሊሆን አይችልም የሚል አቋም አለን።በአሜሪካ የባስኬትቦል ተጫዋቾች በቅርቡ የነጭ ፖሊሶችን ዘረኛነት በሜዳ ውስጥ እንዴት እንደተቃወሙ አይተናል።በተመሳሳይ በአመስተርዳም የሚጫወቱት ክበቦች በጎሰኛው ስርዓትና በሚፈጽመው ወንጀል ላይ የተቃውሞ ትእይንት እንዲያደርጉ ጥሪ እናደርጋለን፤ሰልፋቸው ከሚጨፈጨፈውና ከሚፈናቀለው ሕዝብ ጎን መሆኑን በሜዳ ውስጥ በግልጽ ሊያሳዩ ይገባል እንላለን።ሌላው ቢቀር ሁሉም ተጫዋች ቢቻልም ታዳሚው ሁሉ በክንዱ ላይ ጥቁር ጨርቅ በማሰር የሐዘኑ ተካፋይ መሆኑን እንዲገልጽ ጥሪ እናደርጋለን።አገራችንና ሕዝባችን ሃዘን ላይ መሆናቸውን ተገንዝቦ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አንግቦ በሜዳ ውስጥ የተቃውሞ ድምጹን በማሰማት ሕዝባዊ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን።።እኛም የነሱ ሃዘንና መከራ ተካፋዮች መሆናችንን በዚህ ልናሳያቸው ይገባል።ከያገራቱ የሚመጣው ታዳሚውም የአገሩን ተጫዋቾች ያንን እንዲያደርጉ መጠዬቅና ማስገደድ ይኖርበታል።ይህ ለሚታገለው ወገናችን የሞራል ድጋፍ ሲሆን ለጎሰኛው ስርዓትና ለደጋፊዎቹ ደግሞ የማስደንገጫ ደወል ይሆናል።

በአውሮፓ የተባበሩት ኢትዮጵያውያን የተግባር ቡድን( እንቅስቃሴ)

 

1 Comment

  1. በዚህም በዚያም ሃገርንና ህዝብን ለማዳን እንቅስቃሴ መደረጉ ማለፊያ ነው። እኔ ግን ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለማዳን ጊዜው መሽቷል ባይ ነኝ። ገና ወያኔ የኤርትራን ሃገር መሆን እወቁልኝ በማለት ኤርትራ ሃገር ከሆነች ወዲህ ነገሮች ሁሉ የቁልቁለት ጉዞ እንደነበሩና አሁንም እንደሆኑ ልብ ያለው ያስተውላል። ላስረዳ። በቅርቡ በአውሮፓና በአሜሪካ ” የኤርትራ ፌስቲቫል” “የትግራይ ፌስቲቫል” በማለት ስዎች በመሰባሰብ ሲጨፍሩ፤ ሲዘፍኑ አልፎ ተርፎም ሲቧቀሱ ማየትና መስማት ይዘገንናል። ለመሆኑ ፌስቲቫል የሚለው ቃል ከየት መጣ? አዋቂዎች ቃሉ ከላቲን የመጣ ትርጉሙ ደግሞ “ፌስታ” የሃይማኖት በዓል እንደሆነ ያስተምሩናል። ያው አሁን ነገሩ ሁሉ ንግድ ሆኖ የለ ዛሬ ትርጉሙን ቀይሮ አሸሸ ገዳሜ የሚባልበትና በመንግስት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መካከል ግብግብ የሚገጠምበት በዓል ሆኗል። ልብ ላለው በኤርትራም ሆነ በትግራይ የሚያስጨፍር አንድም ነገር የለም። ግን የሚጨፍሩት ያው እንደ በፊቱ ከባለስልጣኖች ጋር የተጎዳኙና ዘመድ አዝማዳቸውን ከሃገር አስወጥተው የደላ ኑሮ በተዘረፈ ሃብት የሚኖሩት ናቸው። የትግራይ ተዋህዶ ቤ/ክ ከዋናው ሲኖዶስ በመለየት ሹመት መስጠቷን በመቃወም ብዙዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል። የወያኔ የመጀመሪያ ዓላማ እኮ መገንጠል ነው። አሁን ማን ይሙት ቄሶቹ ወያኔ ሳይባርካቸው እንዲህ ያለ ተግባር በራሳቸው ይፈጽማሉ? በጭራሽ። ነገርየው ፓለቲካ ነው። ዛሬ ከአሜሪካ ጋር ቂጥ የገጠሙት ወያኔዎች በ 3 ጊዜ ጦርነት ያስጨረሱትን የትግራይ ወጣት ረስተው በየሃገሩ መዲና በዚህም በዚያም ሰበብ እየተመላለሱ ሲናገሩና ሲደንሱ ማየት ምን ያህል በሃበሻ ምድር እውነት ሙታ እንደተቀበረች ያሳያል።
    አማራው በኤርትራው ፓለቲካ ቀንደኛ ጠላት ተደርጎ እልፎች በሰውርና በግልጽ እንዲያንቀላፉ ተደርገዋል። የኤርትራው የአማራ ጥላቻ ረገብ ሲል ከሻቢያ ጥላቻን የተቃመሰው ወያኔ በ 27 ዓመቱ የስልጣን ዘመኑ በአማራ ህዝብ ላይ ያደረገውን ክፋትና መከራ እዚህ ላይ መጻፍ አይቻልም። ወያኔ ማለት አውሬ ማለት ነው። ሌላው ስም ሁሉ ማስተባበያ ነው። ጊዜው ተለወጠ ተብሎ የኦሮሞ ስብስብ ደግሞ በወረፋ ስልጣን ላይ ሲወጣ አሁንም መከራውን የሚያየው፤ የሚሳደደው የሚሞተው የሚታሰረው አማራ መሆኑ አይናችን እያየ ነው። ቄሱ በአንድ እጁ መስቀል በሌላ እጁ ሽጉጥ በሚይዝባት ምድር መንፈሳዊ አባቶች እያሉ መለፍለፍ ከንቱ ነው። ዛሬ በትግራይ ጳጳሳት ሆነው የተሾሙት ደም አፍሳቾችና በዘራቸውና በቋንቋቸው የሰከሩ የኦሮሞ ቀሳውስት ሌላው ገጽታ ናቸው። ስለሆነም የኢትዮጵያ ጉዳይ በእኔ እምነት ያበቃ እንደ ዪጎዝላቪያ ፍርክርኩ የወጣና የሚወጣ ለመሆኑ ዛሬ የኦሮሞ ፓለቲከኞች የሚሉትን ማዳመጥ በቂ ይሆናል። ሰው በቋንቋውና በዘሩ በኮታ እንዲቀጠር በምታስገድድ ምድር እንዴት ያለ ኢትዮጵያዊነት ነው የሚፈጠረው? የለም ሰው እርሙን አውጥቶ ራሱን ከወያኔና ከኦሮሞ ለማዳን ነገ ዛሬ ሳይል መዘጋጀት አለበት። ትላንት ከወያኔ ጋር የተላተመው የአብይ ጦር አይደል እንዴ ዛሬ አማራን እያሳደደ የሚገድለው? የትምህርት ቤት ጠረጴዛዎችን ልክ እንደ ወያኔ እየፈለጠ በአማራ ክልል ማገዶ የሚያደርገው? ይህ የሚታይ፤ የሚዳሰስ እንጂ እንዲሁ በጥላቻ የሚዘራ ወሬ አይደለም። ወያኔና ኦነግ (ዶ/ር አብይ) ከአሜሪካ ጋር በመወገን ሃገሪቱን ለማፈራረስ ሴራ ካሴሩ ቆዬ። አሁን ወደ ሥራ እየገቡ ነው። ቆይተህ እይ በወልቃይት፤ በማይጠብሪ፤ በራያና በሌሎቹ የአማራ ክልሎች ማን ዘመቻ እንደሚዘምት። ራሱ የአብይ ወታደር ነው (100% ኦሮምኛ ተናጋሪ የሆኑ) ናቸው ከወያኔ ጋር በማበር የህዝቡን ሰቆቃ በማስፋት አማራን አጥፍተው ለወያኔ የሚያስረክቡት። ለዚህም ነው ለምዕራብ ትግራይ የትግሬ ጳጳስ የተሾመለት። ስለዚህ ኢትዪጵያ ኢትዮጵያ እያሉ ከመጃጃል ራስን ለማዳን መዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያን ያሉ ቀይባህር ቀርተዋል፤ ወያኔ መንጥሯቸዋል። ኦነግ እያደነ እያሰረና እየገደላቸው ነው። የወያኔና የኦነግ አንድነት እዚህ ላይ ነው። ኢትዮጵያን መጥላትና የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤ/ክ ማፍረስ። እየተሳካላቸው ነው። ግን አንድም ሰው አትራፊ አይሆንም። ይህን እውነታ ጊዜ በግልጽ ያሳየናል። ሲኦል ድረስ በመውረድ ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን ያለን ሰው በነጻነት ዴንቬር ኮሎራዶ ላይ ሲወሸክት ማየት የእውነትን መኖር ሳይሆን ሞቶ መቀበር ነው የሚያሳየው። የትግራይ ልጆች ደም ይጮሃል? የወሎ፤ የአፋርና የሽዋ ሰዎች ደም ይጣራል፤ በወለጋ በዘራቸውና በእምነታቸው እየተመረጡ ለተጨፈጨፉ ማን አቤት ይበል? ፈጣሪ በስፍራው የለም። ኢትዪጵያን ረስቷታል፡፤ አውቃለሁ በዚህ ቃል ኡ ኡ የምትሉ እንዳላቹሁ። ኡ ኡታ ብቻውን መፍትሄ አይሆንም እውነቱ ይህ ነው። ፈጣሪ የምናስብበት ጭንቅላት ሰጥቶናል። ወደ ሰማይ ከማየት ይልቅ በምድር ያለውን እውነታ ዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖትን ተገን ሳናረግ እንፈትሽ። የብዙሃን ደም ይጣራል። ፌስቲቫሉና ጭፈራው በሰው ደም የደነዘዘን ጭንቅላትና በኑሮና በሌላም ችግር ውስጥ የተዋጠን ችግር ለሰአታትም ያህል ለማስተንፈስ ካልሆነ በስተቀር ጠቃሚነት የለውም። ፌስቲቫሉ በኤርትራ፤ በትግራይ ቢሆን ኑሮ ባማረ ነበር። የሚገርመው እግሬ አውጭኝ በማለት ሃገሩንና ወገኑን ጥሎ የወጣው ሁሉ ውጭ ሃገር ላይ ሲሆን ሃገር ናፋቂ፤ የፓለቲካ ተሟጋች መሆኑ ነው። አንድ ጊዜ የሰዎች ስም ስንመዘግብ ስምህ ማን ይባላል ወንድም አለ መዝጋቢው፤ ፍርድ ያባት ስም ሲል ተዛባ ይላል መዝጋቢው የጦር ሰው ተነስቶ በጥፊ ይመታዋል፡፤ ኸረ ጌታዬ ስሜ ነው። ይኸው መታወቂያዬ በማለት ያሳየውና ለምን ስሙ እንደዚያ እንደተባለ ያስረዳዋል። የጊዜው ባለስልጣንም ስምህ መቀየር አለበት ይላል። አንድ እጎኑ የቆመ የታጠቀ ሰው ጌታዪ እሱማ ለወላጆቹ ነበር መንገር ያለበት በማለት ሁሉን ፈገግ አስደርጎ ታለፈ።
    አዎን ያለቅጥ የተዛባው ፍርድ፤ በሰዎች ላይ የሚዘንበው የመከራ ዶፍ መቼ ይሆን የሚቆመው? ሰው በዚህ ዓለም ስንት ዓመት ነው የሚኖረው? መሰዳደብ፤ መናናቅ፤ መገዳደል፤ ምቀኝነት ምን ትርፍ ያመጣል? አዎን እረዳለሁ ወያኔና ኦነግ ተጋብተዋል። ኢትዮጵያን ለመገነጣጠል ተማምለዋል። ግን ዪጎዝላቪያ ከአንድ ሃገር ወደ 6 ሃገር መከፈሏ ሰላምና ብልጽግናን እንዳላመጣ ሁሉ የኢትዮጵያን ሞት የሚሹ ሁሉ ትርፍ አልባ ቀሪዎች ናቸው። ዛሬ በሱዳን/በደቡብ ሱዳን ያለውን ማየት በቂ ይሆናል። ፓለቲካና ተከታዪቹ በቆሻሻ ክምር ዙሪያ እንደሚናከሱ የውሾች ስብስብ ነው። ስንቶች በውሸት አፈር ተመልሶባቸዋል? የስንቱ ቤትስ ፈርሷል? ስንቶችሽ ለእውነት በቆሙ ወገኖቻችን ላይ ኑሮና ቤታቸውን ሰርተዋል? ቤቱ ይቁጠረው። አሁን ባለው የዓለም የፓለቲካ ስሪት እኔን የናፈቀኝ ለጥቁር ህዝቦች መብት በዓለም መድረክ ላይ የሚፋለም እንጂ ቤቱ በራፍ ላይ ሆኖ የጎጡን ባንዲራ የሚያውለበልብ የሰፈር፤ የዘር፤ የቋንቋ ፓለቲከኛ አይደለም። ሙት ይዞ ይሞታል እንዲሉ ኦነግና ወያኔ ኢትዮጵያዊነትንና የኦርቶዶክስ ቤ/ክን በጥምረት ለማጥፋት ቆርጠው ተነስተዋል። ይሳካላቸው ይሆን? እናያለን። ለአሁን የአማራ ህዝብ በጠላት ተከበሃልና ራስህን ለመከላከል ታጠቅ፤ ተዘጋጅ። እርስ በእርስ መገዳደሉ ይቁም። ዶ/ር አብይና ወያኔ ከአሜሪካ ጋር ሆነው የሸረቡትን ሴራ በቅርቡ በግልጽ ታየዋለህ። ዋ ጊዜ እያለ ምከር። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share