September 27, 2013
7 mins read

እንደ አልባራዳይ ብርታቱን ይሰጠን (ከሎሚ ተራ)

27/09/13

አድነነ ከመአቱ: ከሻአቢያ እና ከ7ቱ ።  ተመሰገን ደሳለኝን  አመሰግኜ ነው ዛሬ መጣጥፌን የምጀምረው። ይገርማል የሰሞኑ ሐሳቤና ጭንቀቴ የነበረው በርግጥም ሰለወያኔ ሥረአት ማክተም ሳይሆን፤  ወያኔ ከተወገደ በሖላ ምን አይነት ሰርአት ነው ሊመሰረት የሚችለው ? የሚለው ነበር። በተለይ ከሻአቢያ ጋር የማበር አባዜ ከተነሣ ወዲህ እረፍት አልሰጥ ብሏኛል። ታዲያ ይህንኑ ሳወጣና ሣወርድ አድሬ፤ እንደወትሮዬ ማልጄ ተነሰቼ ድሕር ገጾችን ሰመለከት የተመሰገን ደሳለኝን ከለውጡ በሖላሰ ?” በሚለው ፅሁፉ እሰካሁን የተወጣበትንና የተወረደበትን የፖሎቲካ ድርጅቶችን እንቅሰቃሴ በቅጡ ከገመገመ በሖላ፤ የወያኔ ውድቀት አይቀሬነቱን አረጋግጦ ከሚመጠው ለውጥ ባሻገር ሊደረጉ የሚገባቸው ናቸው ብሎ ያላቸውን ጠቃሚ ነጥቦቸ ጠቆም ጠቆም አድርጓል ልብ የሚል ልብ ይበል ነው ነገሩ።

እኔም በተመሰገን  መጣጥፍ  ከሞላጎደል የምሰማማበትና በተለይም በመጨረሻው ሃሳቡ “እንደ አልባራዳይ “ የሚለውን ለመጋራት ነው። ከሻአቢያ ጋር ሕብረት ከሚለው “ከመ አቱ ፤ ከ7ቱ “ ሃሣብ መቶ በመቶ የተሻለና የሚደገፍ ነው ብዬ ሰለማምን ነውና የሚሻልበትን ብዙም ሃተታ ሣላበዛ እንደተለመደው በ 2 ሀሳብ ጥንታዊ በሆኑ ተረታዊ አባባሎችን መንደርደሪያ እያደረግኩ ነጥቦቼን ላሰቀምጥ። ምክነያቱም ነገር ቢበዛ በአኸያ አይጫንምና ነው።

ሆኖም አሁንም አንባቢያንን በአክበሮት የምለምነው፤  ያገር ጉዳይ ሆኖ የሻአቢያ ነገር አልዋጥልኸ ብሎኝ እንደዜጋ የዲሞክራሲ መብቴን ተጠቅሜ የሚሰማኛን ሃሳብ ለማካፈል እንጂ፤ ወያኔንን የሚቃወሙና የሚታገሉን ወገኖቼን በምንም አይነት ሁኔታ ማንኛውንም ድርጅትም ሆነ ኢትዬጲያዊ ወገኔን የመቃዎም አባዜ ይዞኝ እንዳልሆነ በትህትና እንድትረዱልኝ አደራ እላለሁ።

1ኛ) “አዘለም አቀፈም ያው ተሸከመ ነው:”። እነዲሉ፤-

ጫካ ገብቶ ለመታገል መወሰንም ሆነ ወደ አገርቤት በመመለሰ የሰላሙን ትግል መቀላቀል የቃላት ልዩነት ካልሆነ በሰተቀር ያው አይመሰላችሁም ? ዋናው ለመሞት መቁረጡ ላይ ነው ።  ለምሳሌ ጂ7 በሻአቢያ እርዳታ ወያኔን ለመጣል ምሁራኖችም ጫካ ገብተዋል ? ብለው ሲሉ ያው በግልፅ እንደሚታወቀው ለመሞት ወሰነዋል አፈር ላይ ለመተኛት፤ አፈር ለመብላት ብሎም ወያኒ አሰኪወገድ በቆራጥነት መታገል መሆኑን ማንም ይረዳዋል። ታዲያ ከሻአቢያ ጎን ቆሞ በሕዘብ ልብ ከፈተኛ ሰጋት ከመጣል ? በእወነት ከቆረጡ የሚሊዎኖችን ልብ ከሰጋት በማዳን በሃገር ውሰጥ መሬት ከወያኔ ጋር ፊት ለፊት እንደ ወጣት ታጋዬቹ የሚሊዎኖቹን አገራዊ ድጋፍ እያገኙ መታገል የተሻለ አይሆንም ትላላችሁ ? በርግጥ ተመሰገንም እንደጠቆመው ጂ7 በወያኔ የታገደና የተፈረደበት እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም ቅሉ የተፈረደባቸው እነማን እንደሆኑና ቁጥራቸውም ቢሆን በግልፅ የታወቀ አየመሰላችሁም ሰንት ናቸው ? ብዬ ብጠይቃችሁም እንኳን ወዲያው ትመልሡታላችሁ ግን አልጠይቅም። ዋናው ጥያቄ ደጋፊዎቹ ጋነው ያለው።  ወገኖቼ ተመሰገን በመጨረሻው መደምደሚያው ላይ የጠቆመንን ተሳትፎ እንዴት ታዩታላችሁ ? “እንደ አልባራዳይ  “ ትግሉን የመቀላቀሉ ጊዜ አሁን አይመሰላችሁም? እኔ እነደሆነ ቆርጫለሁ። እነዴት ነው የሚገባው ? ተበሎ አይጠየቅም ያው እንዳወጣጣችን ነውና።  አቤት ወያኔ ጉድፈላበት ዘንድሮ !!።

2ኛ) “ያልታደለ በሬ ሰጋው ተበልቶ ቆዳው ለከበሮ ይውላል” ። አነዲሉ፤-

በወያኔ የግፍ አገዛዝ ሕዘባችን ይኸ ነው የማይባል መከራና ሥቃይ ላለፉት 22 አመታት እንደደረሰበትና አሁንም በደሉና አፈናው፣ እሰሩም፤ ግድያውም ሆነ ሰደቱ መልኩን እየቀየረ ሂደቱ በመቀጠል ላይ እንደሆነ ያደባባይ ሚሰጥር ሆኖ ሣለ፤ እንደገና ከቀንደኛ ጠላታችንና ወያኔን ኮትኩቶ አሳድጎ በጫንቃችን ላይ ከጫነብን ሻአቢያ ጋር ወግኖ ከወያኔ ነፃ መውጣት ይቻላል ብሎ ማሰብ በጀግኖቹ ወጣት የሰላም ታጋዬች ተገዝግዞ ቢገፉት ሊወድቅ የተቃረበውን ወያኔን እንደገና እንዲያንሰራራ ያለጥርጥር መርዳት ነው። ይሕ ማለት ደግሞ በወያኔ የግፍ ሥረአት መከራውን የበላውን ሕዝባችንን እንደገና አሳሩን ማብዛት ነውና ካልታደለው በሬ ተረት ሰለማይለይ፤ ይቅርብን አይበጀንም ይቅር ። ይልቅ “እንደ አልባራዳይ  “በሙሉ ልብ የተጀመረውን እና ሊጠናቀቅ ጥቂት የቀረውን ትግል ወደፍፃሜ እንዲፋጠን በመትመም እንቀላቀል ። አምላክ ይርዳን ። ብርታትና ፅናትም ይሰጠን አሜን ! ።

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop