«አንተስ…?» February 6, 2017 ነፃ አስተያየቶች Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ( ወለላዬ ) ዓይኔን በዓይኔ ያየሁበት፣ በስተእርጅና ያገኘሁት፣ የትናንቱ ማሙዬ፣ ያሳደኩት አዝዬ የንግሊዞችን ወረራ ሰምቶ፣ በቴዎድሮስ ሞት ተቆጥቶ፣ ለምን? ለምን ሞተ? ብሎ ሲያለቅስ፣ የዓይኑን ዕንባ ላደርቅ- የልቡን መሰበር ላድስ፣ ጀግኖቻችንን ቆጥሬ- ታሪካችንን ባወድስ፣ ዕንባውን ዋጥ አድርጎ- በአትኩሮት ዓይኔን እያየኝ፣ «አንተስ…?» አንተስ!- ምን ሰርተሀል? በማለት ጠየቀኝ። እድሜ ቢደራረብ ተግባር ሳይላበስ፣ እንደዚህ እንደኔ ያስጠይቃል ለካስ! Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Previous Story [ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን] በማሸነፌ ተደስቻለሁ፣ በማሸነፌ አልተደሰትኩም !! Next Story ምጧ የተራዘመባት- ኢትዮጵያ! – ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ