July 31, 2013
5 mins read

የማለዳ ወግ. . . የሳውዲዋ ልዕልት የመብት ገፈፋ ክስና የኢትዮጵያዊቷ ጉብል አበሳ (ከነብዩ ሴራክ)

የሳውዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት እመቤት የቤት ሰራተኛቸውን በአነስተኛ ክፍያ ከ16 ላላነሱ ሰአታት በመክፈል እና የኬንያዊቷን ሰራተኛ ፖስፖርት ለባለቤቷ ባለመስጠታቸው ተከሰው በምድረ አሜሪካ ለወህኒ ከተዳረጉበት በ5 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ቢፈቱም ዛሬም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ሰምተናን። ይህንን ዜና ሳነብ ያን ሰሞን ” ጋዜጠኛ ነህ አሉ እርዳኝ? ” ብላ ከወደ ደማም በተንቀሳቃሽ ስልኬ እየደወለች የምታነባዋ ኢትዮጵያዊት እህት ፍዳ አስታወስኩ። ይህች እህት ወደ ፍትህ አካል የሚያቀርባት ፣ ከገባችበት የመከራ ህይዎት የሚገላግላት የመብት አስከባሪ አካላት አጥታለች ። ኤጀንሲዋን አነጋግራ ” በርረሽ ወጥተሽ እጅሺን ለፖሊስ ስጭበ!” ከማለት ያለፈ መፍትሔ አልሰጧትም። አጣብቂኝ የገባችው እህት መፍትሔ ታገኝ ዘንድ የሪያድ ኢንባሲ ሃላፊዎችን ተንቀሳቃሽ ስልክ ሳይቀር ሰጥች ለማረጋጋት የሞከርኩት ቢሳካም ወደ ሃላፊዎች ስልክ ደውላ ከችግሯ ይታደጓት ዘንድ ብትማጸናቸውም ተስፋ ከመስጠት አልፈው የሰሩት ስራ አለመኖሩን እንባ እያዘራች ስታጫውተኝ አሁን አሁን የኢንባሲው ሃላፊዎች ስልክ ስትደውል እንኳ ሊመልሱላት እንዳልቻሉ አጫውታኛለች ። እኔ እስከ ዛሬ ረፋዱ ድረስ ሃላፊዎችን ደውየ ለማነጋገር ያደረግኩት ሙከራ ስልካቸውን ስለማያነሱ ጥረቴ አልተሳካም !ዛሬ ረፋዱ ላይ ያነጋገርኳት ይህች እህት ዛሬ በጣሙን ከፍቷት እያለቀሰች ከገባችበት ስቃይ እታደጋት ዘንድ ተማጽናኛለች! አቅሙ ኖሮኝ ምንም ልረዳት ባልችልም አበሳዋን ግን እነግራችኋለሁ!

ይህች ግፉዕ ደራሽ ያጣችው እህት በኮንትራት ከኢትዮጽያ ከመጣች አመት የደፈነችው በያዝነው ወር መሆኑን ገልጻልኛለች። ከመጣች ቀን አንስቶ ለ16 ላላነሱ ሰአታት እንድትሰራ ስትገደድ ግልምጫ እርግጫና ስድቡን ችላ እንዳሳለፈች እያሳልፈችው ቢሆንም የማትቋቋመው ፈተና ገጥሟታል! የጋብቻ ቃል ኪዳን አስራ ሰርታ ራሷን ለመለወጥ የመጣችው እህት በአሰሪዎቿ ቤተሰቦች ጥቃት ተማራለች! ሚስት በቅናት ተነሳስታ ቁም ስቅሏን የምታሳያት ሳይበቃ የአሰሪዎቿ ሁለት ጎረምሳ ልጆች በየተራ ” እንድፈርሽ !” ብለው የሚያደርሱባትን ትንኮሳ መቋቋም አለመቻሏን እንባ እያዘራች ምርር ብላ እያለቀሰች አጫውታኛለች ! ይህን ግፍ የሳውዲ ህግና መንግስትም አይደግፈውም! ይህ መሰሉን ግፍ በሰራተኛ ላይ መፈጸም ከባድ ቀጣት ቢኖረውም ህግ ፊት የሚያቀርባት ቀርቶ ከገባችበት መቀመቅ የሚያወጣት የሃገሯ ተወካዮችን አጥታ ኑሮን በመከራ እየገፋች መሆኑን ባደረግነው ውይይት ተረድቻለሁ! የሚያሳዝነው ይህች እህት ከዚህ ሁሉ ጭንቀት በኋላ ምን ልትሆን እንደምትችል አላውቅም! ግፉ ከቀጠለ በሚፈጠር ግጭት ምን ሊፈጠርባት እንደሚችል መገመት ይከብዳል! ጎረምሶቹ በጉልበት እንድረፈርሽ ሲሏትም ሆን ሚስት በቅናት ተነሳስታ በምታደርገው የመልስ ጥቃት እንድትጠነቀቅ አበክሬ ከመምከር ባለፈ ምንም ማለት አልቻልኩም! የሳውዲዋ ንግስት ፈጸመችው በተባለው እኛ የአረብ ሃገር ነዋሪዎች መብት ረገጣውን ለምደነው “እዚህ ግባ የማይባል !” የምንለው ጥፋት በነጻዋ አሜሪካ መድር መብት ነክተዋልና ቁም ስቅላቸውን እያዩ ነው ፣ የእኛዋ እህት ደግሞ የግፍ ግፍ እየተፈጠረባት የሃገሯ መንግስ ተወካዮች እንኳ ድረሱልኝ ተብለው ተጠርተው ሊደርሱላት ባለመቻላቸው በሳውዲ ምድር አበሳዋን እያየች ትገኛለች ! የነገን ግን እንጃ. . .
ለሁሉም እኔ ያየሁ የሰማሁትን ተናግሬያለሁ !
ጀሮ ያለው ይስማ . . .!
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop