July 16, 2013
8 mins read

ዜጎችን ከማሰር ለሕዝብ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ይሻላል? ግርማ ካሳ

ግርማ ካሳ

ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም

ከአርባ ሁለት በላይ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች፣ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ዛሬ እንደታሰሩ ፍኖት ነጻነት ዘገበ።  ከታሰሩት ዉስጥ ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ አብዛኞቹም ወጣቶች ናቸው። በጎንደርና በደሴ የተደረጉ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን ተከትሎ፣  በአዲስ አበባ ከተማ 23ቱ ወረዳዎች ያሉ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ፣ በተመሳሳይ ሰዓት በወረዳዎች ሁሉ በመሰማራት፣  ሕዝቡን በማነጋገር ፔቲሽኖች ሲያስፈርሙ ነዉ ፖሊሶች ያገቷቸው።

አብዛኛዉ የአመራር አባላቱ ከጎንደርና ከደሴ ገና ባይመለሱም፣ በ23ቱም ወረዳዎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች በእኩል ሰዓት የተደረጉት፣ የአንድነት ፓርቲ በየቦታዉ ጠንካራ አባላትና ደጋፊዎች ስላሉት ነዉ። ኢሕአዴጎች እነ አንዱዋለም አራጌንና ናትናኤል መኮንን ቢያስሩም፣ ይኸዉ ከየቦታዉ አንዱዋለም አራጌዎች፣ ናትናኤል መኮንኖች  ትግሉን እያጧጧፉት ነዉ።

የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞችና ፖሊሶች፣ አበባ በማበርከት፣ ፍጹም ሰላማዊና የሰለጠነ ፖለቲካ እንደሚያራምዱ፣ በደሴዉና ጎንደር ሰልፍች ማሳየታቸው፣ በሰፊዉ የተዘገበ ጉዳይ ነዉ። በሰልፎቹ አንድ ጠጠር እንዳልተወረወረ፣ የተሰበረ መኪና፣  የተጎዳ ሰው እንደሌለ በገሃድ ተመስክሯል። አፍቃሪ ኢሕአዴግ አይጋ ፎረም ሳይቀር፣  አንድነት ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ማድረጉን አመስግኗል።

የአንድነት ፓርቲ፣  አበባ እንጂ ጥይት እንደማያበረክት፣ የሰላም እንጂ የጠብና የጦርነት ፓርቲ እንዳልሆነ እየታወቀ፣ በጎንደርና በደሴ ይሄንኑ አስመስክሮም፣ ገዢው ፓርቲ ግን አሁንም አንድነትን ሕጋዊ ፍቃድ እንዳለዉ የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን፣  እንደ «ጠላት» እየቆጠረዉ፣  በአባላቱ ላይ ዱላ እየሰነዘረ ነዉ። እርቅ፣ ሰላም፣ የዴሞክራሲ ስርዓት መገንባትን  ሳይሆን፣ ሕዝብን ማሸበርንና በጉልበት አፍኖ መግዛትን የመረጠ ይመስላል።

የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት «የድርጅታችን ጽ/ቤቶች በሙሉ እስኪዘጉና ሁላችንም እስክንታሰር ትግላቸን ይቀጥላል» በሚል ቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀሱ በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወቃል። ገዢዉ ፓርቲ ጥቂቶችን ቢያስር ሚሊዮኖችን ሊያስር እንደማይችል የሚነገሩት አንድነቶች፣ አገዛዙ የሕዝብ ትልቅ ድጋፍ በየክልሎቹ፣  ያለዉን ድርጅት ከመጋፋትና እንደ ጠላት ከማየት፣  አብሮ ለመስራትና ለእርቀ ሰላም እራሱን ቢያዘጋጅ መልካም እንደሆነ ያሳስባሉ።

የጎንደርን ደሴ ሰልፍ ተከትሎ፣ በመቀሌ ታላቅ ሕዝባዊ ሰብሰባ በቅርቡ ይደረጋል። ቀጥሎም በጂንካ (ከአርባ ምንጭ ወረድ ብሎ በደቡብ ኦሞ ዞን) እና  በወላይታ ሰላማዊ ተቃዉሞ ሰልፎች ይደረጋሉ። አዳማ፣ ባህር ዳር፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ እያለ ይቀጥላል። የመብት፣ የነጻነት የእኩልነትና  የዲሞክራሲ ጥያቄ በምንም ተዓምር ዜጎችን በማሰር አይታፈንም።

አዲስ አበባ ብቻ አይደለም። ይኸዉ በጎንደርና፣ በደሴ ታይቷል። ብዙዎች ከማያውቋት ከጂንካም የዴሞክራሲና የነጻነት ደዉል ይደወላል። የኢሕአዴግ አውራ ፓርቲ ሕወሃት እምብርት ከነበረችውም  መቀሌ፣ የጀግናዉ ኣጼ ዮሐንስ ከተማ፣  ዜጎች ከአንድነት ፓርቲ  ጀርባ በመሰለፍ ኢትዮጵያዊነትን ያወጃሉ። ለዘር ፖለቲካ፣ ለኢፍትሃዊነትና ኢሰብዓዊንት  ፣ ለሙስናና ዜጎችን የማሰርና የማሸበር ፖለቲካ ላይ ያላቸውን ተቃዉሞ ይገልጻሉ። የዴሞክራሲ ድምጽና ደዉል፣  ከሁሉም አቅጣጫ ነዉ የሚመጣዉ። ይሄን  ድምጽ ገዢዎች በፍጹም ሊያፍኑት አይችሉም። ቢፈልጉም ፣ ቢሞክሩም እንኳን አቅም አይኖራቸዉም። የሚያዋጣቸው ፀሐይ ሳትጠልቅ፣ ለሕዝቡ ፍላጎትና ፍቃድ ራሳቸዉን ማስገዛት ብቻ ነዉ። አመራሮቹ ቢያስቡበት ይሻላል እላለሁ።

የታሰሩ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎችን  ስም ዝርዝርን ለማንበብ ከዚህ ይጫኑ !

https://www.andinet.org/archives/13064

http://www.fnotenetsanet.com/?p=4953

 

ሁለት ማሳሰቢያ አለኝ ፡

  1. ለነዚህ ወገኖቻችን ያለንን ድጋፍ በተግባር እንግለጽ። የታሰሩት ፔትሽን ሲያስፈረሙ ነዉና እኛም ይሄንን ፔትሽን በመፈረም፣ ሌሎችን በማስፈረም፣ እነርሱ በአካል ለጊዜዉ የማይሰሩትን በመስራት የነጻነትን ድምጽ እናስተጋባ !
  1. ሰልፎችን፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማድረግ የራሱ የሆነ ወጭ አለዉ። በጎንደርና በደሴ አብዛኛዉን ወጭ የሸፈነው፣ የኑሮ ዉድነት እየከበደዉም፣ አገር ቤት ያለው ሕዝባችን ነዉ። በዚህ ረገድ በኢኮኖሚ የተሻለ ደረጃ ያለነዉ በዉጭ የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን ብዙ ይጠበቅብናል።

ፔትሽን ለመፈረም ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴን በገንዘብ መርዳት ለምንፈልግ ወደ ሚከተለዉ ድህረ ገጽ አድራሻ እንሂድ፡

http://www.andinet.org/

http://www.fnotenetsanet.com

http://www.thepetitionsite.com/174/997/377/millions-of-voice-for-freedom-/?taf_id=9605862&cid=email_na

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop