ስለ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ስም የሚታገሉ ፥ ከኦሮሞ ጋ መነጋገር ግድ የማይላቸው ፥ ከትግሬ ጋ ኣብረው ለመስራት የሚደፍሩ ፥ አማራ ሲባል የሚቆረቁራቸው ብዙ እንደሆኑ በደንብ እየተረዳሁ መጥቻለሁ ። ስለ ኢትዮጵያዊነት ስሰብክ ፥ በይሉኝታ ሳይሆን ስለማምንበት ነው ። በጀርባ እየሆነ ያለው ነገር ግን ፥ ከማየው ፥ ከምረዳው እና ከሚንፀባረቀው ፥ ወያኔም ሆኑ የወያኔ ጠላቶች ነን ባዮቹ ባንድነት ኣማራን በዘዴ ገሸሽ በማድረግ ውስጥ ለውስጥ የሚዶልቱት የፖለቲካ ቁማር ኣማራን እጅግ እየጎዳ ስለሆነ ይህንን ኣካሄድ ለመቃወም ብቻ ሳይሆን ኣማራን ከጥፋት ለማዳን ነብሴን ለመስጠት እንደማልሳሳ ለማሳወቅ እወዳለሁ ።
እርግጥ የፖለቲካ ተፈቃሪነት ፥ የደጋፊ እና የኣጃቢ ኣጃኢብ ( ብዛት ) ቢያሳስበኝ ኖሮ ፥ ይሄን መንገድ ይዤ መጓዝ እንዳልነበረብኝ በደንብ ኣውቃለሁ ። እርግጥ ኢትዮጵያዊነት ጌጥ ነው ፥ ኣንድ መሆን እና ኣንድ ለመሆን ማሰብ ትልቅነት ነው ። ግን ይህንን የኣንድነት ስሜት ኣማራ ሲያቀነቅን ፥ ዘሩ እየጠፋ ብቻ ሳይሆን ፥ መጫወቻ እየሆነ የ ፖለቲከኞች ቁማር መጫወቻ እንደሆነ ግልፅ ነው ። ይህንን ጥሁፍ ኣንብቦ ቡራ ከረዩ የሚለው በኣብዛኛው ኣማራ እንደሚሆን ተስፋ ኣደርጋለሁ ። ለምን ቢሉ ምን እያጠፋው እንደሆነ ስለማያውቅ ። ዘረኛ ሆንኩ እንዴ ። ልሁና! ማን ዘረኛ ያልሆነ ኣለና! ኣንድ ጥራ ኣለ ኣዝማሪው ! ኣረ ነነዌም ከጥፋት የዳነችው ባንድ ዮናስ ነው ። ኣንድ ዮናስን ጥራ!
ሁሉም የኔ ብሎ የሚለውን በልቡ ጓዳ ደብቆ በኣደባባይ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ይልሃል ። እውነት ከልባችን ኢትዮጵያዊ ብንሆን ኖሮ 25 ኣመት ወያኔን ለመገርሰስ ባልፈጀብን ነበር ። ሴረኞች መሆናችን እንጂ !
የሆነው ሆኖ
የኣማራን ህልውና ለመታደግ ፥ ኣማራ የሆነ በሙሉ በኣንድነት ይነሳ ዘንድ እጠይቃለሁ ። እንደዘገየሁ ብረዳም ፥ ለውጥ ማምጣት እንደምችል ግን ኣውቃለሁ!
ኣማራ ከ ገበጣ ሜዳነት ወጥቶ ፈረስ ጋላቢ ፥ ኣልሞ ጣይ ፥ ታግሎ ረች የሚሆነው ኣንድ ሲሆን ነው ። ይሉኝታውን ለዛሬ ኣውጥተን እንጣለው !
ሄኖክ የሺጥላ
ጥቂት ነገሮች ( ሄኖክ የሺጥላ )
Latest from Blog
“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።” መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን
ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች
\በጎንደር እና ወታደራዊ ውጥረት / ፋኖ በላሊበላ ኤርፖርት ዉጊያ/ ባለሃብቱ በአዲስ አበባ ታሰሩ የቀድሞው መከላከያ አመራር ፋኖን ሸለመ || ሻ/ቃ ዝናቡ ስላወቅሁ ደስ ብሎኛል || ጥር 7 አዲስ ቪዲዮ
በጎንደር እና ወታደራዊ ውጥረት / ፋኖ በላሊበላ ኤርፖርት ዉጊያ/ ባለሃብቱ በአዲስ አበባ ታሰሩ
አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ
አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም
ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ
የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ
ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ አንድ አባውራ ምንነቱ ያልታወቀ እህል ከገበያ ገዝቶ ለሚስቱ አምጥቶ ሰጣት አሉ፡፡ ከሰጣትም በኋላ ሚስቱ ያንን እህል ፈጭታ ቂጣ ላርግህ ብትለው፣ እንጀራ ላርግህ ብትለው፣ ገንፎ ላርግህ ብትለው … ምን አለፋህ
ወሰንየለሽ ኦሮሙማዊ ዕብደት!!
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን
የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ
ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?
የቀጠለው ውጊያና የፋኖ ድሎች / የግብፅ ፣ሶማሊያ ፣ኤርትራና ሱዳን ውሳኔ / “የህወሓት መከፋፈል ገደለን “|EN
የቀጠለው ውጊያና የፋኖ ድሎች / የግብፅ ፣ሶማሊያ ፣ኤርትራና ሱዳን ውሳኔ / “የህወሓት መከፋፈል ገደለን “|EN
ከሃይለገብርኤል አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ