March 2, 2016
39 mins read

በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ ወያኔያዊ የክተት ዘመቻ (ነፃነት ዘለቀ)

በሁሉም የሀገራችን ግዛቶች ውስጥ በወያኔ ቅልብ ጦር የጭካኔ እርምጃ ሕይወታቸውን ያጡና አሁንም ድረስ እያጡ ያሉ ወገኖቻችን ነፍሳቸውን ፈጣሪ ተቀብሎ ከፃድቃን አጠገብ እንዲያስቀምጥልን መልካም ፈቃዱ ይሁንልን፤ በየማጎሪያ ቤቶች የሚገኙ ወገኖቻችንንም ጽናቱን ይስጥልን፡፡ የመከራችንን ደብዳቤም እንዲቀድልን ሁላችን ተግተን እንጸልይ፡፡ በዘር፣ በጎሣና በሃይማኖት  ሳንከፋፈል በአንድ ላይ ጸንተን ከቆምን የወያኔ ዕድሜ ከአንድ ደቂቃም ያጠረ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ እንዳንሆን ወያኔ የሚጥልብን ደንቃራ ቀስፎ ስለያዘን ይህን ሁኔታ በእስካሁኑ አካሄድ መቀየር አልቻልንም፡፡ ስለዚህ በመከባበር መደማመጥ እንደሚኖርብን እንረዳ፡፡ መጪው ጊዜ ብዙ ደም የማይፈስበትና በተቻለ መጠን በትንሽ መስዋዕትነት ታላቅ ሀገራዊ የነፃነት ድል የምንቀዳጅበት የትግል ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡  

በቅድሚያ እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ እኔ መሰንበት ከተባለ ደህና ሰንብቻለሁ፡፡ የሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ እየተንተከተከ ያለ ይመስላል፡፡ እነወያኔዎችም ሰይጣን ይሁን እግዚአብሔር የፈቀደላቸውን ሀገርንና ሕዝብን እንደእባብ የመቀጥቀጥ ሥራ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ በአዲስ አበባ ታክሲዎች ሥራ አቁመው ሠራተኛውና ጥቃቅኑ ነጋዴ ከማለዳው ጀምሮ እየተቸገረ ነው፤ በእግሩም እየኳተነ ይታያል፡፡(የካቲት 21 ቀን 2008ዓ.ም) የደኅንነትና የአንዳንድ ትግሬዎች ታክሲዎች ግን- የአድርባዮቹም ጭምር – እየሠሩ እንደሆነ በግልጽ ይታያል፡፡ ከሕንጻውና ከንግዱ በተጓዳኝ አብዛኛው የትራንስፖርት መስክ በትግሬዎች በመያዙ ይህ ዐድማ ትልቅ ለውጥ ከማምጣት አንጻር ብዙም ፋይዳ ያለው አይመስልም፡፡ እነሱ ያልያዙትና ያልተቆጣጠሩት ነገር የለም – ዕድሩም፣ ዕቁቡም፣ ሰንበቴውም፣ መረዳጃ ማኅበሩም፣ ምኑም ምናምኑም በነሱው ቁጥጥር ሥር ነው – የጽዳትና ጥበቃ ኃላፊውንና የቆሻሻ ገንዳ ጠባቂውን ሣይቀር ብትመለከት ከአሥር ዘጠኙ ትግሬ ነው፡፡ አሥርን ካነሳሁ አይቀር በተለይ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ከአሥር ሕንፃ ዘጠኙ፣ ከአሥር ሠርግ ዘጠኙ፣ ከአሥር አውቶሞቢሎች ዘጠኙ፣ ከአሥር ሱቆች ዘጠኙ፣ ከአሥር ሱፐር ማርኬቶች ዘጠኙ፣ ከአሥር ኢንቬስተሮች ዘጠኙ፣ ከአሥር ኮንዶሚኒዮሞች ዘጠኙ፣ ከአሥር የመንግሥትና የመያድ ባለሥልጣናት ዘጠኙ፣ አብረው ከሚጓዙ አሥር ሰዎች መካከል ዘጠኙ፣ በወታደራዊ ተሸከርካሪዎች ተሣፍረው ከሚጓዙ አሥር ወታደሮች ወይም መለዮ ለባሾች ዘጠኙ፣ ምን አለፋችሁ ከማንኛውም ነገር ከአሥር … ዘጠኙ ሀብት ንብረቱ የወያኔ ትግሬዎች ሀብትና ንብረት ሲሆን – ሰዎችም ከሆኑ እነሱው ናቸው( ክርስቶስ “ሁለት ባላችሁበት ሦስተኛ እኔ አለሁ” እንዳለ ወያኔዎችም “አንድ ሆናችሁ በቆማችሁበት ዘጠኝ ሆኜ አጅባችኋለሁ” ሣይል የቀረ አይመስለኝም፡፡) በኃላፊነትና በጥሩ ደሞዝ በመያድ ውስጥ ለመቀጠር ትግሬ መሆን አለብህ፤ በኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለመቀጠር ትግሬ ሆነህ መፈጠር አለብህ፤ በመንግሥት መ/ቤቶች በተለይ በኃላፊነትና ጥቅማጥቅም ባለበት ቦታ ላይ ለመቀጠር ትግሬ መሆን አለብህ፡፡ በደርግ ዘመን “ምርጥ ምርጡ ለሕጻናት” የሚል (የውሸት) መፈክር በየግድግዳው ይጻፍ እንደነበር አስታውሳለሁ፤ ዛሬ ደግሞ “ምርጥ ምርጡ ለትግሬ ወያኔ “ የሚል በህቡዕ የሚሠራጭ (የእውነት) መፈክር ሀገር ምድሩን ሞልቶት አለ – ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈሌ ማለት አሁን ነበር፡፡ ፡ ኢትዮጵያ ከአሥሩ ዘጠኟ — አይ … ዘጠኝ ብቻ? … ከአሥሩ ዘጠኝ ነጥብ ዘጠኟ የወያኔ ጥገት ላም ናት፡፡ ሌላው በድርቅ እያለቀ ነው፡፡ ወያኔ እየተንደላቀቀና እየተምነሸነሸ ሌሎች በጠኔ እየተንጠራወዙ ናቸው – ዕድል ቀንቷቸው ከተገደሉት ውጪ ማለተይ ነው፡፡ ቧይ! ፎጁን እኮ!

በአዲስ አበባ በረንዳ አዳሪውና እሥር ቤቱን የሞላው ማን ነው? ዐማራውና በገዛ የጋ ሀገሩ ባይተዋርና ከርታታ የሆነ ሌላው ዜጋ ነው፡፡ … በየዝጉብኝ ቤቱ የእንግሊዝ ዊስኪና የስዊድን/የራሽያ ቮድካ ሲጨልጥ፣ ጮማ ሲቆርጥ የሚያመሽና የሚያድረው ማን እንደሆነ ዜጎች ብቻ ሣይሆኑ አየሩና መሬቱም ያውቃሉ፡፡ በየጥሩ ት/ቤቶች የሚማሩ ልጆች የትግሬዎችና የአድርባይ ነጋዴዎችና ባለሥልጣን ተብዬዎች ልጆች መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ በጫት ገረባ ደምብሸውና በቁንድፍት ሰክረው በየበረንዳው እጅብ ብለው የሚውሉና የሚያድሩት የነማን እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ አሁን ማን ነው እየኖረ ያለው? ማንስ ነው እያኗኗረና እያጣጣረ ሞትን በመናፈቅ ላይ የሚገኘው? የሀገሪቱን ሀብትና ንብረት በግል ተቆጣጥረው እየተዘማነኑባት ያሉት ወያኔዎች ብቻ ናቸው፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ የሀገሪቷን ዐይን ዐይን ቦታዎች ካለ ገልማጭና ቆንጣጭ የተቆጣጠሩት ትግሬዎች ናቸው – የዋሃኑና ለዘብተኞቹ ሣይሆኑ ብልጣብልጥ ወያኔ ትግሬዎች፡፡ ማርካቶን ያቀናች ምድረ ጉራጌ ከአዲስ አበባ እምብርት ተፈናቅላ የገበያ ማዕከላትን ብቻ ሣይሆን መላ ከተማዋን ትግሬ ተቆጣጥሯታል፡፡ ሌሎችነን በግብርና በኪራይ ፈነቃቅለው ለስደትና ለራስን ማጥፋት ክፍት የሥራ ቦታ አጋልጠው እነሱ የሁሉም አዛዥ ናዛዥ ሆነዋል – ይህን የሰው ልጅ ቅለት እያየሁ ከምኖር በበኩሌና ማን ከለከለህ እንዳትሉኝ እንጂ ሞቴን ብመርጥ ይሻለኛል፡፡ በወያኔ ትግሬዎች ምክንያት የሰው ልጅ ኅሊናዊና ሰብዓዊ ዕድገት እንዳለ ጥያቄ ውስጥ እንደገባ ይሰማኛል፡፡ “እነዚህ ‹ሰዎች› በርግጥም ሰዎች ይሆኑ እንዴ?” እያልኩ ብዙ ጊዜ እጨነቃለሁ፡፡ በአጥንትና ደም አነፍናፊነታቸው ከእንስሳትም በታች ይወርዳሉ፡፡

እኔም ዛሬ ታክሲ አጥቼ በመኪና ነው ወደመሥሪያ ቤቴ የሄድኩት – ማለቴ በልመና መኪና፡፡

ሲያልቅ አያምር ይባላል፡፡ የኛ ይሁን የነሱ ማለቂያ የደረሰ ይመስላል፡፡ ከሁለት አንድኛችን በቅርቡ አሣራችንን ማየታችን አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፡፡ በዚህ መልክ የምንጓዝበት ዘመን ማክተሚያው የተቃረበ ለመሆኑ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ አንድ ቄስና አንድ ሼህ ያንጀት ጓደኛሞች ነበሩ አሉ፡፡ ሼሁ “መምሩዋ ለመሆኑ እስቲ በነቢ ይሁንብዎና ሃቂቃውን ይንገሩኝ – ከእስላምና ከዐማራ(ከክርስቲያን ማለታቸው ነው) ማንኛቸው ይጠድቃሉ?” ብለው ቄሱን ይጠይቃሉ አሉ ዱሮ በደጉ ዘመን፡፡ መምሩም መለሱና “ኧረ በእግዝትነይቱ እንዴት ያለ ጥያቄ ጠየቁኝ ሸኽዬ – መቼስ ከሁለት አንድኛቸው እንታናቸውን ሳይበሉ አይቀሩም!” ብለው መለሱ አሉ፡፡  የዚህን ወግ ጭብጣዊ መልእክት  ወደወያኔ አምጡልኝ፡፡ እንጂ ከጽድቅና ከኩነኔ አኳያ ብንነጋገር እኔ በበኩሌ ተቋማዊ መዳን እንደሌለ ወይም ቢያንስ ሊኖር እንደማይገባ ማመን ከጀመርኩ ቆይቻለሁ፡፡ የመዳን መንገድ አንዲት ብቻ ስለመሆንዋ ደግሞ ብዙም አላውቅም፡፡ መዳኛውን አንድዬ ብቻ ያውቃል – “ሁሉም የየራሱን ሲያደንቅ እሰማለሁ፣ የኔም ለኔ ዕንቁ ናት እኮራባታለሁ.…” የምትል የቆየች የንዋይ ደበበ ዘፈን አሁን በጆሮየ ውልብ አለችብኝ – በዚህ አጋጣሚ ነፍስ ይማር ንዋይ ደበበና ኃይሌ ገ/ሥላሤ፣ ነፍስ ይማር ሠራዊት ፍቅሬና መስፍን በዙ፣ ነፍስ ይማር ሙሉጌታ አሥራተ ካሣና ገነት ዘውዴ፣ … ኦ! የክፉ ቀን ምርጥ ምርጥ ዜጎቻችንን ዘርዝሬ አልጨርሳቸውም – አንድዬ ግን የሚሣነው ነገር የለምና እርሱ ይጨርስልኝ፡፡ ወደገደለው ልሂድ እባካችሁ፡፡ ቀልድና መጠጥ ቤት ያጠፋል፡፡

ሰሞኑን ወደ ትግራይ ሄጄ ነበር – ከምር፡፡ ትግራይ ውስጥ ወንድ ልጀ ያለ አይመስልም፡፡ ሁሉም ተነቅሎ ለማያዳግም አጠቃላይ ክተታዊ የወረራ ዘመቻ ወደተቀረችዋ ኢትዮጵያ የተበገሰ ይመስላል፡፡ በተለይ በገጠር ቤቶች – ብዙዎቹ የድንጋይ ቤቶች – ተንሻፈው ተንጋደውና ፈርሰው ካለሰው ብቻቸውን ይታያሉ፡፡ አንዳንዶች ተዘግተዋል፤ አንዳንዶች ክፉኛ ፈራርሰው ወደጢሻነት ተለውጠዋል – የነማን ቤቶች እንደሆኑ ወዲያውኑ ትገምታላችሁ፤ የነዚያ ቤቶች ጌቶች አዲስ አበባ ላይ በልዩ ሊሞዚን ሲምነሸነሹ በምናባችሁ ይታዩኣችኋል – ከዚያች እልም ያለች በረሃማ የገጠር መንደር ወጥተው ከአዲስ አበባም አልፈው በቅጽበት ውስጥ እልም ወዳለ የኒዮርከና ላስቬጋስ ከተማ ሲሻገሩ ይታያሁ!  እንዲህ የሚያርገው ደግሞ ባላጋሩ ያልተማረ ትግሬ ነው፡፡ ብዙዎቹ የገጠር ከተሞች የተወረሩ ይመስላሉ፤ የሚገርመው ግን ያን ሁሉ በረሃና የድንጋይ ጫካ እያቆራረጠ በየርሻውና በየፈፋው ብቅ ጥልቅ እያለ የሚታይ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ቧምቧ አለ፤ ኦ! ትግራይ ታስቀናለች፤ ልጆቿ ክሰዋታል፡፡ ሥልኩ፣ ውኃው፣ መንገዱ፣ ት/ቤቱ፣… ሁሉም ከሞላ ጎደል ተሟልቶ ይታያል – እንደሚባለው አይደለም፤ በተንጣለለው ገደላማ ኹዳድ እንደዘንዶ ተጋድሞ የሚታየውን ወፍራም የውኃ ቧምቧ ስታዩ “ምነው ይህን መሰል ነገር በጎጃምና በጎንደር ገጠሮች ማየት በቻልኩ?” ሳትሉ አትቀሩም እንደኔ በ“ዐማራነት ልክፍት ከተነደፋችሁ”፤ ወይ ወያኔ ለካንስ ይህን ያህል ቀንድ ማነው ዐይን አውጣዎች ኖረዋል? ችግሩ ግን እነዚያ የገጠር ሥፍራዎች ሰው አይኖርባቸውም – ትግሬ ያለውስ አዲስ አበባ ላይ ነው ወንድሞቼ፡፡ አዲ አበባ ውስጥ በየትም ሥፍራ ስትንቀሳቀስ  በትግርኛ ቋንቋ የሚያወራው የሕዝብ ቁጥር ከሀገሪቱ የሕዝብ ቆጠራ ተመጣጥኖ ጋር ስታወዳድር ትግርኛ ተናጋሪው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ወያኔ ቆሜለታለሁ ለሚለው ወገን ብዙ ደክሟል በውነቱ፡፡ ቅናት አይደለም – ከሆነም በመንፈስ ቀናሁ ልበላችሁ፡፡ እንዲህ የሚያኮራ ውድብ ቢኖረኝ ብዬ ካብ መዓንጣየ – ካንጀተቴ – ቀናሁ፡፡ በፈርሳሙ ብአዴንም በኩራት ተኮፈስኩ፤ ኧረ በዐማራው በረከት ስምዖንም አምርሬ ቀናሁ! በስድብ ባቦነነኝ በአረምነው መኮንንም ቀናሁ፡፡  በዐማራው አካባቢም ስላለፍኩ ብአዴን ስላልሠራቸው የልማት ንድፎች ክፉኛ ኮራሁ፡፡ ቀንደኛው ድርጅታችን ባልሠራልን ነገር ካልተጀነንን በምን እንጀነን? ብቻ በየገጠሩ ያሉ ብዙ ትግሬዎች  ተለቃቅመው “ሪፓብሊኳ”ን በመተው ወደምድረ ገነት ወደ “ኢትዮጵያ” ሄደዋል ማለት ይቻላል – “የነብርን ጅራት አይዙም፣ ከያዙም አይለቁም” ብለው ያመረሩ ይመስላሉ፡፡ ከሞላ ጎደል ሕይወት ያላት የምትመስለው መቀሌ ማለትም መቐለ እንጂ ሌሎቹ ኦና ናቸው፡፡ ምሥጢሩ ታዲያ ወዲህ ነው፡፡ እመለስታለሁ …

ዛሬ ለዚህች ማስታወሻ መጻፍ ምክንያት የሆነኝ ነገር አለ፡፡ በመጣሁበት መኪና ውስጥ ሰዎች ሲያወሩ የሰማሁት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ሕወሓት ያመጣባትን ዳፋ ትግራይ ከፍላ ለመጨረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታትም አይበቋትም፡፡ ወያኔ ትግራይን በሰው ደም፣ በሰው አጥንት፣ በሰው ላብና ወዝ፣ በሰው ሀብት፣ በሀገር ንብረትና ወደር በሌለው ግፍ አጨቅይቷት  -እንደ እግዚአብሐየር ፈቃድ – ኢንሻአላህ – በጣም በቅርቡ መሰናበቱ ስለማይቀር ወዮ ለትግራይና ሕዝቧ!!! ለማንም ፈርቼ በማላውቀው ሁኔታ ፈራሁላት፡፡ ትዕቢትና ዕብሪት ጥፋትንና ውርደትን ቀድመው ይመጣሉና እነኚህ የዲያብሎስ ሽንቶች ሒሣባቸውን የሚያወራርዱበት ዘመን በፍጥነት ሲመጣ ይታየኛል፡፡ የኛ መጥፎ ሥራ እነሱን እንዳመጣብን ሁሉ የነሱ ግፍና በደል ደግሞ እነሱ ቀርተው ትግራይ ልትሸከመው የማትችለውን የመከራ ዶፍ እንደሚያመጣ የእግዜሩን ትተን ታሪክን ብቻ በማጣቀስ መረዳት ይቻላል፡፡ መተት ይረክሳል፤ ደንቃራ ይከሽፋል፡፡ የላላ ይጠብቃል፤ የጠበቀ ይላላል፡፡ የተራቡ አልቅቶችና መዥገሮች ወፍረውና አብጠው ይፈነዳሉ፡፡ ከብቶችም ያኔ ነፃ ይወጣሉ፡፡ የመዥገሮችና የአልቅቶች ዘመን ሲገባደድ የከብቶችና የደገኛ እንስሳት ዘመን ይብታል፡፡ ያኔን ለማየት ዕድሜና ጤና መለመን ብቻ ነው፡፡

ታዲያ ሰው የሚያስፈልገን አሁን ነው፤ ትልቅ ሽማግሌ ትግሬ፣ ትልቅ ሽማግሌ ዐማራ፣ ትልቅ ሽማግሌ ኦሮሞ የሚያስፈልገን አሁንና አሁን ብቻ ነው፡፡ ከደፈረሰ በኋላ ማቄን ጨርቄን ቢሉ ዋጋ ዘይብሉ ከምዝብሃል ኢዩ ሀወይ፡፡ ሦርያንና “ታላቋን” ሶማሊያ ያዬ በእሳት አይጫወትም እህቶቼ፡፡ እርግጥ ነው “ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ” እንዲባል የነዚህ መሬት የጠበበቻቸው ዐይነ ሥውራን ትግሬ ገዢዎቻችን አይተውት ቀርቶ አስበውት የማያውቁት እርዚቅ ውስጥ በታሪካዊ ጠላቶቻችን ሁልአቀፍ ዕርዳታ ታግዘው ሲነከሩበት ጊዜ ቀን የማይገለበጥ መስሏቸው ከሰማይ በታች የማይሠሩት የበደል ዓይነት ጠፋ – በአንድ በኩል እነሱም ያሳዝኑኛል ታዲያ፡፡ ሰው በእርኩስ መንፈስ ካልተሞላ በስተቀር መቼም እነሱ የሚሠሩትን ዘግናኝ ነገር በሰውኛ ተፈጥሮ መሥራት የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ ለይቶላቸው ዐበዱ እኮ! ምድራዊ ንዋይና ሥልጣን እስከዚህ ያሳብዳል? እንዴ፣ እንደዚያ እንደፈረንሣዩ አንድ ንጉሥ ‘after me the deluge’ (እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል …) እንዳለው ይሉኝታና ሀፍረት በጭራሽ አጥተው የለየላቸው ጅቦችና ዓሣሞች ሆኑ እኮ፡፡ እኔ እምለው ከዚህኛው ወገን ባይገኝ ወይም ለመስማት ፈቃደኛ ባይሆኑ ከነሱ በኩል “ኧረ ይሄ ነገር አያዛልቅም!” ብሎ የሚመክራቸው ሃይ ባይ ምራቅ የዋጠ ሰው እንዴት ይጥፋ? ለነገሩ በምን ጆሮ ይሰማሉና! ጆሯቸው በበቀልና በጥላቻ እንዲሁም በሀብት አራራ ያበደ ፍላታቸውን እንጂ ሌላ ነገር መች ያዳምጥና? …

እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አብሬያቸው የመጣሁት ሰዎች፡፡ በ2004 ዓ.ም አካባቢ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ አካባቢ ጥቂት ሰዎች የጨረቃ ቤት ይሠራሉ፡፡ ጥቂት ጊዜ ቆይቶ ግን ቀበሌና ክፍለ ከተማው መጥተው ያፈርሱባቸዋል፡፡ ከነዚያ ከፈረሰባቸው ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ ትግሬዎች ነበሩ፡፡ እነዚያ ትግሬዎች ወደ ክፍለ ከተማ ይሄዱና አብዚሎ ቅብዚሎ ይላሉ፡፡ የቀሪዎቹ (ባጋጣሚ ሆኖ ዐማሮች ናቸው) ጩኸት የቁራ ጩኸት ሆኖ ሲቀር እነዚያኞቹ – የመጀመሪያ ደረጃ ዜጎቹ “አይዟችሁ፡፡ …” የለም ይህን ነገር በትግርኛ ልበለው – “አጆሃትኩም አህዋትና! ወዲተጋሩ ኮይንኹምስ ዝትንክፈኩም የለን፡፡ ውፅዔት ቃልሲኩም ስለዝሆነ ንኣሃትኩም ዝከውን ነገር ብቅልጡፍ ተመኻኺርና ገለ ነገር ክንግብረልኩምኢና ቃል ንኣቱ… ብትዕግስቲ ክትፀብዩና ይግብኣኩም ድማ … ንኣሃትኩም ዘይኮነ ነገር …” አሉና እነዚያን ዐማሮች አመናጭቀው ካባረሩ በኋላ – እንዲህ ጭምልቅልቅ ያለ ነገር ስናገርና ስጽፍ ተገድጄ የወረድኩት መውረድ እየታየኝ ራሴን በራሴ እንዴት እንደምጸየፈው አትጠይቁኝ – ለትግሬዎቹ ሌላ መንገድ ፈለጉና አሁን እነዚያ ትግሬዎች ቢጠሯቸው የደነቆሩ ሚሊዮነሮች ሆነዋል -አሁን እነሱ የሚይዙት መኪና በትንሹ በ500 እና 600 ሺህ ብር የሚገመት ነው፤ “ሀ” ራስህን አድን ለጫማው በኋላ ይታሰብበታል እንደተባለው ማስታወቂያ ነው ነገሩ፡፡ ከጨረቃ ቤት ባዶ ሕይወት ሁለትና ሦስት ዓመታት ውስጥ ወደሚሊዮነርነት፡፡ እንደትግሬ ወያኔ ያለ ደደብና ደንቆሮ ቀትረ ቀላል ቡድን በዓለም ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ በነገራችን ላይ እነዚያ ዐማሮችም ከተፈረደባቸው የዘር ማጽዳትና ጭፍጨፋ ማምለጣቸውና ጨረቃ ቤት በማጣት ብቻ መታለፋቸው ብቻውን ትልቅ ጠጋ ነው፡፡ ዓለመኛ ዳቦ ቅቤ ቀቡኝ ይላል እንዲሉ ሆኖ እነዚያ ምስኪኖች አዲስ አበባ ላይ “መዘባነናቸው” በጃቸው እንጂ ሌላ ቦታ ቢሆን ኖሮ ጠገባችሁ ተብለው በአጋዚ ይረሸኑ ነበር፡፡ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ እኮ እኮ ደም አፍልቶና አንተክትኮ ወደ ጋዝነት የሚለውጥ ነው፡፡

እነፕሮፌሰር መስፍን ግን እንዳይቆጡኝ እፈራለሁ፡፡ እርሳቸው አንዲት አፓርትማ ውስጥ መሽገው የኛን የተራ ዜጎችን እንግልትና የትግሬዎችን የዱባ ጥጋብ ማየት ስላልቻሉ በፍርደ ገምድል ብይናቸው እነሱም እንደኛው አልተጠቀሙም ይላሉ፡፡ ማለቴ እኛ በትግሬ አገዛዝ እንዳልተጠቀምን ሁሉ እነሱም አልተጠቀሙም ባይ ናቸው፡፡ ሰው መቼም መስማትና ማየት የሚፈልገውን ብቻ እሰማለሁና አያለሁ ብሎ ከቆረጠ  ከዚህ ዓይነቱ ሞገደኛና ሸውራራ አመለካከቱ ፈጣሪ ነፃ እንዲያወጣውና እውነቱን እንዲያመላክተው ከመጸለይ በስተቀር ምን ማድግ ይቻላል? ሆ! ትግሬ አልተጠቀመም? ድራማዊ አስቂኝ ዐረፍተ ነገር፡፡

የባንዳ ልጆች ጉድ ሠርተውናል፡፡ የተሰባበርነው ሁሉ እንዴትና መቼ እንደሚጠገን ሳስበው ይጨንቀኛል፡፡ ኢትዮጵያ የሌሎቹም ያልሆነች ያህል ሌሎች እንዲህ ባይተዋር ሆነው ስታዩ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንደጪስ በንና ጠፋች ወይ ትላላችሁ፡፡ በርግጥም ኢትዮጵያ አሁን የለችም፡፡ ሌላው ሁሉ የትግሬ አሽከርና ገረድ ሆኖ ትግሬዎች የጠገቡ ጌቶች ሆነዋል – ማይምነት ደግሞ ትልቅና መድኃኒት የሌለው በሽታ ነው፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም ወያኔዎች ምናልባት ከማንበብና ከመጻፍ ውጪ ብዙም ያላለፉ ፍጹም ማይማን ናቸው፡፡ በዚያ ላይ ጥጋብ አይችሉም፡፡ ጥጋብ ይሆኑትን አሳጥቷቸዋል፡፡

ጥጋብን የማያውቅ ሰው ደግሞ አይግጠምህ፡፡ አስተሳሰበ ድውይ ደካማ አሸናፊ አይግጠምህ፡፡ ከአፍ እስካፍንጫው ማሰብ የማይችል “አሸናፊ ጀግና” አይግጠምህ፡፡ ብሃጺሩ ቀን አይጉደልብህ፡፡ ወያኔ ትግሬዎች ምን ዓይነት ጉዶች ናቸው በል? መጥኔ ለጤናማ ትግሬዎች! ሀፍረቱን እንዴት ይችሉት ይሆን? የ17 ዓመት ታዳጊ ከትግራይ ገጠር አዲስ አበባ መጥቶ በሣምንታት ጊዜ ውስጥ ሚሊዮነር ሲሆን የሚታዘብ ጤናማ ትግሬ በሀፍረት እንደሚሸማቀቅ መቼም ግልጽ ነው፡፡ አይ… እኔ እንኳንስ በግማሽ ብቻ ትግሬ ሆንኩ! ሙሉ በሙሉ ብሆን ኖሮ ነገን በማሰብ ከአሁኑ ነበር አንገቴን ደፍቼ በሰቀቀን የምሞተው፡፡ ውይ ወያኔዎች ሲያሳፍሩ! ሱቅ እንደገባ ሕጻን ዓይነት ሁሉንም ለራሳቸው አፍሰው ሌላውን ባዶ ሲያስቀሩ ስታዩ እነዚህ ሰዎች ምን እንደነካቸው በማሰብ ለነሱም ሣይቀር ታዝኑላቸዋላችሁ፡፡ ደግሞም እምብርት የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም፡፡ እንዴ – አንድ ሰው እኮ በልቶ ይጠግባል፤ ጠጥቶ ይረካል፡፡ ሲያመነዥኩና ሲጋቱ መዋል የጤንነት ምልክት አይደለም፡፡ ለከት የሚባል ነገር አለ፡፡ የሁሉም ነገር ዳር ድንበር አለው፡፡ ለፍቅርም ለጥላቻም ወሰን አለው፡፡

መጨረሻቸው ሦስት ክንድ ለሆነው ቦታ እነሱ 50 እና 60 ቦታ ይዘው አይረኩም – በዚያ ላይ ያልጠገቡ በመሰላቸው መስክ ማታውኑ ዐዋጅ ያወጡና ይደነግጋሉ – ትንሽ ቆይተው ደግሞ ያወጡትን ዐዋጅ በአነስተኛ ቁራጭ ወረቀት ወይም በሥልክ ቀጭን ትዕዛዝ ይሽሩታል፡፡ ለምሳሌ መሬት ከፈለጉ መሬት መውሰድ እንደሚቻል እነሱ ወስደው እስኪጨርሱ ድረስ ዐዋጅ ያውጃሉ፤ የሚፈልጉትን ያህል መሬት በየውሻቸው ስም ሣይቀር ይዘርፉና ያን ዐዋጅ ይሰርዙታል፡፡ ለነገሩ ዐዋጁ ለነሱ ብቻ እንጂ ቀድሞም ቢሆን ለሌላው አይሠራም፡፡ ዕብድና ዘመናይ እንደልቡ ነው – እነሱም፡፡

ከአንድ እንጀራ የማያልፍ ሆድ ይዘው በሚሊዮኖችና በቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ በደቂቃዎች ውስጥ ሲያገለባብጡ በዚህም አይረኩም፡፡ ከምን ተፈጠሩ? ገድለው የማይረኩ፣ በልተውና ጠጥተው የማይረኩ፣ አሥረው፣ ደብድበውና አሰቃይተው የማይረኩ፣ በሕይወት ያለን ገድለውም ስለማይረኩ ዐፅምን ሣይቀር ከመቃብር አውጥተው የሚቀጠቅጡና በዚያም ዕርካታን የማያገኙ፣ ህግን መሬት ላይ ጥለው በመደፍጠጥ መጫወቻ እስሚያደርጓት ድረስ ቢዘልቁም በዚያም የማይረኩ፣ ዐማራን ጨፍጭፈው የማይረኩ፣ ቂምን ከ40 ዓመታት በላይ በልባቸው ቋጥረው በመያዝ እየታደሰ በሚሄድ በቀልና ጥላቻ ሀገርንና ሕዝብን በታትነው የማይረኩ፣ድንበርንና መሬትን ለባዕዳን ሸጠው በሚያገኙት ሥፍር ቁጥር የሌለው ገንዘብ የማይጠግቡ፣ ዓለምን በማታለል ወደር ያልተገኘላቸው እነዚህን የሲዖል ትሎች ፈጣሪ ከየት ላከብን? ለመሆኑ እነዚህን መሰል የእሳት ጅራፎች በሺህ ወይ በሁለት ሺህ ዓመታት ስንቴ ይሆን ፈጣሪ ወደ አንድ ሕዝብ ለቅጣት የሚልካቸው? ይህ ዓይነቱስ ቅጣት አመክሮ የለውምን?

እነፕሮፍ አንዴ ስሙኝማ – ለታሪክ ምሥክርነት ትሆኑ ዘንድ መከላከያን፣ ደኅንነትን፣ ውጭ ጉዳይን፣ ፖሊስን፣ ጉምሩክን፣አየር መንገድን፣ አየር ኃይልን፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤችን፣ ንግድ ቤቶችን፣የከተማ ቦታዎችን፣ ሕንፃዎችን፣ የትምህርት ተቋማትን፣የንግድ ማዕከላትን፣ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን፣…. ለጥቂት ጊዜ ጎብኙ፡፡ ከዚያ እውነትም ለአካለ ዘረፋ የደረሰ ወጣት ወያኔ ትግራይ ውስጥ እንደሌለ ያኔ ትረዳላችሁ፡፡ መጥኔ ለወደፊቷ ትግራይ! ኹልና ጥዑይ ውልቀሰባት ተጋሩ ህጅ እዩ ብዙህ ማሰብ ዜድልየና፡፡ እዚዮም አሻታት ንኣዲና ከምዘሃሰቡ መሲሎምሲ ከመይ ገይሮም ከምዝቀተልዋ ህጅ እዩ ምህሳብን ምጭናቅን፡፡ ጊዜ ካለፈ በኋላ የፈሰሰ አይታፈስምና በነዚህ ወራዳ የባንዳ ልጆች ምክንያት ትግራይ መከራና ስቃይ ስትዝቅ ይታየኛል – አሁን ትግራይ ያለች የመሰለችው በባንዳዎቹ ልጆች ጥንካሬ ሣይሆን በፈጣሪ ቸርነት ብቻ ነው – ነገር ግን ይህ ትዕይንት እንዳለ እስከመጨረሻው አይቀጥልም – ሁልጊዜ ፋሲካ ደግሞ ኖሮ አያውቅም፡፡ ፈጣሪ ክፉዎቹም ደጋጎቹም ሁሉም ልጆቹ ስለሆኑ ለክፉዎቹም ለደጋጎቹም እኩል ዕድልን እንደሚሰጥ መረዳት ይገባል – ወያኔዎች “ደግ ናቸው” ብለን ብናምንም እንኳን “ለሁሉም ጊዜ አለው” ለማለት እንደፈለግሁም በታሳቢነት ይያዝልኝ፡፡ እናም “ክፉዎቹ ዐማሮችና ሌሎች ጭቁኖች” ተራቸውን የሚረከቡበት ዘመን በርግጠኝነት መምጣቱ አይቀርምና ከአሁኑ ሲታይ ለፍርድ የሚያስቸግር በሚመስለው የወያኔዎች ጥጋብ ትግራይና ተጋሩ እንዳይጎዱብን ከአሁኑ እንጠንቀቅ የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ የፈሩት መድረሱ የጠሉት መውረሱ ደግሞ ያለ ነው፡፡

እንደኔ ከሆነ በኅሊና ሠሌዳየ አሁን የሚታየኝ ክፉ ነገር ሲፈጸም ከማየቴ በፊት አሁኑኑ ብሞት ሞትኩ አልልም – በርግጥም ዐረፍኩ እንጂ፡፡ ሰው ሰውነቱን ለምን ይነጠቃል? ሰው በመግደልና በማሰር፣ በመዋሸትና በመቅጠፍ፣ በመዝረፍና ሁከትን በመፍጠር እንዴት ይደሰታል? ለአብነት አንድ ጭቅላ ሕጻን፣ “ዐማራ” የሚል ወያኔያዊ ታርጋ ስለተለጠፈበት ብቻ ካለምርጫው በተወለደበት ዘውግ ምክንያት ከነሕይወቱ በበደኖ ገደል የሚለቀቀው ገዳዩና አስገዳዩ ስንት ሺህ ዓመት ሊኖሩ ነው? ሌባ ጣታችንን ወደሰው ከመቀሰር ይልቅ ውስጣችንን መመርመሩም ክፋት የለውም፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ዐማሮች ላይ የደረሰው ግፍና ሰቆቃ የትኛውም በምናብ የተፈጠረ በሌሎች ማኅበረሰቦች ላይ ደረሰ የተባለ ግፍና ሰቆቃ አይወዳደረውም፡፡ ዱሮ ግፍ ተፈጽሞ ቢሆን አሁን በሚፈጸም ግፍ ሥርየት አያገኝም፡፡ ክፋትን በክፋት መመለስ መፍትሔ ሣይሆን ችግርን ማባዛት ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ዓይነት ወያኔያዊ አካሄድ ደግሞ ለሀገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፍትሔ አይሆንም፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው ወደኅሊናችን መመለስና ራሳችንን መመርመር ነው – አሁኑኑ!!

በሌላ አቅጣጫ ጅሎችና ነሁላሎች ኢትዮጵያውያን በሌለች ሀገር ሲጨቃጩ መስማት የሚገርም ነው፡፡ ጠላት ባቆመላቸው የጡት ቁራጭ ሀውልት፣ በፈጠራ ተደርሶ ዘወትር በሚነበነብ ስብከት ፣ በጠላት ሠርጎ ገቦች መሠሪ ውትወታ፣ በሆድ አዳሪዎች የኅሊናቢሶች ሸርና ተንኮል… የጋራ ትግሎች እየመከኑ የተናጠል ትግሎችም ከድጥ ወደማጥ እየገቡ እህት ነፃነት ከአድማስ ባሻገር ቆማ በምናብ ስትታይ መታዘብ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠርን እስከወዲያኛው ያስረግማል፡፡ ሥልጣን በሬኮማንዴ ውጪ ሀገር ይሄድ ይመስል መቶና ሁለት መቶ ድርጅቶችን በውጪ ሀገራት ነጋ ጠባና አንዳቸውን በአንዳቸው ላይ መመሥረቱ ደግሞ ጥቅም እንደሌለው ከታወቀ ቆይቷል፡፡ በዚህ የተበላ ዕቁብ የሚጃጃሉ ወገኖች ቁጥርም ቀላል አይደለም፡ አየ ኢትዮጵያ! የዕንቆቅልሽ ሀገር፡፡

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop