July 7, 2013
7 mins read

ወያኔና ብልሹ ምግባሮቹ

ባይሌ ደርሰህ ምህረቴ
07/07/2013

የወያኔ መንግስት በሰይጣንና በኣጋንንት ኣነሳሽነት ተከታዮችን በማሰባሰብ የኢትዮጵያን ህዝቦች ሲበድሉ፣ሲረግጡና ሲገሉ ይታያሉ ይህን ስራቸዉን በግልጽ መቃዉም ኣለብን፥ ዛሬ ወያኔወች ያደረሱት ጥፋት በቁጥር ዘርዝረን ለማስቀመጥ ቢያዳግተንም የተወሰኑትን ለመንደርደሪያ ያህል ማየት ያስችለናል፥
ኣመት ኣልፎ ኣመት በተተካ ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ ህይወት ይበልጥ ኣስጊ እየሆነ መጥቷል፥ በጦርነት በሚፈጁ ፌደራሎች ኣጭበርባሪዎች በሆኑ ፖለቴከኞች፣ግብዝ በሆነ የሀይማኖት መሬዎች፣ተነሳሽነትና ኣቅም በጎደላቸዉ ወይም ባነሳቸዉ የህግ ባለሙያወች፣ምግባረ ብልሹና ሙያዊ ስነ ምግባር በጎደላቸዉ ጋዜጣኞችና ርህራሄ በጎደላቸዉ ወንጀለኞች ተሞልታለች፥
በኣጠቃላይ በኢትዮጵያ ላይ ያለዉ የዜጎች የመብት ረገጣ ፣የኣገር ማጥፋት፣ዜጎችን የማፈናቀል፣የዘር ማጥራት፣የመሬት ነጠቃና ኣሳልፎ ለባድ ኣገር ለረጂም ኣመታት በመሸጥ ኢትዮጵያነትን ማጥፋት፥ ዘረኝነትን በማጉላት ኣንድን ብሄር ከፍ ኣድርጎ በመኮፈስ ሌላኛዉን ዘር ሙሉ በሙሉ እንደ ሂትለር እየተከተሉ በፕሮግራም ማጥፋት፥ በተፈጥሮ ሃብትና በኣካባቤ እየደረሰ ያለዉ ጥፋት፣በታሬካዌ ወይም በባህላዌ ቅርስ የደረሰዉ ውድመት፣በሃይማኖቶች ጣልቃ በመግባት ኣገረቷ ባህሏንና ሃይማኖቷን ጠብቃ እንዳትኖር ኣድርጔል፥
ወያኔ በ22 ዓመት ዉስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ ኣዋርዷል ፣ኣስከፊ የተባሉትን ክስተቶች ፈጽሟል እየፈጸመ ይገኛል ወደፌትም ይፈጽማል፥

ኣስከፌ የወያኔ በደሎች
ዘርን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል ኣሁንም እየተፈጽመ ይገኛል፣ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ የህዋት ባለስልጣናት ትዛኣዝ ፥ በጋምቤላ ፣በኦሮማያ ፣በኣማራ፣በኡጋዴን፣በኣፋርና በደቡብ ህዝቦች ላይ ኣስከፌ የዕስራት ፣ግርፋትና የጅምላ ግድያ ወንጀል ተፈጽሟል ኣሁንም ድረስ ድርጊቱ በመቀተል ላ ይ ይገኛል፥ ኢትዮጽያን የራሱ ኣድርጎ ባለማየት ከዜህ በፌት ለኣገራቸ ዉና ለህዝባቸዉ ታሬክ የሰሩትንና ልበሙሉ ጀግኖችን በተለያየ መንገድ ህዝቡን በማደናቆርና ራኣሱን ታሬክ ሰሬ መስሎ በመሳለቅ ታሬካቸዉንና ኣሻራቸዉን ኣጥፍቷኣል በማጥፋት ላይም ይገኛል፥ለዚህም የተጠቀመባቸዉ ስልቶች ከየብሄሩ በሆድኣደሮች፣በበታችነት ስሜት የተጠናወታቸዉን፣ሞገደኞችን፣በራሳቸዉ የማይተማመኑ ከሀዴዎችን ወይንም ሞለጭላጮችን፣የምንቸገረኝ ትዉልድን በመያዝ የኣገሪቱን ታሪክ፣ክብር፣ባህል፣ወግና ኣሻራ ኣጥፍተዋል በማጥፋት ላይም ይገኛሉ፥
የመንግስት ሰራተኛችን በኑሮ በማዳከም ለነጻነታቸዉ ከማሰብ ይልቅ የቀን ቅዠት እንዴያስቡ ኣድርጔቸ ዋል፣በዪንበርስቲ ያሉ መ ምህራንን በተለያዬ ጥቅማጥቅም ራሳቸዉን እንዳይሆኑ ኣድርጔቸዋል፣ገበሬወችን በዱቤ ማዳበሪያ በመስጠት መክፈል ካልቻሉ መሬታቸዉን በመንጠቅና ኣስፈራ ርቶ መግዛት፣ወጣቱን የራሱን ታሬክና ምንነት እንዳያዉቅ ገና ከት/ ቤት ጀምሮ በኣካባቤዉና በኣገሩ እንዳይኮራ መንፈሱን ሽርሽሮታል፣የሰባዉ መብቶ ች ጥሰት፣የዘር ማጥራት ከቤትንብረትንፁሀንን ማፈናቀል፣በሙስሊሙና በክርስትያኑ ላይ ኣያደረገ ያለዉ የሀይማኖት ጣልቃገብነት ግርፋት ኣስራት እንዴሁም በልማት ስምእየተፈፅመ ያለውን ገደብ ያጣ የመሬት ሽያጭ፥
ኢትዮጵያን በዘር በሀይማኖት በጎሳና በተለያዪ መንገዶች በመከፋፈልና በማናቆር እድሜዉን እያራዘመ የሜ ገኝዉ ዘረኛዉ የወያኔ መንግስት ላለፉት22 ኣመታት በስታሊናዊ የደህንነትና ወታደራዊ ሀይል ኢትዮጵያ ኣገራችንና ህዝባችንን በጉልበት ኣፍኖ እየገዛ ይገ ኛል፥በተለያዪ ተቌ ዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶ ና የሲቢክ ማህበራት ዉስጥ ወያኔ ሰርጎ በመግባትና የራሱን ተለጣፊ በማቆቋም በየግዜዉ እንዳይለመልሙ ከጎናቸዉ ሆኖ ይመነጥራቸዋል፣ኣንዳንዶችም የፖለቲካ ድርጅቶች እንደስራ ማግኛና መጠቀሚያ በማድረግ ህዝብን ከማወናበድ ኣልፈዉ የወያኔን እድሜ በማራዘም ወያኔ እንደፈለገዉ ረግጦ እንዴገዛና የውጭዉን ሽፋን በማሰመር ላይ ይገኛሉ፥
በኣጠቃላይ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሁሉንም ቅጣቶች ፈጽሟል እየፈጸመ ይገኛል ወደፌትም ይፈጸማል፣ሁሉንም ኣርጔል ያልሆነዉ የለም ስለዚህ ሁላችንም በኣንድላይ ሆነን በልበሙሉነት ሳንከፋፈል መጋፈጥ ካልቻልን እድሚያችንን ሙሉ በስቃይ እንገፋለን መከራውም ለልጅ ልጆቻችን ይተርፋል፣

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop