በዚሁ ዓመት በነበረ የብር መዳከም 38 ቢሊዮን ብር መክሰሩ ተገልጿል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2024 በአጠቃላይ የባንክ ሥራው 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ፡፡
ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር ኦዲት እንዲደረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት የተቀጠረው ኤምኤስኢ ኦዲት ሰርቪስ ኤልአልፒ (MSE Audit Service LLP)፣ የብሔራዊ ባንክን የ2024 የፋይናንስ እንቅስቃሴ ኦዲት በማድረግ ግኝቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የኦዲት ሪፖርቱ በተያዘው ሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ በብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ የባንኩን የዳይሬክተሮች ቦርድ በመወከል ተረጋግጦ መውጣቱን በሰነዱ መጀመሪያ ገጽ ላይ ተመላክቷል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ወርቅ የገዛበትና የሸጠበት ዋጋ ልዩነት መስፋት፣ ባንኩ ለመንግሥት አበድሮ መመለስ ያልቻለው
DW