ይበቃል ከአንግድህ …….የበላይ ለመሆን March 28, 2017 ነፃ አስተያየቶች Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የበላይ ለመሆን አየተሯሯጠ ሁሉም ሰዉ የራሱን መንገዱን መረጠ ሌላዉን ረግጦ መሰላል አድርጎ አምጦ ሳይወልደዉ ሊያደርገዉ ማደጎ ስም አና አድራሻዉን ቀይሮ አስቀይሮ ልያኖረዉ ፈለገ በስቃይ በአሮሮ አልያም ሊያስወታዉ ከአገር አስመርሮ አረ ለመሆኑ የዚህ ሰዉ መነሻዉ የት ነበረ ጫፉ የስልጣን ደረጃዉ ብቃቱ ሳይኖረዉ ይገባኛል ያለ ስልጣን ተፈናጦ ባደባባይ ዋለ በስዉር መርዝ ዉሸት ስንቱን አታለለ ብቃቱ ሳይኖረዉ የበላይ መሆኑ አለቃ ነኝ ብሎ በራስ መወሰኑ አኔ ነኝ አያሌ አንድህ መዳፈሩ ሰዉ ስለታጣነዉ የሚቆም ላገሩ ተነድቶ ቢገባም ሰዉ ያለ መስመሩ በዘር ቁአት ተጥዶ ያለአገር ሊጠሩ አገር ምን ያረጋል ብለዉ አንድቀሩ ነበር የታሰበዉ ወድቀዉ አንድቀሩ ሀፍረት የለሽ ነዋ አንድህ መናገሩ ጀግኖች በየቦታዉ መች ወድቀዉ ሊቀሩ ይነሳል ከጉአዳዉ ይቆማል ላገሩ ዘር በሀገሩ ነዉ ባህልም በመንደሩ ታዲያ ለምንድነዉ አንድህ መዳፈሩ ራሱን ነግሶ አግዝፎ በወንበሩ ማንም አይነካኝም ብሎ መፎከሩ ጫካ የወለደዉ ገብቶ ከመዳከሩ ሰዉ ስለታጣ ነዉ የሚቆም ላገሩ ? ቁጭት የማይዘዉ ለወገን ለክብሩ ባንድራ ጨርቅ ነዉ አያለ ሲያወራ ላገር ክብር የለሽ ምንም የማይፈራ ለሆዱ የኖረ የባንዳ ጎተራ ሁሉን ሊሸጠዉ ነው ይሄዉ በየተራ ከጫካ አፈትልኮ ከቶ አገር ሊመራ ምን ዓአምሮ ኖሮት ባገሩ ሊኮራ መቼ ብቃት ኖሮት ይህንን ሊሰራ ልሸጠዉ ነው አንጂ ሁሉን በየተራ ምንም ሳይሰማዉ ያገር ልዕልና ተረግጦ ተጥሎ ያገር ስብአና የማንነት ምንጩ ከአገር ዉጭ ሆነና የሰዉ ዉህደቱ ጥምረቱ ቀረና ከፋፍሎ ሊያስከረዉ በዘር ጎጥ ቀጠና ማስደለቅ ጀመረ ከበሮ በገና የበላይ ነኝ አለ ራሱን አንግሶ አለቃ ለመሆን ለአርባ ዓመት ደግሶ የአገር ጠላቶችን አንገት ተንተርሶ በጉያቸዉ ገብቶ የመርዝ ጉርሻ ጎርሶ የዋጠዉን ሲለቅ ሁሉም ተተራምሶ አለቃ ነኝ አለ አገር ደረማምሶ ትዉልድ አበጣብተህ ከፋፍለህ መግዛትህ ይበቃል ከአንግድህ ተቆርጧል ገመድህ የመዉደቂያህ ጊዜ አሁን ነው ሰዓትህ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email