ጥሩነሽ ዲባባ – ጠይሟ ልዕልት August 12, 2013 ነፃ አስተያየቶች Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ጠይሟ ልዕልት የሩጫው ድማሚት ሰዓት ጠብቃ ስትፈነዳ አንድም ታምራለች እንደ ጽጌሬዳ አንድም ታርዳለች እንደ ካባው ናዳ ፡፡ ጠይሟ ቀስተ ዳመና ባለብዙ ልዕልና የስንቱን አይን በረገደች ? በወቸው ጉድ በለጠጠች :: የስንቱን ልብ አሞቀች ? በፍቅር መዳፍ ጣለች :: እናትስ ትውለድ ያንቺን አይነቱን አቦሸማኔ ህዝብ የሚወድ አስተኔ ፡፡ ከአለማየሁ ገበየሁ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email