ኅዳር 7 ቀን 2018 ዓ/ም
አስተማሪ በሆነ ተግሳጽ አቋማችሁን የገለጻችሁ የመኑሴታ ካህናት አባቶቻችን ሆይ! ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ብጹዐን ናችሁ ! ትላችኋለች፡፡ አባቶች ሆይ! እንደምታውቁት ይህን አረፍተ ነገረ የወሰድኩት “ያእምር ኩሉ ለለአሐዱ ምቋመዚአሁ ወይፈጽም ግብሮ በተግሣጽ፡፡ ወይኩኑ ኩሎሙ በአሐዱ ሕሊና ወበአሐዱ መንፈስ (አ 9 294)፡፡ ከሚለው ከቤተ ክርስቲያናችን መርሆ ነው፡፡ እናንተ ያሳያችሁትን አቋም ደፍሮ የቤተ ክርስቲያናችንብ ክህነታዊ አቋም የገለጸ የለም፡፡ ይልቁንም ጦርነት በተነሳበት አገር ወታደር እየተከተለ fast food እና የጦር መሳሪያ በመቸብቸብ ትርፍ እንጅ ስለ ተገዳዩና ገዳዩ ከማይስቡ ነጋዴወች የባሱ አስመሳይ ጳጳሳት ቆሞሳትና ሰባክያን በተደራረበ የማዕርጋት ስሞቻቸውን አጅበው በህዝቡ ወቅታዊ ችግር አዛኝ መስለው የግል ጥቅማቸውን ከሚያጋብሱ አስመሳዮች እጅግ ተሽላችሁ ለተልእኳችሁ በመቆም ድምጽ በማሰማታችሁ እንኳን ለህሊናችሁ እርካታ በቃችሁ፡፡ ሲኖዶሱ ሊያደርገው የሚገባውን ሃላፊነት በመጠቆም አቋማችሁን ያሳያችሁትበት መግለጫ የሚደነቅ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ጌታችን ክርስቶስ “ዘአዝለፈ ትእግሥቶ ውእቱ ይድኅን “ እንዳለው ጀምሮ በመተው የጸደቀ የለም፡፡ —-ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ –—-መኑሰታ (1)