ሪቻርድ ኒክሰን ማሸነፋቸውን እንዳረጋገጡ ለአንዳንድ የካብኔ አባላት ሁለትም ሶስትም ሰዎች ሥም ይዘው ነበረ።እጅግ ጥቂት ለሆነ ቦታዎች ግን አንድ ሰው ብቻ መርጠዋል። ከእነዚህ ሰዎች አንዱ የተለየ ነው፤እርሱም ሄነሪ ኪሲንጀር ይባላል፤ምሁር ነው፤ይጽፋል፤ተናግር የማሳመን ችሎታው ልዩ ነው።ሀሳብ የማፍለቅ ሀይሉ የሚገርም ነው።ብዙ ምሁራንን አይተዋል፤አንዳንዶቹ መናገር አይችሉም፤ዱዳ ናቸው።አንዳዶቹ መጻፍ አይችሉም፤አንዳዶቹ ደግሞ የራሳቸው የሆነ ሀሳብ የላቸውም።ኪሲንጀር ግን ሁሉንም አሞልቶ የሰጠው ነው፤የስራ ሰው ነው፤ሁሉንም በስራ ጠምዶ፣ ሲያሰራ ውሎ አምሽቶ እኩለ ለሊት ነው ቤቱ የሚገባው።
ኒክሰን ያሰቡት ሆነ።በአዳዲስ አሠራሯችና ሀሳቦች ቢሮው ተሞላ።የመረጃ ጎርፍ ከየአቅጣጫው መምጣቱን ተያያዘው። ።ያኔ በኬኔዲ ዘመን ሲገናኙ የፒስ ኮርፕስን ሀሳብ ካቀረቡት ሰዎች አንዱ ኪሲንጀር ነበር።አሜሪካ ምንም መረጃ የላትም።ሲ አይ ኤ 30% ድርሻ ማግኘት አለበት ሲሉ ተከራክሩ።ኬኔዲ ግን ይህን ፈጽሞ ሊፈቅዱ አልቻሉም።እንዲያውም ይህን ድርጅት ተጠግቶ አንድ ሰላይ ቢያዝ የአሜሪካን ስም የሚያጠፋ በመሆኑ በዚህ ድርጅት አማካኝነት ምንም ሰላይ እንዳይሄድ አሉ።ያኔ የነኪሲንጀር ንዴት አይተዋል።አሁን ማ ትክክል እንደሆነ እየታየ ነው።
ኪሲንጀር አንድ አምስተኛ የሚሆነውን የካምቦድያን ህዝብ አጥፍቶል።የፖል ፖት ፈጣሪ ኪሲንጀር ነው።የፖለቲካ ድጋፍ ሁሉ ያደርግለት ነበር።
ሄነሪ ኪሲንጀር
የጀርመን አይሁድ የሆነው ሂነሪ ኪሲንጀር በ15 አመቱ ፣ሂትለር እልቂቱን በአውሮፓ ከመጀመሩ በፊት ነው አሜሪካ የገባው።ስለእልቂት ስለጭፍጨፋው በአይኑ ያየው ነገር የለም ማለት ነው።ከእልቂቱ ተርፈው አሜሪካ ከደረሱ ወገኖቹ የሰማው ብዙ ነገር ይኖራል።በጀርመን ህዝብ ላይ ቂም መያዙ አዋጭ አለመሆኑን ተገንዝቧል።ጀርመናዊ መሆኑ አይደለም ቁምነገሩ ለፖቲካዊ ህይወቱ ክግላዊ ስሜት ነጻ ነኝ ፤ዋናው የአሜሪካ ጥቅም ነው የሚል አቋም መያዙ ነው።
ሂትለር ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች ከመጨፍጨፉ ባሻገር እስከ 70 ሚሊዮን ለሚደርሱ ሰዎች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ ነው።ሄነሪ ኪሲንጀር ግን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ቁጭ ብሎ ሂትለር ከፈጃቸው ሰዎች ብዙ እጥፍ ጨርሷል።የሰላም የኖቤል ሽልማትን ተስገብግቦ ወስዶል።ይህ “የማይታየው ገዳይ“ በአሜሪካ ተወዶ ተፈቅዶ በሁሉም ፕሬዝዳንቶች ለምክር በህይወት ዘመኑ ሁሉ እንደተፈለገ በ101 አመቱ ህይወቱ አልፏል።
በ1969 እ.ኤ.አ ኪሲንጀር ገና ስልጣኑን እንደያዘ ላቀደው ሀሳብ ኢትዮጵያን ማሰለሉን ጀመረ።በፒስ ኮርፕስ ጋር ሰላዮችን በመደባለቅና በተለያዩ መንገዶች በማሰማራት በወዳጅ ሀገር ላይ ሪከርድ የሆነ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰላይ አሰማራ።የእንግሊዞችንም ትብብር ጠየቀ።ስለአባይ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር የሚያደርግ ቡድንም ላከ።መስቀል ክሰላጢን የሚሉት አይነት መሆኑ ነው።
የሓይለ ስላሴ መንግስት አሜሪካን ወዳጅ ሀገር በማለት ተኝቷል።አይነካንም እኛን እንደ ማለት ነው።ዳዊት ቤንጎሪዮን የያዙት የሶስት ሀገር ወዳጅነት የቱርክ የፐርሽያንና የኢትዮጽያን መያዝ ይሻላል የሚል እምነታቸውን ኪሲንጀር ገለበጠው።አረቦችን በመከፋፈል ነው አረቦችን ማሸነፍ የሚቻለን የሚል ድምዳሜ ላይ ነው የደረሰው። ወዳጅ የተባለችዋ አሜሪካ እያንዳንዱን የኢትዮጵያ ቀዳዳ አግኝታለች፤ ኢትዮጽያም ለወዳጅ ያልሆነ በማለት አስተካክላ ሰጥታለች ። ከኢትዮጽያውያውን አስፈላጊ የተባሉ ሰዎችን ይዘዋል።ብዙዎቹ ግን አድፍጠው እንዲጠብቁ የተነገራቸው ናቸው። የሀይለ ስላሴ መንግስት በ1960ዎቹ ያሳየው ምንድን ሊባል ይችላል አሜሪካ ኮሚኒስት አታረገን የሚል የዋህነት ይመስላል ።
የዮም ኩፐር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የጸጥታውንና የውጭ ጉዳይን ኪሲንጀር ጠቅልሎ ይዟል።እዚህ ላይ ብዙ የሚያስቁ ነገርች አሉ።የዮም ኩፐር ጦርነት ተጀምሮል፤የሞሳድ ባለስልጣን ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነበር፤አንድ ሰው ትንሽ ማስታወሻ ለሞሳዱ ሰው ሰጣቸው፤ጋዜጠኞቹን ይቅርታ ጠይቀው ፕሮግራሙን አቋርጠው ሄዱ፤ጋዜጠኞቹም ወዲያው የጦርነቱን መነሳት ሰሙ።እንዲህ አይነቱን ቀልድ አሁንም ከሓማስ ጋር በተካሄደው ጦርነት ተጠቅሞበታል።ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚር ናታንያሁ አንድ ቤተ እስራኤላዊ ይሁዲ በሩጫ ያደረገውን አንስተው ቀልደዋል።ቀልዱን ትተው በሙዚቃ ኮንሰርቱ የነበሩ ዜጎቻችውን ባዳኑ።
ለጠላት ትንሽ ልብ ለመስጠት ነው፤ጦርነቱ ትንሽ ተራዝሞ አስራ ሰባት ቀን ፈጀ።እስራኤል ከግብጽ የሲናይ ሰርጥን ከሶርያ የጎላን ተራሮችን ያዘች።የተባበሩባትን፣ጦርነት ያወጁባትን ሁሉ ደቆሰች።
ከጦርነት በኋላ የሰላም ስምምነት ማድረግ ወሳኝ ነው።ኪሲንጀር ዲፕሎማቶቹን ሁሉ አሰማራ።ማንም ይሳካል ብሎ አልጠበቀም።ከአረቡ አለም ማንም ንቅንቅ ያለ የለም።ክፍተት ያሳየ የለም።ኪሲንጀር ግብጾችን ወደ አሜሪካ ጋበዛቸው፤አንዋር ሳዳት ጭምር መጥተዋል።በአንድ አዳራሽ ሰበሰባቸው።ራሱን እንደ ተደራዳሪ ሳይሆን አስተማሪ መሰለ።
’’ይህ ወንዝ ናይል በመባል ይታወቃል፤በአለም ረዥሙ ወንዝ ነው።’’ አንዳንድ የግብጽ ተደራዳሪዎች እንደ መሳቅ አሉ።ይህ ሰው ምንድን ነው የሚያወራው አሉ።ግብጽ የናስር ግድብ የሚባል ከሶቬየት ህብረት ጋር በመሆን ሰርታለች።ከግብጽ አንዲትም ውሃ ጠብ አይልም፤የሰው ሀገር ውሃ አምናችሁ ነው ግድቡን የሰራችሁት።እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተናል።አባይ በተባለው ወንዝ ላይ ከሚሲሲፒ ያልተናነሰ ጥናት አድርገንበታል።የት የኤሌትሪክ ግድብ መገደብ አለበት፤የት የመስኖ ልማት መካሄድ አለበት የሚለው አጥንተነዋል።የናንተን ውሳኔ ብቻ ነው የምንጠብቀው።የሰላም ስምምነቱን ከፈረማችሁ በሀይል የተያዘው መሬታችሁ የሲናይ ሰርጥ ይለቀቃል፤በአመት የአንድ ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ይደረግላችኋል፤ ከሁሉም በላይ የናይል ወንዝ የናንተ ይሆናል።ኢትዮጵያ አንዲትም ውሃ እንዳትጠቀም እናረጋለን።ይህን ስምምነት ካልፈረማችሁ ወደ ሁለተኛ እቅዳችን እናመራለን።ለኢትዮጵያ አባይን በተመለከተ ሁሉንም እናረግላቸዋለን።ኢትዮጵያውያን ብልሆች ናችው ፤ትንሽ ከረዳናቸው ብዙ ይሰራሉ።ኢትዮጵያን የሰለጠኑና በወታደራዊ ሀይልም ማንም የማይደፍራቸው ይሆናሉ።ይሄ በናንተ ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።አስራ ሁለት ሰአት ሰጥቼአቸኋለሁ።የእናንተን ውሳኔ ካጣን የአዲስ አበባው ቡድን ስራውን እንዲጀምር ይደረጋል።ግድብ ይኖራችኋል፤ግን ያለ ውሀ በጣም ያስጠላል።የመጀመሪያ ወሳኝነቱን ለእናንተ ተሰጥቷል።’’አዳራሹ በጸጥታ ተዋጠ።
ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ አንድ ሰው መናገር ጀመረ። “ኢትዮጵያ ይህን ስምምነት እንዴት ትፈርምልናለች?’’
ኪሲንጀር ፈገግ አሉ“ኢትዮጵያ ስለዚህ ምንም አታቅም፤እሱን ለኛ ተዉት ፤ቃል ከገባነው የጎደለ ነገር ሲኖር እኛን ጠይቁን።ይህ ስብሰባ እስኪያልቅ ቢያንስ ሚስጥራችንን ጠብቁ።’’
አንዋር ሳዳት በድንጋጤ ደረቁ።የውሀ ባለሙያዎቻቸው የሚያደርጉላቸውን ገለጻ ካዳመጡ በኋላ “አዎ !ነገሩ ከባድ ነው፤ህይወቴን ሰጥቼያለሁ፤ለሀገር ሲሉ መስዋትነትን መቀበል ተገቢ ነው፤ስምምነቱን እፈርማለሁ።”
‘’ያ አላህ!እንግዲህ እፈርማለሁ እንጂ’’ኪሲንጀር ፈገግ አለ
‘’በጣም ጥሩ!የአባይ ጉዳይ በድብቅ ያዙት ፤ይህን ልንፈርምላችሁ አንችልም፤አፈጻጽሙን ግን የእናንተ ሰዎች መከታተል ትችላላችሁ’’
ቀጥሎ የሆነውን ሁሉም ያውቀዋል።የኢትዮጵያ አብዮት ፈነዳ።አንዋር ሳዳት ተገደለ።ሀይለ ስላሴ ታፍነው ሞቱ።ኪሲንጀር ኖቤል አሸነፉ።የኢትዮጵያ ሶማሌ ጦርነት ተካሄደ።በኢትዮጵያ ነጭና ቀይ ሽብር ተነሳ።የኤርትራ የነጻነት ንቅናቄ ተፋፋመ።ሴጣን ነገሰ።
ስለ ኪሲንጀር ያነሳ ግን ማንም አልነበረም
መለስ ዜናዊ
አንድ ቀን አባይ ወንዝ ፣ጉባ ላይ መለስ ዜናዊ ታየ። ‘’የአባይን ወንዝ በገዛ ገንዘባችን እንገድበዋለን።”እንቺ ንግግሩ ታዋቂ ሆነችለት።ግድቡን ሲመርቅ ላየ ማንኛውም ሰው ጭንቅላት የሚመጣ ጥያቄ አለ።ብሄርተኞች ያልተገኙበት ቦታ መገኘታቸው ገርሞታል። ፤’’አባይን የደፈረ መሪ ‘’ጥሩ ስም ሰጥተውታል።
መለስ ዜናዊ እ ኢ አ 1981 ላይ ስብሃት ነጋ ቁልፍ ስልጣኑን ለመለስ ሰጠው።’’ኢትዮጵያ እንደ አንተ ያለ ጭንቅላት ያለው ሰው ነው መመራት ያለባት።”ይህ የሀገሪቱን ትልቁን ስልጣን በገዛ ፈቃዱ የለቀቀ ሰው አንድም ስልጣን በኢሕአዲግ ዘመን አልነበረውም ይሉናል።ይህ ውሸት ነው።ስብሃት ራሱን የሚያውቅ ሰው ነው።ለጠቅላይ ሚኒስተርነት የሚሆን ነገር የለውም።ከታች ሆኖ እንዴት መምራት እንደሚቻል አይቶል።አረጋዊን ያበረረው ከታች ሆኖ ነው።አረጋዊ ሁሉንም ያውቀዋል፤ሁሉም የሱ ይመስለው፤ ግን ምንም የለውም፣የመለስን ድክመት ያውቃል።ለመለስ ትልቁን ስልጣን ሰጥቶ እሱ ሁሉንም ሆነ።
ለመለስ ከሚስት አንስቶ የሰጠው ስብሃት ነው።”ለፖለቲካችን ይበጃል፤የወልቃይት አማራ በመሆንዋ እሷን ማግባትህ ጥሩ ነው።’’ ስብሃት ሚስትና ስልጣን ሲሰጥህ ሰላይ አይነሳህም።በነገራችን ላይ ስብሃት የአሜሪካ ሰላይ ነው።በአፄ ሀይለ ስላሴ እንደ ነበሩት ደጅ አዝማች ከበደ ብቃት ያላቸው ናቸው።ሁለቱም መሪዎች ወደ ስልጣን እንዲመጡ ያደረጉና ወደ ሞትም የመሯቸው የወሰዷቸው ናቸው።ሁለቱም እጅግ አደገኛ ሰዎች ናቸው።
አሜሪካ በግብጽ ችግር ገጠማት።ሙስሊም ብራዘርሁድ እንቅስቃሴ አሠጋት።የግብጽ መንግስት ሊቆጣጠረው አልቻለም፤አልቻለም ሣይሆን አልፈለገም። ኢትዮጵያ ክልላዊ የናይል ህብረት እንድትፈጥር ተነገራት።ሆስኒ ሙባረክ ስልጣኑን ለሙስሊም ብራዘርሁድ ሰጥቶ አረፈው።
አሜሪካ ሩጣ ኢትዮጵያ ደረሰች።’’አባይን እንድትገድቡ እንፈልጋለን’’የአሜሪካ ትልቁ ባለስልጣን ተናገሩ።ኢትዮጵያውያኑ አፍጥጠው አዩአቸው።’’ማለቴ 75% የኛ ስጦታ 25%በብድር የምታገኙት ይሆናል።የምትገነቡት ትልቁን የአፍሪካ ግድብን ነው።ግን ለአለም በራሳችሁ ገንዘብ እንደሰራችሁ ትገልፃላችሁ።’’
መለስ በወሩ ጉባ ተገኝቶ ግድቡን መረቀ።
ግድቡ እየተካሄደ እያለ አንዳንድ ችግሮች ተከሰቱ።የሙስሊም ብራዘርሁድን የግብጽ ሠራዊት አስወገደ።አል ሲሲ ይቅር በይን አሜሪካ አለ።ሆስኒ ሙባረክን አሰረ።አሜሪካኖች ተመልሰው መጡ።ግድቡ ላይ አንዳንድ ማሻሻያ ኢትዮጵያ እንድታደርግ ጠየቁ።
‘’ ራሳችሁ መጣችሁ ፤ገንቡ አላችሁን።ይህን ሀሳብ የሚያስለውጥ ነገር ከየት አገኛችሁ?’
‘’ ግብጽ ’’
‘’እ ,,,ግብጽ ’’
አሜሪካኖች እየተመላለሱ መለስን መጨቅጨቅ ቀጠሉ።መለስ በሀሳባቸው ፀኑ።’’በቃ ተዉ!ግብጽ እወራችኋለው ካለች ትምጣ፤እናንተን የሚያስቸግራችሁ ነገር የለም’’
አሜሪካኖች ነገሩን ተዉት !መለስን በሽታውን ያስያዙት አሜሪካኖች ናቸው የሚባል ነገር አለ።ይህም በካምፕ ዴቪድ ተፈፀመ መባሉ ነው የሚገርመው።
በስተመጨረሻ መለስ በጩሐት ይፈርሳል ። የጮሐው አበበ ነው።ማን ነው ወደ አዳራሹ ያስገባው መልሱ የሚገኘው እዚህ ነው።አንድም ሁለትም ሶስትም መንገዶች ሊያስኬደን ይችላል ።ስብሃት ይኖርበት ይሆን?
ሓይለ ማርያም ደሳለኝ
ሓይለ ማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን እቅድ አልነበራቸውም።የፖለቲካ ፓርቲም አባል እሆናለው ብለው አስበውም ኣያውቁም።አንድ ቀን አዋሳ ሄደው በወላይቶች ላይ የሚፈፀመውን ግፍ አዩ።ከተፈራ መስቀሌ ጋር ሲወያዩ ‘’እኛ መሀይማን ነን ፤እናንተ የተማራችሁት ድርጅት ውስጥ አልገባ አላችሁን።ሲዳማዎች ምሁራን ኢሕአዲግ ውስጥ በብዛት አሉ፤ይደመጣሉ።’’በዚህ አይነት ለሕዝቡ ብለው ነው የገቡት።ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አንብበው የማያውቁ ሰው (የትምርታቸውን አይጨምርም)ምን ለመሆን አስበው ኢሕአዲግ ውስጥ ይገባሉ?
በሓይለ ማርያም የሕአዲግ አባል መሆናቸው የክልሉ መሪ ለመሆን ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም።ፍላጎታቸውን ኢሕአዲጎች ሰምተዋል ።ክልሉን ሲያስተዳድሩ በቅንነት መርተዋል።ያንቺን የሎቄ ጭፍጨፍ ታነሱ ይሆናል።’’የአዋሳ ህዝብ ሊጨፈጨፍ ነው፤የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ፈርም።’’አሏቸው።ፈረሙ።ወደ አዋሳ እየመጣ የነበረውን ህዝብ የፌደራል ፖሊስ ፈጀው።ከዛ በኋላ ሶስት ቀን ሙሉ ሓይለ ማርያም እንቅልፍ አልተኙም።ብዙም አልቆየም በሲዳማና በወላይታ መካከል የነበረውን የድንበር ውዝግብ እንዲፈታ አደረጉ።በወላይታ ይሁዳ ተባሉ፤ዘፈን ወጣላቸው።ግን ትክክል ነበሩ።
አዲስ አበባ ሄዱ ።’’ከዛ እሳት አውጡኝ’’አሉ።
‘’እሺ እንፈልግልሀለን’’ ተባሉ።እኝህን ሰው ስብሃት ገና እንዳዮቸው ወደዷቸው’’በደምብ እንጠቀምበታለን’’አሉ ለራሳቸው።’’ያባቱ ስም ደሳለኝ ነው ያለው። እዚሁ መሰልጠን አለበት።ዳግማዊ ደሳለኝ!! ‘’
መለስ ፈግግ ብሎ ሳቀ።ደሳለኝ የሚባለውን ስም ሁሉም ታጋይ ያውቀዋል።
አዲስ አበባ ተመቸችው፤ስልጣኑ ፈጣን ነበር።ሳያስቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሞታቸው ‘’ሓይለ ማርያም ተተኪ ነህ’’ ሲባሉ ደነገጡ።ካንተ የተሻለ ሰው አናገኝም ተባሉ።እውነት አያገኙም!ህወሐት ተፍረከረከ።የሀይል የበላይነቱን አግኝቶ ማንም ሊቆጣጠራቸው አልቻለም።ለሁሉም እሺ ነበር መልሳቸው።ሓይለ ማርያም ‘’ስለ ፀጥታው እኔ አልገባም፤ፈጽሞ አላውቀውም’’ ብለዋል።
አንዴ አንድ አባት ወደ ሊቢያ ስለ ሄደው ልጁ ከደላላው ጋር ያወራል።ደላላው እጅግ የጥጋብ አስተያየቶችን ነበር የሚሰነዝረው።አባትየው ድምጹን ከፍ አድርጎ ነበር የሚያሰማኝ።
‘’ለምን በፖሊስ አታሲዘውም’’አልኩት።
‘’አስዤው ነበረ፤ከደብረ ዘይት የመጣ ኮረኔል አስፈታው።እዚሁ የጨርቆስ ልጅ ኤርትራዊ የነበረ ምን ታረገዋለህ! ’’ወያኔ ወደቀች አልኩ።ማስለቀቅ አንድ ነው፤እንዲያ እንዲያብጥ መፍቀድ አደጋ አለው።
ወያኔ መፍረሷ የታወቀ ሆነ።ከውስጧ እራሷን እያፈራረሰች ነበር።ስልጣን የሌለው ሰው የመንግስት የትኛውም አካል እንዲጨፍር ከፈቀድንለት ምንም አያማጠም ልንል እንችላለን!! ሓይለ ማርያም የወላይታ ብሔርተኛ ቢሆኑም ራሳቸው ያደራጇቸውን ብሔርተኛ ሰዎች እንኳ መቆጣጠር አይችሉም።በመጨረሻ ባገኙት አጋጣሚ ስልጣን አስረክበው አመለጡ
አብይ አህመድ
አብይ አህመድ እንዴት መጣ ፤እንዴት ወጣ እንተወውና።አባይን በተመለከተ እምሰነዝረው አስተያየቶች ይኖሩኛል።’’ታሪካዊ ጠላት’’ይህን ስም ለግብጽ መስጠት የለብንም።ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋራ መጋጨት የማትፈልገው ግንኙነታችን ሊቋረጥ እንደማይችል ስለምትረዳው ነው።ያኔ ስላሸነፍቸው አይደለም።ታሪካዊ ጠላት የሚባለው ሊሰራ የሚችለው ቢያንስ ቢያንስ ለ60 አመት ሲያርዱን ለኖሩት አሜሪካና እስራኤል ነው።የአሜሪካ ህዝብ ጨዋ ና ጥሩ ህዝብ ነው።ብዙ ህዝባችን አሜሪካን ከሀገሩ በላይ ተመችቶት ይኖርበታል።የእሥራኤል አምላክ እያሉ የሚደፉ ብዙ ዜጎች አሉን።ዋና ገዳያችን ግብጽ ሳትሆን እሥራኤል ናት ብንል የሚያምነን አለ።አሁን ዘመቻ መጀመር አለብን።በአሜሪካም በእሥራኤል ሕዝብ ጨዋነት እርግጠኛ ነኝና።
ለሀገር መሪ አሜሪካን ተጋፈጥ አልልም። ብዙ ሀገራት መሪዎች ተገዢዎች ናቸው።አባይ ኢትዮጵያን ከማንም ጋር የሚያጣላ አይደለም።አሜሪካን ይዘው ለአስር ለአስራ አምስት አመታት የሚቆይ የአባይ የወዳጅነት ስምምነት ይፈርሙ።ለሰላም በሩን ይቅደዱ።የጀርባ ስምምነት አያድርጉ።ስለ ውሃ ስምምነት የማውቀው ነገር የለም፤ብዙ ግድቦች ቢገደቡ ግብጽን ነው የሚጠቅሙት።መስኖ መጠቀም እንዳለብዎት ግልጽ ያድርጉ።በእውቀት ፣በፍቅር ፣በስምምነት ከተጠቀምንበት በቂ ውሃ ይመስለኛል።በእልህ ፣በተንኮል ከተጠቀምንበት ግን የሚያመጣው ነገር አይታወቅም ።
እስራኤል የሚያጠራጥር ነገር እየፈጸመች ነው።የእስራኤል ጋዜጠኞች የአውሮፕላን ጠለፋውን ያጣሩ።ለመነሻ የሚሆኑ ነገሮች አሉ።የምርጫው መቃረብና ናታንያሁ ተናገሩት የተባለው ንግግር፣በአንድ አውሮፕላን ስንት ፓይለቶች ዶክተሮች ወታደሮች ሊገኙ ይችላሉ ጥናታዊ ስራ መስራት ይጠበቃል።ወጊውን ፓይለት ፣ታዳጊዎችን ፓይለቶች፣ዶክተሩንና ወታደሮቹን በሚገባ መጠየቅ ይጠቅማል።
ኪሲንጀር ከሞቱ ቆዩ።ሞቶም ቢሆን ይህ ከመቶ ሚሊየን በላይ ያስጨፈጨፈ ሰው ፣እጅግ ጨካኙ ሰው የኖቤል ሽልማቱን ሊነጠቅ ይገባል።ጨካኝ ሰው ሂትለር ሳይሆን ኪሲንጅር ነው መባል ያለበት።
============