በአገራችን በህወሃትና በአማራው በኩል ለተቀሰቀሰው የሰሞንኛው ውጥረት በዋናነት የወልቃይት ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል:: በዚህ ጥያቄ ላይ የቀድሞው የትግራይ እንደራሴ የነበሩት ልዑል እራስ መንገሻ ስዩም ሳይቀሩ ወልቃይት በእኔም ሆነ በአያት ቅድመአያቶቼ ዘመን የትግራይ ሆኖ አያውውም በማለት የምስክርነት ቃላቸውን በይፋ እንደተናገሩ ሁሉም ያውቀዋል:: እሳቸውም በህይወት ስላሉ ዳግም ሊመሰክሩ ይችላሉ::
ሌላው ተመሳሳይ ምስክርነት የሰጡት የወያኔ መስራች የሆኑት አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘራፅዮን ናቸው:: የእነሱ ምስክርነት በይፋ ባይገለፅም አብረን ሸንጎ በሚባለው ስብስብ ውስጥ የትግራይ አንድንድነት ለብሄራዊ ዴሞክራሲ (TAND) በሚል ስያሜ ተቀላቅለው በነበርንበት ጊዜ ስለወልቃይት አንስተን ስንወያይ በነሱ በኩል ውልቃይትን ለትግላችን መውጫና መግቢያ ለማድረግ የያዝነው የጎንደር መሬት እንጂ የትግራይ አልነበረም ሲሉ ተናግረዋል:: ይህንን አሁን ይድገሙት አይድገሙት ባይታወቅም ዳግም ሊጠዬቁ ይገባል:: ሌሎቹም የሸንጎ አባላት የሆኑት ይህንን የእኔን መረጃ ሊያብራሩት ይችላሉ ማብራራትም አለባቸው::
ነገሩን ያነሳሁት ቀውሱን ለማፋፋም ሳይሆን እውነተኛ ታሪኩን ተከትሎ መፍትሄ እንዲሰጠው ካለኝ ጉጉት በመነሳት እንደሆን እንዲታወቅልኝ እጠይቃለሁ:: በእኔ በኩል ሁሉም በኢትዮዽያ ውስጥ ያለ ምድር የሁሉም ኢትዮዽያዊ የጋራ ይዞታ ነው:: የከባቢውን ነዋሪና መልክአምድር እስካላናጋ ድረስ ኢትዮዽያዊ ዜጋ የትም ቢሆን ባገሩ ድንበር ክልል ውስ የመኖር መብት አለው:: የትም ይሁን የትም የጎሳ ታፔላ ለጥፎ በመሬት መጨቃጨቁን አልደግፍም:: ትክክልም አይሆንም ኽላቀርነት ነው::ለእድገትና ለእኩልነት ብሎም ለአንድነት ፀር ነው::
ለአስተዳደር አመችነት ሲባል በከባቢ ደረጃ በክፍላተ አገር መሸንሸኑ በሌላውም የሰለጠነ አገር ያለ ሃቅ ነው:: በአሜሪካ ሳይቀር 51 ግዛቶች( States) አሉ : በሌሎቹም አገሮች እንዲሁ::ከኛ የሚለዩበት በጎሳ ተዋረድ እርስበርስ ጎራ ለይተውና ግንብ ገንብተው አይንህ ላፈር አለመባባላቸው ነው::እኛም ብንሆን በዚህ አይነቱ አገራዊ ልእልና ቀደም ሲል በ14 ከዚያም በኽላ በ13 ጠቅላይ ግዛትና በክፍላተአገር ስያሜ በሰላምና በአንድነት ለዘመናት መኖራችን አይካድም የቅርብም ጊዜ ታሪካችን ነው:
የወልቃይት ሆነ የሌላውን ያገራችንን መሬት በጎሳ ተዋረድ ሸንሽኖ መጨቃጨቅ ከታሪክና ከእራስ ጋር መጣላት ይሆናል:ነውም:: ስለሆነም ወደነበርንበት ክብራዊ አንድነታችን ለመመለስና በሰላም አብረን ለመኖር ላለፉት 35 ዓመታት የሰፈነውንና ለተለያዩ ቀውሶች የዳረገንን የጎሳ አገዛዝ በህብረት ማሶገድነው::ያም ሲሆን ብቻ ነው እንደቀድሞው ይህ ጎሳ ያጎሳ ሳይባባል የአሁኑና መጭው ትውልድ የኢትዮዽያ ዜጋ በሰላም አብሮ በመኖር ለተሻለ እድገትና ኑሮ የሚበቃው::
ከግጭቱ የሚያተርፍ ቢኖር ችግር ጠማቂዎቹና በእያንዳንዱ ጎሳ ስም ተነስተው የሚያባሉት ቡድኖችና የጦር መሳሪያ ሻጮች እንዲሁም የቅርብና የሩቅ ታሪካዊ የኢትዮዽያ ጠላቶች ናቸው::
የተፈጠረውን ቀውስ ለማሶገድና ሕዝብንና አገርን ልማዳን ሁሉም የሚችለውን ያበርክት ሌላውም የዚህ መድረክ ተሳታፊ የሚያውቀውን ይመስክር አለያ ተያይዞ ለመውደቅ ፈቃደኛ መሆን ነው::የወንጀለኞች ደጋፊም መሆን ነው::
አገሬአዲስ