ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዐት በቀጥታ ጦርነት ታውጆበት የዘር ፍጅት የሚፈጸምበት የዐማራ ሕዝብ ነው ። ነገር ግን ነጻ አወጣንችሁ ብልው የሚበላውን አጥቶ በረሀብ የሚያልቀውን ሕዝብ አስጨንቀው በግብር በታክስና በተለያዩ ምክንያቶች ከሚሰበስበው ገቢ በቢሊዬን የሚቆጠር ብር ወጭ አድርጎ በየዓመቱ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን አክብሩ እያሉ ፣ በኮሪዶር ልማት ፣ በፓርክ ስራ ፣ በቤተመንግሥት ግንባታ እና ለጦር መሳሪያ ግዥ እያለ በማባከን በረሀብና በችግር የሚያማቅቀው ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመሆኑ በዘለለ ሀገርቷን ጭምር አጥፍተው ሊጠፉ ተቃርበዋል ።
የዐማራ ሕዝብ የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግሉን በቆራጥ ልጆቹ (በፋኖዎች) በማካሄድ ላይ ይግኛል። የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈጽሙት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት (ህወኃት) እና በኦሮሞ ሕዝብ ስም የተደራጁ ስመ ብዙ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጅት ነን ባይ ኦነግና ውላጆቹ ናቸው ።
ታሪካዊ የውጭ ጠላቶቻችን ካሁን ቀደም በቀጥታ ወረራ ሊያሳኩ ያልቻሉትን ግብ የውስጥ ባንዶችን አሰልጥነውና አስታጥቀው በሁለቱ ኤትኖ ፋሺስት ድርጅቶችን በመጠቀም ሕዝባችንን በጎሣ ለያይተው እርስ በርሳችን እንድንተላለቅ አገዛዙን ተጠቅመው በማድረግ ላይ ናቸው።
እህአደግም ሆነ ኦነግ እና እሱ እንደ ጫጩት የቀፈቀፋቸው ድርጅቶች የአላማና የግብ ልዩነት የላቸውም የሚያጣላቸው ነገር ቢኖር ከኢትዮጵያ ሕዝብና በተለይም ከዐማራ የሰረቁትን እና ወደፊት ሰርቀው ሲገነጠሉ በሚደርሳቸው ድርሻ ላይ ብቻ ነው ። በእነዚህ ሁለት ኤትኖ ፋሺስት ድርጅቶች ሰላሙን ያላጣ ፣ ሀብት ንብረቱን ያልተቀማ ፣ መሬቱን ያልተነጠቀ እና ህይወቱን ያላጣ የኢትዮጵያ ማህብረሰብ የለም ።
የዐማራውን ልዩ የሚያደርገው ሁለቱም ድርጅቶች የሀሰት ትርክት ፈጥረው ፣ ስሙን አጠልሽተው ፣ ተደራጅተው ፣ ተከታይ አዘጋጅተው ፣ በጠላትነት ፈርጀውት ፣ አደራጅተውና ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተው በጎሣ ማንነቱ እና በእምነቱ ለይተው ለማጥፋት ጦርነት ማወጃቸው ነው ።
- የ(ት.ህ.ነ.አ.ድ) ማኒፌስቶ
- የኦሮሞብልፅግና እና ኦነግ ጥምረት ግብረ ሀይል በ April 1 2023 ባደረገው ዝግ ውይይት ለኦሮሞ ነፃ አውጪ ሰራዊት አመራሮች ያስቀመጠው ሰነድ ።
እነኚህን መረጃዎች በአንክሮ የተከታተለ ዜጋ ዐማራ ለምን ነፍጥ አነሳ ሳይሆን እስካሁን ድረስ ማን ኢትዮጵያዊነቱ ይነጥቀኛል ብሎ ነበር ለዐማራነቱ ቁብ ሳይሰጥ ቀርቶ ከሁለት ያጣ ጎመን እስከ መሆን የበቃው እንደሚል እርግጠኛ ነኝ ። ለማንኛውም ከመቅረት መዘግየት ይሻላል የባላልና አርፍዶም ቢሆን ህልውናውን የማትረፍ ተጋድሎ ጀምሯል ፤ ዐማራ ላይጨርስ አይጀምርምና በድል አድራጊነት ይጨርሰዋል ። የማይቀረው ድል ግን እውን መሆን ያለበት በአነስተኛ መስዋዕትነት መሆን ሲገባው ሁሉንም የሚመለከት ሕዝባዊና ሀገራዊ ችግርን ዐማራው ብቻ ታግሎ ነጻ ያወጣናል በሚል እሳቤ ሌላው ኢትዮጵያዊ “እየመጣ ነው እየመጣ ነው “ እያለ መጠበቁ ጊዜና ብዙ መስዋዕትነትን በማስከፈል ላይ ይገኛል ።
ስለሆነም
1) ለትግራይ ሕዝብ ፦
የትግራይ ሕዝብ ሆይ ከላይ የተቀመጠው የ1968 ዓም የልጆችህ የመታገያ መኒፌስቶ አንተን ነጻ እናወጣለን ብለው ያዘጋጁት የውሸት ድሪቶ በመጠቀም በታሪካዊ ጠላቶቻችን ታግዘው ለመንበረ ስልጣን በቅተው ለ27 ዓመት በጎሣ የከፋፍለህ ግዛው ታግዘው ገዝተዋል ። በስምህ ታግለው እና በስምህ ልጆችህን ፈጅተው እና አስፈጅተው ፣ በስምህ ስልጣን ተቆናጥጠው ፣ በስልጣን ዘመናቸው በስምህ የኢትዮጵያን ሕዝብ ዘርፈው ፣ በስምህ ንጹሀንን አስረው አስቃይተው ፣ በስምህ ገለውና አስገድለው ሲነቃባቸው አንተኑ ዋሻ አድርገው በተዘረዘሩትና በሌሎች ወንጀሎ ላለመጠየቅ ሲሉ ዳግም ከዐማራና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖችህ ጋር በሰላም እንዳትኖር ለዳግም ጦርነት እየቀሰቀሰህና እያዘጋጀህ ይገኛል።
የትግራይ ሕዝብ ሆይ ልጆችህ የህወኃት አመራሮች የታሪካዊ ጠላቶቻችንን የማይሳካ ተልዕኮ ለማስፈጸም የእሳት እራት እያደረጉህ መሆኑን ተገንዝበህ በቃችሁ በስሜ አትነግዱ ልትላቸው ይገባል ። ከዐማራ ወገንህም ጋር ሆነ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ተስማምተህ እንደ ጥንቱ ዘመኑ የሚጠይቀውን የሁሉም ዲሞክራሲያዊ መፍት ተጠብቆ የምንኖርባት ሀገር እንድትሆን ለማድረግ ከታሪክም ሆነ ከራሳቸው ስህተት ለመማር የማይፈልጉ የባዕድ ተልዕኮ አስፈጻሚ ልጆችህ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ ይኖርብሀል ። ሕወኃት የጎሣ አፓርታይዳዊ ስርአትን በአገራችን ያነበረ በመሆኑ በትግራይ ሕዝብ ስም እየነገደ መቀጠል ይቅርና እንደ ጀርመኑ ናዚ ፓርቲ እንዳይኖር በህግ ልታገድ የሚገባው ወንጀለኛ ድርጅት ነው።
በማጠቃለያ የትግራይ ሕዝብ ከእናት ሀገሩ የመገገንጠል ፍላጎት አለው የሚል እምነት የለኝም እምነቴ ስህተት ሆኖ ሕዝቡ ፍላጎቴ ነው ቢል እንኳን ከአጎራባች ክልሎች መሬት ቆራርሶ ይቅርና እፍኝ አፈር ዘግኖ መገንጠል ስለማይችል እየተገዳደልን ዝንተ ዓለም እንኖር ይሆናል እንጂ መፍትሔ አናመጣም ።
2) ለኦሮሞ ሕዝብ ፦
የተከበርከው የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ በስምህ የተለያዩ መጠሪያ ይዘው የተቋቋሙ የኦነግ ውላጅ ድርጅቶች እና ራሱ ኦነግ በስምህ እልቆ መሳፍርት ወንጀል ፈጽመዋል በመፈጸምም ላይ ይገኛሉ ከወንጀሎች ሁሉ የላቀውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዐማራ ሕዝብ ላይ በገሀድ ጦርነት አውጀው ኢሰባዊ በሆነ መገድ እየፈጸሙ አስቃቂነቱን እንድናየው ራሳቸው ቀርጸው በማህበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ ጭምር “ጀግንነታቸውን” እያስመሰከሩ ነው ። ድርጊቱን የሚፈጽሙት ልጆቻችሁ ፣ የሚፈጽሙበት ስፍራ በክልላችሁ እዚያው ዐይናችሁ ስር ሆኖ እያለ ማንኛውንም የአብሮነት ታሪካችንን ብንተው እንኳን ሰው መሆናቸውን ከግምት አስገብቶ ዝሆን የገደለ በሺህዎች የሚቆጠር ብር እንዲቀጣ የሚደነግግ አባ ገዳ ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጡር በማንነቱና በእምነቱ ተለይቶ ሲጨፈጨፍ ቢያንስ አንዲት ቃል ሰው ያለፍርድ በመንጋ አትግደሉ ማለት እንዴት ይሳነዋል ? የደንቢ ዶሎ ተማሪዎችን እጣ ፋንታ የአካባቢው ሕዝብ አያውቅምን ? በአርሲ ትናንትና በእምነታቸው ሳቢያ የተጨፈጨፉትን ኦርቶዶክሳዊያን ጉዳይ የአካባቢውን ነዋሪ አይመለከትም ? በስማችን ወንጀል አትፈጽሙ ከማለት ይልቅ ዝምታው መስማማት ሊሆን አይችልም ? የኦሮሚያ ክልል የይገባኛል ጥያቄ አንስቶ ግጭት ውስጥ ያልገባበት ክልል የለም ይህ ሁሉ ድርጊት የሚደረገው መሬት ጠቧችሁ በእናንተ ፈቃድና ድጋፍ ካልሆነ ዝምታችሁ እስከመቼ ነው? እያልኩ ብዙ ጥያቄዎችን ጥያቄዎችን መደርደር እችላለሁ ።
ልጆቻችሁ ልክ እንደ ህወኃቶች የታሪካዊ ጠላቶቻችንን ተልዕኮ አንግበው በፕላንና በእቅድ ፕላን A እና ፕላን B ብለው ዐማራውን እየፈጁት እንደሆነ በቁጥር 2 የተቀመጠውን መረጃ መመልከት ይቻላል ።
በእቅዳቸው መሰረት ኦሮሞ የታገለለትን አላማ በተሳለጠ ሁኔታ መተግበር አማራ በወያኔ ህዝብ ቆጠራ ውጤት እንደተባለው ከኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ሁለተኛ ሳይሆን ምናልባትም ከሶማሌ ከትግሬና ከሲዳማም በታች የሆነ ማይኖሪቲ ነው : ሊኖረው የሚገባው ቦታና ውክልናም በልኩ ነው : እረብሻውን ካላቆመ ደግሞ ውጤቱ ሙሉ በሙሉ መወገድ ነው ይላል ። ይህንን መሰረት አድርገው የጀመሩትን ጦርነት እየመከቱ ካሉት ሁለት የፋኖ አደረጃጀቶች አንዱ የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የማታገያ ፍኖተ ካርታ አውጥቷል አንባቢ ሶስቱንም ሰነዶች ተመልክቶ ማን ለምን እንደሚታገል መፍረድ ስለሚችል የትግራይና የኦሮሞ ሕዝብ በጽንፈኛ ልጆቻቸው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እውነት መስሏቸው ሲደግፉ የነበሩ ወደ ቀልባቸው በመመለስ ልጆቻቸውን አደብ ሊያስገዙ ይገባል ።
የአፋሕድ ማኒፎስቶ ለንጽጽር
3) ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ህወኃትና የኦነግ ውላጆች አግርቷን በአንድ ላይ ሆነውና በተናጥል ተራ በተራ ሲገዙ ከ30 ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል እኔ በጽሑፍ ከማስረዳችሁ በላይ እይኖራችሁበት ያለው ሀገር አቀፍ ቀውስ የምትረዱት ነው። ሀቁ እየኖራችሁበት ያለው ሁኔታ ሲሆን በብልጽግና ወንጌል (prosperity gospel) ፍልስፍና እየደሄየህ በልጽጌአለሁ ፣ እየራበህ ጠግቤአለሁ ፣ ሀገር እየፈረሰች ተገንብታለች እና ወዘተ ብሎ አያመሰኘኝም ብሎ አብይ አህመድ ስሣድብ መስማት የተለመደ ነገር ሆኗል ። ቤትህን እላይ ላይ አፍርሶ ‘ከህገወጥ ድህነት አላቀን ህጋዊ ደሀ አደረግናቸው’ ብለው ይዘባበታሉ ፤ ዘይት ተወደደ ስትል “ጎመን በጨው ቀቅለህ ብላ” ይሉኃል ፤ ኑሮ ከብዶናል ስትል ዳቦና ሙዝ በገንዘብ የማይሸመቱ እቃዎች ይመስል “ሙዝ በዳቦ ብላ” ብለው ያላግጡብሀል ። አንተም ለጥያቄህ አግባብ ያለው መልስ ያገኘህ ይመስል አርፈህ ከመቀመጥ ከፋኖ ጎን ቆመህ በመታገል መብተህን ማስከበር ይኖርብሀል ። ዝም ብለህ ተቀምጠህ እየመጡ ነው ካልክ እስከሚመጡ ታልቃለህ ።
3) የእምነት አባቶች
ቤተ እምነቶች ፈርሰው ሲያልቁ ምዕመናን እና አገልጋዮች እንደ ዱር አራዊት ታድነው በካራ ሲታረዱ የአሁኑ ዝምታችሁ ይህ ጊዜ ማለፉ አይቀርምና አሁን በትናችሁ ያለ ጠባቂ ለተኩላዎች ያስረከባችኋቸውን ከሞት የተረፉ በጎቻችሁን ዐይን ቀና ብላችሁ ልታዩና መስቀል ልታሳልሙ ይቻላቺኋልን ? ድፍረቱን ለእናንተ ፍርዱ ለፈጣሪ መተው ነው ።
በማጠቃለያ ዐማራ እየተዋደቀ ያለው ህልውናውን ለመታደግ እና እንት ኢትዮጵያን ከጥፋት አድኖ እንደ ዜጋ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር እኩል መብቱን አስከብሮ ለመኖር እንጅ እንደ ህወኃትና ኦነግ ዲቃላዎች እናቱን ገሎ ወላጅ አልባ (orphen) ለመሆን አይደለም ። ይህንን በመገንዘብ የባዕድ ተልኮ አንግበው ከሚራወጡት በቀር ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፋኖ ጎን ቆሞ የድርሻውን በመወጣት በአነስተኛ መስዋዕትነት ለድል ለምስብቃት መስራት ይኖርበታል ።
ድል ለዐማራ ሕዝብ
ክብር ለሰማዕታት