ህወሓትና ኦነግ የዐማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጀው ከምድረ ኢትዮጵያ ለማጥፋት ተደራጅተውና ታግለው መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ አንስቶ የዘር ማጥፋት ፣ የዘር ማሳሳትና ማጽዳትን መርሁ ያደረገ ህገመንግሥት ቀርጸው እና መንግሥታዊ ስርአት ዘርግተው በተግባር መተርጎ ከጀመሩ እነሆ ከሶስት አስርተ ዓመታት በላይ ሆኖታል ። ካሁን ቀደም ብሴራና በድብቅ ይካሄድ የነበረውን የዘር ፍጅት የኦነግ መራሹ የኦህደድ ብልጽግና አገዛዝ መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ ከነሐሴ 2023 ጀምሮ ግልጽ ጦርነት ስለታወጀበት የዐማራ ፋኖ ራስን የመከላከል ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛል ።
የዐማራው የህልውና አደጋ መንስዔዎች ፦
- ያልመከረበትና ያልተሳተፈበት ህገመንግሥት ፣
- ዘውግን መሰረት ያደረገ የመንግሥት አወቃቀር ፣
- የወሰንና የማንነት ጉዳይ ፣
- እየተካሄደበት ያለው የዘር ፍጅት ፣
እነኚህ ከላይ የተጠቀስኳቸው የዐማራው የህልውና አደጋ መሰረታዊ መንስዔዎች በመሆናቸው ላለመጥፋት መሳሪያ አንስቶ በመዋደቅ ላይ ይገኛል ። በትረ ሥልጣኑን በፈረቃ የተቆጣጠሩ ፋሺስታዊ አገዛዞች ዐማራን ማጥፋት እንደ ህገመንግሥታዊ መብታቸው አድርገው በመቁጠር የሚፈጽሙትን ወንጀል መግታት የሚቻለው አፓርታይዳዊ የሆነውን ህገመንግሥት እና ዘውግን መሰረት ያደረገውን መንግሥታዊ አወቃቀር በማስወገድ ፣ በተቀማው ማንነትና በአጽመ እርስቱ ላይ ያላቸውን ያልተገባ የይገባኛል ጥያቄ ሙሉ በሙሉ በማስነሳት እና እየተካሄደ ያለው የዘር ፍጅት በዐማራ ሕዝብ አሸናፊነት ሲደመደም ቢቻ ነው ።
ሁለቱ ፋሺስታዊ ድርጅቶች ህወኃትና ኦነግ) ህገመንግሥቱ እና የጎሣ ፌደራሊዝሙ የሚቀየረው በመቃብራችን ላይ ነው እያሉ ሲሆን አጽመ እርስቱን (ወልቃት ጠገዴ ፣ ጠልምት ፣ ራያ እና ማንነትን በተመለከት ዐማራነታቸውን ነጥቀው በግድ ትግሬዎች ናችሁ የሚሉ ህወኃቶች ደግሞ ቀይ መስመራቸው እንደሆነ እየነገሩን ሲሆን የአብይ አህመድ ፋሺስታዊ አግዛዝ የዐማራውን ማንነትና አጽመ እርስቱን አሳልፎ ለመስጠት በመዳከር ላይ ይገኛል ። የጦር ሜዳ ሽንፈቱን አምኖ መቀበል ኅፍረት የሆነበት አገዛዝ ከገባበት የውርደት አረንቋ መንጥቆ የሚያወጣው ኃይልና ዘዴ በማፈላለግ በድርድር ስም የባዕዳንን ጣልቃገብነት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ድርጅቶችን ያላሳተፈ የብልጽግና ካድሬዎችን አሰባስቦ ባቋቋመው “አገራዊ ምክክር ኮሚሽን” ተብዬውን በመጠቀም ትግሉን ለመጥለፍ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አግልልው ያካሄዱትን “የፕሪቶሪያ ስምምነት” አይነት የማጭበርበሪያ እና የጊዜ መግዣ ድርድር የዐማራ ሕዝብ የሚቀበለው አይሆንም ።
የዐማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ ምክንያት የሆኑ ከላይ የተጠቀሱ ጉዳዮች ለወራሪዎች ቀይ መስመራቸው እና በመቃብራቸው ላይ የሚቀየሩ ከሆነ ችግሩ በውይይትና በድርድር ይፈታ የሚሉ ሴረኞች የዐማራው ሕዝብ ሰጥቶ የሚቀበለው ነገር በለለበት ነው ። ምክንያቱም የዐማራ ሕዝብ ሊያጠፋው ከተነሳው ህወሓት ታግሎ ህልውናውን ከማስጠበቅ ውጭ ሰጥቶ የሚቀበለው አንዳችም ነገር የለም ። ጠላት ምንም ጊዜ ቢሆን የሚጓዘው ጥቅሙን አስልቶ ነው ግራ አጋቢው ለዐማራ ህልውና ዘምቻለሁ እያለ አብይን ከስልጣን ለማስወገድ ሲባል ከህወሓት ጋር ግንባር ፈጥራለሁ የሚለው ወገን ወትሮውንም ቢሆን ፋኖን የተቀላቀለው ተልዕኮ ተቀብሎ መዝመቱን የሚያሳብቅ ነው ።
ከሁሉም የከፋው ነገር የዐማራን ህልውና እታደጋለሁ ብሎ አብሮት የዘመተውን ወንድሙን የሚያሳድድና ከጀርባ የሚመታ ቡድን ከዝንጀሮ ቆንጆ ሁለቱን መርጬ (ህወሓትና ሻቢያ) ጋር ግንባር በመፍጠር የዐማርን ችግር ፈታለሁ ማለት ዐይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ ማለት በመሆኑ የዐማራ ሕዝብ ጣልቃ በመግባት አብሮ የዘመተውን ወንድሙን ከመግደል እና አፈና ከማካሄድ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሳይቃጠል በቅጠል ነውና በጊዜ ሊያስቆሙ ይገባል ፤ አፍነው ያሰሯቸውን እንዲለቁ ጫና መፍጠር ያስፈልጋል ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ፋኖዎች ጎራ ለይተው እርስ በርስ መዋጋት ከጀመሩ ለጠላት ሰርግ እና ምላሽ እንደሚሆን ልንገነዘብ ይገባል ።
የአብይ አህመድ አገዛዝ ዐማራውን በጎጥ ለመከፋፈል ብዙ ለፍቶ ያልተሳካለትን ታክቲክ ፋኖዎቻችን አንግበው እንደ አዲስ ነገር በመጀመሪያ በየጎጣችን ተደራጅተን ከዚያ በኋላ ወደ አንድ አመራር እናድጋለን የሚል ከፋፋይ አጀንዳ ማንሳታቸው እጅግ በጣም አደገኛ አካሄድ መሆኑን ተገንዝበው የአካሄድ ለውጥ ሊያደርጉ ይገባል ። የተሰባሰበን ኃይል በትኖ ዳግም እንሰበስባለን ማለት ድሉን ለጠላት አሳልፎ ከመስጠት የተለየ ስላይደለ መሳሳት ተፈጠሮአዊ ሲሆን ከስህተት ተምሮ መመለስ ብልህነት በመሆኑ ትንሽ ሽንቁር አግኝቶ ጠላት እንዳይገባ ቀዳዳውን መድፈን ያስፈልጋል ።
ያዳቆነ ስይጣን ሳያቀስ አይተውም እንደሚባለው ሳልሳዊ ብአደኖች ዐይናቸውን በጨው አጥበው ከውስጥና ከውጭ ግንባር ፈጥረው እንደ ልማዳቸው ትግሉን ለመጥለፍ በመራወጥ ላይ በመሆናቸው በቃችሁ ሊባሉ ይገባል ። እነኚህ ቡድኖች (ሳልሳዊ ብአደኖች) ፣ ጎጠኞች እና ግለሰብ አምላኪዎች ከሀገር ውጭ ራሳቸውን እያደራጁ በፋኖዎች ውስጥ በዝምድናና በትውውቅ ሰርገው እየገቡ መሆናቸው ታውቆ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰብ እወዳለሁ ።
ድርድር ቅራኔን ለመፍታት የሚደረግ ሰላማዊ የመፍትሄ ማፈላለጊያ መንገድ መሆኑ ግልጽ ነው ነገር ግን ማንኛውም ቅራኔ በውይይት ይፈታልም ማለት እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል ። ፋሺዝም ከጀርመን የተወገደው በድርድር እና በውይይት አልነበረም። በፋኖዎቻችን መካከል የሚከሰቱ መሰረታዊ ያልሆኑ ጥቃቅን ልዩነቶች በሰጥቶ መቀብል መርህ በይይት መፍታት ይቻላል ። ምክንያቱም የሚዋጋቱ ጠላት የጋራ ሲሆን የሚያካህዱት የህልውና ተጋድሎ ዓላማና ግቡ አንድ በመሆኑ የአካሄድ ልዩነቶችን በይይት መፍታት ስለሚቻል ነው ። ሌሎች ለዲሞክራሲና ለፍትህ ከሚታገሉ የፖለቲካና የሲቭክ አደረጃጀቶች ጋር ፍኖ ተወያይቶ በሰለጠን መንገድ የጋራ ችግርን ለመፍታት ፍላጎት አይኖረውም የሚል እምነት የለኝም ።
ህወኃት የሚባል ድርጅት ከጅማሮው የዐማራን ሕዝብ ጠላቴ ነው ብሎ ፈርጆ ማኒፌስቶ ቀርጾ ከ30 ዓመት በላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመ እና ከላይ ከአንድ እስከ አራት ተራ ቁጥር የተቀመጡትን የህልውና አደጋ መንስዔዎች ፈጣሪ ሆኖ ለፈጸመው ወንጀል ቢያንስ እውቅና ሰጥቶ ለማረም ፈቃደኛ ያልሆነ ፣ አጽመርስቱን ነጥቆ ለመገንጠል ከሚፈልግ ድርጅት ጋር ዐማራ ተደራድሮ የሚያገኘው ነገር ምንድን ነው ? የህገመንግስት ለውጥ የማይቻል ነው የሚሉ ፣ ጎሣን መሰረት ያደረግ የምንግሥት አወቃቀር የሚቀረው በመቃብራችን ላይ ነው ካሉ ፣ የወሰንና የማንነት ጥያቄ ቀይ መስመራችን ነው ከሚሉ ቆሞ ቀር ስብስብ ጋር ተወያይቶ የሚገኝ ነገር ሊኖር አይችልም ። ይህ ጫፍጫፊ ቡድን በፌደራል ደረጃ ያጣውን ስልጣን ትግራይም ውስጥ ካጣ እስካሁን ለፈጸመው ወንጀል በህግ ተጠያቂ ስለሚሆን የትግራይን ሕዝብ እነደ መያዣ በመጠቀም ላይ ይገኛል ። የዐማራ ሕዝብ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ችግር የለበትም ስለ ሆነም ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ያለምንም ችግር ይቀጥላል።
https://amharic.zehabesha.com/wp-content/uploads/2025/10/tplf_manifesto_-_1968_e-c.pdfየ1968 ዓም ማኒፌስቶ
የሕወኃት የንሰሀ ልጅ የሆነው ኦህደድ ብልጽግናም ቢሆን በፈጠራ ትርክት ዐማራን በጠላትነት ፈርጆ ከገጸ ምድር ለማጥፋት በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ስሞችን እየሰጠ ባሰማራቸው ቡድኖች (ኦነግ ሸኔ ፣ ኮሬ ናጌኛ ፣ አባ ቶርቤ ወዘተ) የዘር ማጥፋትና ማሳሳት አልበቃ ብሎት ከ2023 ዓም ጀምሮ የአገሪቷን የመከላከያ ኃይልን ከእነ ሙሉ ባጀቱና የኦሮሚያን ልዩኃይልና ሚሊሺያ አሰማርቶ የዐማራን ሕዝብ በመፍጀት ላይ ሲሆን ማንኛውም በኦሮሞ ሕዝብ ስም የተቋቋመ ድርጅትና ሚዲያ ወንጀሉን በማስተባበልና የውሽት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።
የዖሮሞ ብልፅግና እና ኦነግ ጥምረት ግብረ ሀይል ዐማራን ለማጥፋት በ April 1 2023 ባደረጉት ዝግ ውይይት ለኦሮሞ ነፃ አውጪ ሰራዊት አመራሮች ካስቀመጡት አቅጣጫ ሰነድ ተቀንጭቦ የተሰራጨው የአማርኛው ትርጉም የሚከተለው ነው ።
ይህ ሰነድ የኦሮሞ ብልፅግና እና ኦነግ ጥምረት ግብረ ሀይል በ April 1 2023 ባደረገው ዝግ ውይይት ለኦሮሞ ነፃ አ ውጪ ሰራዊት አመራሮች ካስቀመጡት አቅጣጫ ሰነድ ተቀንጭቦ የተሰራጨው የአማርኛ ትርጉሙ ነው ። “የተከታታዩ ሰባ አመት የኦሮሞ ህዝብ የታገለለትን አላማ አሳክቷል ለዚህም ካስፈለገ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ድጋፍ ባለው የዲሞክራሲ አስራር : እሱ ካልሆነም ሙሉ በሙሉ በሀይልና በማስገደድ ወይ ሙሉ ኢትዮጵያን የኦሮሞ መልክ ያላት አድርጎ ኦረማይዝድ የተደረገች ኢትዮጵያን ይፈጥራል : ወይንም ያ የማይቻልበት አስቸጋሪ ሁነታ ከተፈጠረ ደግሞ ወሎን እስከ ራያ አዘቦ : ጎጃምን እስከ ቡሬና ወደ ደቡብና ምስራቅም ያሉን የኦሮሞ ጎሳወች እርስት ያካተተ ግዛት ያለው የኦሮሞ ሀገርን ይመሰርታል።
ታዲያ ይህ እንዲሆን ከተፈለገ አማራ ሙሉ በሙሉ መበተንና ሀይል የሌለው ደካማ መሆን አለበት : የኦሮሞ ሀይል አሁን የአማራ ክልል የሚባለውን ዞንና ወረዳ ሁሉ ተቆጣጥሮ ለፕሮጀክቱ ምቹ ሁኔታን መፍጠር አለበት : ይህ እንዲሆን ደግሞ የአማራን ታጣቂም ሀይሎች ልዩ ሀይል፤ፋኖና ሚሊሻ ) ሙሉ በሙሉ ትጥቅ በማስፈታት : ቀጥሎ ደግሞ በመከላከያ ውስጥ ያለን የነፍጠኛ እርዝራዥ ሁሉ ከመከላከያም በማፅዳት : የኢትዮጵያ መከላከያን ሰራዊት ሙሉ የአማራ ክልልን አስተዳደር ብቸኛ ሰላም አስከባሪ በማድረግ ::
ኦሮሞ የታገለለትን አላማ በተሳለጠ ሁኔታ መተግበር አማራ በወያኔ ህዝብ ቆጠራ ውጤት እንደተባለው ከኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ሁለተኛ ሳይሆን ምናልባትም ከሶማሌ ከትግሬና ከሲዳማም በታች የሆነ ማይኖሪቲ ነው : ሊኖረው የሚገባው ቦታና ውክልናም በልኩ ነው : እረብሻውን ካላቆመ ደግሞ ውጤቱ ሙሉ በሙሉ መወገድ ነው ።
የኦሮሞ ብሄራዊ ትግል ውጤት ግምገማና ቀጣይ አቅጣጫ : ከወታደራዊ ኮማንድ ግብረ ሀይል አንፃር ይህንን ያስቀምጣል
በኦሮሞ ህዝብ እምብርት ላይ የምትገኘውን ደብረብርሀንን ጨምሮ ቀጥሎ ያሉን ከተሞች መብረቃዊ በሆነ ፍጥነት ሙሉ በሙሉ መውረርና : የሚፈለጉ ነገሮች ወደ ኦሮሞ ህዝብ ካዘና ከገቡ በሗላ ደብረብርሀንንና ጎረቤቶቿን ሁሉ ወደ አመድነት እስኪቀየሩ ድረስ በእሳት ማንደድ : የአጣየን መልክ መድገም ::
ፋብሪካወችን በሙሉ ከሰል ማድረግ ከወለጋ በኩል ያለው የሸኔና የልዩ ሀይል ጥምር ጉልበት ወደ ቡሬና ፊኖተሰላም በመግባት አካባቢወችን መቆጣጠር : በአመራሩና ሌሎች ላይ እርምጃ መውሰድ : የኢንዱስትሪ ፓርኩንና ከተሞቹን በኢሳት ማጋየት : የኦሮሞን ህዝብ ትግል መራራነት ማሳየት።
በሸዋ በኩል የአባይን ወንዝ ተከትሎና ተሻግሮ የደጀንንና የደብረማርቆስን ከተማ በፍጥነት መቆጣጠርና የምስራቃዊ ጎጃሙን ክፍል ሞጣንና ብቸናን ጨምሮ በጃል ዳውድ የሚመራው የሸኔና የኦሮሞ ልዩ ሀይል ጥምር ግንባር እንዲቆጣጠረው ማድርግ : ከተሞቹንም ሆነ ሙሉ የኢንዱስትሪ ቦታወችን ወደ ፍርስራሽነት መቀየር።
አራተኛውና ትልቅ ስራ የሚጠይቀው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በኩል በጃዊ አድርጎ ባህር ዳር ከተማን ለመቆጣጠር የሚደረገው ኦፕሬሽን ሲሆን : በተመሳሳይ ሳዓት ከትግራይ አጋር ሀይሎቻችን በኩል ወደ ሙሉ ጎንደርና ወሎ የሚደረገው ግስጋሴ ሽብር ውስጥ ስለሚከታቸውና የኦሮሞን ሀይሎች ለመቋቋም የሚሞክር ብዙም ሀይል ስለማይኖር ባህር ዳርንና ዙሪያውን ለመቆጣጠር ምቹ ሁኔታየሚኖር ቢሆንም በቂ ዝግጅትና ከአጋር ሀይሎች ከጉምዝ ፤ ከቅማንትና ከትግራይ ሀይሎች ) ጋር መናበብ አስፈላጊ ነው።
አዲስ አበባን ከሁሉም አቅጣጫ ወደ አንድ ማዕከል መክበብና መቆጣጠር : የነፍጠኞችን አከርካሪ ለመበጠስ መረር ያለ እርምጃ መውሰድ : በተለይ በተለይ የኦሮሞን ሀብት ዘርፈው ባለ ፎቅና ባለ ንብረት በሆኑ ባለሀብት ነፍጠኞች ላይ እርምጃ መውሰድ።
OLA በሚቆጣጠራቸው የጎጃም የሰሜን ሸዋና የወሎ ከተሞች የሚገኙን የክልል : የዞን : የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እርምጃ
መውሰድ። ይህንን በሚገባ ስንተገብርና የአማራን ግዛት መቶ ፐርሰንት ስንቆጣጠር : የኦሮሞ ህዝብ ትግል የመጀመሪያ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ በተሳካ ሁነታ ተጠናቀቀ ብለን ወደ ምዕራፍ ሁለት እናልፋለን። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ አብይ አህመድ የኦነግ ወራሪ ሰራዊት በዐማራ ክልል አሰማርቶ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸምላይ የገኛል ።
ፋብሪካወችን በሙሉ ከሰል ማድረግ ከወለጋ በኩል ያለው የሸኔና የልዩ ሀይል ጥምር ጉልበት ወደ ቡሬና ፊኖተሰላም በመግባት አካባቢወችን መቆጣጠር : በአመራሩና ሌሎች ላይ እርምጃ መውሰድ : የኢንዱስትሪ ፓርኩንና ከተሞቹን በኢሳት ማጋየት : የኦሮሞን ህዝብ ትግል መራራነት ማሳየት።
በሸዋ በኩል የአባይን ወንዝ ተከትሎና ተሻግሮ የደጀንንና የደብረማርቆስን ከተማ በፍጥነት መቆጣጠርና የምስራቃዊ ጎጃሙን ክፍል ሞጣንና ብቸናን ጨምሮ በጃል ዳውድ የሚመራው የሸኔና የኦሮሞ ልዩ ሀይል ጥምር ግንባር እንዲቆጣጠረው ማድርግ : ከተሞቹንም ሆነ ሙሉ የኢንዱስትሪ ቦታወችን ወደ ፍርስራሽነት መቀየር።
አራተኛውና ትልቅ ስራ የሚጠይቀው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በኩል በጃዊ አድርጎ ባህር ዳር ከተማን ለመቆጣጠር የሚደረገው ኦፕሬሽን ሲሆን : በተመሳሳይ ሳዓት ከትግራይ አጋር ሀይሎቻችን በኩል ወደ ሙሉ ጎንደርና ወሎ የሚደረገው ግስጋሴ ሽብር ውስጥ ስለሚከታቸውና የኦሮሞን ሀይሎች ለመቋቋም የሚሞክር ብዙም ሀይል ስለማይኖር ባህር ዳርንና ዙሪያውን ለመቆጣጠር ምቹ ሁኔታየሚኖር ቢሆንም በቂ ዝግጅትና ከአጋር ሀይሎች ከጉምዝ ፤ ከቅማንትና ከትግራይ ሀይሎች ) ጋር መናበብ አስፈላጊ ነው።”
አዲስ አበባን ከሁሉም አቅጣጫ ወደ አንድ ማዕከል መክበብና መቆጣጠር : የነፍጠኞችን አከርካሪ ለመበጠስ መረር ያለ እርምጃ መውሰድ : በተለይ በተለይ የኦሮሞን ሀብት ዘርፈው ባለ ፎቅና ባለ ንብረት በሆኑን ባለሀብት ነፍጠኞች ላይ እርምጃ መውሰድ።
OLA በሚቆጣጠራቸው የጎጃም የሰሜን ሸዋና የወሎ ከተሞች የሚገኙን የክልል : የዞን : የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እርምጃ መውሰድ። ይህንን በሚገባ ስንተገብርና የአማራን ግዛት መቶ ፐርሰንት ስንቆጣጠር : የኦሮሞ ህዝብ ትግል የመጀመሪያ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ በተሳካ ሁነታ ተጠናቀቀ ብለን ወደ ምዕራፍ ሁለት እናልፋለን።” ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ አብይ አህመድ የኦነግ ወራሪ ሰራዊት በዐማራ ክልል አሰማርቶ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸምላይ ይገኛል ።
ጽንፈኛ የኦሮሞ ኃይሎች ልዩነት በመካከላቸው ያለ ለማስመሰል ቢሞክሩም የዐላማና ግብ ልዩነት እንደለላቸው ማረጋገጫ በአቶ ጃዋር መሀመድ መጋቢት 2023 “ያለንበት ሁኔታና ቀጣዩ የትግል ምዕራፍ”በሚል ርዕስ የጻፉትን ጽሑፍ መመልከቱ በቂ ነው ።
ሁለቱ ኤትኖ ፋሺስት ድርጅቶች የዐላማም ሆነ የግብ ልዩነት ስለላቸው የተጣሉ መስለው በጓሮ በር ስለሚገናኙ እንደለመዱት በየወንዙ ሊማማሉ ይችላሉ የዐማራ ፋኖ ተደራድሮ የእነርሱን ፋሺስታዊ ስርእት የሚያጸና ሳይሆን የሚታገለው በስር ነቀል ለውጥ ለዜጎቿ ያለ መድሎ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያውና ማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉን ያሳተፈ የሽግግር ፍትህ በማስፈን ሉአላት ኢትዮጵያን ለመገምባት በመሆኑ በመቃብሯ ላይ ሌላ አገር ለመመስረት ከሚፈልጉ አፍራሽ ኃይሎች ጋር የሚደራደርበት አመክኒዮ የለም ። ዐማራ ነን የሚሉ ፣ ባለሞያ ሴት አሥራሁለቱን የዶሮ ብልት እንደምታውቀው ሁሉ የፖለቲካን ብልት ጠንቅቀን እናውቃለን ባዮች የህወኃት ጠበቃው አቶ ልደቱ አያሌውና አቋም የለሹ እንጂነር ይልቃል ጌትነት አይነቶች ከበሬ ብልት ፍሬው ዎድቆ አንስታ ለመብላት ቀኑን ሙሉ ተከትላ እንደምትባዝን ቀበሮ ሌላ ተልዕኮ ለማስፈጸም ካልሆነ በቀር እንደነሱ ከፋሺስቶች ጋር የሚወያይ ለስር ነቀል ለውጥ የሚታግል ፋኖ አይኖርም ።
በማጠቃለያ ሀገር ብትፈርስ ፍርስራሹ የሚወድቀው በዐማራ ሕዝብ ላይ ብቻ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይና የዖሮሞና የትግራይ ሕዝብ በተለይ ከተመልካችነት ተላቆ የትግሉ ተሳታፊ በመሆን የድርሻውምን መወጣት ይኖርበታል ።
ከንጉሤ አሊ