“ጡት በመቁረጥ ፣ቆዳ በመግፈፍ ጭራቅነቱን በአደባባይ ያሳየበት የአብይ አገዛዝ አረመናዊው ተግባር ሰለባ የሆነቺው ፋኒት

የህወኃትና የኦሮሞ ጽንፈኞች የደርግን አገዛዝ አስወግደው መንበረ ሥልጣኑን ሲቆጣጠሩ በጋራ ባዘጋጁት ህገመንግሥት ተብየው ሆን ብለው ባስቀመጡት አንቀጾች መሰረት መግሥታዊ ስርአቱን የጎሣ ፌደራሊዝም እና የሥልጣን ክፍፍሉን መስፈርት በጎሣ ተዋጽኦ ኮታ ያለ ክህሎት አድርገውታል ። ይህንን ያደረጉት ሁለቱም የየራሳቸው ምክንያት ነበራቸው ።
ህወኃት በወቅቱ በሁሉም ነገር የበላይነትን የያዘበት ወቅት በመሆኑ የክልል ውክልናውንም ሆነ የፌደራል ተወካዮችን የመመደብ ጉልበት ስለነበረው በሕዝብ ብዛት አብላጫ ያላቸውን ጎሣዎች በምርኮኞች እና እውቀት አልባ ግለሰቦች እንዲወከሉ አደረገ ። ሀግሪቱ ፖሌቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች የሚወሰኑትና ተግባራዊ መመሪያዎች የሚተላለፉት ከአንድ ማዕክል (ከህወኃት ማኢከላዊ ኮሚቴ) በመሆኑ በወቅቱ የሚያሰጋቸውና የሚያሳስባችው አንዳችም ነገር አልነበረም ፤ ዐማራውን ከሆነ አከርካሪውን ሰብረን ትክሻው ለእስክስታ ትተነዋል ብለው የሚሳለቁበት ወቅት ነበር ፤ የመገንጠል ግባቸውንም ቢሆን ቀስ ብሎ ይደርሳል ብለው በይደረ ተውት።
ኦነጋዊያን ደግሞ የሕዝብ ቁጥራችን ከፍተኛ በመሆኑ በብሔር ተዋጽዖ ከሆነ ብዛት ስላለን ለዘለዓልም ስልጣን ከእጃችን አይወጣም በሚል ቀቢጼ ተስፋ ነበራቸው ።
ሁለቱ ጽንፈኛ ድርጅቶች መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጥረው የጫጉላ ሽርሽር ሳይጨርሱ መርህ አልባ የግንኙነት ቀጭን ክር ተበጠሰና ተለያይተው አንደኛው (ኦነግ) ጥሎ ሲፈረጥጥ ሌኛው (ህወኃት) ስልጣኑን አደላድሎ ለሃያ ሰባት ዓመት የኢትዮጵያን ሕዝብ ረግጦ ገዛ ።
ከበግ ቆዳ የተሰራ ቤት በጅብ ጩሄት ይፈራስል እንዲሉ መሰረት አልባው የኢህአድግ አገዛዝ ያለ ምንም የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅት በሕዝባዊ አመጽ እንደ ጉም ተነነ ። ይህ በሕዝብ ተጋድሎ የመጣው ለውጥ ህልናዊ ሁኔታው ባለመሟላቱ የተነሳ ታሪክ ራሱን ይደግማል እንድሉ ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከስልጣን መወገድ በኋላ እንደነበረው በሕዝቡ ተጋድሎ የመጣው ለውጥ በምሊተሪው እጅ እንደወደቀ ከህወኃት መወገድም በኋላ በጽንፈኛ የኦነግ መር ስብስብ እጅ ገባ ። ብልህ ከሰው ስህተት ይማራ ጅል ግን ከራሱም አይማርም ይባላልና አሁንስ ካለፉት ሁለት ስህተቶቻችን ተምረን ምን ያክል ተዘጋጅተናል የሚለውን ጥያቄ እንዲመልሱ ለምሁራኖቻችን እተወዋለሁ ።
ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ እንዲሉ ኦነጋዊያን ስም ቀይረው ወደ መንበረ ስልጣን በመምጣት የፈረደበትን ዐማራ በፈጠራ ፍረጃ (ቅኝ ገዥ ፣ነፍጠኛ ፣ ገዢ መደብ ፣ ጡት ቆራጭ ወዘተ) እያለ በጠላትነት ፈርጆ የዘር ማጥፋት ወንጀል በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ፖለቲካ ህደት ነውና እንዳሰቡትና እንደተመኙት ሳይሆን በነባራዊ ኩነቶች የሚጓዝ በመሆኑ የህወኃት ጀንበር ጠልቃ የኦነጎችም ጀንበር በማዘቅዘቅ ላይ ትገኛለች።
ጎሣን መስፈርት አድርጎ የተዘረጋው መንግሥታዊ ስርአት የጎሣ ብዛኃነት ባላት ኢትዮጵያ ለሃያ ሰባት ዓመት ተሞክሮ የከሸፈ መሆኑ እየታወቀ አዲሶቹ ኦነጋዊያን ከፈጣሪያቸው ከትህነግ የላቀ የሴራ ክህሎት ያላቸው ይመስል ፖለቲካን በቁማር መስለው እየተበሉ በላን ይሉናል ።
እውነቱን ለመናገር የትግራይም ሆነ የኦሮሞ ሕዝብ ችግር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር የተለየ ባለመሆኑ የሚፈታው በጋራ ነው ፤ አገሪቷም የጋራ በመሆኗ አንዱ ለሌው የመኖሪያ ስፍራ ፈቃጅና ከልካይ ሊሆን አይችልም ። ይህ የጎሣ ሥርአት አዋጭና የሚሰራ ቢሆን ኖሮ ከአንድ ጎልማሳ ዕድሜ (ከ30 ዓመት) በላይ ያስቆጠረ በመሆኑ ቢያንስ ደም ባላፋሰሰ ነበር ።
ኢትዮጵያ ከትግራይ ጽንፈኛ ኃይሎች ወደ ኦሮሞ ጽንፈኞች አገዛዝ ከተሸጋገረች እነሆ ስድስት ዓመት አስቆጥሯል ፤ ይህ ወቅት ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ አብይ አህመድ በኦሮሞ ሕዝብ ስም የያዘውን የፌደራል ሥልጣን በዐማራ ሕዝብ ደም ኦሮሚያ የምትባል አገር ለማዋለድ በመጣር ላይ ይገኛል ።
ካሁን ቀደም በስውር ይካሄድ የነበረው የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ዘመቻ ከሶስት ዓመት ወዲህ በገኃድ በጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ መሪነት ፤ በአቶ ሽመልስ አብዲሳ አዝማችነት እና በስም የሚለያዩ በገቢር ግን አንድ በሆኑ በኦሮሞ ሕዝብ ስም የተቋቋሙ ድርጅቶችና ሚዲያዎች የተቀናጀ ጦርነት ተከፍቶበት እንዲያልቅ እየተደረገ ነው። አብይ አህመድ ኦነግን ዘመናዊ መሳሪያ አስታጥቆ አማራን እያስፈጀ ከትህነግ ወረራ የታደገውን ፋኖ ለመምታት እና የአማራን መሬት አሳልፎ ለመስጠት በእርቅ ስም የተሰረውን ሴራ ለመተግበር እንቅልፍ አጥቶ ይባዝናል።
የአብይ አህመድ አገዛዝ ዐማራን ለማጥፋት ቆርጦ መነሳቱን ማረጋገጥ የሚቻለው ሰሞኑን በዐማራ ክልል ጎጃም ውስጥ “ጡት በመቁረጥ ፣ቆዳ በመግፈፍ ጭራቅነቱን በአደባባይ ያሳየበት አረመናዊው ተግባር ነው”።
አቶ ለንጮ ባቲ “ኦሮሚያ የምትባል አገር ለመመስረት እየጣርን በመሆኑ አንዲት ሴት ስትገላገል ደም እንድሚፈሳት ሁሉ የምናዋልደው አገር ስለሆነ ደም መፍሰሱ አይቀሬ ነው” ባሉት መሰረት የዐማራን ደም ያለ ከልካይ ያፈሳሉ ሥጋውንም ቆራርጠው ይጥላሉ ።
በዚህ መንገድ ህልውናውን ለመታደግ የዘመተውን ፋኖም ሆነ ስንቅና ምሽጉ የሆነውን የዐማራ ሕዝብ አሸብሮ ሊያንበረክክ አይችልም በተቃራኒው እንደ አራስ ነብር አስቆጥቶ ያጀግነዋል እንጅ ።
የመስዋእትነት መጠኑን ለመቀነስ የፋኖዎቻችን አንድነት ወሳኝ በመሆኑ በጎንደር የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ ሲቻል አንድ ወጥ አመራር ካልሆነም ሁለቱ አደረጃጀቶች (አፋህድና አፋብሀ) ተናበው ይህንን ሕዝብ በታኝና ሀገር አፍራሽ የሆነውን ከእነ ርዝራዦቹ በማስወገድ አዲስ ታሪካዊ ገድል ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል ።
ኢትዮጵያ እንደ ሀገርና ሕዝቦችዋ እንደ ዜጋ በገዛ ሀገራቸው ለመኖር አንዱ ፈቃጅ ሌላኛው አስፈቃጅ ወይንም አንዱ ሟች ሌላው ተመልካች ሊሆን ስለማይችል በስሙ የሚነገድበት የኦሮሞ ሕዝብ ጭምር ይህንን ሥርዐት አስወግዶ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት በሚደረገው ትግል ሁሉም ተሳታፊ መሆን አለበት።
ከሁሉም በላይ ዐማራ ይህንን ትግል ካላሸነፍን ባሪያ ሆነን ለመኖር እንኳን የማይፈቀድልን መሆኑን ተገንዝበን አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ለመድረግ በረባ ባረባ መከፋፈሉን ትተን በአንድነት መነሳት ይኖርብናል ። የተዘመተብን በዐማራነታችን በመሆኑ ወደ ጎጥ ከረጢት ሳንሸከፍ በዐማራነት ጸንተን መቆም ይኖርብናል ።
ህወኃትና ኦነግ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ሕዝብ የሆኑ ጽንፈኞች ከስህተታቸው የማይማሩ ቆሞ ቀር ድርጅቶች በመሆናቸው የተነሳ የፈጸሙት እልቆ መሳፍርት ወንጀል ስለአለ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሕዝቡን እንደ መያዣ እየተጠቀሙት በመሆኑ በስሙ የሚነገድበት የትግራይና የኦሮሞ ሕዝብ በቃችሁ ልላቸው ይገባል።
ሌላው የዐማራን የህልውና ትግል ተከትሎ በዐማራው ስም እንደ አሸን የፈሉ መሰረታዊና ማኅበራዊ ሚዲያዎች ከዐማራዊም ሆነ ከሚዲያ ስነምግባር በወጣ ለግል ጊዜያዊ ጥቅም ብለው የሚያደርጉትን ከፋፋይ ፕሮፖጋንዳ ሊያቆሙት ይገባል ። ወንድምን ከወንድሙ ደም አቃብቶ የሚገኝ ገንዘብ በሞራልም ሆነ በታሪክ ተጠያቂነትን ያስከትላል ።
ድል ለኢትዮጵያ
ድል ለዐማራ ሕዝብ
ድል ለፋኖ
ንጉሤ አሊ