ኢትዮጵያ ሀገራችን ዛሬ ከምንጊዜውም በላይ የመፈራረስ አደጋ ላይ ነች ይህ ሟርት ሳይሆን መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔት የሚያረጋግጠው ሀቅ ነው ። ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አህመድና ድርጅታቸው ብልጽግና ፓርቲ ይህንኑ ተግባር ደረጃ በደረጃ በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ ። ውድ አገርህን የምትወድ ኢትዮጵያዊ በሙሉ አጽንዖት ሰጥተህ ካየህ ጠቅላይ ሚንስትሩ አገር ወዳዱ ዜጋ መስማት የሚፈልገውን ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ እያጮሁ ድምጻቸውን አጥፍተው ግን ከሀገር አፍራሾች ጋር ተመሳጥረው ብዙ እርምጃ ወደፊት ተራምደዋል
- ከቅንነት የተነሳ አብዛኞቻችን ኢትዮጵያ አትፈርስም እንላለን አዎን አትፍረስብን ግን ላለመፍረሷ ምንም ማረጋገጫ የለንም ስልታዊ በሆነ መንገድ የውስጥና የውጭ አፍራሽ ኃይሎች በመተባበር በዓለም ላይ ብዙ አገሮችን በታትነዋል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለመበታተን እጅግ በጣም ቀላልና ውጣ ውረድ የማያስፈልገው ነገር ነው ይሄውም ትህነግና ኦነግ ህጋዊ በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ እንድትፈረስ የጫኑብን ህገመንግሥት አንቀጽ39 የብሔሮች፣ብሔረሰቦች፣ መብት በሚለው ተራ ቁጥር አንድና 4 ሀ እንዲህ ይላል፦ „ተራ ቁጥር ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ፣ ብሔረስብ ፣ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከ መገንጠል ያለው መብት በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው ። „ „ተራ ቁጥር 4. የብሔር ፣ ብሔረስብ ፣ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት ከሥራ ላይ የሚውለው„
„(ሀ) የመገንጠል ጥያቄ በብሔር ፣ በብሔረሰቡ ወይም በሕዝቡ የሕግ አውጭ ምክር ቤት በሁለት ሶስተኛ የድምጽ ድጋፍ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥ ፣ ነው ይላል ። ይህ ማለትመገንጠል እፈልጋለሁ የሚለው ጎሣ (ክልል) የህግ አውጪ ምክር ቤት በሁለት ሶስተኛ ድምጽ 130 ሚሊዬን ሕዝብ የሚኖርባትን ኢትዮጵያ ለመበታተን ህጋዊ መብት አለው ማለት ነው
ኢትዮጵያን አፍርሰን በመቃብሯ ላይ ኦሮሚያን እንመሰርታለን የሚለው ኦነግ አርቅቆ ያጸደቀውን ይህንን ሕገመንግሥት ይዘንና ፓርቲውን ሥልጣን ላይ አስቀምጠን ኢትዮጵያ አትፈርስም ብሎ ራስን ማታለል ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል ደረጃ በደረጃ እየፈረሰችም ለመታዘብም በቅተናል ። ኢትዮጵያን ደረጃ በደረጃ የማፍረስ ህደቶች ፦
- ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍና በብሔራዊ ደረጃ የምትታወቅባቸውን ቅርሶችና ታሪካዊ እሰቶችን ስልታዊ በሆነ መንገድ ማውደም ፦
ሀ)የሚንልክን ቤተመንግሥት በእድሳት ስም ያለ ሕዝብ ይሁንታ ታሪካዊ ይዘቱን መለወጥና ስም መቀየር ፤
ለ)በዩኔስኮ የተመዘገቡ ታሪካዊ ቅርሶችን ከአዲስ አበባ ለማስወገድ የተጀመረው ጥንታዊና ታሪካዊ ቤቶችን ማፍረስ ፤
ሐ) የአደዋ የድል በዓል በሚንልክ አደባባይ እንዳይከበር መንግሥታዊ ክልከላና ትንኮሳ ፤
መ)በሕዝበ ውሳኔ ያልተቀየረውን ነባርና ታሪካዊ ሰንደቅ ዓላም ሕዝቡ እንዳይጠቀም መከልከል ፤
ሠ)ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያንን ለማዳከምና ብሎ ለማጥፋት እየተካሄደ ያለው ሴራ ፤
- ሕገመንግሥቱን ተገን በማድረግ ከትህነግ የቀሩ ተግባራትን በመፈጸም ግንጠላውን እውን ማድረግ
ሀ)የክልሎችን ቁጥር በመጨመር መበታተኑን (disintegration) ማፋጠን ፤
ለ)የክልሉ ነዋሪ የአንድ ዘውጌ አባላት ብቻ እንዲሆኑ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንዲካሄድ መፍቀድ ፤
ሐ)በመለስ ዜናዊ ጊዜ ተፈርቶ እንዳይነካ የተባለውን ውህድ
የአዲስ አበባ ነዋሪ ዲሞግራፊ ለማስተካከል ተብሎ የሚፈጸም ግፍና እንቅፋት የሚሆኑትን በጉልበት ለማንበርከክ 50 ሺህ ፖሊስ ከአዲስ አበባ ውጭ መመልመል እና አስልጥኖ ማሰማራት ፤
መ) ለግንጠላው እንቅፋት ይሆንብናል ያሉትን የአማራን ዘውግ በዘዴ በጦርነትና ከክልሉ መሬት እየቆረሱ ወደ ሌላ ክልል በመስጠት ማዳከም ፤
ሠ) በአማራ ክልል ራሱን ለመከላከል የተደራጀውን ፋኖና ሚሊሺያ ለማፍረስና ትጥቅ ለማስፈታት ተብሎ በታወጀው ጦርነት የዘር ማጥፋትና የዘር ማሳሳት ወንጀል መፈጸም ።
ረ)እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው የተሰጉ የዐማራ ልህቃንን የፓርላማ አባላትን ጨምሮ አስሮ ማሰቃየት እና መግደል ፤
- በሰላምና በእርቅ ስም የሚደረግ ስውር ሴራ ፦
ሀ) የጦር ወንጀለኞችን ከእስር ፈቶ መልቀቅ( የቀድሞ የህወኃት አባላትን) ፤
ለ) ወልቃይት ጠገዴና ራያን ለትህነግ ሰጥቶ ትግራይ
እንድትገነጠል ሁኔታዎችን ማመቻቸቱ በዶክተር አብይና ዶክተር ደብረጽዮን እየተካሄደ ሲሆን ይህም የኦሮሞ ተስፋፊዎች ከአማራ ክልል አለን ለሚሉት መሬት በር ከፋች መሆኑ ፤ እነዚህ ከላይ ከብዙ በጥቂቱ ለመጠቃቀስ የሞከርኳቸው ደረጃ በደረጃ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሂደቶች የሚተገበሩት በትረሥልጣኑን በጨበጠው የኦህደድ ብልጽግና መንግሥት ነው ።
ከሁሉ አስቀድሜ ዶክተር አብይ ያሻግሩናል ፣ ከእኔ የበለጡ ኢትዮጵያዊ ናቸው ፣ ጊዜ እንስጣቸው ፣ የሚናገሩት በሙሉ ስለ ኢትዮጵያ ነው የሚትሉ ቅንና አፍቃሬ ኢትዮጵያ እህትና ወንድሞቼ ዶክተር አብይ አህመድ ኢትዮጵያን የሚወዱ ዜጎች መስማት የሚፈልጉትን ነገሮች እንደ ውዳሴ ማሪም ሸምድደው በበአለ ስመታቸውና ለተወሰኑ ወራቶች ሁላችንንም አታለውናል እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ ውሎ ሲያድር ትክክለኛው ማንነታቸው አፍጥጦ ወጣና ተቀባይነታቸውም እንደ ጉም ተነነ። አሁንም ዶክተር አብይን እንደ ለውጥ ፈላጊ አድርገው የሚያዩና የሚደግፉ ቅን ኢትዮጵያውያን መደገፍ መት ቢሆንም ሀገርን ለማፍረስ ሲንደረደሩ በቃህ ሊሉ ይገባል የሚሉትንም ቢሆን መርጦ ከመስማት ሁሉንም አድምጦ ሚዛን ላይ ማስቀመጥ ለሀገርም ለወገንም የሚጠቅም ተግባር ነው ።
ዶክተር አብይ ሕጉን ሊያጸኑ እንጂ ሊያፈርሱ አለመምጣታቸው ፦
የአማራ ሕዝብ ባልተሳትፈበትና በማያውቀው ሕግ መተዳደር የለብትም ተብሎ ለሚቀርብ የብዙኃን ጥያቄ ዶክተር አብይ ለአንድ ክልል ተብሎ ሕግ አይቀየርም ብለዋል ። ሰሞኑን ከብልጽግና የጉባኤ ድራማ መልስ ብልጽግናም ሆነ ሌላ ሕገመንግሥቱን ማሻሻል አይችልም ቢሻሻልም በህጉ መሰረት ነው ብለዋል በሌላ አባባል ሕገመንግሥቱን መቀየር አይቻልም ማለት ነው ምክንያቱም ሕገ መንግሥቱ ሊሻሻል የሚችለው በአንቀጽ 105 ተራቁጥር 1 (ሀ) መሰረት ነው ።
አንቀጽ 105 ሕገ መንግሥትን ስለ ማሻሻል ፦
- በዚህ ሕገ መንግሥት ምዕራፍ ሦስት የተዘረዘሩት መብቶችና ነጻነቶች በሙሉ ፣ይህ አንቀጽ ፣ እንድሁም አንቀጽ
104 ሊሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳኻን ብቻ ይሆንል
ሀ) ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች የቀረበውን ማሻሻያ በድምጽ ብልጫ ሲያጸድቁት ፤ ይህ ማለት በሕጉ መሰረት የማሻሻያ ሀሳቡን የአንድ ክልል
ምክርቤት ውድቅ ሊያደርገው ይችላል ማለት ነው ። በሌላ አነጋገር ያለ ትህነግና ኦነግ ፈቃድ እንዳይሻሻል ሆን ብለው የደነቀሩት አንቀጽ እስካልተወገደ ወይንም የፖለቲካ ውሳኔ እስካልተሰጠ በቀር በምንም አይነት ማሻሻል እንደማይቻል እያወቁ ጠቅላይ ሚንስቴሩ አንዴ ለአንድ ክልል ተብሎ አይቀየርም ሌላ ጊዜ በህጉ መሰርት ይሻሻላል እያሉ ያላግጣሉ ። አጾንኦት መስጠት የሚገባን በኦህደድ ብልጽግናና በትህነግ ኢትዮጵያን በማፍረሱ ጽንሰ ኃሳብ ምንም ልዩነት የላቸውም ችግር የተፈጠረው ትህነግ በምሊቴሪ ጉልበቱን አፈርጥሞ ፤ በኢኮኖሚ ደርጅቶና የግዛት ይዞታውን አስፍቶ አቶ መለሰ ሁሌም ሁሌም እንደሚያስፈራሩን ለኦነግ አስረክበውን መሰሥ ሊሉ ነበር ነገር ግን የለውጡ ድንገተኝነት ያበሳጫቸው ህወኃቶች ቂማቸውን ለመወጣት ሲኦልም ቢሆን ገብተን ለዚህ እንድንበቃ ባደረገን አማራ ላይ ህሳብ እናወራርዳለን ብለው በአብይ ታዛቢነት ወረራ አካሔዱ ። ዶክተር አብይም ይህንን ሳይዋሹ ትህነግ አዲስ አበባ ቢገባ እናንተን ጠራርጎ ያጠፋችኋል እንጂ ኦሮሞን አይነካም ነበር ብለዋል ። ኢትዮጵያን እንዴት ከጥፋት እንታደጋት ?
ይህ ጥያቄ የሚመለከተው ኢትዮጵያ በምትባል ሉአላዊ ሀገር የሚኖሩ በዘውጌው የሕዝብ ብዛት ቀሚሴ በቁመቴ ልክ
ይሰፋልኝ በሚል ፍልስፍና ሳይሆን ሁሉም እንደዜጋ ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ ተከብሮ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያውና ባህላዊ ነጻነቱ እንዲረጋገጥ የሚፈልገውን ዜጋ በሙሉ ነው ። በመሆኑ የትህነግና የኦነግ ኦህዴድ ብልጽግና ከላይ የተጠቀሱትን ፕላኖቻቸውን እውን ለማድረግ የሥልጣን ጥላቸውን ለጊዜው ወደጎን ብለው ለእርቅ በውይይት ላይ ናቸው የትግራይ ህዝብ የወያኔን ሂትለራዊ ተግባር እንዲረዳ ፣ መከላከያው ለጊዜው ፣ ገለል ማለቱ ተገቢ ነው ፡፡
እዚህ ላይ እርቅ ለምን ይደረጋል እያልኩኝ አይደለም እንኳንስ በወንድማማቾች መካከል ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን የተከሰተ አሸናፊ የሌለው ጦርነት ይቅርና ከውጪ ጠላት ጋር የሚደረግ ጦርነት እንኳን መቋጫው እርቅ ነው ። ጥያቄው የጦርነቱ ሰለባ ከሆነው ሕዝባችን ጀርባ በምስጢር እንዲደረግ ለምን ተፈለገ ? የእርቅ ውጤቱ ሰጥቶ መቀበል እንደመሆኑ መጠጥን ማን ምን ሰጥቶ ምንስ ለመቀበል እየተደራደረ ነው የሚለውን መንግሥት ለሕዝብ ግልጽ ለማድረግ ለምን ፈራ ? በዚህ መልኩ በሚካሄድ ውይይት የሚደረግ ስምምነት ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል ወይ ?
ካለው ነባራዊ ሁኔታ የምንረዳው ሁለቱ ውይይቱን የፈለጉት ሰላም ለማስፈን ሳይሆን ዓላማቸውን ከማሳካታቸው በፊት ሁለተኛው ሕዝባዊ ማእበል እንዳይነሳ ለማደናገርና እንቅፋት ይሆንብናል የሚሉትን አሁን በፋኖ ላይ እንደጀመሩት ለይተው በመምታት ለማዳከም ነው ። ግባቸው የሚሆነው ትህነግ የበላይ በነበረችበት ወቅት ከሌሎች ክልሎች ቀምታ የተመለሱ ቦታዎችን መመለስና የትህነግን የታላቋን ትግራይ የመመስረት ቅዠት እውን ማድረግ ነው ። በዚህ ተግባር ላይ ከውጭ ጠላቶቻችን ጭምር ሁሉ አቀፍ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ።
ኢትዮጵያን እንደ ዶሮ ብልት ለመገነጣጠል የሚፈቅድ ህገ መንግሥት ስላለ ቀሪውን ኦህዴድ ብልጽግና ይገባኛል የሚለውን መሬት ከክልሎችና ከከተማ መስተዳድሮች በመውሰድ የቀሩትን ከፈለጉ በገዳ ስርአት ደንብ ገርባ ሆኖ በኦሮሙማ እንዲዋጡ ማድረግ ያልፈለገውን በህገ መንግሥቱ መሰረት የክልሎችን ቁጥር በመጨመር አቅመ ቢስ አድርጎ እንዲገነጠሉ መፍቀድ ነው ። በእትዮጵያ መቃበር ኦሮሙማን መገንባት ማለት ይህ ነው ።
የኦህዴ ብልጽግና በዶክተር አብይ አህመድና በአቶ ሽመልስ አብዲስ መሪነት በቅድሚያ በአማራ ሕዝብ ቀጥሎ ሌላውን ተራ በተራ በህግ መስከበር ሽፋን በኦሮሞ ልዩ ኃይልና ኮማንዶ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ህጻንና አዛውንት ሳይለይ ህገወጥ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በመገንዘብ ያለ ኢትዮጵያ የሚኖር ዘውጌ (ብሔር ፣ ብሔረሰብ ወይንም ሕዝብ) ስለማይኖር ማንኛውም ግለሰብ ፣ ቡድንና ድርጅት የትህነግንና የኦሮሞ ድርጅቶችን ሀገር የማፍረስ ተግባር ለማስቆም አገር አቀፍ ሕዝባዊ እምቢተኝነት መደረግ አለበት ። አገር አቀፍ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድርጎ ለውጥ ለማምጣትየሚያስችሉ ነባራዊ እና ህልናዊ ሁኔታዎች አሉወይ?
ነባራዊ ሁኔታን በተመለከተ ከሚፈለገው በላይ ተሟልቷል በመሆኑም አገር አቀፍ ቀውስ ተፈጥሯል ያም ማለት አገዛዙ በነበረው መንገድ የመግዛት አቅም የለውም ፣ እሕዝቡም በነበረው አይነት ለመገዛት የሚያስችል ሁኔታ ላይ አይደለም ጠቅለል ሲደረግ አገር አቀፍ ቀውስ አለ ። ቀውሱ ያስከተላቸው ችግሮችን ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም ፤ አገዛዙም ቢሆን በውሸትና በፕሮፖጋንዳ ሊሸፍነው አልቻለም ። ህልናዊ ሁኔታን አስመልክቶ መቶ በመቶ የተሟላ ነው ማለት ባይቻልም ካሁን በፊት የተሰባሰቡና አሁንም በመሰባሰብ ላይ ያሉ ሀይሎች ግለኝነትን በመተው ግንባር ፈጥረው እንዳለፉት ጊዜያቶች ትግሉ ተጠልፎ ሌላ አዙሪት ውስጥ እንዳንገባ የአላማ አንድነት ያላቸው ሰርገኛ መጣ እንዳይሆን ከወዲሁ ቢዘዘጋጁ መልካም ነው ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ ካሉ መቃብርም ይሞቃል ከሚል አጉል ብህል ወጥቶ የህንን አገዛዝ ለመቃወም አደባባይ መውጣት ይኖርበታል እንጂ እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ እየመጣ ነው እየመጣ ነው ቢል ጥቅም የለውም ። ስለሆነም ጥቃቅን ልዩነቶችን ለጊዜው በመተው በአገራዊና ሕዝባዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ በመሆን የህንን ወቅታዊ አደጋ በጋራ ለመመከት ሕዝባዊ እምቢተኝነት የህሊውና ጉዳይ እንጂ አማራጭ አይደለም። በሀገር ሏላዊነትና በሕዝባችን አንድነት ላይ የሚሸረብ ሰሞነኛ ሴራ የሀገራችንን ችግር አልፋና ዖሜጋ አብይና አብይ ብቻ አድርገው እየኮነኑ ሰላም ፈላጊ በመምሰል ደም መፋሰሱ ቆሞ ኢትዮጵያ ሁለትም ሶስትም ሀገር ሁና በጥሩ በጉርብትና አብረን ብንኖር ይሻላል እያሉ የሚያመቻምቹ ጸረ አንድነት ሀይሎችን የሚያጅቡ አደናጋሪዎችን እያዬን በመሆኑ የአገር ወዳድ ምሁራን ዝምታ መስማማት ነው ወይንስ አድርባይነት
ፈጣሪ ኢትዮፕያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅልን