ተዋናይ ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራ እና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል ። በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል ፣ በአትላንታ ጆርጂያ በበረከተው የሙያው ሥራ ኖቬምበር 24 ቀን በስሙ ተሰይሞለታል። (ጋሽ ደቤ) በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት ካሉት አርቲስቶች ግንባር ቀደሙና አንጋፋው ነው።
መጀመሪያ በቴያትር የታዩት በመንግስቱ ለማ በተጻፈው ያላቻ ጋብቻ ሲሆን ከዚያ በአንዳንድ እንግሊዝኛ ትርኢት (The game of chess, ‘Waiting for Godot’) እንዲሁም በራዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን ተጫወቱ።
አርቲስት ደበበ እሸቱ (ጋሽ ደቤ) ለታሪክ የሚተላለፉ ህያው ስራዎች ሰርቷል እስቲ ጋሽ ደቤ ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ በጥቂቱ እንያቸው፤ በሃገር ውስጥ ካለው ታዋቂነትና ለሙያው ካደረገው አስተዋጽኦ ለመጠቀስ ያህል ፡-
ያላቻ ጋብቻ ተዋናይ
ሮሚዎባ ዡልየት ተዋናይ
ጠልፎ በኪሴ ተዋናይም አዘጋጂም
ዳንዴው ጨቡዴ ››
ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ (በእንግሊዝኛ) ተዋናይ
ኦቴሎ (በአንግሊዝኛ) ተዋናይም አዘጋጂም
አዳ ኦክ አራክል (በእንግሊዝኛ)ከሎ.ጸ.ገ.መ ተዋናይ
በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ(ብሔራዊ) ቴአትር፡-
የበጋ ሌሊት ራዕይ ተዋናይ
አንድ ዓመት ከአንድ ቀን ተዋናይ
እናት ዓለም ጠኑ ተዋናይ
ኪንግ ሊር ተዋናይ
ዋናው ተቆጣጣሪ ተዋናይ
ጠያቂ ተዋናይ አዘጋጅ
በቀይካባ ስውር ደባ አዘጋጅ
ተሓድሶ አዘጋጅ
የአዘውንቶች ክበብ አዘጋጅ ተዋናይ
በሃገር ፍቅር ቴአትር፡-
ጠልፎ በኪሴ አዘጋጅ/ተዋናይ
የወፍ ጎጆ ተዋናይ
ኪንግ ሊር ተዋናይ
የቬኒሱ ነጋዴ ተዋናይ
ናትናኤል ጠቢቡ ተዋናይ
ድብልቅልቅ ተርጓሚ/ ተዋናይ
ማዕበል ተርጓሚ አዘጋጅ
በፊልም በሃገርና በዓለም አቀፍ፡-
ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር
ሻፍት ኢን አፍሪካ
ጉማ
ዚ አፍሪካን ስፓይ
ዜልዳ
አፍሪካ
ዘግሬቭ ዲገር
ዘ ግሬት ሪቤሊየን
እነዚህ ለምሳሌ ያህል የቀረቡ እንጂ የደበበ ስራዎች በርካቶች ናቸው፡፡ ከመድረክና ፊልም ስራዎቹ ባሻገር ተማሪዎችም አሰልጥኗል፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በብሔራዊ ቴአትር የተዋንያን ስልጠና ማዕከል ሲያቋቁሙ ከመምሃራኖቹ መሃልና በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው መምህር ደበበ ሲሆን ለተማሪዎቹም መማርያ እንዲሆን የተረጎመው የስታንስላቭስኪ የተዋናይ ሀሁ ለበርካታዎች የሙያ ተማሪዎች የሙያቸው ፊደል መቁጠርያ ሆኖ ይገ ኛል፡፡
ያልታመመው በሽተኛ
ድብልቅልቅ
ጎርፉ
ከመጽሐፍ ደሞ
የዳዊት ወልደጊዮርጊስን
የደም እንባ
የራሱን ወጥ ሥራ በተመለከተ
የእምነቴ ፈተና
ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው
ደበበ ለአፍሪካ ጥበብ ያለውን አመለካከትና ግንዛቤ ከቅኝ ገዢዎች ትርጓሜ ለማውጣትና ሶስተኛው ዓለም ኋላ ቀር ሲባልም በኤኮኖሚና በቴክኒዮሎጂ እንደሆነ፤ ይህም የሆነው ነጩ የአፍሪካን የዋህነት፤ እንግዳ ተቀባይነትና ሩህሩህነት መንጠላጠያ በማድረግ ቅኝ አድርገው ህሊናውን ስለዘጉበትና ስላሰሩት መሆኑን፤በባህል በኩል ግን ጨርሶ ሊደርሱበት የማይችሉትና ሊያጠፉትም ያደረጉት ሙከራ ዋጋ ቢስ ሆኖ እንደቀረ የሚያስረዳ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ተቀባይነትን አግኝቶ ድል ያደረገና፤ ቀደም ሲል የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በ1985 ዓ/ም እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በርሊን ላይ በተካሄደው የዩኔስኮ የባህል(አይ ቲ አይ) ኢንተርናሽናል ቴአትር ኢትዮጵያን ወክሎ በመገኘት በአፍሪካ ውስጥ የመጀመርያው ፕሮፌሽናል ቴአትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር መሆኑን በማስረጃ አስደግፎ ተቀባይነትን አገኘ፡፡
በዚሁ ዓመት የዩኔስኮ የባሕል ክፍል አይ ቲ አይ የአፍሪካ ተጠሪ ሆኖ በመመረጥ፤ በዚያው ዘመን ዝምባብዌ ላይ በሚካሄደው ቴአትር ለልማትና ዕድገት ወርክሾፕ ላይ በመሪነት እንዲገኝ በዩኔስኮ ተወክሎ በመሄድ ወርክሾፑን በአጥጋቢ ችሎታውና የአመራር ብቃቱ ከመፈጸሙም ባሻገር ለብዙ ጊዜ ተሞክሮ ሲወድቅ ሲነሳ የነበረውን የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማሕበርን አስተባብሮ በማቋቋም የማሕበሩም መስራች ፕሬዜዳንት ሆኖ ለ12 ዓመታት መርቷል፡፡ አሁንም መስራች ፕሬዛዳንት በመባል ይጠራል፡:
ደበበ በችሎታውና በብቃቱ በማስተባበር ችሎታው ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቴአትር ኢንሳይክሎፒዲያን ለማዘጋጀት ሲወስን ደበበንም አፍሪካን በመወከል የኤዲቶርያል ቦርድ አባል አድርጎ መድቦት ሥራውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡
ደበበ ቴአትር ለልማትና ለእድገት በሚል የሚታወቀውን የቴአትር ዲሲፕሊን ስልጠና ለበርካታ ሃገራት ባለሙያዎች ያስተማረ ሲሆን በርካታ ወርክሾፖችም በየሃገራቱ እየተጋበዘ መርቷል፡፡ ይሀን ዘዴ ካዋቀሩትም አምስት አፍሪካዊ ባለሙያዎች አንዱ ደበበ ነው፡፡
ወርክሾፕ የሰጠባቸው ቦታዎች፤ ታንዛኒያ፤ኡጋንዳ፤ኬንያ፤ማላዊ፤ኮንጎ ብራዛቪል፤አይቮሪ ኮስት፤ ካሜሩን፤ ናይጄርያ፤አይርላንድ፤ብራዚል፤ሰሜን አሜሪካ፤እንግሊዝ፤ ኩባ፤ በርሊን፤ካናዳ ይገኙበታል፡፡
ደበበ ላለፉት ከ40 በላይ ዓመታት በቴአትር ጥበብ ውስጥ ኖሮ በ1995 በተካሄደው ሃገራዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ‹‹ቀስተደመና›› የፖለቲካ ፓርቲን ተቀላቅሎ፤ በኋላም ቅንጅት ሲፈጠር የምክር ቤት አባልና የሕዝብ ግንኙነት በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ቅንጅትን ለድል ያበቃ፤ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዝግጅቶቹ ገዢውን ፓርቲ ያንበረከኩና ቅንጅትና ያገዘፉ ነበሩ፡፡በዚህም ከሌሎች አመራሮች ጋር ለአንድ ዓመት ከአስር ወራት ለእስር ተዳርጓል፡፡ እንዲሁም በ2002 በድጋሚ ለአንድ አመት ታስሮ ተፈቷል፡፡
ደበበ በሃገሩ ለመሸለም ባይበቃም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ለሽልማቶች የበቃ ባለሙያ ነው፡፡ ለዚሁ የሙያ አስተዋጽኦ ክፍተኛው ክብሩ በአትላንታ ጆርጂያ ኖቬምበር 24 የደበበ እሸቱ ቀን ተብሎ እንዲሰየም የከተማው ምክር ቤት ማጽደቁ ነው፡፡
ጋሽ ደቤ ጋደኛም ሚስትም ከሆነችው ከአልማዝ ደጀኔ ጋር 4 ልጆች እና 6 የልጅ ልጆች አሉት።
viaጌጡ ተመስገን
————————————–
ዝክረ ደበበ እሸቱ!

ጋሽ ደቤ !
የፖለቲካ አቋሙን እንተው ፤ ምክንያት እኔም ከእርሱ ጋር እጅግ በጣም የተራራቀ አቋም ነው ያለኝ። “ሙት ወቃሽ አትሁን” የሚባለው ፤ ሙት መወቀስ ስለሌለበት ብቻ ሳይሆን ‹መልስ ለመስጠት በማይችልበት ሁኔታ› መውቀስ ለሰማዩም ለምድሩም የከበደ እንዲሁም ጥቅም ስለ ሌለው ጭምር ነው!
ጋሽ ደቤ’ን በቅርብ የምናውቀው ጋሽ ደቤ እያልን “አንተ” ብለን የምንጠራው ፤ እንደ አባትህ ፣ እንደ ታላቅ ወንድም፣ እንደ እኩያ እንዲሁም እንደ ጓደኛ ስለ ምንቀራረብ ነው። እንደ ቀረቤታችን መጠን ያተረፍነው ብዙ ነገር አለ!
ጋሽ ደቤ በማኅበራዊ ሕይወቱ እጅግ በጣም ምስጉን ሰው ነው።
ተዋናይ፣ ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል። በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል፤ በአትላንታ ጆርጂያ ባበረከተው የሙያው ሥራ ኖቬምበር 24 ቀን በስሙ ተሰይሞለታል።
ጋሽ ደቤ ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፡- ያላቻ ጋብቻ ፣ ሮሚዮና ዡልየት ፣ ጠልፎ በኪሴ ይገኙበታል። እንዲሁም ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ ፣ ኦቴሎ እና አዳ ኦክ አራክል በተመልካች አድናቆትን ያተረፉ የሙሉ ጊዜ ቲያትሮችን በእንግሊዝኛ የተወነ ድንቅ አርቲስት ነው። የበጋ ሌሊት፣ አንድ ዓመት ከአንድ ቀን ፣ እናት ዓለም ጠኑ ፣ ዋናው ተቆጣጣሪ ፣የአዛውንቶች ክበብ ፣ የወፍ ጎጆ ፣ ኪንግ ሊር ፣ የቬኒሱ ነጋዴ የተሳተፈባቸውና ምርጥ ብቃቱን ያሳየባቸው ሥራዎች ናቸው።
በፊልም የሙያ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳተፈባቸው ፤ ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር ፣ ሻፍት ኢን አፍሪካ ፣ ጉማ ፣ ዚ አፍሪካን ስፓይ፣ ዜልዳ ፣ አፍሪካ ዘግሬቭ ዲገር ፣ ዘ ግሬት ሪቤሊየን ይገኙባቸዋል። የአርቲስት ደበበ ስራዎች በርካታ ናቸው፡፡ ከመድረክና ፊልም ስራዎቹ በተጨማሪ የስታንስላቭስኪ የተዋናይ ሀሁ መማሪያ መፃፍ በመተርጎም ለበርካታ አርቲስቶች የሙያቸው ፊደል መቁጠርያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡
ጋሽ ደቤ ደከመኝ የማይል ብርቱ ሰው ነው። በትርጉም በኩልም የሙሉ ጊዜ ቲያትር ፤ ያልታመመው በሽተኛ፣ ድብልቅልቅ እንዲሁም ጎርፉ የተሰኙ ቲያትሮች የተረጎመ ሲሆን፤ ከመጽሐፍ የባሩድ በርሜል የእሱ የትርጉም ሥራዎች ናቸው። የራሱን ወጥ ሥራ በተመለከተ የእምነቴ ፈተና የተሰኘ መጽሐፉ ለንባብ አብቅቷል።
አርቲስት ደበበ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቴአትር ኢንሳይክሎፒዲያን አፍሪካን በመወከል የኤዲቶርያል ቦርድ አባል በመሆን አገልግለዋል። በተጨማሪ የቲያትር ሥልጠናዎችን በየሃገራቱ እየተጋበዘ አስተምሯል፡፡ አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ቀያይ ቀምበጦች በሚለው ፊልም ላይ ባሳየው የተዋናይነት ብቃቱ በካናዳ ቫንኩቨር የGolden Leopard Award ተሸላሚ ሆኗል።
ዝነኛው እውቁ የብዙ ተሰጥኦ ባለቤት አርቲስት ደበበ እሸቱ፤ ጋሽ ደቤ እግዚአብሔር ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን !!!
ለወዳጅ ዘመዶቹና የቅርብ ቤተሰቦቹ እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን። ነብስ ይማር !
ዋርካው ! የኔታ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም እግዚአብሔር ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን !!!
፨ ፎቶ
ጋሽ ደቤ ቆሞ እኔ የተቀመጥኩት አክብሮት ባለማወቅ የሆነ አይደለም ፤ ከጋሽ ደቤ የወገብ ህመም ጋር በተያያዘ ነው !!!