amhara map
ይህ እቅድ ከሰባ ዓመት በፊት እስራኤል የተባለች በታሪክ የማትታወቅ አገር ለመፍጠርና በአይሁድ እምነት ሽፋን የአውሮፓን ወራሪዎች ለማስፈር ሲታሰብ ከታጩት ቦታዎች መካከል በኢትዮዽያ ውስጥ ሐረርና ወልቃይት እንደነበሩ የወጣ ምስጢር አጋልጧል:: እቅዱን ለመፈፀም ከንጉሥ ሰለሞን ትውልድ ጋር የተሳሰረ ነው ለሚሉት በወቅቱ ለነበረው ለአፄ ሃይለሥላሴ መንግሥት ጥያቄው ቀርቦ ውድቅ እንደተደረገም ይታወቃል:: ከቀረቡት አማራጭ አገሮች አንዱ በእንግሊዞች በቅኝ ግዛትነት ተይዞ የነበረው የፍልስጥኤም አገር ተጋላጭ በመሆኑ እስከአሁን ድረስ ላልቆመው የሰው ልጆች ጭፍጨፋና መፈናቀልና ተጋልጦ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ደርሷል:: አገር ወዳድ መሪዎቻችን እምቢ ባይሉ ኖሮ በፍልስጥኤም የሚታዬው የፋሽስቶቹ የአይሁዶች ጭፍጨፋና ማፈናቀል በእኛ ላይ ይፈፀም ነበር::
መሪዎቻችን እምቢ በማለታቸው ግን የምንከፍለው ዋጋ ቀላል አልሆነም::በምዕራባውያን ጥርስ ውስጥ ገብተናል:: የመጀመሪያው ለካቶሊክ እምነት አለመንበርከካችን ሁለተኛው ለወራሪዎች ሳንገዛ በድል አድራጊነት ነፃነታችንን ማስከበራችን ሲሆን ሶስተኛው የአይሁዶችን ሰፈራ መቃወማችን ነው:: የአይሁድ ዘር የሆነው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበረው ሄንሪ ኪሲንጀር በፃፈው የምክር ሰነድ ላይ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ በጎሳ መበታተን ይገባል ብሏል:: ይህንኑ ሃሳብ ለመተግበር ሻእብያ ወያኔና ኦነግ የተባሉ ፀረ ኢትዮዽያ ተገንጣይ ሃይሎችን በመፍጠር ሰላምና አንድነት እንዲናጋ አድርገው ከ35 ዓመት በኽላ ሌለኛው የአይሁድ ዘር የሆነው ኽርማን ኮህን የተባለ ሽማግሌ የአሜሪካ ባለስልጣን ወደ ተግባር ለውጦት ጎሰኞቹ ስልጣን እንዲይዙ አደረገ ኤርትራንም አስገነጠለ:: ላለፋት 33 ዓመት ኢትዮዽያን የግጭት የጭፍጨፋ የመፈናቀልና የስደት ጎርፍ አጥለቀለቃት ለመበታተንም ጫፍ ላይ ደረሰች:: የአይሁድ ወሪዎችም ሰተት ብለው ገብተው የአይሁድ እምነት ያላቸውን ኢትዮዽያውያን ፈላሻ ወይም ቤተ እስራኤላውያን በሚል ታርጋ ከኖሩበትና ከተዋለዱበት ከጎንደር መሬት በአውሮፕላን በግልፅና በድብቅ አውጥተው በማያውቁት መሬትና ሕዝብ መሃል በተኗቸው:: እንደ አፈ ታሪኩ ቢሆን እንኳን ከሶስት ሽህ ዓመታት በፊት መጡ የተባሉት ጥቂት ሰዎች ከሶስተኛ ትውልድ በኽላ በመዋለድና በመቀላቀል በመጋባት አብሮ በመኖር ኢትዮዽያዊነትን ሙሉ ለሙሉ ተላብሰዋል:: የኖሩበትን እንጂ የመጡበትን አልሆኑም:: ይዘውት የዘለቀው ቢኖር የአይሁድ እምነታቸውና ብሉይ ኪዳን ብቻ ነው:: እምነት ደግሞ የዜግነትና የማንነት መግለጫ አይደለም:: የቻይና ካቶሊክ አማኝ ጣልያናዊ እንደማይሆነው ሁሉ የኢትዮዽያም ያይሁድ አማኝ የይሁዳ ዘርና ዜጋ አይሆንም::እስላሙም የሳውዲ ዜጋ ይሆናል ማለት አይደለም::
በተምታታ አፈ ታሪክ የተወናበደውና ብችግር ምክንያት የወጣው በተለይም ወጣቱ በወታደርነት ተሰልፎ የተለቃቀሙ አውሮፓውያኑን ወራሪዎችን ህይወትና ጥቅም ለመጠበቅ የህይወት ዋጋ እንዲከፍል ተገደደ:: ድህነትና ችግር የጎዳውንና ያስመረረውን ኢትዮዽያዊ ማንነቱን እንዲክድ አስገደዱት::የኢትዮዽያ አበሳ አሁንም አላለቀም የመበታተኑ አደጋ ፈጦ ይታያል:: ወያኔና ኦነጋውያኑ ያንን ለማድረግ ተግተው በመስራት ላይ ሲሆኑ ወራሪዎቹም በግልፅና በስውር ድጋፋቸውን እዬቸሯቸው ይገኛሉ::
አሁን ከሰሞኑ የወጣው ፍልስጤማውያንን ከአገራቸው ነቅሎ ኢትዮዽያ ውስጥ የማስፈሩ ዜና የዚያ እቅድ አካል እንደሆነ መገመት አያቅትም:: ኢትዮዽያ ስትበተን የአይሁድ ወራሪዎችም በጎንደር የይገባኛል ጥያቄ ያነሱና ቤተ እስራኤላውያንን ለማዳን በሚል ሽፋን ላለመግባት የሚያግዳቸው ሃይልና ህግ አይኖርም::በሥልጣንም ላይ ያለው የኦሮሙማ አገዛዝና ሻእብያ እንዲሁም ወያኔ ለዚያ የሚረዱና የተፈጠሩ የውስጥ አርበኞቻቸው ናቸው::በቤተ ክህነትም በኩል “የእስራኤል አምላክ” እዬተባለ የሚሰጠው ሰበካ የሕዝቡን ስነልቦና ለመስለብ የተዘጋጀ ማደንዘዣ እንደሆነ ልብ ማለት የስፈልጋል:: ፈጣሪ የሁሉም ፍጥረት አባት እንጂ የአንድ ጎሳና መንደር ብቻ አይደለም::መታረም አለበት::
ይህንን እውነታ ተቀብሎ መዘጋጀትና አደጋውን ለመቀልበስ አሁን ያለውን አገዛዝ ማሶገድና በአገር ወዳድ ፍፁም ኢትዮዽያዊ በሆነ ሕዝባዊ ስርዓት መተካት ነው::ይህ ትውልድ ይህንን ግዳጅ የመወጣት ሃላፊነት አለበት::ያ ካልሆነ የነገው ፍልስጤማዊ መሆኑ አይቀርም:: አገር አልባ ሆኖ ይቀራል::ማርእፊያና መጠለያ አይኖረውም::
አገርን ማዳን እራስን ማዳን ነው:: ተባብረን አገራችንን እናድን!
አገሬ አዲስ