የአፋህዱ መሪ እስክንድር ነጋ፣ እነ መከታው ማሞ፣ የአፋህድ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ፋኖዎች ጉያ ተቀምጦ፣ ለሁሉም አገር ወዳዶች አሳዛኝ የሆነውን የነሻለቃ ከፍያለው ህልፈት ተከትሎ አሳፋሪና ሰይጣናዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ እሳት ላይ ነዳጅ እያርከፈከፈ ነው፡፡
ሻለቃ ከፍያለው ደሴ የሞተው፣ እነ እስክንድር ነጋና አፋህዶች፣ በጎንደር በፈጠሩት ክፍፍል ምክንያት፣ ከፍያለው ደሴና አብረዉት የነበሩት፣ ከሌሎች የጎንደር ፋኖዎች ጋር አላስፈላጊ የተኩስ ልውውጥ ውስጥ በመግባታቸው ነው፡፡ “ጎንደር አንድ መሆን አለብት፣ ሁለት ወታደራዊ አደረጃጀቶች አንድ ቦታ ካሉ፣ ወደ ግጭት መሄዳቸው አይቀርም” በሚል፣ ብዙዎቻችን ስንመክርና ስናስጠነቅቅ የነበረው ባለመሰማቱ ነው ፣ ግጭት ተፈጥሮ እነ ሻለቃ ከፍያለው የሞቱት፡፡ ለነሻለቃ ከፍያለው መሞት አንደኛ ተጠያቄው አፋህድና እነ እስክንድር ነጋ ናቸው፡፡ ወንድማማቾች እንዲጣሉ፣ እንዲቃቃሩ በማድረጋቸው፡፡
ታዲያ እኮ አያፍርም፣ አፉን ሞልቶ፣ የነሻለቃ ከፍያለውን ሞት ለፖለቲካ ቁማር ጨዋታ በማዋል፣ “ከበስተጀርባ ወጉት” ብሎ፣ ሌላው የጎንደር ፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ ያሉትን ይከሳል፡፡ እርቅ፣ ይቀር መባበል፣ ስምምነት እንዲኖር ከማድረግ፣ የበለጠ የጎንደር ፋኖዎች በበቀል ስሜት እንዲገዳደሉ ለማድረግ !!!!
ይህ ሰው ፣ ” በቅንነት አብሮ ከመስራት፣ ወይንም አማራጭ ሃሳብ የያዘ ድርጅት ከመመስረት ይልቅ፣ ለአማራ ህዝብ አንድያ የሆነውን ድርጅታችንን ለማፍረስ እንቁ መሪዎቻችንን ለመምታት ቃታ ስበዋል፡፡ በሚያሳፍር መልኩ ደግሞ ወልቃይትና ራያን በሃይል እናስመልሳለን ከሚሉ ጽንፈኞች ጋር እንደሚሰሩ በአደባባይ መናገራቸውን፣ ከጽንፈኞች ተልእኮና የጦር ቁሳቁሶች ተቀብለው ጦር እስከማዝመት መድረሳቸውን፣ በአደጋ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት የወልቃይትና የራያ የአማራ ኃይሎች እንዲሁም መላው የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ እንዲልልን እንወዳለን” ይላል፡፡ ይህን የሚለው አራቱ የፋኖ አደረጃጀቶችን ነው፡፡
እዚህ ጋር ልብ በሉ፡፡
1ኛ ልክ አብይ አህመድ፣ ፋኖዎች የአንድነት ዘመቻ ሲያውጁ፣ ከጀነራል ምግበይ ነው መመሪያ እየተቀበሉ የሚሰሩት እንዳለው፣ እስክንድር ነጋም፣ “ተልዕኮና የጦር ቁሳቁሶች” ተቀብለው ሲል ነው ሽምጥጥ ያለ ውሸት የተናገረው፡፡ አራቱ አደረጃእጅቶች በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
2ኛ አራቱ አደረጃጀቶች፣ ለወልቃይት ለራያ አያስቡም፣ እኛ ነን የምናስበው እያለን ነው፡፡ እርሱ አሁን ፣ ከነ አብይ አህመድ ጋር ለመስማማት እያሰበ ነው፡፡ አብይ አህመድ እርሱን አስሮ ሲያሰቃየው በነበረ ወቅት ነው፣ ህወሃት ውጊያ የከፈተችው፡፡ በዚያን ወቅት፣ አሁን እርሱ ከወያኔ ጋር የሚሰሩ የሚላቸው፣ እነ ምሬ ወዳጆ፣ እነ ሻለቃ ሃብቴ፣ እነ ሻለቃ መሳፍንት፣ እነ ዘመነ ካሴ ከህወሃት ጋር ሲዋጉ ነበር፡፡ የህወሃትን ጦር ለማሸነፍ፣ እነ ባጫ ደቤሌ ሲሸሹ፣ የወገን ጥምር ጦርን እየመራ ህወሃትን ያሸነፈው፣ በህወሃት ከዘጠኝ አመት፣ በአብይ አህመድ ለሁለት ጊዜ ታስሮ የነበረው ጀነራል ተፈራ ማሞ ነው፡፡
እስቲ አስቡት እስክንድር ነጋ ከወያኔ ጋር ይሰራሉ የሚለው፣ እነ ሻለቃ መሳፍንትን፣ እነ ሻለቃ ሰፈር መለስን ነው፡፡ ለወልቃይት አያስቡም የሚላቸው፡፡ እነ ዋርካው ምሬ ወዳጆችን ነው ለራያ አያስቡም የሚላቸው፡፡
3ኛ እስክንድር ነጋ አፋህድን አንድያ የአማር ድርጅት አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡ 100% የጎጃምና የወሎ ህዝብ ያልደገፈው፣ 80% የጎንደርና የሸዋ ህዝህ ያልደገፈው ድርጅትን አንድያ የአማራ ድርጅት አድርጎ ማቅረቡ አስቂኝ ነው፡፡ አፋህድ በአሁኑ ጊዜ ማን ይመስላል ብትሉኝ የሚመስለው የበለጠ ሞላን አብንን ነው፡፡
4ኛ “ቃታ ሳቡብን” ይላል እስክንድር፡፡ እርሱ እነ መከታው ማሞን ሆይ ሆይ እያለ፣ በቀስተ ንእብ ብርጌድ ላይ በሬማ፣ የ7 ለሰባ ብርጌድ ላይ በይፋት ውጊያ እንዲከፈት አላደረግም እንዴ ? በቅርቡም መጋቢት 20 ቀን ለርሱ የሚታዘዙት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ፋኖዎች በነጎድጓድ ክፍለ ጦር ላይ ውጊያ ከፍተው ፣ ብዙ ፋኖዎች በሸዋ አላለቁም እንዴ ?
ወገኖች፣ በፋኖዎች መካከል ለተፈጠረው ችግር፣ አለመግባባት፣ ደም መፋሰስ ዋናው ተጠያቂ አፋህድ ነው፡፡ አፋህድ በአገዛዙ ተገዝቷል፡፡ በዳዎንት በተደረገው ውይይት አፋህዶች ከብልጽግና ጋር በነጮች በኩል ሳይስማሙ አልቀረም፡፡ ፋኖን አዳክሙ የሚል ሚሽን የተሰጣቸው ይመስለኛል፡፡
ይኸው በጎንደር እሳት ለኮሱ፡፡ እሳቱን ለማጥፋትና የበለጠ ደም መፋሰስ እንዳይኖር የጎንደር ልጆች ትልቅ ርብርብ እያደረጉ ባለበት፣ እነ እስክንድር እሳቱ የበለጠ እንዲቀጣጠል ነዳጅ እያርከፈከፉ ነው፡፡ በሸዋም እነ አማን እሸቱን፣ እነ መከታው ማሞን ወደ እሳት እየወሰዷቸው ነው፡፡ እንደውም የምሰማው ከብልጽግናዎች መመሪያ ተቀብለው ጀነራል ተፈራን ለማፈን እቅድ ይዘዋል ይባላል፡፡ ደግነቱ፣ መጋቢት 29 ያደረጉት ትንኮሳ፣ አቅማቸው እስከምን ደረጃ እንደሆነ እንዲገነዘቡ አድርጓቸዋል፡፡ ብዙ በነርሱ ስር ያሉ ፋኖዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም እያሏቸው ነው፡፡