ሻለቃ ናሁ ሰናይ ለማን ሞተ? | ከፋኖ አንድነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ!

/

ናሁ ሰናይ ብዙ የተደላደለ ህይወትና ሌሎች የሚመኙት የወደፊት እድል በእጁ ነበር።

ሰው እንደ እንስሳ ሲታረድ፣ እናቶች ሆዳቸው ተቀዶ ሲጣሉ፣ ድሆች በጅምላ በዶዘር ሲቀበሩ፣ መናኞች በገዳማት ሲታረዱ፣ ቤተ ክርስትያኖችና መስጊዶች ሲፈርሱ፣ ህጻናት ወላሂ “ሁለተኛ አማራ አልሆንም” ሲሉ፣ ህዝብ በወጠጤዎች ተንቆ ቤቱ በላዩ ላይ ሲፈርስ ከዳር ሆኜ ከማይ እኔ ህይወት ይሰዋ ብሎ ነው።

ናሁ ሰናይ አንዳርጌ የንጹሀን ደም እንደጎርፍ ሲፈስ እንደ አብዛኛው ዳር ይዞ የተደላደለ ኑሮ መኖር ይችል ነበር። ወይንም እንደ አብዛኛው አሜሪካ  ወይም አውሮፓ ተሰዶ፣ ሰዎች ሲታረዱ በፌስ ቡክ ሻማ እያበራ የተደላደለ ኑሮውን ማስቀጥል ይችል ነበር።

ሌሎች ይታገሉ እኔ በገንዘብ፣ በሃሳብ፣ በጽሁፍና በአመራር አግዛለሁ ማለትም ይችል ነበር።

ይሁንና ናሁ ሰናይ አንዳርጌ የልጆችን መታረድ፣ የእናቶችን ሆድ መቀደድ፣ የአዛውንቶችን መዋረድ የገዳማትን መፍረስ እያየ አርፎ የሚተኛ ልብ እና ህሊና አልነበረውም።

 

ናሁ ሰናይ አንዳርጌ ሻማ በፌስ ቡክ በማብራት፣ ጸሎትና ተማጽኖ የነ አብይ አህመድን፣ የነ ሽመልስ አብዲሳን፣ የነ ብርሀኑ ጁላን፣ የነ አዳነች አበቤን እና የነ ይልማ መርዳሳን የአማራና የክርስቲያን ደም ማፍሰስ ማስቆም እንደማይቻል ሲረዳ፤ የሞቀ ህይወቱን፣ የተደላደለ ኑሮውን እርግፍ አድርጎ ትቶ የንጹሀንን ደም ለመታደግ አምባገነኖችን ለማስቆም ጫካ ገባ። ቆሎ ቆርጥሞ፣ በወንዝ ውሀ በሶ በጥብጦ፣ ጭቃ ላይ ቅጠል ጎዝጉዞ፣ አንድ ጀለቢያ ተከናንቦ መተኛት መረጠ።

በመጨረሻም ህጻናት የሚያርዱትንና ህዝብን የናቁትን ለመበቀልና ከእኩይ ስራቸው ለማስቆም ተመልሶ አዲስ አበባ መጣ። በመጨረሻም፣ ለሚሞቱት ለሚፈናቀሉት እሱ ህይወቱንም ሰጠ።

ናሁ ሰናይ ከኛ ሲለይ ልባችን ቢሰበርም የትግሉን ችቦ በማቀጣጠሉና በጀግንነት ጠላቱን ጥሎ በመውደቁ፣ ለአዲስ አበባ ወጣት የትግሉን መንገድ አመላክቷል። በጠላቶቹ ልብ ፍርሀት ዘርቶ፣ ለበርካታ ወጣቶች ደግሞ አርአያ ሆኖ አልፏል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: አ.አ አዲስ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸውን የአገዛዙ ሰዎች የት እንዳደረሱ ማረጋገጫ እየጠየቅሁ ነው አለ (ልዩ ዘገባዎች በአንዳርጋቸው ዙሪያ)

———–

ታሪክ ደግሞ መዝኖ ፍርዱን ይሰጣል።  ለማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ የታቀደውን የዘር ማጥፋት ዝግጅት ማስቆም የሚያስችል ሀሳብ አለኝ የሚል ካለ መደመጥ አለበት።

https://fanolisan.org/346/

1 Comment

  1. ጊዜው እየመሸ ነው። ያው ልክ እንደበፊቱ አሁንም የሟች አስከሬን አልሰጥም የሚል መንግስት መኖሩ የሃገሪቱን ከንቱነት ያሳያል። የፓለቲካ አተካራውን ትተን ሰውን በሰውነቱ ብናይ ኑሮ የእነዚህ እናቶች ለቅሶና ዋይታ በተሰማ ነበር። ያ ግን አልሆነም። የአማራ መከራ የጀመረው ገና ድሮ ድሮ ነው። ይህ ክፋት ለሰው ቁልጭ ብሎ የታየው ወያኔና ሻቢያ የሃገር አለቆች ከሆኑ ወዲህ ነው። የዚህ ህዝብ መከራ ጀመረ እንጂ ገና የከፋ ነገር እንደሚከተል አሁን ሃገሪቱ ያለችበትን ያስረሽ ምችው የፓለቲካ ጥልፍልፍ ለሚረዳ ብቻ የሚገባው ይሆናል። ወያኔ የአማራ ክልል እያለ በሚጠራቸው አካባቢ መንግስትና ፋኖ ሲፋተጉ በአላማጣና ራያ በሌሎችም የትግራይ አዋሳኝ ቦታዎች ወያኔ ለ 4ኛ ጊዜ ጥቃት ከፍቶ ሰዎች በመሰደድ ላይ ይገኛሉ። እንደ ብረት የጠነከረ የሃገር ሰራዊት የሚባለውም ዓይኑ እያየ ወያኔ ስፍራዎችን ሲቆጣጠር ዝም ብሎ ያያል። የአካባቢው ሚሊሻም እንዳይመክት ይከላከላል። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ እኛ መከላከል አልቻልንም ተብሎ ፍርጠጣ ይሆናል። ይህ የፓለቲካ ሴራ ሁሉንም አመድ የሚያደርግ እንደሆነ ማንም ሊዘነጋው አይገባም። መዋጋት ብቻ ሳይሆን ጦርነትንም መስራት እንችላለን የሚለው ወያኔ ፊቱን ወደ አዲስ አበባ ዳግመኛ ማቅናቱ ከጀርባው አይዞህ የሚለው ስለ በዛ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ የኤርትራው መሪ ድንበሩ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰምሯል ሲለን ከየት ወደየት እንደሆነ በውል የሚያውቅ የለም። ለንገሩማ በባድሜስ ተፎክሮ ነበር አይደል። ዘመቻ ጸሃይ ግባት በማለት ወያኔና ሻቢያ ተፋልመው እልፍ ሰው ያለቀበት ያ ጊዜ ለማን አሁን ትዝ ይለዋል። ከቀኑ ጋር አብሮ መንጎድ ነው። ሰቆቃው ይረሳል፤ የሚራበውና የሚሰደደው ዋና የንግድ ማምረቻና የመለመኛ ከረጢት በመሆኑ የታጠቁ ሃይሎች ይፈልጉታል። እንግዲህ መጠራቅቅ ውስጥ የገባው ይህ የአማራ ህዝብ በኦሮሞና በወያኔ ሆን ተብሎ እንዲከስም የተሰራ ደባ እንደሆነ ሰው ሊገነዝብ ይገባል።
    የብልጽግናው መንግስት ለወያኔ ተጎንብሶ ቢሄድ እንኳን በላዪ ላይ ታንክ ይነድበታል እንጂ ለሰላም እጅና ልቡን አይሰጥም። ይህን መሰሪ ቡድን የሚያውቁት ከውስጡ የወጡ ወገኖች ብቻ ናቸው። አቶ ታዲዪስ ታንቱንና ሌሎች የሃገሪቱ ምጥቁ ልጆችን አስሮ ስብሃት ነጋን ወደ አሜሪካ ያሻገረው የአብይ መንግስት ምን ለማግኘት ፈልጎ እንደሆነ በውል የሚያውቅ የለም። አሁን በፋኖና በመከላከያ መካከል የሚደረገው ፍልሚያም የሚጎዳው የአማራን ህዝብ ነው። ወያኔ የተዳከመ፤ የተራበ፤ የተበተነውን ህዝብ እንደገና ዳግም ይጫወትበታል። ለዚህ ነው እኔ በተለያዪ መድረኮች ላይ የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገን ማየት አስፈላጊ ነው በማለት አክራሪ ፓለቲከኞችን የሞገትኩት። ፓለቲካ ጥላ ነው። ታይቶ የሚጠፋ። በነጮች በ1970 አካባቢ ኢራን በነዳጅ ዘይት ሃብት ተጥለቅልቃ ነበር። በዚህም የተነሳ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ አሜሪካ ሰራሽ የሆኑ ተዋጊ አውሮጵላኖችን ታዛለች። ልክ የመረካከቢያው ጊዜ ሲደርስ አያቶላ ሆሚኒ መንግስት ገልብጠው ስልጣን ይይዛሉ። አሜሪካ ለእስራኤል ያለምንም ክፍያ እነዚያን አውሮጵላኖች በስጦታ ትሰጣለች። እነዚሁ አውሮፕላኖች ናቸው የኢራቅን የዪራኒየም ሪአክተር ለመደብደብ የተጠቀሙበት። ፓለቲካ ወረተኛ ነው። የዛሬ ሽርከኛ የነገ ጠላት! የዛሬው ጠላት የነገ ሽርከኛ የሚሆኑት።
    የእነዚህን እናቶች ድምጽ ማቅረቡ መልካም ሆኖ እያለ ነገርየውን ለቅሶ ቤት ማስመሰሉና ሊሰማ የተፈለገውን ወሬ በትክክልና በጥራት አለማቅረቡ መልካም አይደለም። ለምን አለቀሱ አልልም። ግን ከተረጋጉ በህዋላ ቢቀርቡ ኑሮ የተሻለ በሆነ ነበር። ግራም ነፈሰ ቀኝ የሃበሻ እናቶችን የሚያስለቅሳቸው ሞት ብቻ አይደለም። የኑሮውም ጫና ጭምር እንጂ። ስርዓትና ደንብ በሌለበት ምድር ላይ እንዴት ተብሎ በሰላም ወሎ መግባት ይቻላል። ዛሬ እድሜ ለቱርክ ይህ ነው የማይባል የጠበንጃና የጥይት ገቢያ ደርቷል። እህል የሚሰፈርበት ኩባያ ዛሬ ጥይት የሚሰፈርበት ሆኗል። ግን ወዴት እያመራን ነው? ይህን የሚነግረን ይኖር ይሆን? በመገዳደልስ የምናመጣው ለውጥ ምንድን ነው? የእኔ ትልቁ ፍራቻ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ልክ እንደ ሶሪያና እንደ የመን ትሆናለች የሚል ነው። ያ ከሆነ ደግሞ እልፈት የለሽ የመገዳደል አዙሪት ውስጥ እንገባለን ማለት ነው። ለነገሩ አሁንስ እዚያው አይደለን? ፉከራው ቀረርቶው፤ በለውና በያቸውን ትተን የት ላይ ቆመናል፤ የት ነው የምንሄደው ብሎ ራስን መጠየቅ አስፈላጊ ነው። የፓለቲካ ዜና ሁልጊዜም ሰንካላ ነው። እውነቱን አይነግረንም። ገደሉ፤ ቀሙ፤ ተቆጣጠሩ፤ ተደመሰሱ ወዘተ የሚለው ሁሉ ምድር ካለው እውነት ጋር አይገናኝም። አይንና ጀሮ የሌለው የፓለቲካ ቱልቱላ በሁሉም ጎራ ይነፋል። ያን ይዞ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ጅልነት ነው። በውጊያ ላይ ቀዳሚዋ ሟች እውነት ራሷ ናትና! ዋ በህዋላ ምድሪቱ ልትወጣው ወደማትችልበት ማጥ በጋራ እንዶላትና ነገሩ ሁሉ ኦሮማይ እንዳይሆን ከአሁኑ እንስጋ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share