February 12, 2024
17 mins read

የፋኖ እስክንድር ነጋ የመስቀል አደባባይ ንግግር  

image

ፋኖ ዘመነ ካሴ እንዳለው አማራን ቆረጣጠሞ ለመብላት ቆርጦ የተነሳው የኦሮሙማው አውሬ ጭራቅ አሕመድ ወገቡን ተመቶ ተሽመድምዷል።  የሚቀረው በተገኘው ዱላ አናቱን በጥርቆ ከነዱላው አሽቀንጥሮ መጣል ነው፣ እባብ ግደል ከነብትሩ ገደል እንዲሉ።  እባቡ ከነብትሩ ገደል በተጣለበት የተቀደሰ ዕለት ደግሞ፣  ወያኔና ኦሮሙማ ተጣምረው የገደሏት የኢትዮጵያ ዳግሚያ ተንሳዔ ሀ ብሎ መጀመሩን መስቀል አደባባይ ላይ በንግግር ማብሰር ነው።   ንግግሩን ማድረግ ያለበት ደግሞ ፋኖ እስክንድር ነጋ (የጦቢያ አምላክ የዚያ ሰው ይበለውና) ወይም ደግሞ ጭራቁን ለማሰወገድ ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሌላ የፋኖ አመራር አባል ነው።  በኔ በመስፍን አረጋ እይታ ደግሞ ንግግሩ የሚከተሉትን ሐሳቦች ያካተተ መሆን ይኖርበታል።

ታላቁ የጦቢያ ሕዝብ ሆይ፣ በዚች በዛሬዋ በተቀደሰች ዕለት እንጦረንጦስ የተሸኘው ታላቁ የኦሮሙማ አውሬ ጭራቅ አሕመድ፣ ባማራ ሕዝብ ላይ በታሪኩ አይቶት የማያውቀው፣ ባሰቃቂነቱ ወደር የሌለው፣ ጣልያንም ሆነ ሌላ ማናቸውም የውጭ ጠላት ከፈጸመበት ግፍ ሺ እጥፍ የከፋ፣ ለመናገር የሚሰቀጥጥ፣ ማስረጃ ባይኖር ኖሮ ተፈጽሟል ተብሎ ሊታመን የማይችል ግፍ ፈጽሞበታል።

GGITktWWgAALW6S

ጭራቅ አሕመድ ያማሮችን ማሕፀን ዘርከቷል ወይም ደግሞ እንዲዘረከት አድርጓል፣ ሽሉን ደግሞ በልቷል ወይም ደግሞ አስበልቷል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ያማራ ሕፃናትን ጎጆ ውስጥ ዘግቶ በሰደድ እሳት አንጨርጭሯል ወይም ደግሞ እንዲንጨረጭሩ አድርጓል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማሮችን የፊጥኝ አስሮ ባደባባይ ረሽኗል ወይም ደግሞ አስረሽኗል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማሮችን ባደባባይ ዘቅዝቆ ሰቅሏል ወይም ደግሞ አሰቅሏል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማሮችን አጋድሞ አርዷል ወይም ደግሞ አሳርዷል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማሮቸን ቆዳ በቁማችው ገፏል ወይም ደግሞ አስገፍፏል፡፡   ጭራቅ አሕመድ ያማራ ወጣቶችን የፊጥኝ አስሮ በማጋደም በዲንጋ እየፈጠፈጠ ገድሏል ወይም ደግሞ አስገድሏል።  ጭራቅ አሕመድ ያማሮቸን ሬሳ በሞተር ሳይክል ገትቷል ወይም ደግሞ አስገትቷል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማሮችን እንደቅጠል አርግፎ ሬሳቸውን በግሬደር እየገፋ ቀብሯል ወይም ደግሞ አስቀብሯል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ካማራ አስከሬን በተቆረጡ እጆችና እግሮች ሆያ ሆየ ጨፍሯል ወይም ደግሞ አስጨፍሯል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ላማራ ተቆርቋሪ አመራሮችን ያለ ርህራሄ ርፍርፏል ወይም ደግሞ አስረፍርፏል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ያማራ ከተሞችንና ነዋሪወቻቸውን በሰደድ እሳት አቃጥሎ አውድሟል ወይም ደግሞ አስወድሟል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ያማራ ባለሃብቶችን ሐብትና ንብረት ዘርፏል ወይም ደግሞ አስዘርፏል፣ እንዲሰደዱም አድርጓል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ባንድም በሌላም መንገድ በሚሊዮኖች ቀንሷል ወይም ደግሞ አስቀንሷል፡፡

ዛሬ ግን ለጦቢያ አምላክ ትልቅ ምስጋና ይግባውና የኦሮሙማው ጭራቅ የጁን አግኝቷል።  የጁን እንዲያገኝ ደግሞ ያማራ ሕዝብ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል፣ ምትክ የማይገኝላቸው አያሌ ጀግኖቹንም አጥቷል።  ጀግኖቹን ያጣቸው ግን በአካል እንጅ በመንፈስ አይደለም፣ ዘላለም ሲዘክራቸው ይኖራልና።  ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ የሚሰኘው አጉል ብሂል ከዚች ከዛሬዋ ከተቀደሰች ዕለት ጀምሮ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ውድቅ ተደርጓል።  ጦቢያ የዋሉላተን የምትረሳ ውለታቢስ መሆኗ፣ የጦቢያ ጀግኖች ደግም ወለታቸው የማይቆጠርላቸው ዐመድ አፋሽ መሆናቸው በዛሬዋ ዕለት አክተሟል።

ጦቢያን ከወያኔና ከኦሮሙማ መንጋጋ ፈልቅቀው ያውጡት የፋኖ ጀግኖች፣ እንደ ቀደምት የጦቢያ ጀግኖች እንዳይረሱና ዘላለም እንዲታወሱ ጦቢያ ያቅሟን ሁሉ ታደረጋለች።  የጦቢያ ጀግኖች በያመቱ የሚዘከሩበት የጀግኖች ዕለት ይታወጃል።  ተራሮች፣ ሸለቆወች፣ ከተሞች፣ አድባባዮች፣ አውራ ጎዳናወች፣ ታላላቅ ሕንፃወች ወዘተ. በጀኖቻችን ይሰየማሉ፣ ሐውልቶች ይቆማሉ፣ መታሰቢያወች ይቋቋማሉ።  ጀግኖቻችንን ባግባቡ መተቸት ቢቻልም፣ የኦሮሙማ ጋጠወጦች ያደርጉ እንደነበሩት መዘለፍ ግን በሕግ እንዲያስቀጣ ይደረጋለ።  ወያኔ በትግላችን ሐውልት ላይ ያደርግና ያስደርግ እንደነበረው የጀግኖች መታሰቢያወችን ሥራየ ብሎ ማቆሸሽ (መሽናት፣ መጸዳዳት ወዘተ.) ለከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትና ለረዥም እስር እንዲዳርግ ይደረጋል።  የጦቢያ ሕጻናት የፋኖን ገድሎች በሥርዓት እያጠኑ እንዲያድጉ ሥርዓተ ትምህርቱ እንዳዲስ ይቀረጻል፣  ጀግኖቹን የማያከብር ትውልድ ጀግኖች ማፍራት አይችልምና።

በድጋሚ ለጦቢያ አምላክ ትልቅ ምስጋና ይግባውና ጭራቅ አሕመድ በዛሬዋ ዕለት ተወግዷል። ካሁን በኋላ ደግሞ እሱን የመሰለ አውሬ በጦቢያ ምድር ላይ ዳግመኛ መብቀል የለበትም።  እንዳይበቅል ደግሞ ክልሎችን ማፈራረስን፣ በዘር መደራጀት መከልከልን፣ ወያኔንና ኦሮሙማን ይረዱ ከነበሩት፣ ያማራ ሕዝብ መሠርታዊ ጠላቶች ከሆኑት ምዕራባውያን መንግስታት ጋር ያለንን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደገና መፈተሽንና ከቀንድኞቹም ጋር ሙሉ በሙሉ መቆራረጥን የመሳሰሉት አስፈላጊ ርምጃወች ሁሉ በሂደት ይወሰዳሉ።  የመጀመርያውና አጣዳፊው እርምጃ ግን የጭራቅ አሕመድ ግብራበሮች በሙሉ በወንጀላቸው መጠን አይቀጡ ቅጣት እየተቀጡ፣ ለመጨው ትውልድ ዘላለማዊ መቀጣጫ እንዲሆኑ ማድረግ ነው።

ለማ መገርሳ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ጃዋር ሙሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ መራራ ጉዲና፣ በረከት ስምዖን፣ ፃድቃን ገብረተንሳይ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ደመቀ መኮንን፣ ተመስገን ጡሩንህ፣ ዳንኤል ክብረት ወዘተ. ከሚገኙበት ተለቅመው፣ ለፍርድ ቀርበው፣ እንደወንጀላቸው የጃቸውን አግኝተው፣ የሚረሸኑት ተረሽነው ባደባባይ የሚሰቀሉት ይሰቀላሉ።  ዳቢሎሳዊ ሥራቸው መቸም እንዳይረሳ፣ ውጉዝ ከመ አርዮስ እየተባሉ፣ በስማቸው እየተጠሩ ዲንጋ በመጣል የሚወገዙበት መካነ ውግዘት ባዲሳባና በሌሎች ከተሞች ይተከላል።  በየትኛውም ዓለም ያስቀመጡት ከጦቢያ ሕዝብ የዘረፉት ሐብትና ንብረት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተወርሶ ለባለቤቱ ለጦቢያ ሕዝብ እንዲመለስ ይደረጋል።  ይህ ሁሉ የሚደረገው ግን ለበቀል ሳይሆን፣ በወንጀል ማትረፍ እንዳማይቻል፣ ወንጀልኛ ሁሉ ፈጥኖም ሆነ ዘግይቶ የጁን እንደሚያገኝ ለተተኪው ትውልድ ለማስተማር ሲባል ብቻ ነው።

ፋኖ ወያኔና ኦሮሙማ የፈጽሙትን ስሕተት አይፈጽምም።  ወያኔ ያማራን ሕዝብ እርዳታ ለማግኘት ሲል ብቻ ራሱን ኢሕአደግ ብሎ ያማራ ሕዝብ ባደረገለት ከፍተኛ ድጋፍ (እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ በከፈሉት ከፍተኛ መስዋዕትነት) ደርግን ከጣለ በኋላ፣ ያሸነፍኩት ደርግን ሳይሆን አማራን ነው አለ። ያማራን እና የኦርቶዶክስን አከርካሪ የሰበርኩ፣ ተራሮችን ያንቀጠቀጥኩ ትውልድ ነኝ እያለ አማራንና ኦርቶዶክስን ለሃያ ሰባት ዓመታት የግፍ ጽዋ ጋተ።  ኦሮሙማ ደግሞ ባማራ ሕዝብ ለመደገፍ ሲል ብቻ ኢትዮጵያ ሱሴ ብሎ፣ ባማራ ሕዝብ ታዝሎ አራት ኪሎ ከገባ በኋላ፣ ነፍጠኛን በሰበረን ቦታ ሰበርነው በማለት እየደነፋ አማራን ክፉኛ ገፋ።

ፋኖ ግን የሰበረው ኦሮሙማን እንጅ ኦሮሞን አይደለም።  ፋኖ ኦሮሞን አልሰበረም፣ ሊሰብርም አይፈልግም፣ ቢፈልግም አይችልም።  በተመሳሳይ መንገድ ፋኖ የሰበረው ወያኔን እንጅ ትግሬን አይደለም።  ፋኖ ትግሬን አልሰበረም፣ ሊሰብርም አይፈልግም፣ ቢፈልግም አይችልም

የኦሮሙማ አረመኒያዊ ወንጀሎች፣ የአማራን ሕዝብ እጅግ የሚያንገበግቡና ለበቀል የሚያነሳሱ ቁስሎች ቢሆንም፣ ቁስልነታቸው ግን የመንፈስ ሳይሆን የሥጋ ብቻ ነው፡፡   በሌላ በኩል ግን ኦሮሙማ አረመኔያዊ ወንጀሎቹን ባማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በኦሮሞ ሕዝብ ስም ነው፡፡  ኦሮሙማ በስሙ በፈጸመው አርመኔያዊ ወንጀል ሳቢያ ደግሞ ታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ባረመኔነት ታይቷል፡፡  በዚህ አንጻር ሲታይ ኦሮሙማ የበላው ያማራን ሥጋውን ቢሆንም፣ የኦሮሞን የበላው ግን ኦሮሞነቱን (ማለትም ነፍሱን) ነው፡፡  መጽሐፉ የሚለው ደግሞ ሥጋን የሚገሉትን ሳይሆን ነፍስን የሚገሉትን ፈሩ ነው (ማቴወስ 10፡28)።  ስለዚህም ኦሮሙማ ጠላትነቱ ካማራ ሕዝብ በላይ ለራሱ ለኦሮሞ ሕዝብ ነው።  በመሆኑም ኦሮሙማን ካማራ ሕዝብ በላይ አጥብቆ ሊዋጋው የሚገባው ራሱ የኦሮሞ ሕዝብ ነው።

በተመሳሳይ መንገድ ወያኔ የበላው ያማራን ሥጋ ቢሆንም፣ የትግሬን የበላው ግን ትግሬነቱን (ነፍሱን) ነው።  በወያኔ ዳቢሎሳዊ ወንጀሎች ሳቢያ የትግራይ ሕዝብ አለስሙ ስም ተሰጥቶት ጨካኝ፣ አረመኔ፣ የቀን ጅብ፣ ስግብግብ፣ ቀማኛ፣ ዘራፊ ተደርጎ ተስሏል።  ስለዚህም ወያኔ ጠላትነቱ ካማራ ሕዝብ በላይ ለራሱ ለትግሬ ሕዝብ ነው፣ ካማራ ሕዝብ ይበልጥ አጥብቆ ሊዋጋው የሚገባውም ራሱ የትግሬ ሕዝብ ነው።

የፋኖ ዓላማ ግን ባማራ ሕዝብ ስም በሌሎች ጦቢያውያን ላይ ወንጀል ለመፈጸም አይደለም።  ባማራ ሕዝብ ስም በሌሎች ጦቢያውያን ላይ ወንጀል ሊፈፅም ቢሞክር ደግሞ ከማንም በላይ አጥብቆ የሚፋለመው ራሱ ያማራ ሕዝብ ነው።  አብዛኛው የትግሬ ሕዝብ ወያኔ በስሙ ወንጀል ሲፈፅም በዝምታ እንደተመለከተ፣ አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብም ኦሮሙማ በስሙ ወንጀል ሲፈፅም ደምፁን አጥፍቶ እንደተቀመጠ፣ ያማራ ሕዝብ በስሙ ወንጅል እንዲፈፀም በጭራሽ አይፈቅድም። ለምስክርነት ደግሞ ያማራ ሳይሆኑ ያማራ ናችው ይባሉ የነበሩትን የንጉሱንና የደርግን አገዛዞች አጥብቆ የታገላቸው ያማራ ሕዝብ መሆኑን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።

የፋኖ ዓላማ ወያኔና ኦሮሙማ ያፈራርሷትን፣ የሁሉም ጦቢያውያን የጋራ ቤት የሆነቸውን ጦቢያን ለሁሉም ጦቢያውያን አመቺ በምትሆንበት መንገድ እንደገና ለመሥራት የተመቻቸ መድረክ መፍጠር ነው።  መድረኩ ደግሞ እነሆ ጭራቅ አሕመድ በተወገደባት በዛሬዋ በተቀደሰች ዕለት ተፈጥሯል። እያንዳንዱ ጦቢያዊ በቅን ልቦና ተነሳስቶ፣ እኛን ከኔ አስበልጦ፣ አገርን ከጎጥ አስቀድሞ፣ በተመቻቸለት መድረክ ላይ በየሙያው ተሳትፎ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት፣ ጦቢያን በፍትሕና በርትዕ በፀና፣ ማናቸውም ማዕበል በማያናውፀው ፅኑ መሠረት ላይ በመገንባት የጦቢያዊነት አሻራውን ያስቀምጥ ዘንድ በክብር ተጋብዟል።  የጦቢያ አምላክ ጦቢያን ለዘላለም ይባርክ።

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop