November 9, 2023
7 mins read

ኢጆሌ ጉዲና ከኦነግ ጋር ይነጋገራል፣ ኢጆሌ መርዳሳ በድሮን አማራውን ይጨርሳል

56664ግርማ ካሳ

የጀርመን ድምጽ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ዋና አዛዥ ኩምሳ ዲሪባ (ጃል መሮ) እና ምክትሉ ገመቹ እንዲሁም የታጣቂ ቡድኑ ደቡብ ኦሮሚያ (ጉጂ አካባቢ) አዛዥ ገመቹ ረጋሳ፣ ከኦሮሞ ብልጽግናዎች ጋር ፣ ፊት ለፊት ለመደራደር፣ ታንዛኒያ መሄዳቸውን ዘግቧል፡፡ ገመቹ ረጋሳ ከጉጂ፣ እነ ጃል መሮ ከምእራብ ወለጋ ቤጊ አካካባቢ ነው፣ በብልጽግና አገዛዝ እውቅና ከአገር እንዲወጡ፣ ወደ ኬኒያ እንዲሄዱ የተደረጉት፡፡

በኦሮሞ ብልጽግና በኩል ፣ የብልጽግና ጦር የደህንነት ጉዳይ ሃላፊ፣ በአብይ አህመድ በሁለት አመት ውስጥ ከባለ ሁለት ኮከብ ሜጀር ጀነራልነት፣ ወደ ባለ አራት ኮኮብ ሙሉ ጀነራልነት ሹመት ያገኘው፣ በመከላከያ ውስጥ ከብርሃኑ ጁላም በላይ ለአብይ አህመድ ታማኝ የሆነው ጌታቸው ጉዲና ነው ተደራዳሪ የሆነው፤ የጀርመን ድምጽ እንደዘገበው፡፡

በነ ጃል መሮና በነ አብይ መካከል የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶች የሉም፡፡ በመካከላቸው ያለው ችግር የስልጣን ብቻ ነው፡፡

እነ ጃል መሮ አሁን ባለው ሁኔታ በጦርነት መቀጠል እንደማይችሉ ገብቷቸዋል፡፡ ወለጋ ከጦርነቱ የተነሳ በህዝብ ላይ ከፍተኛ እልቂት ነው የተፈጠረው፡፡ ህዝቡ በጦርነቱ ተማሯል፡፡ በብዙ ቦታዎችም ከፍተኛ ወታደራዊ ሽንፈቶችን ተከናንበዋል፡፡ ታጣቂዎቸውም ተሰላችተዋል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት በቄሌም ወለጋ አንፌሎ ወረዳ በነበረው ትልቅ የኦነግ ካምፕ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ትልቅ ጉዳት ነው ያደረሰው፡፡

እነ አብይ አህመድ ደግሞ፣ በአማራ ክልል ወታደሮቻቸው እያለቁባቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም ከነ ጃል መሮ ጋር መስማማት ከተቻለ ፣ አንደኛ በወለጋ የተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ከወለጋ ወደ አማራ ክልል ማንቀሳቀስ ይችላሉ፡፡ ሁለተኛ የኦነግ ታጣቂዎችንም እንዳለ በመከላከያ ውስጥ በመጠቅለል የጦሩን ቁጥር የማሳደግ እቅድ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ በዚህ መልኩ፣ አዳዲስ ወደ አማራ ክልል የሚልኳቸው ታጣቂዎችን አገኙ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ መስማማቱ ለሁለቱም ስለሚጠቅም ፣ ከአንድ ስምምነት ይደርሳሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ አብይ አህመድ ይመስለኛል በኦሮሞ ክልል የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ይስማማል፡፡ አንዱና ትልቁ የኦነጎች ጥያቄ፡፡ ሺመልስ አብዲሳ ስልጣን እንዲያጋራ ይደረጋል፡፡ ከኦነግና ከኦሮሞ ብልጽግና የተወጣጣ የክልሉ መንግስት ካቢኔ ይቋቋማል፡፡ እነ ጃል መሮ ስልጣን ይሰጣቸዋል፡፡ እነ ቀጀላ መርዳሳ እንደተሰጣቸው፡፡

በፌዴራል አገዛዝ ግን የሚለወጥ ነገር አይኖርም፡፡ አብይ አህመድ የሚያጋራው ስልጣን አይኖርም፡፡ እነ ጃል መሮም አብይ አህመድን እንደነ ጌታቸው ረዳ፣ የመታዘዝ፣ “አቤት ጌታዬ” የማለት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ በአጭሩ አነጋገር በኦሮሞ ብልጽግና ይዋጣሉ፡፡ ልክ እነ ቀጀላ መርዳሳ እንደተዋጡት፡፡

ሌላው ከስምምነት ይደርሳሉ ብዬ የምልበት ምክንያት ፣ የነ ጃል መሮን ከአገር መውጣት አስቤ ነው፡፡ ከወዲሁ የተቋጨና መስመር የያዘ ነገር ባይኖር ኖሮ፣ ወደ ድርድር አይሄዱም ነበር፡፡ ለምን ድርድሩ ከከሸፈ እንደገና ወደ ወለጋና ጉጂ የመሄድ እድሉ በጣም ጠባብ በመሆኑ፡፡

በግሌ ቢያንስ የወለጋ ህዝብ እረፍት ሊያገኝ የሚችልበት ሁኔታ ሊመጣ ስለሚችል፣ ድርድሩን በአዎንታዊነት ነው የምቀበለው፡፡ እንዲሳካም ጸሎቴ ነው፡፡ ላለፊት አምስት አመታት ወለጋ ስላለው ጦርነትና በዚያ በህዝቡ ላይ ሲደርስ የነበረውን ሁኔታ በተመለከተ፣ ብዙ ጊዜ ጽፍያለሁ፣ ጦምሪያለሁ፡፡

ይህ ከነ ጃል መሮ ጋር የታየው የመደራደር ፍላጎት፣ ከአማራ ኃይሎችም ጋር መኖር ይገባዋል የሚል አመለካከት ብዙዎቻችን ሊኖረን ይችላል፡፡ ግን አንሳሳት፡፡ እነ አብይ አህመድ ከነ ጃል መሮ ጋር ለመደራደር የፈለጉት፣ በመርህ ደረጃ በድርድር ስለሚያምኑ አይደለም፡፡ ሞቲቫቸው በርግጥም ጦርነት ይቁም ከሚል አይደለም፡፡ በጭራሽ፡፡ ከፋኖዎች ጋር ለምናደርገው ጦርነት ከነ ጃል መሮ ጋር መስማማታችን ይጠቅመናል ከሚል ሰይጣናዊና እኩል አመለካከት በመነሳት ነው፡፡ ፋኖ ባይነሳና በአማራ ክልል ባይደቁሳቸው ኖሮ፣ እመኑኝ ሸኔን እንደመሣለን ብለው አሁን ጦርነቱን ይቀጥሉት ነበር፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop