December 6, 2022
3 mins read

የጀርባ ሕመምዎን ለማስታገስ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

318484912 217762267275133 8351252871562097050 n
318484912 217762267275133 8351252871562097050 n
✔ አቋምዎን ያስተካክሉ
የጀርባ ሕመም የሚያሰቃይዎት ከሆነ በመጀመሪያ አቀማመጥዎን እና ከባድ ዕቃን የሚይዙበትን ሁኔታ ያስተካክሉ፡፡ ለብዙ ሰዓት ተቀምጠው የሚሠሩ ከሆነ ለወገብዎ መደገፊያ ማዘጋጀት ይኖርብዎታል፡፡ ከመቀመጫዎ ሲነሱ ቀጥ ብለው መነሳት እና ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በሚያነሱበት ጊዜ ከጉልበትዎ በርከክ ብለው ጀርባዎን ቀጥ በማድረግ መሆን አለበት፡፡
✔ የኤሎክትሮኒክስ ዕቃዎችን የሚጠቀሙበትን ሰዓት ይቀንሱ
በሥራም ሆነ በማኅበራዊ ጉዳይ ምክንያት ለረጅም ሰዓታት ከኮምፒዩተሮችና ሌሎች የኤሎክትሮኒክስ ዕቃዎች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ መወሰን ተገቢ ነው፡፡ አጎንብሰን እና ለረጅም ሰዓት ተቀምጠን የምንጠቀምባቸው ከሆነ የጀርባ ሕመም እና የራስ ምታትን ያስከትላሉ፡፡
✔ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያድርጉ
የጀርባ ሕመምን ቀላል በሚባል የአካል ማፍታታት እና አንገትን እና ወገብን በማንቀሳቀስ መከላከል ይችላሉ፡፡
✔ ጭንቀትን ይቀንሱ
ጭንቀት ለብዙ ዓይነት ሕመሞች እንደ ምክንያት የሚጠቀስ ሲሆን ከጀርባ ሕመም ጋርም ተያያዥነት እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም ለራስዎ ጊዜ በመስጠት እና በመዝናናት ጭንቀትዎን ይቀንሱ፡፡
✔ የሰውነት ክብደትዎን ይቀንሱ
የሰውነትዎ ክብደት መጨመር በተለይም በወገብ አካባቢ ስብ ከተከማቸ የጀርባ ጡንቻዎችን ስለሚጎዳ የጀርባ ሕመም ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ አመጋገብዎን ማስተካከል እና ክብደትዎን መቀነስ የጀርባ ሕመምዎን ይቀንሳል፡፡
✔ በቂ ዕረፍት ያድርጉ
በቂ እረፍት ማድረግ ለሙሉ ጤናማነት ጠቃሚ ነው፡፡ እንቅልፍ በሚተኙ ጊዜ በጎንዎ በኩል መተኛት የጀርባ ሕመምዎን ይቀንሳል፡፡
✔ በቂ የፀሐይ ብርሃን ያግኙ
የፀሐይ ብርሃን ቢያንስ በቀን ለ10 ደቂቃ መውሰድ ለአጥንትዎ ጠንካራነት እጅግ ጠቃሚ እና ለጀርባ ሕመምዎ አንደኛው መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡
✔ ሲጋራ ማጤስን ያቁሙ
ሲጋራ ማጤስ ወደ ታችኛው የጀርባችን አጥንቶች የሚሄደውን የደም ዝውውር ስለሚቀንስ ለጀርባ ሕመም ይዳርጋል፡፡ ስለዚህም ሲጋራ ማጤስዎን እንዲያቆሙ ይመከራል፡፡
እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!
ጤና ይስጥልኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

178048
Previous Story

ሀዘናቸውን የተቀሙ የወለጋ ግፉአን | ድንኳን ሰባሪዎቹ ፖለቲከኞች

318133516 10161280219274587 8708789585471186889 n
Next Story

ድህነቷን እናፍቀዋለሁ፤ ሊያሳስበኝ ግን ልቦናዬ ጊዜ የለውም፡፡ ህይወት ረከሰ፤ ሞት ነገሰ! (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop