ጠ/ሚ/ሩ በፓርላማ “በቀጣይ የሚያሰጋን አዲስ አበባ ነው” በማለት የወለጋን አጄንዳ ለማስቀየር ሞከሩ!! ዜና July 7, 2022 Facebook X Pinterest Linkedin Whatsapp Reddit Email በከፊል የመንግሥት ባለሥልጣናት የሚደገፈው ኦነግ-ሸኔ በወለጋ በአማራዎች ላይ እየፈፀመ ያለውን የዘር ማፅዳት በተመለከተ ማብራሪያ ለመስጠት በፓርላማ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌላቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። በአዲስ አበባ ስድስት የሽብር ጥቃቶች ተሞክረዋል ሲሉም ተደምጠዋል። ጠ/ሚ/ሩ በከተማዋ የሚኖሩ አንዳንድ የእስልምና እምነት ተከታዮችን በሽብር ድርጊቱ ሞካሪነት ወንጅለዋል። “ሙስሊም ነኝ ብሎ ጀለብያ ለብሶ ቦምብ ይወረውራል። በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ 6 የሽብር ሙከራ አክሽፈናል። ባንዳው ሸኔ ብቻ አይደለም። አዲስ አበባም ባንዳ አለ፤ በየመጅሊሱ የሚሸቅል ማለት ነው” በማለትም ገልፀዋል። “በቀጣይ የሚያሰጋን አዲስ አበባ ነው። ለገጣፎ ላይ ብቻ 55 አሸባሪ ትናንት ይዘናል። አዲስ አበባ በየቀኑ ቦምብ እየያዝን ነው” ሲሉም በከተማዋ ኗሪዎች ላይ ጭንቀትን የሚያባብስ አባባል ጨምረዋል። በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ፍጅት የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ስለመሆን ወይም አለመሆኑ፤ ብሎም መንግሥታቸው ጅምላ ጭፍጨፋውን መቼና እና እንዴት እንደሚያስቆመው ለቀረበላቸው ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ማፅዳት “የንፁሃን ሞት” በማለት አድበስብሰውታል። “እናንተ በየሳምንቱ መርዶ ትሰማላችሁ። እኛ ግን በየቀኑ፤ በየሰዓቱ እንሰማለን” በማለትም ለመገናኛ ብዙሃን ያልደረሱ ሌሎች ጅምላ ጭፍጨፋዎች እንዳሉ ፍንጭ ሰጥተዋል። ሽብር በኢትዮጵያ ብቻ ያልተከሰተ፤ ዓለም አቀፍ ስጋት መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለወለጋው የአማራ ጭፍጨፋ የዘገባ ሽፋን መስጠቱን በአሉታዊ ገፅታ በማቅረብ፣ በተለይ አሜሪካን ከፍተኛ የሽብር ሰለባ አስመስለው አብራርተዋል። በኒውዮርክ፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በፊላደልፊያ፣ በቺካጎ ወ.ዘ.ተ. የሽብር ጥቃቶች በተደጋጋሚ እንደሚፈፀሙ ጠቅሰዋል። በመሆኑም በኢትዮጵያም ቢፈፀም አይደንቅም የሚል አንድምታ ያለው መደምደሚያ ሰጥተዋል። ቀጣይ ዘገባዎች ይኖሩናል!! #ኢትዮጵያ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ Facebook X Pinterest Linkedin Whatsapp Reddit Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Latest from Blog ህወሃትን ከደሙ ንጹህ ለማድረግ የታቀደ ስብሰባ ወይስ በአብሮ የመኖር ስም አንድን አገዛዝ ብቻ ተጠያቂ ለማድረግ የታቀደ የውይይት መድረክ!! ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) (ሰኔ 23፣ 2017) June 30, 2025 እ.አ.አ በሰኔ 7፣ 2025 ዓ.ም “የርዕዮት ሚዲያ” ባለቤት የሆነው ቴዎድሮስ ፀጋዬና፣ “የአብሮነት ኢትዮጵያ” አሰባሳቢ መሪ ነኝ የሚለው ልደቱ አያሌው “ታላቅ የተቃውሞ ትዕይንተ-ህዝብ” በሚል፣ ይሁንና ዋናው መሰረተ-ሃሳብ” ጦርነት ይቁም፣ ግፋዊ አገዛዝ ያቁም፣ ዘላቂ ሰላም ይስፈን” በሚሉ ልዩ | ‹ ከቤተመንግስት አልወጣም› ዓብይ | የሽመልስ እና ዝናሽ ግዙፉ ካምፓኒ ልዩ | ‹ ከቤተመንግስት አልወጣም› ዓብይ | የሽመልስ እና ዝናሽ ግዙፉ ካምፓኒ እ.ኤ.አ. በ2024 ብሔራዊ ባንክ 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ በዚሁ ዓመት በነበረ የብር መዳከም 38 ቢሊዮን ብር መክሰሩ ተገልጿል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2024 በአጠቃላይ የባንክ ሥራው 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ፡፡ ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር ኦዲት 58 የአብይ አህመድ ነጭ ውሸቶች! – ነዓምን ዘለቀ ቆጥራቹህ ስለላካቹህልን እናመሰግናለን! የተረሳ ካለ ጨምሩበት update አደረጋለሁ! 1. ሳናጣራ አናስርም 2.ጊዜ ስለሌለኝ ከኖቬል ሽልማት ፕሮግራም ላይ አልገኝም 3. አንዲት ፈረንሳዊ ላግባህ ብላኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ 4. በተከልነው ችግኝ የሀረማያ ሀይቅ ወደነበረበት ኢዜማ ወ ብልጽግና – ቆሎ የመጎራረስ ውል አልባ ጋብቻ ኢዜማ ወ ብልጽግና – ቆሎ የመጎራረስ ውል አልባ ጋብቻ
ህወሃትን ከደሙ ንጹህ ለማድረግ የታቀደ ስብሰባ ወይስ በአብሮ የመኖር ስም አንድን አገዛዝ ብቻ ተጠያቂ ለማድረግ የታቀደ የውይይት መድረክ!! ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) (ሰኔ 23፣ 2017) June 30, 2025 እ.አ.አ በሰኔ 7፣ 2025 ዓ.ም “የርዕዮት ሚዲያ” ባለቤት የሆነው ቴዎድሮስ ፀጋዬና፣ “የአብሮነት ኢትዮጵያ” አሰባሳቢ መሪ ነኝ የሚለው ልደቱ አያሌው “ታላቅ የተቃውሞ ትዕይንተ-ህዝብ” በሚል፣ ይሁንና ዋናው መሰረተ-ሃሳብ” ጦርነት ይቁም፣ ግፋዊ አገዛዝ ያቁም፣ ዘላቂ ሰላም ይስፈን” በሚሉ
ልዩ | ‹ ከቤተመንግስት አልወጣም› ዓብይ | የሽመልስ እና ዝናሽ ግዙፉ ካምፓኒ ልዩ | ‹ ከቤተመንግስት አልወጣም› ዓብይ | የሽመልስ እና ዝናሽ ግዙፉ ካምፓኒ
እ.ኤ.አ. በ2024 ብሔራዊ ባንክ 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ በዚሁ ዓመት በነበረ የብር መዳከም 38 ቢሊዮን ብር መክሰሩ ተገልጿል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ. በ2024 በአጠቃላይ የባንክ ሥራው 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት ተረጋገጠ፡፡ ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር ኦዲት
58 የአብይ አህመድ ነጭ ውሸቶች! – ነዓምን ዘለቀ ቆጥራቹህ ስለላካቹህልን እናመሰግናለን! የተረሳ ካለ ጨምሩበት update አደረጋለሁ! 1. ሳናጣራ አናስርም 2.ጊዜ ስለሌለኝ ከኖቬል ሽልማት ፕሮግራም ላይ አልገኝም 3. አንዲት ፈረንሳዊ ላግባህ ብላኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ 4. በተከልነው ችግኝ የሀረማያ ሀይቅ ወደነበረበት