ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተያዘች

“ሮሃ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መዓዛ መሐመድ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ተይዛ መወሰዷን የስራ ባልደረባዋ እና ጓደኛዋ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገረች። የጋዜጠኛዋ እስር በኢትዮጵያ ከሰሞኑ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ቁጥር 19 አድርሶታል።
ጋዜጠኛ መዓዛ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ ሁለት ፖሊሶች እና የሲቪል ልብስ ባደረጉ ሶስት የጸጥታ ኃይሎች የተያዘችው በአዲስ አበባ ሰሚት ኮንዶሚኒየም ከሚገኝ የእርሷ መኖሪያ ቤት እንደሆነ የ“ሮሃ ሚዲያ” ጋዜጠኛ ምስራቅ ተፈራ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጻለች። የጸጥታ ኃይሎቹ መዓዛን ለ“ጥያቄ እንፈልጋታለን” በሚል ምክንያት ቢይዟትም ወዴት እንደሚወስዷት ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ጋዜጠኛዋ አስረድታለች።
መዓዛ እርሷ ቤት ያደረችው ያላጠናቀቁትን ስራ ለመጨረስ እንደነበር የምትናገረው ምስራቅ፤ ጠዋት ሶስት ሰዓት ገደማ የመኖሪያ ቤቷ ሲንኳኳ በከፈተችበት ወቅት ሁለት ፖሊሶችን እና ሌሎቹን የጸጥታ ኃይሎች በበር ላይ ማግኘቷን አስታውቃለች። የፍርድ ቤት መጥሪያ “አልያዙም ነበር” የተባሉት የጸጥታ ኃይሎቹ፤ የመዓዛን አድራሻ እና መታወቂያዋ ላይ ያለውን መረጃዎች ከመዘገቡ በኋላ በያዙት ካሜራ ፎቶ እንዳነሷት ጋዜጠኛ ምስራቅ አብራርታለች።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምትሃታዊ ማጭበርበር ተፈጽሞብናል ያሉ ደንበኞች ቅሬታ አሰሙ

1 Comment

  1. ክሚገባሽ በላይ ላገርሽ ለህዝብሽ ሰርተሻል ይህንን ታላቅ ስራሽን የሚያደበዝዝ ምንም ነገር ሊመጣ አይችልም አንች ለሌሎች እንደታገልሽ ላንች ያልታሰርነው እንጮሃለን ለሙያሽ ኤቲክሱ በሚፈቅደው ልክ ተዋድቀሻል ለሆድ አደሮች ምሳሌ ሁነሻል ምናልባት ስዩም ተሾመም የሚቆረጥለት ቀለብ ከቆመ እንዳንች ይሞክረው ይሆናል አይሞክረውም መቼም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share