March 18, 2022
3 mins read

በኢትዮጵያ…ከ3ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 65 በመቶው ማንበብ አይችሉም፤

 የሚያስተምሩትን ትምህርት ከተፈተኑ መምህራን 85 በመቶው ብቁ አይደሉም
275977039 266356392354490 4196900398557230098 n

275977039 266356392354490 4196900398557230098 nበኢትዮጵያ ካሉ የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 65 በመቶ ማንበብ እንደማይችሉ፤ የሚያስተምሩትን ትምህርት ከተፈተኑ መምህራን 85 በመቶ የሚሆኑት ብቁ አለመሆናቸው ተገለጸ።

ለትምህርት ስርዓቱ ውድቀትና ማነቆ ናቸው በተባሉ ተግዳሮች ላይ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጅማ ዩኒቨርሲቲ መክረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታዉ ዶክተር ፋንታ በላይ ዛሬ የጅማ ዩኒቨርሲቲን በጎበኙበት ወቅት የትምህርት ስርዓቱ በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ በግልፅ አስቀምጠዋል።

የትምህርት ስርዓቱን ከውድቀት ለመታደግና ሀገር ከሚገጥማት ተግዳሮት ሊታደግ የሚችል ትውልድ ለመፍጠር ችግሮች ላይ ግልፅ ውይይት ማድረግና ለመፍትሄ ማስቀመጥ ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ካሉ የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 65 በመቶ ማንበብ እንደማይችሉ፣ የሚያስተምሩትን ትምህርት ከተፈተኑ መምህራን 85 በመቶ የሚሆኑት ብቁ አለመሆናቸው ፣ ላለፋት ሰባት ዓመታት በየጊዜው የሀገር አቀፍ ፈተና መሰረቁም በመረጃ የተደገፈ ድክመት ሲሆን ፥ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶችም 99 በመቶ አስፈላጊውን መስፈርት እንደማያሟሉ ተጠቁሟል ።

ለስርዓቱ ድቀት መነሻና ማነቆዎች የትምህርት ስርዓቱን ከፖለቲካው ጋር በመለየት ዩኒቨርሲቲዎች ከክልላዊና ብሄር ተኮር እሳቤ በማላቀቅ ተማሪን ማብቃት ግባቸው ሊሆን እንደሚገባ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን የኤፍቢሲ ዘገባ ያሳያል።

ዩኒቨርሲቲዎችም የሚያከናውኑት የህንፃ ግንባታ ተማሪን ከማብቃት ግብ ጋር ሲነፃፀር የላቀ በመሆኑ የሚያስተቻቸው ስለመሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተጣረሰ አሰራር መውጣትና ከፖለቲካ መነጠል የትምህርት ስርዓቱን ከውድቀት ይታደገዋል ተብሏል ።

በቀጣይም ምክክሩ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እንደሚቀጥል ታውቋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እንደ አይሁዳዊያን አገር አልባና በሚሊዮን እስክንፈጅ መጠበቅ አለብን? —  ፊልጶስ

276161615 334950742004333 6133125007597817927 n
Next Story

የትምህርት ሚኒስቴር ከ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ውጤት እና ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop