March 5, 2022
53 mins read

መንግሥት ሆይ! ለራሥህ ሥትል ጣፍጥ! – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ 

” Man’s nature is made up of four elements, which produce in him four attributes, namely, the beastly, the brutal, the satanic, and the divine. In man there is something of the pig, the dog, the devil, and the saint.

AL  Ghazali

Abiy stiupid” የሰው  ተፈጥሮ ከአራት አካላት የተሠራ ሲሆን እነሱም በሰው ህሊና ውሥጥ አራት ባህሪያትን ያመነጫሉ ። (እንደየሰዉ  የህይወት ተመክሮና ነባራዊ ሁኔታ)  በአንድ ግለሰብ ውሥጥ ፣ የአውሪያዊ ፤ የጭካኒያዊ ፤ የሰይጣናዊ ፣  እና የመለኮታዊ ባህርያት ፣ ኮስሰውና ገነው ፣ ሊታዩ ይችላሉ  ።ሥለዚህም ነው ፣ በየሰው ውስጥ  ፣ የአሳማ  ፤ የውሻ ፤ የዲያብሎስ እና የቅዱሰነትን ዕለታዊ ተግባራን እና  ክንዋኔንን የምናሥተውለው ። ” (ነፃ ትርጉም)

(አንባቢ ሆይ ፣  ” አል  ጋዚል” ን  በፅሑፊ ውሥጥ በተገቢው ሥፍራ ጠቅሼልሃለሁ ።)

 ዛሬም ጥርጣሬ በህዝብ ውሥጥ ነግሦል 

” ምንድነው ነው እየሆነ ያለው ?   በጠቅላዩ    ፊት ላይ ፣ ህዝቦችና ብሔር ብሔረሰቦች ሣያውቁ  ፖለቲካዊ ቀዶ ጥገና ተደረገ እንዴ ?! የምናውቃቸው እና በለውጡ ሰሞን ”  ያበድንላቸው ” አብይ አህመድ የት ሄዱ ? ”  እንጠርጥር እንዴ ?!  አለ እያዩ ፈንገሥ ። እያለ ፣ ህዝብ በየቤቱ ከጥርጣሬው በመነሳት ፣ መንገሥትን ፣ በተለይም ጠ/ሚ  አብይ አህመድን ( ዶ/ር ) እያማ ነው ።

እውን ፣ ፈንገሱ  ይሆን እንዴ   በጥላቻ አሳብዶ ፣ ጠመንጃ አስነክሶ እያጋደለን ያለው ?  ዛሬ ና አሁን   ህዝብ ወደሚጠይቀው  ልማት ፊታችንን መልሰን የዳቦ ጥያቄን መመለስ ያልቻል ነው ፣ ዛሬም ፈንገሥ ሥለወረረን ነው እንዴ ? ዛሬም የ200 ዓመት የክፋት ታሪክን ወርዴ በጉያችን ሠንቀን ፤ ያለማወቅ የወለደውን ጉድ እንደ በጎ ነገር ተሸክመን ፣  ህልምን እውን አድርገን ፣ በአባት ጥፋት ልጅን ለማረድ ካራ የምናነሰው  ፣  ዛሬም ፣ ከድንቁርና የባሰ ህሊናዊ ዝቅጠትን    ፈንገሱ  ሥላጎናፀፈን ይሆንን ? ዘረኝነት ፣ ጎሰኝነት ፣ ወዘኝነት ፣ ቋንቋ አምላኪነት ፣ ድንቁርና  ፣ መሐይምነትን ፣ ጥላቻ፣ ሥግብግብነት ፣ ሥሥታምነት ፣ ሌብነት የመሣሠሉት  ፈንገሦች ሁሉ ሥለሰፈሩብን ይሆንን ?    ( ይኽም ተደጋግሞ የተነሳ የዜጎች ጥያቄ ነው ። )

ህዝብ እነዚህን  ጥያቄዎች በመጠየቅ ፣ ራሱ መልሥ እየሰጠ ባለበት ወቅት ነው  ፣ የአያሌ ታሪካዊ ኩነቶች ማብሰሪያ በሆነው  የካቲት ወር በቀን  15  ፣ 2014 ዓ/ም ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  ”  ያልተቀየረ ፊት  ፣ አለኝ ፣ አቋሜ ከሦስት ዓመት በፊት በንግግሬ   ቃል ከገባሁት ፍንክች አይልም ።  “ በማለት ፣  የምክር ቤት ዓባላቱ ላነሱት ጥያቄ  ፣ አርኪ ፣ አነጋጋሪ ፣ አጠያያቂ ፣ አከራካሪ ፣ እንዲሁም በፓርቲያቸው ውሥጥ ያለውን ሙሥና ፣ ዳተኝነት ና ገመድ ጉተታን ያሳበቀ       መልሽ በመሥጠት   በገደምዳሜ የፊታቸውን ያለመቀየር  ያሳወቁን  ። ያውም የመንግሥት ሌቦች ከላይ እሥከታች ፣ በመንግሥት መዋቅር ውሥጥ መሽገው እንደማገኙ በምሬት በመናገር ።

” ከላይ እሥከታች በመንግሥት ማዋቅር ውሥጥ  ፤ ሙሥና ሠፍኗል ። ” በማለትም የሀገርን ትንሽ  ጣት  እየቆረጡ የሚበሉትን ፣  ህሊና ቢሥ ሌቦች  ” ከትንሿ ጣት ላይ ምኗ ይቆረጣል ? ” በማለት የመንግሥት ሌቦችን ለማጋለጥ እና ወደ ፍርድ ለማምጣት ፣ በምርመራ ጋዜጠኝነት የመንግሥት ጋዜጠኞች እንዲሰማሩ ግልፅ የቃል ትዕዛዝም በመሥጠት  እሳቸው መሆናቸውን ያረጋገጡልን ።

ይኽንን ትዕዛዝ የሰጡት ፣በመንግሥት ውሥጥ የተሰገሰጉ  ሌባ ባለሥልጣናት ፣ ከደሃ መቀነት ላይ አሥገድደው እንደሚዘርፉ ሥለሚያውቁ ነው ። ይሁን እንጂ መረጃ እንጂ ማሥረጃ የላቸውም ። ደሞም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በሥተቀር ፣ ማንም ሌባ ሌባ አይባልም ። ሥራተኛ እንጂ ¡ ¡

የኢትዮጵያን ድህነትም ከናጄሪያ ሀብታምነት ጋር አነፃፅረው በማሳወቅ ፣ ” በሌብነታችሁ ፣ ልታፍሩ ይገባል ። ” በማለት ። አክለው ገልፀዋል ። ” ይኽንን አገርን ና ህዝብን አጥፊ ሙሥና በቁርጠኝነት ካልተዋጋን በሥተቀር ፣ ህዝብ አንቅሮ ሊተፋን እንደሚችል እወቁ   ። ” በማለትም አሥጠንቅቀዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ አፅዕኖት በመሥጠት ፣ በሙሥና ተዘፍቀው ህዝቡን የበለጠ እንዲጎሣቋል  እያደረጉ ያሉ ፣ ባለሥልጣናትን የመንገሥት ጋዜጠኞች ፣ በምርመራ ጋዜጠኝነት ተሣትፈው የማጋለጥ ና ሌባ ባለሥልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ የማሥቻል ሥራ እንዲሰሩ  እናደርጋለን ሲሉ ፣ ” ከእንግዲህ ፣ ‘ አይጥ በበላ ፣ ዳዋ መምታት የለበትም  ‘ ። ” በማለት ፣ ቢያንስ እሳቸውን መሠል ሃቀኛ የህዝብ አገልጋይ የብልፅግና አባለት ” ከኑግ ጋር የተገኘ ሠሊጥ …” መሆን እንደሌለባቸው በግልፅ አሥምረው ተናግረዋል  ።

በነገሬ ላይ ፣ ጠቅላይ ሚኒሥትራችን  የትላንቱን “  የናሁ ቴሌቪዢንን የምርመራ ጋዜጠኝነት ቱሩፋት  “  የሚዘነጉት አይመሥለኝም ። የነገርየው ትኩሣት ሲፋፋም እና ጣሪያ ሲነካ ነው   ” ቄሱም ዝም በል ። መፅሐፍም አትገለጥ ” የተባለው ። ”  በአናቱም ፣  የህዝብን ቀልብ ገዝቶ  መነጋገሪያ የሆነውን ፣ “ የምን ልታዘዝ  “   አንቂ ድራማን ጨምርበት ። ይኽ ድራማ ፣  ገመናችንን በማስጣት በገዛ እኩይ ምግባራችን  አፍረን ፣ ወደ ቀልባችን እንድንመለሥ የሚያደርገን  ድንቅ የኪነት ውጤት ነበር ። ሆኖም ደራሲው ” ደራሲ መሆን ስቃይ ነው ። በሥንት መከራ ፣ በጥበብና በዕውቀት ያረገዝኩትን ህዝብና አገርን የሚጠቅም ሃሳብ ወልጄ ሣጥን ውሥጥ ልቆልፍበት ። ያሳዝናል  ።  ” በማለት ፣ ፈጣሪነቱን እንዲረግም መደረጉን አንዘነጋም ። ፣ ድራማው በእንጭጩ  ሲቀጭ ፣ ድንቁርና የበለጠ እየነገሰ መጣ ። የወያኔ ደናቁርት ባለሥልጣናትም ፣ ምንም ፣ ዓላማ እና ግብ በሌለው ጦርነት  ወገን ፣ ወገንን እንዲገል በማድረግ በምሥኪን የኢትዮጵያ ልጆች ደም ታጠቡ  ።  ( ዛሬም ይኸው የሤጣን ዛር  አቅላቸውን አሳጥቶ ፣ የሚሰሩትን አሳጥቷቸዋል ።

ዛሬ ላይ ሆነን   ያንን ምርጥ ” ሂሳዊ ኮመዲን”  እንደ ጉም ያበነነው ማነው ? … “  ብለን ብንጠይቅ ፤ በበኩሌ ፣ በሥርቆት ላይ የተሰማራው ሥለ ህዝብ ንቃተ ህሊና ማደግ ደንታ ቢሥ የሆነው ፣ ዛሬ በግልፅ ሌባ ነው ያሉት ባለሥልጣን እንጂ ሌላ እንደማይሆን አምናለሁ  ።  ዕውን ሙሥናንን ራሱ መንግሥት ብቻውን ተዋግቶ ማሸነፍ ይቻለዋልን ? 

የተከቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ( ዶ/ር )  ፤  ሙሥናንን ለማጋለጥ ፣ ለመንግሥት መገናኛ  ብዙሃን የተናጥል የምርመራ ጋዜጠኝነት ፍቃድ ና ከለላ ከመሥጠት ይልቅ ፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውሥጥ የሚንቀሳቀሱ ጋዜጠኞች የህዝብን ቅሬታ ፣ የባለሥልጠናቱን ሙሥና እግር ፣ በእግር እየተከታተሉ ፣ እንዲያጋልጡ ፣  መመሪያ ቢሰጡ ና ለዚኽ የሚረዳ ምህዳርም እንደማፈጥሩ ቃል ቢገቡ የተሻለ ና ቁርጠኝነትዎን የሚያመላክት እጅግ የተባረከ  አገርን ከዘራፊዎች የሚታደግ ሃሳብ ይሆን ነበር ። በማለት ትሁት አሥተያየቴን አቀርባለሁ ።

ሁላችንም እንደ አሥተዋል ነው  ፤ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃኖች ፣ በዜጎች   መካከል ሆን ተብሎ  የመረጃ ክፍተት እንዲፈጠር  ፣ በአገር ጠላቶች የሚፈጠርን ሐሠተኛ ወሬ ወይም ፕሮፖጋንዳ ለማክሸፍ የተጫወቱት ሚና እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ። እንደውም  በየዘርፉ የመጠቀ ዕወቀት ያላቸውን ምሁራን በመጋበዝ ህዝብ እውነትን እንዲያውቅ ከማድረግ ይልቅ ፣ በአመዛኙ ፣ በየሙያው   ጥልቀት የሌለውን ግለሰብ ለውይይትና ለማብራርያ እየጋበዙ ፣ ህዝብን በቂ መረጃ እንዳያገኝ አድርገዋል ።   በድንገት የተከሰተውን ጡት ነካሽነት  እንኳን ፣ በበቂ መጠን ለማሳየት የሞከሩት እጅግ ዝግይተው እንደሆነ ይታወቃል ።

ዛሬም ከመንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ይልቅ ፣ በየጊዜው   የሚፈጠረውን የህዝብ መፈናቀል ፣ ሞት ና ሥቃይ  እንዲሁም ፖለቲካዊ ድንገቴ ክሥተቶችን ፣ የጦርነት ሂደቶችን ፣ ወዘተ ።  እንደ ወያኔ ዘመን  ፣ ከዩቲዩብ ፣ ከጀርመን እና ከአሜሪካ ድመፅ ሬዲዮ ነው ህዝብ የሚሰማው  ።

በብልፅግና እና በኢትዮጵያ መንግሥት ሥር ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች (ተለይም ዋና ፣ ዋናዎቹ ሦሥቱ …)  ሰው ሰውን በአውሬነት እየጨፈጨፈ እያዩ ና እየሰሙ ፣ እንደ ተራ ሰው ዝም እንዲሉ ኃላፊዎቻቸው እና ኤዲቶሪያል ሹሞቹ  በቀጭን ትዕዛዝ የሚከለክሏቸው  ይመሥላል   ። በተቃራኒው ሶሻል ሚዲያው  ፣ የአንዱን ሰበር ዜና እየደጋገመ  በማስጮኽ ህዝብ በወሬ እንዲታመሥ ያደርጋል   ። የሰበር ፣ ሰበር ፣ ሰበር ፣ሰበር ዜናንን ደጋግሞ  በማሰማትም ፕሮፕጋንዳን እንደ አሜባ ያራባል ። የአንዳንድ ዩቲዩቦቹ የወሬ  ቦይ ” በግደል ተጋደል … ” የተሞላ ነው ።  በዚህ ላይ በውጪ አገር ያሉ ፣ ከአገር ጠላቶች ድጋፍ የሚደረግላቸው ፣ የድምፀ ወያኔ፣ የድምፀ ሸኔ  ፣ የሳተላይት ቴሌቪዢን ጣቢያዎች ” ሟልቃቃ ጋዜጠኞቻቸው ” የሚሞተውን ፣ ዜጋ ቱሃንና ቁንጫ  አሥመሥለው ፣ አሁንም ለእልቂት ተዘጋጅ ” እምበር ተጋዳላይ ! ትግራይ ጃገኖ ! ጀጋኖ ! …” በማለት በየቴሌቪዢናቸው  ይጮኻሉ  ።  አህያ የጅብን ማጅራት አንቃ ሲጥ እንዳደረገችው እና ማንም ሰው ፣ ራሱን ከሞት ለመከላከል ሲል ፣ እንደሚጀግን እንኳን ለመረዳት የሚያሥችል ህሊና እንደ ጌቶቻቸው ፣ አልፈጠረባቸውም  ።

ከዚሁ የነፃ  ፕሬሥ ጣጣ ሳልወጣ ፣ በየካቲት 15/ 2014  ጠ/ሚሩ አብይ ለምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች በሠጡት መልሥ ፣ መንግሥታቸውን በፍላጎቱ ልክ እንዳይራመድ ያደረገውን ፣ በተዋረድ ከላይ እሥከታች የተንሰራፋውን     ሙሥና ፣ የራሳቸውን ሚዲያ  ፣ ” እውነተኛ የፕሬሥ አርበኛ ሁን ። ሙሥናንን በነፃነት አጋልጥ ። የምርመራ  ጋዜጠኝነት ሥራን  አድምተህ ሥራ ፤ ይኽንን ሙያዊ ኃላፊነትህን ሥትወጣ   ደንቃራ የሚሆንብህ ካለ አልምረውም ። ” ብለዋል ። በቃል። በፅሑፍ ለየፕሬሥ ድርጅት ኃላፊዎች ግልፅ መመሪያ እሥካልሰጡላቸው ጊዜ ድረሥ ግን ፣ ጋዜጠኞች  ዋሥትና እንደሌላቸው የታወቀ ነው ። የቃል መመሪያ ብዙን ጊዜ በህግ ቅቡልነት የለውም ።… ለጋዜጠኞች በራቸውን የጠረቀሙ አያሌ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለጠቀላይ ሚኒሥቲሩ የቃል መመሪያ እንደማይበገሩ የታወቀ ነው ።

ደግሞም  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣” ዩቲወበሮች የኑሮ ግብ እንጂ ህዝባዊ ተልዕኮ የላቸውም ። አትስሞቸው ። ፍራንካ ፍለጋ ነው የሚተረተሩት ። ” ይሉናል ። እሥከዛሬም በቀቀንነትና ትርትርነት ያለቀቃቸውን የመንግሥት ሚዲያዎችን ” ኃቀኛ በመሆን “እውነተኛ  ጋዜጠኛ” መሆናቸውን በተግባር እንዲያሥመሰክሩ ግን  ነፃነታቸውን አሠሪዎቻቸው እንዲሰጦቸው ፣ ግልፅ መመሪያ በደብዳቤ ሳይሰጥ እውነትን በአደባባይ ማሥጣት እንዴት ይቻላል ?    ህጋዊ መብታቸውን በግልፅ ለቀቅ መቼ ተደረገና ?!      ገመዱን አሥረዝሞ መልቀቅ መፍታት አይሆንም   ። በበኩሌ  የዜና ዘገባቸው በራሱ ፣ አይመቸኝም ። ከእውነት ይልቅ ፕሮፖጋንዳ ላይ ትኩረት ያደርጋልና ! እንዲያ በመሆኑም ፣ እውነትን  ከማሳወቅ ይልቅ ያደናግራል ። ሚዛናዊ ዘገባ ከማቅረብ ይልቅ የአንድ ወገን አሥተያየትን ብቻ መቀበል ማደናገሩን ያብሰዋል ። ደጋግመን በሰማነው ጉዳይ ላይም ችክ ይላል ።   …

የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ሁሉ፣   “ መንግሥት  መሥማት የሚፈልገው ይሄን በቻ  ።  ነው ።  “ ብሎ በማመን ፣ ከጋዜጠኝነት ዓላማ ይልቅ ፕሮፖጋንዳ ላይ ብቻ ካተኮሩ  ፣ በበኩሌ መንግሥትን ገዝግዞ ለመጣል ሳያውቁት ለሙያው ያልተገባ ሥራ እያከናወኑ እንዳሉ መገንዘብ አለባቸው ። … ገዢው ፖርቲ መሥማት የሚፈልገውን ብቻ የሚሰማ ከሆነ ቆሞ ቀር አይሆንም እንዴ ! ?  የሰማውን እና የሰማነውን መደጋገምስ በቀቀንነት አይደለም ወይ ?  ይኽ ለማንኛውም ወሬ ፣ ቅርብ ና  ተቀዳሚ የሆነ  የሚዲያ ተቋም   ፣ ህዝብን ከመደናገር ለማውጣት ፣ በእሥረኞች መለቀቅ ና በአሥቸኳይ ጊዜ አዋጁ  ዙሪያ እንዲሁም በብልፅግና ፖርቲ ዓባላት  ውሥጥ አለ የሚባለውን ያለመግባባት ፣ ወዘተ ። ቀደም ብሎ ልዩ ፕሮግራም በመሥራት ፣ ህዝብን ማረጋጋት  አይችልም ነበር ወይ ?

( በበኩሌ የብልፅግና  ፖርቲ  ፣ ወይ እንደ ቻይና እና ሩሲያ ኮሚኒሥት ፖርቲ በአንድ ማዋቀር  የሚመራ መሆኑንን ያሣየን ፤ አልያም በምዕራቡ የፖርቲ አደረጃጀት መንገድ ራሱን ያደራጅ ፤  ጥልቅ መሠረት ያለው ፖርቲ መሆኑን ያሳይ ። ለአገሪቱ ሠላም በእጁጉ የሚበጀው የጠራ ርዕዮት ነው ። በዓለም ፖለቲካ ፣ ቅቡልነት የሌለውን  ጎሣዊ አደረጃጀትን ና የቋንቋ አምልኳን  ይዞ ገዢው በልፅግና  ከቀጠለ ግን ፣ የልሲናዊና ጊርቫቾቫዊ  ውድቀትን በአገር ላይ መጋበዙ አይቀሬ ይሆናል   ። ፑቲን ዛሬ በሰርጀሪ የቀድሞዋን ሩሲያ ለመገጣጠም እየሠራ ያለው የነየልሲንን ጥፋት ለማረም መሆኑንን ተረዳ  ። )

የመንግሥት የሳተላይት ቴሌቪዢኖች  ፣ የፌደራል መንግሥቱ የአሥቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያነሳው ፣ በመደበኛው የህግ መሥከበር መንገድ ፣ “የህዝብን ሠላም ፣ ደህንነት እና የአገሪቱን ፀጥታ ማስከበር እችላለሁ ። ” ብሎ ነው ወይ ? …  የአሥቸኳይ ጊዜ አዋጁ  መነሳት አለበት ወይም የለበትም በሚል ግልፅ የውይይት መድረክ የመንግሥት ሚዲያ  ማዘጋጀት   ይችል ነበር ።አዋጁ  ከመነሳቱ በፊት  ።  ይሁን እንጂ ጅብ ከሄደ ውሻ ሲጮኽ ነው የምንሰማው ። በበኩሌ ጋዜጠኞች ግንባር ቀደም  እንጂ ጭራ መሆን የለባቸውም ። የሚል እምነት አለኝ ።

ይኽ የአሥቸኳይ ጋዜ አዋጅ መነሳት ፣ በህዝብ ዘንድ ጥያቄ የጫረው ፦  ክልሎች ራሳቸው የብሔር ብሔረሰብ  መንግሥት  በመሆናቸው ፤  የሚጠሩትም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት የትግራይ ፣ የኦሮሚያ ፣የአማራ የሱማሌ ፣ የአፋር ፤ እየተባሉ  በመሆኑ ነው ።  በህገ መንግሥቱ አንቀፅ 51 ንዑስ አንቀፅ 14 መሠረተ  በክልሎቹ የፀጥታ ጉዳይ የፌደራል መንግሥት ክልሎቹ ሳይፈቅዱለት ጣልቃ ለመግባት አይችልም   ። አራት ነጥብ ። ደግሞም አዲስ መሥመር ። ወየው ጉዴ !” አለች አሉ ፍትህ ። ( … )

የፌደራሉ መንግስት ፣ በህገመንግሥቱ መሠረት ፣ ክልሎቹ እንዲገባ ካልፈቀዱ በስተቀር ሺ ሰው ቢሞት ፣ ወደ ክልሎቹ  እንደ አሥጊነቱ ፣ የክልሉን መንግሥት ፍቃድ ሣይጠይቅ የፌደራሉ የጦር ሠራዊት  እንዲገባ  ፣ የአገሪቱ የጦር ኃይሎች አዛዥ ለማዘዝ አይችልም ። ይኽ ፍትሐዊ ያልሆነ ህግ በመሆኑ ነው ፤  ፍትህ በሰው ተመሥላ ” ወይኔ ጉዴ ! ”  ያለችው ።

ፍትህ በአሳሪው ህገ መንግሥት  “ ወይ ጉዴ !” ብላ ሣትጨረስ  ፤     በአንቀፅ 74 ንዑሥ አንቀፅ  13  ጠ/ሚ ህገ መንግሥቱን የመጠበቅና የማስከበር ግዴታ ሥለተጣለባቸው ፣ ” የዜጎች መብት ሲጣስና የህዝብ ሠላም ሲናጋ ዝም ብለው ለማየት አይችሉሙ ። ” በማለት በገደምዳሜ ማሳሰቡን አሥተውል ።  እንዲህ ዓይነት ድፍንፍን ያለ ህገመንግሥት የትም አገር  ተፅፎ አያውቅም ።   … በግልፅና በጉልህ ፣    ” የክልሎችን ፈቃድ ሳይጠይቁ ፤ ህገ መንግሥቱን አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር በህቡም ሆነ በገሃድ ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል ። ብሎ የደህንነት መሥሪያ ቤቱ ፣ መንግሥትን ካሳወቀ ፣ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል   የዜጎችን ሠላምና ደህንነት ለመጠበቅ ና ፍትህን ለማንበር ፤ ህገ መንግሥቱን ለማስከበር    ፤ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒሰቴር  የአገር መከላከያ ሠራዊቱን የማዘዝ ሥልጣን አለው ። ”  ተብሎ  መደንገግ ነበረበት  ። …

በእውነቱ  ይኽ ህገ መንግስት   ካሉት 106 አንቀፆች ውሥጥ ፣ ከረቂቅ ሃሳባቸው ጀምሮ ፣ የማያግባቡ ፣ የማያኗኑሩ ፣ የሚያሻሙ ፣ የተደፋፈኑ ፣  ጠብ ዘሪ ና  አጫሪ የሆኑ  አንቀፆችን ከአንቀፅ 1 ፤ 39፤  እና ከምእራፍ 4 እሥከ 11 እንዳሉበት ይታወቃል ።

ለምሳሌ  _ ህገ መንግሥቱ  በምዕራፍ 2 ሥለ ልዩ ፣ ልዩ  መብቶች  እያወራ ሣለ ፤  አብሮነትን የሚጠላ ፤ ፍቅርን የሚገድል ፤ ሥግብግብነትን የሚያገዝፍ ፤ ከፋፋይ አንቀፅ 39 ተብሎ ተደንቅሮበታል ።    …

ሥለ  ሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብቶች የተጠቀሱት  30 አንቀፆች  አንቀፅ 39ኝ ሳይጨምር  ከአንቀፅ 13 እሥከ 44 ያሉትን ማክበርና ማሥከበር ፣ ህገ መንግሥቱ በሰጣቸው ሥልጣን የሚችሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሆኑ ግልፅ ነው ። ( ለዚህም ነው ፣ ህዝብ ፣ ሽብር ፣ ሁከት ፣ ውድመት ጭፍጨፋና ግድያ እዛና እዚህ ተከሰተ ሲባል ፤” መንግሥት የት ሄዶ ነው ? ” ብሎ የሚጠይቀው ። ይሁን እንጂ ፣ ህገ መንግሥቱ እጅግ የተለጠጠ ሥልጣን ፣ በተለይም ፀጥታን በተመለከተ ፣ ለክልሎች በመሥጠቱ እና በአንድ ዕዝ የማይመራ  የፖሊስና የፀጥታ ኃይል በየክልሉ ሁሉ በመኖሩ   ፣ በመንግሥት ላይ ሌሎች ፈላጭ ቆራጭ  መንግሥታትን   ህገ መንግስቱ  በመፍጠሩ ፤ አገሪቱ ላይ ከባድ አደጋ ተደቅኗል ። ለዚህ ነው ይኽ ህገ መንግሥት ፣ ከፋፋይ ና  የካድሬ ሰራዊት በየቀበሌው ሰግስጎ ዘላለም ዓለሙን በምርጫ ሥም የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያ እንዲነግስ በምዕራባዊያኑ የተሸረበብን እንጂ በህዝብ ይሁንታ  የተገኘ የእኛ የምንለው አይደለም የምንለው  ።  በመሆኑም የብልፅግና ፖርቲ ፣ “ እኔ   ከወያኔ የተለየ የፖለቲካ እምነት ነው ። ያለኝ ። “ ብሎ የሚያምን ከሆነ እምነቱን በተግባር ያሳየን ። ልክ እንደኃይማኖት ፖለቲከኛም ፖለቲካዊ እምነቱን በሥራ ማሳየት ይጠበቅበታል ። …

እምነቱን በሥራ ወይም በተግባርየማያሳይ ኃይማኖት   እንደሌለ  ሁሉ ፤  አንድ የፖለቲካ ፓርቲበማይተገበር   መርህ ና ፕሮግራም የሚመራ ከሆነ ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ሊባል ከቶም አይችልም ና  ለገዢው የብልፅግና ፓርቲ ቁንጮ አመራር ይኽንኑ እውነት  ማሳወቅ ወቅቱ ያስገድደናል ። የፀሐፊው ዓለማ ” ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ብቻ ና ብቻ እንደሆነ  ግን ፣ ይሰመርበት  ።

ገዢው የብልፅግና ፓርቲ አሁን እና ዛሬ ፣ ጨውነቱ እየጠፋ ነው ። የራሱ ዓባላት ፣ በሥጋ አስገዳጅነት    ገማሽ አካሉ ቆስሎ ፣ ቁስሉን ወደ ጋንግሪን ወይም ቂመኛነት እየቀየሩት ነው ። እልፍ አእላፍ   ጀርሞች በቁሥሉ ላይ እየተራቡበት ነው ። ቁስሉ  ከባድ  ኢንፊክሺን ፈጥሯል ። የዚህን ኢንፊክሺን ምክንያት ና የቁስሉን ጥልቀት በወጉ ተረድቶ ፣ ተገቢ ህክምና በማደረግ ፣ ቁስሉን በጊዜ  ማከም ካልተቻለ ብልፅግና መድረሻው የምድር ገሃነም ነው ። ወደ ምድር ገሃነምም  ብቻውን አይገባም ። … ህዝብን ና አገርን ጭምር ይዞ ነው ፤ ወደ ምድር ገሃነም የሚገባው ።

እናም ወደ ምድር ገሃነም ህዝብ ና አገርን ይዞ ከመግባቱ በፊት ፣ ቆም ብሎ በማሰብ ፣  የ21 ኛውን ክ/ዘ የፖለቲካ ንስሃን በወጉ ማድረግ ይጠበቅበታል ። የኃይማኖት ንሥሐ ብቻ ሳይሆን ፣ የፖለቲካ ንሥህ ማድረግና  ወደ መልካሙ  መንገድ  መመለስ ወደ ምድር ገሃነም ከመግባት እንደሚያድን ማወቅ ብልህነት ነው ።

ከመርህና ከፓርቲ ፕሮግራም አኳያ ፣ ብልፅግና ያለውን የፖለቲካ አምነት ለመገምገም ያግዘው ዘንድ ፣  በዓለም ካሉት በመልካም አስተምህሮታቸው  እንደምሳሌ ከሚቆጠሩት ኃይማኖቶች  ውሥጥ  የሱፊዝምን ዋና የእምነት ምሰሶ እንደምሳሌ አቀርብለታለሁ ። ለመማር ከተፈለገ በዚህ ዓለም አያሌ የመማሪያ መንገዶች እንዳሉ ይኽ ፅሐፍ  ያምናል ።      እነሆ ሱፊዝም !

ሱፍ ኢዝም የባለ ሱፍ ካባ ወይም የበግ ፀጉር ለባሽ የኢሲያ ጥንታዊ ኃይማኖት ነው ።አንዳንድ ጥናቶች ይኽ ኃይማኖት    ከኃይማኖቶች በፊት የተፈጠረ እምነት ነው  ይላሉ ። ዊኪፒዲያ ያብራራልሃል ።… ። የእምነቱ መሠረታዊ  መመሪያም ፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ መሠረታዊ የሐዋርያነት መሥፈርት አንዱ እና ዋነኛው  መሆኑም ያሥገርማል  ።  ሉቃስ 14

  • . እንግዲህእንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
  • . ጨውመልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፈጣል?
  • . ለምድርቢሆን ለፍግ መቈለያም ቢሆን አይረባም፤ ወደ ውጭ ይጥሉታል።  የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ። የክርስቲያን መንገድ   ካለበት ቅርፅ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ነው ።

በሱፍ ኢዝም አስተምህሮ አንድ ሰው ፍፁም ሆኖ ፣ ከፈጣሪ የተስተካከለ  ተአምር ለሰዎች ለማሳየት ፣ በፍፁምነት ደረጃ ላይ  ለመድረስ  አራት የተለያዩ ደረጃዎችን ማለፍ ይጠበቅበታል ። ይለናል ።  እነሱም ፦

1ኛ .ንስሃ ገብቶ ከከፉ ነገር ሁሉ መራቅ ።

2ኛ .ሃብትና ንብረትን ንቆና ትቶ  ደኸ መሆን

3ኛ .በእምነት  ተጠናክሮ  እና ፀንቶ በትዕግስት መቀመጥ

4ኛ .የመጨረሻ ደረጃ እውነትን መጨበጥ መቻልና እርካታ ማግኘት ናቸው ።  ” የመጨረሻው ደረጃ ቅዱስ ወደ መሆን ያደርሳል ። ” ይሉናል ። ሱፊስቶች ።  “ሦሥቱን ተግብረህ ፣አራተኛው ደረጃ ላይ ከደረስክ ፣  የፈጣሪ ኃይል ሁሉ ይገለጥልሃል ። ሁሉንም ታውቃለህ ። ማወቅህም  ታምር ለመሥራት ያስችልሃል ። ” ነው ተረኩ ። በተረኩ መሠረት ተጉዘህ አራተኛውን የመገለጠ ደረጃ ሥትጨብጥ ፣ ” የፈጣሪን ሚና መጫወት ጀሞሬአለሁ ” የምትል ከሆነ ፣ የላቀ ዕውቀትህ ብቻ ሳይሆን ህልውናህ  በቀናተኛ ሰዎች ሊያከትም ሥለሚችል ከሰው ተገልለህ በገደም መመሸግ ይጠበቅብሃል  ።

ይኽንን እውነት ፣ በሱፍ ኢዝም እምነት  ውስጥ  ትልቅ ደረጃ የደረሰው የማንሱር አልሃጂ  አሳዛኝ መረጨሻ ያረጋግጥልሃል ።

ማንሱር ፣  የሱፍ ኢዝም እምነትን ለማንበር  ቢተጋም ፣ ኃይማኖቱን ያለማሰለስ ቢሰብክም   ፣    በ922 ዓ/ም  እኤአ ” አራተኛውን ደረጃ ወጥቻለሁ ። ሁሉን ማወቅን ተጎናፅፊለሁ  ። እኔ ፃድቅና የበቀሁ ፤ የነቃሁ ነኝ ። የበራልኝ ነኝ ። ” በማለት በአደባባይ የተናገረውን ፣  ማንሱር  አላሃጅ (  Mansour Hallaj (Persian  romanized: Mansūr-e Hallāj) (c. 858 – 26 March 922) (Hijri

  1. 244 AH – 309 AH) was a Persian mystic, poet and teacher of Sufism. He is best known for his saying:   “I am the Truth” ( እኔእውነትነኝ ። ) በሚል ንግግሩ ና   ቀጥታ ከፈጣሪ ጋር መነጋገር እችላለሁ ። ” በማለቱ ፣   የእምነቱ    ተፃራሪ የሆኑ  ፣ የሌላ እምነት ተከታዮች ለሸንጎ አቅርበውት   በሞት እንዲቀጣ አድርገውታል  ። ” ሰው ሆነህ ሳለ አምላክ ነኝ ። ” ማለት ሴጣንነት ነው ። እብደት ነው ።” በማለት ። …

ወዳጄ ሆይ ! በዚህ ዓለም ላይ ፣ በራልኝ ። ተገለጠልኝ ። እናንተ ያላያችሁትን አየሁ ።  ወዘተ ። ” በማለት  “የሰዎችን የተሰወረ ሐጢያት ”   አደባባይ ብታወጣ እና በድፍረት ትላለቅ ባለሥልጣናትን ፣ ” የተሰወረው ሐጢያታችሁ ” ይህ ና ይሄ ነው ።  በጊዜ ንስሐ ግቡና ከፓለቲካዊ  ሐጢያት ነፅታችሁ ህዝብን አገልግሉ ። ዳግመኛም መሠል ሐጢያት አትስሩ። ” በማለት ሐጢያታቸውንን እንደብቅል ብታሰጣባቸው ፤ እጣህ የመጥመቁ ዮሐንስን ዓይነት ሊሆን ይችላል   ። ደሞም የምናውቀውና የለመድነው ፣ በእልፍኝ ማማት  እና በአደባባይ ማንቆለጳጰስ እንደሆነ ለአፍታም አትዘንጋ ! በአናቱም የሚከተለውን ዘላለማዊ  የአልጋዚልን ምክር ሥማ ። በዚህ ምክር ውስጥ መኖር  ዕድሜህን ለማርዘም እንደሚረዳም  ተገንዘብ ።

የሱፍ ኢዝም እና ሌሎች የሙስሊም እምነቶች እንዳይጋጩ ያደረገው ፣ ከዘመናት በኋላ በታላቅ የማሥተዋል አእምሮ ተሞልቶ ፣ ለሙስሊም ኃይማኖት መስፋፋት   ታላቅ አሥተዋፆ  ያበረከተው ና  ” ሊቀ ሊቃውንት ” ተብሎ የተወደሰው  ፣ፈላስፋው ፣ ኢማም መሐመድ   አልጋዚል ነው ። ( 1058 ዓ/ም እስከ  1111 ዓ/ም  እ ኤ አ የኖረ ።

ኢማም አልጋዚል ፣ እችን ዓለም ከመሰናበቱ በፊት እንዲህ በማለት ኃይማነተኞችን ፣ በጥብቅ መክሯል   ።   “ጠርዝ ላይ የደረሰ ፣ ሥጋ መልበስን የረሳ መንፈሳዊነት  ህልመኛ ያደርጋል ። እጅግ ጠርዝ ረግጦም  በሥጋ ፍላጎት መቅበዝበዝም  ( አለማዊ መሆንም  )  ከፈጣሪ ( ከአላህ) ያርቃል ። ሥለዚህ ሁለቱም ጠርዞች መልካም ሥለአይደሉ መካከለኛውን መንገድ መያዝ ይበጃል  ። ”  በማለት   እንደ እርግብ የዋህ ። እንደ እባብ ብልህ መሆን ” እጅግ ጠቃሚ መሆኑን በገደምዳሜ  ተናግሯል  ።

ይኽ ልባምነትን ከየዋህነት ጋር የተጣመረበት ፣ የኑሮ ፍልስፍና ለሁሉም ሰው ህይወት መቃነት ትልቅ አስተዋፆ ቢኖረውም ፣ በተለይም ፣ አገርን የማበልፀግ ግልፅ ተልኮ ያላቸው ፣ በኑሮና በተልዕኮ መካከል ያለውን ልዩነት በጥልቀት ተረድተው ለተልዕኮቸው ተግባሪያውነት

፣ በወጉ በልባምነት ና በየዋህነት ወደ ግባቸው በፅናት ለመጓዝ ቁርጠኛ መሆን ብቻ ሳይሆን እንደ እርግብ የዋህ መሆን ይጠበቅባቸዋል

ፅሑፊን ከመቋጨቴ በፊት ጠ/ሚ አብይ ከህዝባዊ ተልዕኳቸው እንዳያፈገፍጉ በብርቱ ለማሳሰብ እፈልጋለሁ ። ጠ/ሚ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ፣ ከተልዕኳቸው ይልቅ ኑሯቸው ላይ እንዲያተኩሩ ፣ የሚወተውቷቸውን ፣ አጠገባቸው ያሉ ፣ ቅርብ ሰዎችን ፣ ተው ፣ እረፉ፣ የመሪ ተልዕኮና ኑሮ እጅግ ይለያያል ። የመሪ ተልዕኮ የሚመራውን አገር እና ህዝብ ጥቅም ለማሥጠበቅ ዘወትር መትጋት እንጂ ሥለ ግል ኑሮው መጨነቅ አይደለም ። …በማለት ሊያሳፍሯቸው ይገባል ። ጠ/ሚ ብዙ ጊዜ ስኳር እንደ ፈተናቸውና ለስኳር ደንተ የሌላቸወ ኢትዮጵያን ባለፀጋ ለማድረግ እንጂ ራሳቸውን እና የዘመድ አዝማዳቸው  ኑሮ ለመቀየር ፣ በዜጓች ፊት ቃል እንዳልገቡ ፣ በመንገር እነዚህን አግበሥባሽ ከበርቴዎችን  አሳፍረው መመለሳቸውን ስምተናል ። ግን አሁን እና ዛሬ ምን እንደተከሰተ በአመራራቸው ውስጥ ያለውን ፖለቲካዊ ፍጭት ባለማወቃችን ፣ በጠረጴዛቸው ላይ ካለው አጀንዳ አንፃር ትልቅ ሥጋት ውሥጥ ብንገኝ ማን ይፈርድብናል ?

ከዚህ  ሥጋታችን ተነሥተን ፣ በመግቢያዬ ላይ ፣ የአገሪቱ ዋና መሪ የሆኑት ዶ/ር አብይ አህመድ በህይወት እያሉ ነው ፣ ወይስ ሞተው ፊታቸው በሰርጀሪ  እንደ  FACE OFF የተሰኘ  ፊልም መልካቸው ለሌላ ተሠጥቶ ? በፊልሙ እንዳያችሁት  የወንጀለኞች ፀር የሆነውን  የጆንትራ ቮልታን እና የማፍያ ቡድን መሪ የነበረውን የኒኮላስ ኬጅን ፊት  በሠርጀሪ  በመቀያየር ፣ወጀለኛው ኒኮላስ ኬጅ ፣ ፖሊሥ ሆኖ  ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ያሥከተለውን ቀውሥ  ከፊልሙ ትገነዘባላችሁ … ብዬ በማሰብ ነው  ፣  የህዝብን    ጉምጉምታ በመጊቢያዬ በዚህ ምሳሌ ለመጥቀስ  ለማሥረዳት የሞከርኩት  ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop