ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ የተመደቡበትን ስራ እንደማይቀበሉት ነዉ የታወቀዉ ከልዩ ሃይሉ አዛዠነት የተነሱበትም ምክንያት ያለቀ ጦርነት የለም የአማራ ህዝብ ተደራጅቶ ራሱን መጠበቅ አለበት ወጣቶች ሰልጥነው ፋኖ መሆን አለባቸው አለበለዚያ የአማራ ልዩሀይልን መቀላቀል አለባቸው በማለተቻዉ እነደሆነ ተናግሯል።
በአማራ ህዝብ ረጅም ታሪክ ውስጥ ለአማራ ህዝብ መከራና ሰቆቃ ከገባቸው በእጣት ከሚቆጠሩ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ጀኔራል ተፈራ ማሞ አንዱ ነው የአማራ ልዩ ኃይል ሰራዊት ካደራጁት ጀግኖች መካከል ጀነራል ተፌራ ግንባር ቀደምም ናቸዉ ።
የአማራን ህዝብ ህይወቱን ሁሉ ገብሮ ማገልገል ፍላጎት ያለው ለአማራ ህዝብ ተወልዶ ለአማራ ህዝብ ለመሞት ቃል የገባው ፤ ሸማቂው ኮማንዶ ተፈራ ማሞ ስራን በነጻነት እንዳይሰራ ፣ የሚፈልገውን እና የሚያግዘውን አካል ወደ ፊት እንዳያመጣ ፣ የሚያቀርበውን እቅድ እና የሰው ሀይል ውድቅ ሲያደርጉበት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል ።
ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:-
አሻራ ሚዲያ
—–
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት የብ/ጄነራል ተፈራ ጠባቂዎች መታሰራቸው ተገለጸ
ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ተጠርጥሮ ከታሰሩ በኋላ ክሱ ተነስቶለት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ተደርጎ ተሹመው ባለፉት ሁለት ዓመታት የአማራ ልዩ ኃይልን እና ፋኖን በማደራጀት በጦርነቱ ቁልፍ ተሳትፎ እንደነበራቸው የሚነገርለት ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን በፌዴራል መንግስት እና በፋኖ አደረጃጀት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ከሥልጣናቸው ተነስተው የፕሬዚደንቱ የደህንነት አማካሪ ሆኖ እንዲሰሩ ብመደብም አልቀበልም ማለታቸው ይታወቃል።
ትናንትና ምሽት ደግሞ የጄነራሉ ጠባቂዎች የሆኑት ሁለት ልዩ ኃይል አባላት ታፍነው መወሰዳቸው ከባህር ዳር የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።
ማለዳ ሚዲያ