December 26, 2021
9 mins read

እኛ ኢትዮጵያዊያን አጎዋንን መተካት እንችላለን ? ጥሩ ሰው ለመሆን ጥሩ ጓደኛ ይኑርህ – ፊልጶስ

agoaየተሳካለህ ሰው ለምሆን ግን ጠላት ይኑርህ።” የሚለው አባባል ከግለሰብ ጀምሮ እስከ አገር ድረስ  ለሁሉም ባይሆን ላወቀበት ይሰራል።

ብዙ ጠላት ያላቸው አገሮች፣ ራሳቸውን ለመከላከልና ብሎም አጠፋውን ለመመለስ ፤ ”ለጠላቶቻችን እጅ አንሰጥም!” በማለት ራሳቸውን ነጻ ከማውጣት አልፎ   የተደበቀ ኃይላቸውን እና እውቀታቸውን  ለመጠቀም በቅተውበታል።  እስራኤል እንደ አገር ለመመስረት ያበቃት የጠላት መብዛት  በአንድነት እንዲቆሙና ብሎም አሜሪካንና አውሮፓን ከጎናቸው አሰልፈው ዛሬ ዓለምን ለመዘውር በቁ፤ ከዚህ ላይ ጥራት እንጅ የቁጥር ብዛት ወሳኝነት እንደሌለው መገንዘብ ያሻል።  ኢራን  ከ1979 ጀምሮ በአሜሪካና በአውሮፓ የተጣለባትን  ማንኛውንም ማዕቀብ ተቋቁማ አሁን ካለችበት ደረጃ ደርሳለች።

ጥያቄው ዛሬ እኛስ……  አሜሪካና  አውሮፓ   በአገራችን ላይ ያላቸው ዓላማ   ከምጣኔ ሃብት ማዕቀብ ባለፈ ” እጃችሁን ጠምዝዘን  በ’ኛ ትዛዝ ትኖራላችሁ ወይም  ወያኔን እና ኦነግን ተጠቅመን እናፈርሳችኋላን።”  የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ በድብቅ ሳይሆን በግልጽ  ‘ርምጃ  መውሰድ ከጀመሩ ውለው አድረዋል።

”ፕሬዝዳንት ባይደን ኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት የሚያግደውን ውሳኔ ፈረሙ” የሚለውን ዜና ሳንብና ስሰማ  በግሌ እንደ አገር፤ እንደመንግሥት  እና እንደ ህዝብ ማንነታችን የሚፈተንበት ግዜ መድረሱን ገሃድ አድርጎታል።

ይህ አጎዋ የተባለው አሰራር ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ  ተመጽዋች  አገራት የተለያዩ ምርቶችን ወደ አሜሪካ ገበያ ከቀረጥና ከታሪፍ ነጻ በሆነ ሁኔታ በማስገባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ስምምነት ነው ይባላል። ግን በዚህ የንግድ ስምምነት

ማን የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚሆን ለባለሞያዎች ለተወውና በተለይም አሜሪካኖች በዚህ እንደማያቆሙ በወያኔና በኦነግ በኩል ያልቻሉትን ኢትዮጵያን የማፈረስ ዓላማ ፣ በሌላ መንገድ ማንኛውንም ኃይላቸውን እንደሚጠቀሙ እሙን ነው። ይህ  ያለተገልጸለት ካለ መጸሃፍ እንደሚለው ፤

”ማየትስ ታያላችሁ ግን አታስታውሉም፤ መስማትስ ትሰማላችሁ ግን አታዳምጡም ”  የተባለው ለእኛ ነው።

ዘገባዎች እንደሚሉት ” ኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚ ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ እስከ ከ150 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅና የአልባሳት ምርቶችን ወደ አሜሪካ ስትልክ ቆይታለች።” ይላል።

ታዲያ መንግሥት በርግጥም ከኦነጋዊ እመለካከቱ ራሱን አጽድቶ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ቆሞ፤  በህዝብ ላይ እምነት ካሳደረና ፤ በውጩ ዓለምም የሚኖረውንም ዜጋ ” ሲበርደው እቅፍፉኝ ፤ ሲሞቀው ዘወር በሉ” ማለት ካቆመ፤  በአሜሪካ ከታገደችበት ከአጎዋን የምታግኘውን ገቢ በራሷ በዜጎቿ ትብብር  መተካት ይቻላል።

ይኽውም፤

1/ መንግሥት፣ የፋብሪካና የአምራች ባለቤቶች ግልጽ የሆነ በባለሞያዎች የተጠና መረሃ-ግብር መንደፍ፤ መረሃ -ግብሩ ከአጎዋን የታጣውን ገቢ በአገር ወስጥና በሌላው ዓለም እንዴት   ምርታቸውን መገባየት የሚችሉበትን መንገድ ማጥናት።

2/ የፋብሪካ አምራች ባለቤቶች ምርታቸውን ለዓለም ገብያ የሚያቀርቡበትና የሚሸጡበት   ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄድ የኦንሊን (online)  ድህረ-ገጽ ማዘጋጀት።

3/ መንግሥት ከውጭ የሚያስገበውን  የጨርቃ-ጨርቅና የቆዳ ምርት በአገር ውስጥ እንዲመረትና እንዲሸጥ ማደርግ::

4/ የኢትዮጵያ ህዝብም በተቻለ መጠን የአገር ምርትን እየገዛ እንዲጠቀምና  ከውጭ ከሚመጡ አልባሳትና የቆዳ ምርት ውጤቶች ራሱን መከላከል።

5/ በተለይም በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያያኖች ለራሳቸው፣  ለአገር ቤት ቤተስቦቻቸውና እንዲሁም በስጦታ መልክ   የአገር ውስጥ ምርትን መግዛትና በኦንላየን (online) ግብይቱ ላይ ቀዳሚ አስተዋአጾ ማድረግ፤ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ምርት በተላላቅ “ኦንላየን “ ድህረ-ገጾች ላይ እንዲገኙና እንዲሸጡ  የተቀናጀ ስራ መስራት።

ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑን ህዝቦች ህንዶች ናቸው፤ ህንዶች ክአሜሪካም ሆነ ከአውሮፓ ወደ አገራቸው ሲሄድ ቁራጭ ልብስና ቁሳቁስ ገዝተው አይሄዱም።የሚሄዱት ጥሬ  ዶላራቸውንና ኢሯቸውን ይዘው ነው። እነሱ የሚያደርጉት በአገራቸው በህንድ የሚመረተውን ለእንድ ዓመትና ለሁለት ዓመት የሚበቃቸውን ሸምተው፣ በወዳጆቻቸውም በስጦታ መልክ ገዝተው ወደ አሜሪካና አውሮፓ ይመለሳሉ። ባሉበት አገርም ሆነው ለቤተሰቦቻቸው ሆነ ያስፈልጋል የሚሉትን በዚያ በእገራቸው  (online) የሸምታሉ።ታዲያ እኛም ይህን መሰሉን ነገር ብናደርግ ለአገራችን ኢኮኖሚ የምናደርገው አስተዋአጾ ከአጎዋን የምናጠውን ገቢ ከመተካት በላይ የአገርቢቱን ምርት ያበረታተል።

ከላይ ያነሰዋቸው ሃሳቦች  ያጋራኝና ይህችን መጣጥፍ እንድጽፍ ያደረገኝ የባሮቲዮብ አዘጋጅ ባልደረባ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ የሃሳቡ ባለቤት እሱ መሆኑን መግለጽ እወዳለሁ። በተጨማሪም ማሳሰብ የምፈልገው  በአገራዊ ምጣኔ ሃብት ዘርፍ የተሰማራችሁ የአገር ውስጥም ሆናችሁ በውጭ አገር የምትኖሩር ባለሞያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ማስገንዘቢያ ብትሰጡበት ፣ እንዲሆም የሚመለከታችሁ  ክፍሎች ይህን  እንደ መጀምሪያ ሃሳብ ወስዳችሁ የተሻለና ገንቢ ስራ እንዲሰራ ብትተባበሩ  በአጎዋን  የምናጠውን መተከታ ብቻ ሳይሆን ራሳችን ለራሳችን መሆን እንደምንችል ዓለምን እናስተምርበታለን፤ እኛም እንማርበታለን።

 

አመሰግናለሁ!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

——–//——–ፊልጶስ

ታህሳስ / 2014

E-mail: [email protected]

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop