November 12, 2021
8 mins read

የአሜሪካና ምዕራባውያን ጫናና መፈንቅለ መንግሥት በግርማዊነታቸው መንግሥት ላይ!! – መስፍን ማሞ ተሰማ

000 9L93W9

የአሜሪካና ምዕራባውያን ጫናና መፈንቅለ መንግሥት በግርማዊነታቸው መንግሥት ላይ!! [መስፍን ማሞ ተሰማ]

ንጉሠ ነገሥቱ [ ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ ] ርዳታ ለመጠየቅ [ኢትዮጵያን በግብርናና በኢንዱስትሪ ለማልማት] የተለያዩ የአሜሪካንና የአውሮፓ ሀገሮችን ከግንቦት 10 ቀን እስከ ሐምሌ 28 ቀን1946 /ም ከሁለት ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ጎብኝተው ለትምህርትና መከላከያ ከሚውሉ ጥቃቅን ርዳታዎች በስተቀር [ ይህንን ነጥብ ልብ ማለት ያስፈልጋል ] ባዷቸውን ተመለሱ። ብዙም ሳይቆዩ ከመስከረም 25 ቀን 1947 /ም አስከ ህዳር 28 ቀን 1947 /ም በዘጠኝ የአውሮፓ ሀገሮች በመዘዋወር የልማት ገንዘብ ፍለጋ ከሁለት ወር በለሠይ ጉብኝት ቢያደርጉም አሁንም ለልማት የሚውል ርዳታ ሳያገኙ ቀሩ።

በእነዚህ ሁለት ጉዞዎች አሜሪካንና አውሮፓን ጎብኝተው ከምዕራቡ ዓለም ምንም ርዳታ በማጣታቸው ወደ ምሥራቅ ሀገሮች ሄደው ርዳታ ለማግኘት ከወዳጃቸው ከዩጎዝላቪያው መሪ ከፕሬዚዳንት ማርሻል ብሮንዝ ቲቶ ጋር ሲመክሩ ቆዩ። በነሐሴ ወር 1951 /ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስሊዎስ የፓትሪያርክ ሹመት ላይ ለመገኘት ወደ ግብፅ እንደሄዱ ሳይታሰብ በዚያው ጉዞ ድንገት ሶቪየት ኅብረት ሞስኮ መግባታቸው ተሰማ። 

ሞስኮ በገቡ በሶስተኛው ቀን ለልማት ሥራዎች ሁሉ የሚያስፈልግ እና በረጅም ጊዜ የሚከፈል አራት መቶ ሚሊዮን ሩብልስ አግኝተው ተመለሱ። [ ይህ የርዳታ ገንዘብ በዚህ ወቅት የምንዛሪ መጠን ከአምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማኒያ ሺህ ዪኤስ ዶላር በላይ ሲሆን ዶላሩ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ደግሞ ከሁለት መቶ ስልሳ ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ መሆኑን ልብ ይሏል ] ለልማት የሚያውሉትን መጠነ ሰፊ የርዳታ ገንዘብ አግኝተው ነሐሴ 18 ቀን 1951 /ም ኢትዮጵያ እንደተመለሱ በአራተኛው ቀን ነሐሴ 22 ቀን 1951 /ም ማታ እና በ14ኛው ቀን መስከረም 7 ቀን 1952 /ም ከቀኑ በስምንት ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለልማት ታጥቆ እንዲነሳ በሬዲዮ ሰፊ ንግግር አሰሙ።

ንጉሠ ነገሥቱ ከምዕራቡ ዓለም የተነፈጉትን ለልማት ሥራዎች() ለጭሰኞች መሬት እየሰጡ ለማስፈር  የሚውል የገንዘብ ርዳታ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ተቀናቃኝ ከነበረችው ከኮሚኒስቷ ሶቪየት ኅብረት በማግኘታቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣ በየዘርፉ በሚገኙ የልማት ሥራዎች ላይ ለሥራ ታጥቀው እንዲነሱ የሚቀሰቅስ ሰፊ ንግግር አደረጉ። ከዚህ ሁኔታ በሁዋላም ከምሥራቅ ሀገሮች ጋር የተደረገው ግንኙነት የምዕራቡን ኃያላን መንግሥታት ስላስቆጣቸው በየአቅጣጫው በኢትዮጵያ ላይ ጫናቸውን ያሳድሩ ጀመር። [እዚህ ላይ በኛ ዘመን ኢትዮጵያ በቀንደኛነት ከአሜሪካ ከእንግሊዝ ከፈረንሳይና ከተመድ የገጠማትን ጫናና ጣልቃ ገብነት ልብ ማለት ያስፈልጋል ] በተለይ በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ኮሎኔል ፒንክ የኦጋዴን ሶማሌዎችን በታላቋ ሶማሌ የህልም እንጀራ የመመገብ ፕሮፓጋንዳ ኦሮሞዎችንም እንዲጨምር ለማድረግ እንቅስቃሴውን አጠናከረ። በደጋው የሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ለሚኖሩ የኦሮሞ አርሶ አደሮች ኃይለ ሥላሴ ከኮሚኒስቷ ሶቪየት ኅብረት ያመጣው ብድር እናንተን ጭሰኞችን ባለዕዳ ለማድረግ አማራውን ለማበልፀግ እና ከቀድሞውም በበለጠ ለአማራው ባለርስቶች ተገዥ እንድትሆኑ ለማድረግ ነውና ተነሱየሚል ፕሮፓጋንዳ ይነዛ ጀመር። 

ፕሮፓጋንዳው በዚህ መልክ እየተነዛ እያለም ንጉሠ ነገሥቱ በዘመነ መንግሥታቸው ረጅምና ታሪካዊ የሆነውንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ልማት ታጥቆ እንዲነሣ በመድረግ ላይ ያተኮረ ንግግር በሬዲዮ አስተላለፉ። ንግግሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብሮ ከሰራ በጓዳው፣ ደጁ፣ ጓሮው፣ ሜዳው ሸለቆው ጋራውና ሸንተረሩየሚገኘው ሀብት ተዝቆ የማያልቅ መሆኑን በመጥቀስ በዋዛ ፈዛዛ ጊዜውን ሳያባክን በተለያዩ የልማት ዘርፎች ላይ ተሰማርቶ የሚቀሰቅስ ነበር። ያ የንጉሠ ነገሥቱ ንግግር ለዚያን ጊዜም ሆነ ለአሁኑ እና ለወደፊቱም ትውልድ ጭምር ኢትዮጰያውያን ከድኅነት ተላቀው በብልፅግና መኖር የሚችሉበትን መንገድ የሚያመላክት ነው። [በምዕራባውያን በተቀነባበረ  ከፍተኛ አሻጥሮችና ሁዋላም በ1953 /ም በአሜሪካውያን ድጋፍ በነግርማሜ ነዋይ የተሞከረውና በርካታ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት የልማት ውጥን ደጋፊ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በወንድማማቾቹ ግርማሜና ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ የተረሸኑበት መፈንቅለ መንግሥት ተደርጎ የልማት ውጥኑም እንዲከሽፍ ተደርጓል።]

* ሕይወቴ ለአገሬ ኢትየቀጵያና ለወገኖቼ ኢትዮጵያውያን ዕድገት የነበረኝ የሥራ ጥማት –  ቅፅ አንድ (1917 እስከ 1967 /) ደጃዝማች ወልደ ሰማዕት ገብረ ወልድ ገፅ ብዛት 636 * [ ከላይ ባቀረብኩት ፅሁፍ ውስጥ በቅንፍ የተቀመጡት ከመፅሀፉ በቀጥታ ቃል በቃል የተወሰዱ ሳይሆኑ ነገር ግን የመፅሀፉን መልዕክት የጠበቁ ጭማሮዎች ናቸው መማተ ]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop