November 9, 2021
15 mins read

ደማችን እንደተከዜ ወንዝ ይፈሳል እንጂ የሰማዕታት አደራ አይታጠፍም!

254301582 3263528027217840 5111975773710134758 nየትግራይ ወራሪ ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረዐማራ እና ፀረኢትዮጵያ ሆኖ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ የዐማራን ህዝብ እንደ ቀዳሚ ጠላት ፈርጆ መነሳቱ በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው፡፡ ጥላቻውንም በፖለቲካ ዓላማ ማብራሪያው ማኒፌስቶ ላይ በግልፅ ያሰፈረ፣ በሐሰት ትርክት ለበቀል የተነሳ የጥላቻ መንጋ ነው፡፡ ሴረኝነት፣ ተስፋፊና ተገንጣይነት የዚህ ድርጅት መገለጫ ባህሪያት ናቸው፡፡

የትግራይ ወራሪ ገዳይ ነው፣ አፋኝ ነው፣ አሳዳጅ ነው፣ የግዛት ተስፋፊ ነው፣… ስንል ለሁሉም ድርጅታዊ ክፋቱ ከወልቃይት ጠገዴ ዐማራ በላይ የተሻለ አስረጅ ምሳሌ የለም፡፡ በዐማራ ደምና ሀብት ታላቋን ትግራይ የመመስረት እቅዱን ለማሳካት ሲል፤ ዐማራን ገድሏል፤ አኮላሽቷል፤ ሀብቱን ዘርፏል፤ መሬቱንም ወርሯል፡፡ ለዚህ ምስክር ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያን መጥቀስ ይቻላል፡፡

አሁንም እየሆነ ያለው የዚሁ የጥፋት ታሪኩ አዙሪት አካል ነው፡፡ ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በመኾኒ፣ ቆቦ፣ አጋምሳ፣ ንፋስ መውጫ፣ ጭና፣ ውጫሌ፣ ኮምበልቻ፣… የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ወያኔ በዐማራ መቃብር ሀገረትግራይን የመፍጠር ምኞቱ አካል ነው፡፡

የትግራይ ወራሪ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ከተዘረጋ ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ታውጆ ተፈጻሚ ተደርጓል፡፡ ለዚህም የሰውና የጅምላ መቃብር ምስክሮችን አስረጅ ምሳሌ አድርገን እናቀርባለን፡፡ ከሁመራ ኤርፖርት ግቢ የጅምላ መቃብር እስከ ማይካድራው ጭፍጨፋ፤ እንዲሁም በየዋሻውና የምድር ውስጥ እስር ቤቶች በጅምላ ያለቀው ወገናችን ስፍር ቁጥር የለውም፡፡

ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ጀሮ የነፈገው የዘር ማጥፋት ወንጀል በወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ሕዝብ ላይ ተፈጽሟል፡፡ ምናልባትም በብዙሃኑ ኢትዮጵያውያንና በተወሰኑ የዓለማቀፉ ማህበረሰብ አባላት ዘንድ የተሰማው ጥቅምት 24/2013 .. የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ በኋላ ጥቅምት 30/2013 .. በማይካድራ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ብቻ ነው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ግን ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በርካታ ማይካድራዎችን አይቷል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል የተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አንዴ ተጀምረው በተወሰነ የጊዜ ገደብ የተጠናቀቁ ቢሆንም፣ ወልቃይት ጠገዴ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ግን በአይነትም ሆነ በድርጊት የተለየ ነው፡፡

ለሠላሳ ዓመታት ያለማቋራጥ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ነባሩን ሕዝብ የማጥፋት ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማራዎች በማንነታቸው ተገድለዋል፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወገኖቻችን ወደ መቀሌና ወዳልታወቁ ስፍራዎች ታፍነው ተወስደው በእስር ሲማቅቁ ኑረዋል፤ ብዙዎችም ባሉበት አልፈዋል፡፡

በሠላሳ ዓመቱ የወያኔ አፓርታይዳዊ ዘመን ከቆላ እስከ ደጋ አምስት መቶ ሺህ የሚደርስ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ከእርስቱ ተፈናቅሎ፣ ወደጎረቤት ሀገራትና ወደጎንደር አልፎም ወደ መሀል ሀገር እንዲሰደድ ተደርጓል፡፡

የትግራይ ወራሪ በግዛት ተስፋፊነቱ ተከዜን ሲሻገር በእብሪት መንፈስ የጥላቻ ንግግሩን እንዲህ ነበር ያንፀባረቀው፡– “ ካብ ወልቃይት ንህና ንደልዮ ደቂ አንስትዮምን መሬቶምን ጥራህ ዩ” (ትርጉም፡– “እኛ ከወልቃይት የምንፈልገው ሴቶቹን እና መሬቱ ነው”)። ይህን በትግረኛ ቋንቋ የሚነገር ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት የወጣ የጥላቻ ንግግር ገና ከመነሻው ሲናገረው ነበር፡፡ ይህ ንግግር አስቀድሞ የነበረ ከመሆኑ አኳያ፣ በሕግ ቋንቋ የዘር ማጥፋት የሀሳብ ክፍልን የሚያስረዳ የጥላቻ አባባል ነው፡፡ ከጥላቻ ማኒፌስቶው ጀምሮ መሰል የጥላቻ ንግግሮችን በማሳዳግ የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ ላለፉት ሦስት አስርት አመታት በስውርና በግልፅ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፅምበት ኑሯል። ማይካድራ አንዱ ማሳያ እንጂ፣ በዐማራ ላይ የተፈፀመ ብቸኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል አይደለም፡፡

የማይካድራን ጭፍጨፋ ስናስብ ጭፍጨፋው የፀረዐማራ ትርክት ውጤት ስለመሆኑ ልብ ልንለው ይገባል፡፡ ጥቅምት 30/2013 .ም በማይካድራ ከተማ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ በ1968 .ም ወያኔ ያዘጋጀው ዐማራን የማጥፋት ፍኖተ መርሁ አካል ነው።

የጅምላ ጭፍጨፋው የተፈፀመው ‹ሳምረ› የሚባለው የሰፋሪ ትግሬ ወጣቶች ቡድን ከትግራይ ወራሪ ልዩ ኃይል ፖሊስና ሚሊሻ ጋር በመሆን ነበር፡፡ አፈፃፀሙም በየጎዳናውና ከቤትቤት በመዘዋወር አስቀድመው የለዩዋቸን ወገኖቻችንን በከፍተኛ ግፍና ጭካኔ በዱላ በመደብደብ፣ በጩቤ በመውጋት፣ በገጀራና በፈራድ (ወይም ፋስ መጥረቢያ) በመምታት፣ በገመድ በማነቅና በጥይት ተኩሶ በመምታት በጅምላ ጨፍጭፈዋቸዋል፡፡ በዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራን መሬት በመውረር ሀብት ንብረት ያፈሩ የትግራይ ባለሃብቶች በአካል፣ በሀሳብና በገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ጥቅምት 30/2013 የጅምላ ጭፍጨፋው ከመጀመሩ ቀደም ብሎ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፃሚዎቹ የትግራይ ተወላጅ የሆኑና ዐማራ የሆኑትን ለመለየት መታወቂያ ካርድ እየተመለከቱ ማጣራት አድርገዋል። የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ሴቶች እና ህፃናት ጥቃቱ ከመጀመሩ በፊት አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸው ሊወጡ ችለዋል። ጭፍጨፋው ሲጀመር በልዩ ሁኔታ የዐማራ ብሔር ተወላጆች በብዛት በሚኖሩበት ልዩ ስሙ ‹‹ግንብ ሠፈር›› በሚባለው መንደር እስከወልቃይት ቦሌ ሠፈር ድረስ የሚገኙ ወገኖቻችን፣ ግፍና ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ተገድለዋል።

ጭፍጨፋው የተጀመረው ዓብይ ፀጋዬ የተባለን ዐማራ ከቤቱ ፊት ለፊት በጥይት በመግደል፣ ቤቱንና አስከሬኑን በእሳት በማቃጠል ነው። በሰማዕቱ ዓብይ ፀጋዬ የተጀመረው ጭፍጨፋ እስከ ለሊቱ 9:00 ድረስ በወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ የጅምላ ጭፍጨፋው ተጠናክሮ በመቀጠሉ 1,644 ዐማራዎች የጉዳት ሰለባ ሁነዋል። የተገደሉ1,563 ሲሆኑ፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ 81 ናቸው፡፡ በዚህ ጭፍጨፋ የተነሳ በርካታ ሕጻናት ያለ ወላጅ ቀርተዋል።

የማይካድራ የዘር ማጥፋት ድርጊት ፈፃሚዎች የዘር ማጥፋት ድርጊቱን የፈፅሙት በጀኔቫ ቃልኪዳን አንቀፅ ቁጥር 2 እና በሮም ድንጋጌ አንቀፅ ቁጥር 6 እና 7 ከዘር ማጥፋት ወንጀል ጥበቃ የሚደረግለት አንድ የሆነን የብሔር፣ የዘር… ቡድን የሆነውን (የወልቃይት ዐማራ) ዘር በመላ ወይም በከፊል ለማጥፋት በማሰብ ነው፡፡

በመሆኑም የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ፣ የማይካድራ የዘር ማጥፋት ወንጀል መርምሮ የወንጀል ድርጊት ፈፃሚዎቹ ላይ ክስ በመስረት ለማይካድራ ሰለባዎች አለም አቀፍ ፍትህ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

የፌደራል መንግሥት የወልቃይት ሕዝብ ለዘር ማጥፋት ወንጀል የተዳረገው የማንነት ጥያቄ በማንሳቱ ምክንያት ስለሆነ በሕግና በሥርዓት ላቀረበው ጥያቄው ምላሽ በመስጠት ህጋዊ መልክ እንዲያሲዝ በሰማዕታት ስም እንጠይቃለን፡፡

የወልቃይት ዐማራ ለደረሰበት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሥነልቦናዊ ጉዳት እና ለተፈፅመበት የዘር ማጥፋት ወንጀል በደረሰው ጉዳት እና በተፈፀመው ጥፋት ልክ ካሳ እንዲከፈል እንጠይቃለን፡፡

የትግራይ ወራሪ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአካባቢው ሀገራት የደህንነት ስጋት ስለመሆኑ በተጨባጭ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ እርሱ ከሚመራው መንጋ ጋር ከነ አስተሳሰቡ በሕዝባዊ ትግል ወደመቃብር እንዲወርድ፣ የህልውናና ሀገር የማዳን ተጋድሎው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችንን ጥሪ እናቀርባለን፡፡

በመጨረሻም

ማንነታችን ዐማራ፤ ድንበራችን ተከዜ ነው!› በሚል ለቃላቸው ታምነው ሰማዕት የሆኑ የወገኖቻችንን ዓላማ ከግብ ሳናደርስ የሚዘል ክንድም ሆነ ሸብረክ የሚል ጉልበት እንደማይኖረን በተግባር ማረጋገጣችንን እንቀጥላለን፡፡ ተከዜ በትላንት፣ በዛሬና በነገ ሰማዕታት የሚጸና የዐማራ ወሰን ነው!! የህልውና ትግላችን በዘላቂና አስተማማኝ ድል በመቋጨት የሰማዕታቱን አደራ እንወጣለን!!

እንደሀገር፤ ነፃ ሕዝብ እንደነበርነው ነፃ ሕዝብ ሁነን የጋራ ኢትዮጵያን በወንድማማችነት ስሜት እንገነባለን፡፡ ለመጭው ትውልድ ነፃነት ዛሬ ለመሰዋት ዝግጁ ነን፡፡ ይህ ትውልድ በወያኔ ቀንበር ስር በዳግም ባርነት ከሚያልፍ፣ በመስዋዕትነቱ የደም ባህር ፈጥሮ መጭውን ትውልድ ወደነፃነት ማሻገርን መርጧል፡፡ ለዚህም ነው ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋና ጎጃም የዐማራ አንገቱ አንድ ነው ብሎ በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ መንጋ ላይ የተነሳበት፡፡፡ በዚህ ሳያበቃ የወያኔን የክፋትና የወንጀል ጥግ የተረዱ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች ወያኔና የጥፋት አጋሮቹን ለማጥፋት በሰንደቅ ዓላማው ምለው ተነስተዋል፡፡ ወያኔ ትላንት ከወራሪው ዚያድባሬ ጎን ወግኖ ኢትዮጵያን እንደወጋው ሁሉ ዛሬም ይህንኑ የክህደትና የባንዳነት ታሪኩን በመድገም ላይ ነው፡፡ ይህም ሁኖ በኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ወደተመኘው ሲዖል ይላካል፡፡ የግፉዓን ኢትዮጵያውያን እንባም በአጠረ ግዜ እንደሚታበስ እምነት አለን፡፡ ለዚህ የሚከፈለውን ትርጉም ያለው መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን!!

ደማችን እንደተከዜ ወንዝ ይፈሳል እንጂ የሰማዕታት አደራ አይታጠፍም!

Amhara Prosperity Party /APP/ 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop