ይሄ ሰውዬ በርግጥም በሽተኛ ነው፤ “አትግደሉኝ” ማለት በየትኛው ሒሣብ ነው የሥልጣን መያዣ አቋራጭ መንገድ የሚሆነው? ይነጋል በላቸው

በርዕሴ መንዘላዘል አስቀድሜ ይቅርታ መጠየቅ አለብኝ፡፡ ለነገሩ በሀገራችን ያልተንዘላዘለ ነገር የለም፡፡ የአማራ መታረድ ራሱ 45 ዓመት ሆነውም አይደል? 17 ሲደመር 27 ሲደመር 3 ይሆናል 45፡፡

ብዙ እምለው የለኝም፡፡ አጭር ነው፡፡ የማተኩረውም “አቢይና አቢያዊነት ከኢትዮጵያ ምድር በቦሌም ይሁን በባሌ በአስቸኳይ እንዲጠፋ ካልተደረገ የኢትዮጵያ የመንግሥትነትም ሆነ አጠቃላይ የኅልውና ዕድሜ በሣምንታት የሚቆጠር ነው፡፡” በሚለው ወቅታዊ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ይሄ የበሻሻ ልጅ ግዴላችሁም ሊያዋርደን ነው፡፡ (ቢሆንም አንድዬ አለልን!)

አቢይ በሥልጣን ስካር ያበደና ብዙዎቻችን በውል በማናውቀው ሰይጣናዊ ሀገራችንን የማውደም በተለይም አማራን የማጥፋት ተልእኮ የተጠመደ መሆኑ በተለይ ሰሞኑን ግልጽ ሆኗል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ከተኙበትና ከተመረዙበት የአቢይ አፍዝ አደንግዝ እየወጡ እውነቱን መገንዘብ ጀምረዋል፡፡ የጊዜ ወርቅነት ድንቅነቱ እዚህ ላይ ነው፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ አማራው በየቦታውና የራስህ ነው ተብሎ በወያኔ ተቆራርሶ በተሰጠው ክልል ተብዬ መዋቅር ውስጥ ሳይቀር የሚደርስበትን ግፍና በደል ከረጂም ጊዜ በኋላም ቢሆን ተረድቶ በክልሉ ውስጥ ሰሞኑን ፍጹም ሰላማዊ የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግ ይህ በሽተኛ ሰውዬ “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” እንዲሉ ነውና ቀን ከሌት እያባተተ እንቅልፍ የሚነሣውን የሱን ሥልጣን የፈለገ ኃይል ሰልፉን የጠነሰሰው በማስመሰል የማታለል ዲስኩሩን ያላንዳች ሀፍረት ሲናገር አሁን ላይ ሰማሁት፡፡ በዚህ ሰውዬ መመራት እንዴቱን ያህል በሀፍረት እንደሚያሸማቅቅ ይበልጥ በዚህ ንግግሩ ስረዳ ኢትዮጵያዊነቴን አምርሬ ተጠየፍኩት፡፡ ግን የት ይኬዳል? ምንስ ሌላ አማራጭ አለ? ቀሪው ዓለምም በብዙ ጭንቆች ተወጥሯል – ወደዚያ እንኳን እንዳናማትር፡፡ በሻሻው ማለት የፈለገው ሕዝብ እንዲህ በነቂስ ወጥቶ “አትግደሉኝ” ያለበትን መሠረታዊ ምክንያት በመገልበጥ የሚታለል ያለ መስሎት የሰልፉን አቅጣጫ ለማስቀየስ ሲል ወደ አብን ለማላከክ ነው፡፡ አብን አማራን በመቀስቀስ እንደዚህ ያለ ሰልፍ ማስወጣት ቢችልማ ኖሮ እስካሁን አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ገብቶ ነበር፡፡ የሕዝቡ ቁጣ የገነፈለበትን ምክንያት እንኳንስ ምድር ገሃነመ እሳትና መንግሥተ ሰማይም ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ይህ በሽተኛ ሰውዬ የአማራን ሕዝብ መናቁን ለተደጋጋሚ ጊዜ ከመግለጹ ውጭ አዲስ ነገር አልተናገረም፡፡ ስለሆነም ይህ ሰልፍና ቀጣይ እንቅስቃሴዎች አማራው መታረድ በቃኝ የሚሉ እንጂ አቢይ እንደሚቃዥበት ማንም የፖለቲካ ፓርቲ በሤራም ይባል በሸርና በተንኮል የሚያቀነባብረው ሊሆን እንደማይችል በበኩሌ የክሬን መመስከር እችላለሁ፡፡ ይህ ሰልፍ እንዲያውም 45 ዓመታትን ዘግይቶ ከብዙ ሚሊዮን መስዋዕትነት በኋላ የመጣ ነው – በብዙ ጎኑ ሊተረጎም የሚችል ሚሊዮን፡፡ እነ “እሽ አትበሉኝ የሹም ዶሮዎች” በዚህ ሰልፍ መደንገጥ የለባቸውም፡፡ እኛ እንኳን እርጉዝ ሴቶቻችንን ሆድ ቀድደው ጽንሱን በፊታችን ሲበሉ፣ የሕጻናትንና የሴቶችን አንገት ሲቆርጡ … እያየን የነሱን ያህል አልተርበተበትንም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከገዛ ራሳችን ግዙፍና መሪር እውነታ እየሸሸን ሃይማኖትን መደበቂያ የማድረጉ አስቀያሚ እኛነታችን ይብቃን!

አማራው ማድረግ ያለበት፡-

  1. ሁሉም አማራ ይንቃ፡፡ ጠላት ወዳጁን ይለይ፡፡ ትግሉንም ሆነ አጠቃላይ እንቅስቃሴውን ብአዴንና የብልግና ፓርቲ ፊታውራሪ ኦህዲድ-ሸኔ እንዳይ(ጠ)ልፉት ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ ይህን ሕዝባዊ ትግል ለግል ፍላጎት ለመጠቀም የማያቆበቁብ የውስጥም ሆነ የውጭ ኃይል አይኖርምና ውሻ በቀደደው ጅብ እንዳይገባ የተማራችሁና ፓለቲካ የገባችሁ ሰዎች እንቅስቃሴውን በአግባቡና በጥበብ ምሩት፡፡ ይህ ትግል ከተጠለፈ የአማራው ስቃይ ከእስካሁኑ በከፋ ሁኔታ ለመቶዎች ዓመታት ይቀጥላል፡፡ ነገና ከነገ ወዲያ ጎንደር ከተማና ባሕር ዳር የኦነግ ባንዲራ ይውለበለቡባቸዋል፡፡
  2. በሰልፎችም ሆነ በማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ አባባሎችም ሆኑ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዳይወሰዱ ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ አለበለዚያ እንደነሱው መሆን ነው፡፡ ሕዝብን የሚሳደቡና ማንነትን የሚያንቋሽሹ የትግል ሥልቶች ምንጫቸው ቢታወቅም በስሜት እየተነዱ እነዚህን አላዋቂዎችና ዋልጌዎች ተከትሎ መንጎድ ትግሉን ይጎትተዋል ብቻ ሳይሆን ሊያደበዝዘውና ከናካቴውም ሊያከስመው ይችላልና ብዙ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡
  3. ንብረት ማውደምና መዝረፍ የትግሉ አካል እንዳይሆን ስውር ተላላኪዎችንና፣ ዜጎችን ወደዚህ ድርጊት የሚነዱ የብአዴንና የኦህዲድ ሠርጎ ገቦችን በዐይነ ቁራኛ እያዩ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይገባል፡፡ እንዲህ ሲባል ደግሞ ሰዎችን ቀጥቅጦ በመግደል እንደደናቁርቱ ዘቅዝቆ በመስቀል የነሱን አጋንንታዊ መንገድ በመከተል ሳይሆን በሽማግሌዎች እጅ እየገቡ እንዲመከሩና ከጀማው እንዲለዩ በማድረግ መሆን አለበት፡፡ አማራን ከሚያዋራዱ ድርጊቶች እንታቀብ፡፡ የደቦ ወይም የመንጋ ፍርድ እጅግ ጎጂ ነው፡፡ መልካም ነገር እንጂ መጥፎ ነገር አይኮረጅም፡፡
  4. በሽተኛው አቢይ የአእምሮ ታማሚ መሆኑን ከንግግሩም ከተግባሩም በመረዳት የሚዘላብደውን ቢቻል አለመስማት – ይህኛው ብዙም ባይመከርም – ከሰሙትም ንቆ መተው ይገባል እንጂ መናደድ አይኖርብንም፡፡ እርግጥ ነው – “አማራው የተሰለፈው ለሥልጣን የቋመጡ ቡድኖች አሰማርተውት ነው” ብሎ ሲዘባርቅ አለመናደድ አስቸጋሪ ነው፡፡ ቢሆንም የተጨነቀና በዘረኝነትና በቂም በቀል ጥላቻ ያበደ ብዙ ይለፈልፋልና እንደዚህ ዓይነት የሕይወት ትርጉም የጠፋባቸው አምባገኖች የማይቀባጥሩት ነገር እንደሌለ ተገንዝቦ የራስን ትግል ያዋጣል በሚባለው ማንኛውም ዓይነት መንገድ ሁሉ ማካሄድ ተገቢ ነው፡፡
  5. ኢትዮጵያ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መሆኗ ግልጽ ነው፡፡ ሁሉም ክልል በተለይ የኦሮሞው ለረጂም ጊዜ በመዘጋጀቱ ብዙ ጦር አለው፤ በዚያ ላይ አሁን የሀገሪቱ ሀብትና ገንዘብ ሁሉ በእጁ ነው፡፡ አማራው ግን እላዩ ላይ በጠላቶቹ ተመርጠው በተጫኑበት አማራ መሳይ አመራሮች ሆን ተብሎ በሁሉም ነገር እንዲጫጫ ተደርጓል፡፡ ይህም ሁኔታ ጠላቶቹን ሳያኩራራቸውና አማራን ለማጥቃት ይህን ጊዜ እንደምቹ አጋጣሚ እንዲቆጥሩ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ ስለዚህ ብዙ ጠላት ያለው አማራ አካሄዱን ጥበብ የተሞላበትና የተናበበ እንዲሆን ካላደረገ እጅጉን ይጎዳል፡፡ በጎጥና በሸጥ መከፋፈሉን በፍጥነት ማቆም አለበት፡፡ ወታደራዊ ሥልጠናውን በጎበዝ አለቃ እየተመራ ያካሂድ፡፡ ለቁርጥ ቀን ልብ እንጂ መሣሪያ ብቻውን ዋጋ የለውምና በድንጋይም፣ በቆመጥም፣ በዱላም፣ በናዳም፣ በሚጥሚጣና በርበሬም፣ በተገኘው መሣሪያም … በአንድ ልብና በአንድ መንፈስ ተረባርቦ ኅልውናውን ያስጠብቅ፡፡ በክልሉም ሆነ በፌዴራሉ መንግሥት በፍጹም መተማመን የለበትም፡፡ እነዚህ ተቋማት ራሳቸው አሁን እየተንገዳገዱ በመሆናቸው በራሳቸው ጊዜ በቅርቡ ሊጠፉና ሕዝቡንም ለውስጥና ለውጭ የቀን ጅቦች ሊያስረክቡ የሚችሉበት መጥፎ ዕድል ፊታችን ላይ በመደቀኑ አማራው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዚህ አስፈሪ የጨለማ ወቅት ዝግጁ እንዲሆን በተለይ ምሁራንና ሚዲያዎች የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ ሩዋንዳ በአንድ ቀን አልፈረሰችም፤ ሮምም፡፡ አማራውም ሆነ ሌላው ወገን የነጻነት ትግሉን በብስለት እንጂ በስሜትና በበቀል እንዳያካሂድ ይጠንቀቅ፡፡ በድጋሚ ልንገራችሁ – በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱ ያለ መሪና ያለ መከላከያ ለማንም ወንበዴ ክፍት ልትሆን እንደምትችል በመገመት ሁሉም ለዚህ አስፈሪ ጊዜ ዝግጁ ይሁን፡፡…
  6. አቢይ የሚባል ሰው ከእንግዲህ አይደለም ኢትዮጵያን ለምታክል ታላቅ ታሪካዊት ሀገር ይቅርና አንድ መንደርም መምራት የሚያስችለው የዕውቀትም ሆነ የሞራል ስብዕና እንደሌለው ከዚህ የአማራ ሕዝብ ንቀቱ ብቻ መረዳት ይቻላልና ከአሁን ወዲያ ኢትዮጵያም ሆነች የአማራ ክልል መሪ እንደሌላቸው መገንዘብ ይገባል፡፡ ከ30 ሚሊዮን የማይተናነስን ሕዝብ በዚህ መልክ የአንድ ተራ ፓርቲ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ ብሎ መፈረጅ ለዚያ አይደርስም እንጂ በነገዋ የነጻነት ቀን ፍርድ ቤት የሚያስገትር ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ መካሪ ያጣው ይህ አምባገነን በሽተኛ ገና ብዙ ጥፋቶችን ሳያመጣብን እግዚአብሔር እንዳመጣብን እንዲሰበስብልን በርትተን እንጸልይ፡፡ እውነቴን ነው – እንደዚህ ንግግሩ መቼም ተስፋ ቆርጬና ውስጤ ተነክቶ አያውቅም፡፡ ሰላም ለሀገራችን፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  የፖለቲካ ካሊፕሶ - "ከፕ/ት ግርማ ይልቅ ቴዲ አፍሮ አስመራ ቢሄድ ይሻል ነበር" - (ከተስፋዬ ገብረአብ)

 

3 Comments

  1. እንዲህ እሥከዶቃ ማሠሪያው ንገርልኝ እንጂ! ግሩም እይታ ነው። አማራ ለመነሣት ዳተኛ ነው እንጂ ከተነሳ ያሰበውን ሣያሣካ እንደማይመልሥ ጠላቶቹ ያውቃሉ፤ ለዚህም ነው አበሣውን የሚያበዙበት። ከውሥጡ ድረሥ ሰርገው ገብተው አሣሩን የሚያበሉት። አሁን ግን በቃኝ እያላቸው ነው። ግን ይህ ጸሓፊ እንደሚመክረው ትግሉን ዳር ለማድረሥ ብዙ ጥንቃቄ ያሻል። ጠላቶቹ ቀላል አይደሉም። በውሥጡ ገብተው እንዳይከፋፍሉትና ለአማራ የተቆረቆሩ መሥለው በአማራ ሥሞች አሥቀያሚ ነገሮችን በሶሻል ሚዲያ በመጻፍ በሥሙ እንዳይነግዱበት መጠንቀቅ ነው። ለሚወረወር አልባሌ መፈክርና አልባሌ ድርጊት ሆ እያሉ መከተል ጎጂ ነው። ማሥተዋልን ገንዘብ ማድረግ ለሁሉም ይበጃል።

  2. “ወረቀት በታኞች” ከባላባት ከበርቴዎች በተሰረቀ ላንድ ሮቨር መኪና እየተንቀሳቀሱ የአማራን ጄኖሳይድ ማነሳሻ ወረቀት በመዲናዋ ከበተኑ ሀምሳ አመታት ሊሆን ተቃርብዋል። የአማራ መታረዱ አርባ አምስት አመታት ቢሆንም የአማራ መታረድ ጥንሰሳው ሀምሳ አመታት ሊሆነው ነው።

  3. ኧረ በሽታ ብቻ? ይሄ ወንጭላ ንቀቱ እኮ ከልክ አለፈ! ይሄ አዛባ ፕ/ሚር ኢትዮጵያ ላይ እንዳላገጠ ማንም አላላገጥም። ኢትዮጵያን በትልቅ ላጲስ ይህው ሲያጠፋ ዓመቶች አስቆጠረ። አሁንም አራት ኪሎ ቁጭ ብሎ ስለአሻንጉሊት ዙፋኑ ነው የሚቀባጥረው፡፡ አስጊ ሁኔታ ላይ ነን፡፡ ብዙ የአባቶቻችን ጸሎት ያስፍልገናል ከኛ የበረቱ ስልሆነ፡፡
    ፕ/ሚሩ እስከአሁን 4 ዓመት ሙሉ ካሳየን ስቆቃ የባሰ ምንም አይመጥም ዛፍ ላይ ጅሌዎቹ ሰው ከሰቀሉ ብኋላ ነው የበቃን፡ ይቅረታ ይሄንን ስል UN በነገሩ ገብቶ ጊዚያዊ መንግስት የግድ ይላል፡፡ የባሰ እንጂ የተሻለ ነገር የሚያመልክት ምብም ፍንጭም የለም፡፡ ሰው በገዛ አግሩ እንዴት ይሰደዳል??? ይሄ አዛባ እንድዚህ እንደቀለድብን ሊቀጥል አይችልም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share