April 8, 2021
25 mins read

አንድነት፤ አንድነት ስንል አምሳ ዓመት ሊሆነን ነው- – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

-የብሄራዊ አንድነት መሰረቱ የዜጎች ደህንነት ነው–

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ክፍል ሁለት

እኛ ኢትዮጵያዊያን የምናሳፍር ፍጥረቶች ሆነናል። ድርጊቶቻችን ሁሉ አሳፋሪዎች መሆናቸውን አንካድ። በየቀኑ ዘውግንና እምነትን ለይቶ እልቂት ከሚካሄድባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ እየያዘች ነው። በክልል ደረጃ ሲገመገም፤ ከፍተኛ ቀውስ የተከሰተበት ክፍለ ሃገር ትግራይ ነው።

የኢትዮጵያ መአከላዊ/ፌደራላዊ መንግሥት የመጀመሪያ ሃላፊነት የንጹሃን ዜጎችን ደህንነት መታደግ ነው። አለያ ኢትዮጵያ መንግሥት አላት ብሎ ለመናገር አይቻልም። በውጭ ለኢትዮጵያ ሽንጣችን ገትረን ለምንከራከር ትውልደ ኢትዮጵያዊያያን ዋናው የሞራል ፈተና በየቀኑ የንጹሃንን ሞት እየሰሙ ሁኔታው ከአቅማችን በላይ መሆኑ ነው። እልቂቱ መቸ ነው የሚያቆመው?

ህወሃት/ትህነግ የቀሰቀሰውን አገራዊ ክህደት፤ ጦርነትና ይህ ጦርነት ያስከተለውን እጅግ የሚዘገንን ሰብአዊ ሁከት (Humanitarian Crisis) ሳጤነው እንዴት እዚህ አሳፋሪ ደረጃ ላይ ደረስን? የኢህአዴግ/ብልጽግና መሪዎችና ሃላፊዎች ራሳቸው የፈጠሩትን ስርአትና መዋቅር እንዴት ለመፍታት አልቻሉም? ማን እዚህ ላይ አደረሰን? ብየ ራሴን እጠይቃለሁ።

አስቡት፤ በትግራይ ክልል የተካሄደው ጦርነትና ያስከተለው እልቂት በኢትዮጵያ ታሪክ ጥቁር ቀለም ጥሎብናል። እልቂቱና ጥፋቱ፤ በንጹሃን አባቶች፤ እናቶች፤ እህቶች ወጣቶች ወዘተ ላይ ያስከተለው ግፍ እና በደል ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ትልቅ ሸክምና አሳፋሪ ሆኗል። በአጭሩ፤ ዘውጋዊነት፤ መንደርተኛነት፤ የእርስ በእርስ እልቂት የሚያስከትለውን አሉታዊ አደጋ በትግራይ ክልል እያየነው ነው። ትግራይን መልሶ ለማቋቋም ብዙ ዓመታትና ክፍተኛ የመዋእለንዋይ ፈሰስ ያስፈልጋል። ይህንን ለማሟላት ኢትዮጵያ አቅም የላትም። ከዚህ እልቂት ብንማር ኖሮ ንጹሃን በማንነታቸው በየቀኑ አይገደሉም ነበር።

ወንጀሉንና ክህደቱን፤ እርስ በእርስ መወነጃጀሉን ወዘተ በእያንዳዳችን ህሊና ብንመራመረው እንኳን እኛ የልጅ ልጆቻችን የሚረሱት ሆኖ አይታየኝም። የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (USAID) በቅርቡ ያካሄደው ጥናትና ምርምር በትግራይ ክልል በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ለህሊና የሚቀፍ መረጃ አቅርቦልናል። ጠባብ ብሄርተኛነት፤ የብሄር ጽንፈኛነት፤ ተረኛነት ወዘተ አደጋው ለልሂቃኑ አይደለም። ተራውን ሕዝብ እንደዚህ ላለ ሁከት ማጋለጡ ነው። በተጨማሪ፤ የእርስ በእርስ ግጭት አገርን ያፈርሳል። ከዚህ አሰቃቂና መደገም ከሌለበት ክስተት ለመማር ካልቻልን ከምን ልንማር እንችላለን?

ለወደፊቷ ኢትዮጵያ በጎ የምንመኝ ሰብአዊ ፍጥረቶች ሁሉ መረባረብ የሚኖርብን ላለፈው እልቂት ብቻ አይደለም። ካለፈው ተምረን ራሳችንና ሌሎች እንዲቀየሩ ማድረግ እና ሰብአዊ ርህራሄ (Human Empathy) እንዲኖራቸው መጎትጎት ነው። ሰላም፤ እርጋታ፤ ብሄራዊ አንድነት፤ ዘላቂና ፍትሃዊ ልማት ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ ወሳኝ ነው። ለዚህ መሰናክል የሆነው ምንድን ነበር? አሁንስ ምንና ማነው? ብለን በድፍረት መጠየቅ አለብን።

ኢትዮጵያ የአንድ ዘውግ አገር አይደለችም። ኢትዮጵያዊነት የአማራ ዘውግ አባት እሴት ብቻ አይደለም። ሊሆንም አይችልም። ኢትዮጵያ በዘላቂነት ተክብራ ትኑር! ታላቅ አገር ትሁን! ድህነትን እንቅረፍ! ኢትዮጵያን ታላቅና የበለጸገች አገር እናድርግ! እነዚህ ሁሉ መፈክሮች በምኞት ስኬታማ አይሆኑም። ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት በዘውጋዊነት እሴት አይደለም። አይቻልም። ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት በኢትዮጵያዊነት ወይንም በዜግነት መብት ስኬታማነትና በፍትሃዊ አስተዳደር ብቻ ነው። ዜግነት ስል እያንዳንዱንና ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የሚያስተናግድ ሁሉን አቀፍ ስርዓት ማለቴ ነው። የዜግነት መብት ብሄራዊ ውይንም አገራዊ ካልሆነ አይሰራም። ህወሓት የተሳሳተው ከዚህ ላይ ነው። ራሱንና እወክለዋለሁ የሚለውን ሕዝብ ከፍ አድርጎ ተመለከተ። ሌላውን አገለለ። በሚወክለው ሕዝብ ነገደበት፤ ዘረፈበት። ለውጥ ሲመጣ ወደ ዋሻው ገባ። የዘውጋዊ አጥር ሰለባ ሆኖ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለመታደግ አይቻልም። ሰብእነት አይኖርም።

የማንነት ጥያቄን መርህ የሚያስተጋቡ ልሂቃንና ምህራን እንደሚሉት ከሆነ ኢትዮጵያዊነት ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር አብረው አይሄዱም። ወደ አዙሪኝ ውስጥ የገቡ ይመስሉኛል። ራስን በራስ ማስተዳደር መብት ነው። ለልማት ወሳኝ ነው። ይህ መርህ የፌደራል ስርአት አካል ነው። የፌደራል መንግሥትን ሞዴል ስኬታማ ያደረጉ አገሮች፤ ለምሳሌ አሜሪካ፤ ካናዳ፤ ቤልጅየም፤ በአንድ በኩል ጠንካራ ብሄራዊ መንግሥትና አመራር አላቸው። በሌላ በኩል ደግሞ ክፍለ ሃገሮቻቸው የዜጎችን ተሳትፎ ያጠናክራሉ። ጥራትና ቅልጥፍና ያለው ማህበረሰባዊ አገልግሎት ይሰጣሉ። ለማእከላዊ መንግሥት ድርሻቸውን ይወጣሉ። የሕግ የበላይነትን ያስከብራሉ ወዘተ። አንዱን ዘውግ ወይንም የእምነት ተከታይ ከሌላው ለይተው ግፍና በደል እንዲደርስበት አይፈቅዱም።

የኢትዮጵያው ፌደራል ስርዓት ግን ይህንን መስፈርት አያሟላም። አጥር ነው ያልኩት ለዚህ ነው። አጥር በሚሆንበት ሁኔታ የዝግ ችሎት የተለመደ ይሆናል። በሌላው ላይ ማሴር የተለመደ ይሆናል። ችግሩ ከእኔ አይደለም፤ የችግሩ መነሻና መድረሻ ሌሎቹ የሚያደርጉት ነው የሚለው ብሂል የተለመደ ይሆናል። መመካከር፤ መወያየትና ችግሮችን በጋራ መፍታት አይታሰብም። “የኔን መንገድ ብቻ ተከተሉ” የሚል ስልት ለአብሮነት መሰናክል ነው።

ከላይ ያቀረብኩት መነሻና አቅጣጫ ወደ ዋናው ትንተናየ ያመራኛል።

የአማራው ዘውግ በምን ምክንያት ተከታታይ ግፍና በደል ይደርስበታል?

በተለየና በሚዘገንን ደረጃ በዘውጉና በእምነቱ ብቻ ተለይቶ የሚጨፈጨፈው አማራው ኢትዮጵያዊ ነው። ሌላው አይገደልም ማለቴ አይደለም። ወጥቶ መግባት ወይንም በህይወት መመለስ ብርቅ በሆነባት ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከተፈጥሯዊ ሞት ውጭ የሚሞቱት ወገኖቻችን ብዙ ናቸው። ህወሃት በፈጠረው ጦርነት ስንት ወገኖቻችን ሞተዋል? ቁጥሩን አናውቅም። አማራውን በሚመለክት ግን አንድ የማይካድ ልዩነት አለ። በተለይ ኦነጋዊያን፤ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ መሪዎችን ጭመሮ እና ህወሃታዊያን የማይቀበሉት የአማራ እልቂት ሁኔታ አለ። ትርክቱን ግን ግብጽ በዘዴና በረቂቅ ትጠቀምበታለች።

ይኼውም የአማራው ዘውግ አባላት በየትኛውም ቦታ እድል ተጠቅመው የሌላውን ዘውግና እምነት አባላት አይጨፈጭፉም። ለማነጻጸር፤ ህወሓትና ኦነጋዊያን በጋራ የሚጋሩት መርህ ኢላማ ያደረገው አማራውን ነው። አማራው ሲጨፈጨፍ ይህንን የሚዘገንን፤ በተከታታይና በተቀነባበረ ደረጃ የሚካሄድ ዘውግንና እምነትን ትኩረት ያደረገ እልቂት ሲካሄድ ሌላው ቀርቶ በስሙ አማራ ተጨፍጭፏል ብለው ለመናገር አይፈልጉም፤ እንዲያውም ይክዳሉ። ይኼ ብቻ አይደለም።

ራሱ የፌደራሉን መንግሥት የሚመሩት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የክህደቱና የእልቂቱ አካል ሆነዋል። የአማራው እልቂት በተከታታይ ሲካሄድ፤ አንድ ጠንካራ መግለጫ ማውጣት ለምን አልተቻለም? የአማራው ሕዝብ ወገናችን ነው፡፤ የሚጨፈጨፉት ህጻናት ልጆቻችን ናቸው። በአማራው ወገናችን ላይ የሚካሄደው እልቂት ያሳፍረናል፤ ያሳዝነናል፤ ተቀባይነት የለውም፤ አገራችንን ያጠፋታል፤ እንታገለዋለን ወዘተ ለማለት የማይቻልበት ምስጢር ምንድን ነው? በሰሜን ሸዋ በተካሄድ እልቂት እናትና አባት ከዘጠኝ ወጣት ልጆቻቸው ተነጠለዋል/ተገድለዋል። እነዚህን ህጻናት ማን ያሳድጋቸዋል?

ስንት አማራ ሲሞት ነው ቀይ መስመር ተሻግራችኋል የምንለው? ስንት ሲጨፈጨፍ ነው የአማራ እልቂት (Genocide)  ተካሂዷል ተብሎ የሚነገረው? ብሄራዊ አቋም ለመውሰድ ያልተቻለበት መሰረታዊ ምክንያት ማን ይቀየማል ተብሎና ተፈርቶ ነው?

በኢትዮጵያ በዘውግና በእምነት እየለዩ መጨፍጨፍ የተለመደ ከሆነ ቆይቷል። ፕሮፈሰር አስራት ሲታገሉና ሲሟገቱ  የነበረው ለምንድ ነው? ደርግ የፖለቲካ ሥልጣን እልቂት አካሄደ። ከዚያ በኋላ ግን እልቂት የተለመደና ተራ ነገር ሆነ። እኔ በአሁኑ ወቅት፤ ህወሓት በመደምሰስ ላይ ነው ሲባል ሁኔታው ይሻሻላል የሚል ተስፋ ነበረኝ። በተለይ፤ ማይካድራ የተካኔደው የአማራ የግፍ እልቂት ያስተምረን ይሆን ወይ? የሚል ጥያቄ በህሊናየ አንሰላስል/አስብ ነበር። ግን ማነህ ባለሳምንት? የሚለው ቀጥሏል። እልቂቱ ያማል፤ ይዘገንናል፤ ያሳፍራል። እያንዳንዳችንን ከእንስሳዎች በታች ዝቅ አድርጎናል።

የፈረንጅ የመስሪያ ቤትና ሌላ ወዳጅና ጓደኛ ያለን ግለሰቦች “በአገራችሁ ለምንድን ነው በተከታታይ ግድያ፤ ጭካኔ፤ የዘውግና የእምነት ጭፍጨፋና እልቂት ይካሄዳል ተብሎ በተከታታይ የሚወራው? እናነተ ኢትዮጵያዊያን አገራችን ጥንታዊና በነጻነቷ የኮራች ናት ብላችሁ የምታወሩት ምን ይዛችሁ ነው?” ብለው ሲጠይቁን ምን አይነት መልስ ለመስጠት እንችላለን። “ለመሆኑ አገራችሁ መንግሥት አላት?” ሲሉንስ። አይ፤ ምንም አይደለም፤ የሚጨፈጨፉት እኮ ዛሬ አማራዎች ናቸው፤ ትላንት ትግሬዎች ናቸው፤ ከጥቂት አመታት በፊት ደግሞ ኦሮሞዎችና ሶማሌዎች ናቸው፤ ከዚያ ቀደም ሲል ደግሞ አኟኮች ናቸው ወዘተ ልንል ነው?

የፈለገውን መለያ ብንሰጣቸው የሚጨፈጨፉት ወገኖቻችን ሰብአዊ ፍጥረት መሆናቸውን እንዴት ለመካድ እንችላለን። ህወሓትን ያስወገደው ለውጥ ሲካሄድ ጎንደሬው “የኦሮሞ ደም ደማችን ነው” ማለቱ እንዴትና ለምን ተረሳ? የአማራው ሕዝብ ደምና ህይወት የለውም ለማለት የሚያስችል ምን አይነት መረጃ አለ? አማራው ከሌላው ዘውግ የተለየ የተሻለ ኑሮ ይኖራል? ሌላውን ይበዘብዛል? ሌላውን ይጨቁናል? ምንም አይነት አወንታዊ መረጃ የለም። የሚጨፈጨፈው የአማራ ሕዝብ ጥሮና ግሮ፤ ሌላውን አክብሮ የሚኖር አገር ወዳድና የአገር መከታ ሕዝብ መሆኑ በመረጃ የተደገፈ ነው።

በአማራው ላይ “የበላይነትና የጥላቻ” ትርክት የጸነሰው ማነው?

በአማራው ዘውግ ላይ የተመሰረተው ጥላቻና ትርክት በህወሃታዊያንና በኦነጋዊያን የተፈጠረ አለመሆኑን አውቃለሁ። የራሷ ጥንታዊ ታሪክ፤ ስልጣኔና የመንግሥት ስርዓት የነበራትን ኢትዮጵያን እንደ ሌላው አፍሪካ ሙሉ በሙሉ እንደ ሃረር ሰንጋ ሊቀራመቷት  የፈለጉት የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ሲዶልቱ የመስፋፋት ማነቆው ማነው? ብለው ጠይቀው ነበር። የበርሊን የአፍሪካ ቅርምት ጉባኤ ተካሂዶ በ 1930ዎቹ ዓመታት የጦፈ ውይይትና ድርድር ሲደረግ ናዚዎችና ፋሽስቶች የአውሮፓንና የመላውን ዓለም የወደፊት እድል በሚመለከት በሚያርበረብድ ደረጃ አይናቸውን ከኢትዮጵያ ላይ አደረጉ።

የደመደሙት ምን ብለው ነው? በነጭ የአውሮፓ አገሮች ለሚመራው የቅኝ አገዛዝ ተስፋፊነትና የበላይነት ስርዓት ከፍተኛዋ ማነቆ ወይንም መሰናክል ኢትዮጵያ ናት የሚል ነበር። ፍልስፍናውንና ትርክቱን ለነሱ ያቀረበው የአውስትርያ ተወላጅ የነበረው ናዚስት/ፋሺስት ፈላስፋ፤ ደራሲና በአዲስ አበባ ከተማ ዲፕሎማት ሆኖ ይሰልል የነበረው ባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ (Baron Roman Prochazka) ነው። ይህ ሰላይ በ 1935 የጻፈው መጽሃፍ በጣሊንኛ ሲተረጎም “ABISSINIA PERICOLO NERO” ወይንም “ሃበሻ፤ የጥቁሯ አደጋ” የሚል ነበር። ይህ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች የተተረጎመ መጽሃፍ የሚታወቀው Abyssinia: the powder barrel (ሃበሻ፤ የባሩድ በርሚል” በሚል መለያ ነው።

ኢትዮጵያ ወይንም አቢሲኒያ ተብላ የምትታወቀው የጣሊን ሰለባ የሆነችው አገራችን “የባሩድ በርሚል” ናት ተብላ ስትሰየም፤ የማያቆምና በልዩ ልዩ ወቅቶችና ሁኔታዎች ሊፈነዳ በሚችል የውስጥ ቦምብ የተበከለች አገር መሆኗ ነው። ህወሓት ይህንን የውስጥ ችግር ሙሉ በሙሉ ተጠቅሞበታል፤ የውጭና የአገር ውስጥ ወዳጆች ገዝቶበታል፤ ተተኪዎች አፍርቶበታል። ከውጭ ጠላቶች መካከል ግብጽን፤ ከውስጥ ተተኪዎች መካከል በብልጽግና ስም ተደራጅቶ የበላይነቱን የያዘውን የኦነግን ብልጽግና ፓርቲን ይመለከታል።

ፕርቻስካ መጽሃፉን በጻፈው በአመቱ ጣልያን ኢትዮጵያን ወረረች። ፕርቻዝካ ተክሎብን የሄደውንና መፍትሄ ያልተገኘለትን አውዳሚ የዘውጋዊነት ቅርስ መንስኤዎች በሚገባ ለማስተዋልና የትርክቱን ወራ ለመታገል፤ የሚከተሉትን ማስታወስ ያስፈልጋል።

አጼ ኃይለ ሥላሴ የሊግ ኦፍ ናሽንስን ተማጽመነው ልክ የአሁኑ የተባበሩት መንግሥታት እንደሚያደርገው የኢትዮጵያን ሉዐላዊ መብት እና ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር አልተቻለም ነበር:: ሁለቱንም በበላይነት የሚያዟቸው የምእራብ መንግሥታት መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም።

ደራሲው አጼ ኃይለ ሥላሴ ከጃፓን ጋር “ያላቸው ግንኙነት” ለነጭዎች የበላይነት አስጊ ሆኗል፤ ኢትዮጵያ ወይንም “አቢሲንያ” በነጭዎች ቀንበር ስር ካልገባች እነዚህ “ሃበሻዎች” ከነጭዎች “በላይ እንጅ በታች አይደለንም” የሚል እምነት ስለሚከተሉ ለቅኝ ገዢዎች የበላይነት ነቀርሳ ናቸው። መወገድ አለባቸው። ኢትዮጵያ የነጭዎች ቅኝ ግዛት መሆን አለባት የሚል አቋም ወስዶ ቀሰቀሰ። የካቶሊክና የፕሮቴስታንት እምነት የበላዮችም ይህንን ትርክት ሙሉ በሙሉ ተቀበሉ፤ አጋር ሆኑ። ፕሮቻዝካ የነጭዎችን ታላቅነትና የበላይነት ፉርሽ የሚል ኃይል ሊኖር አይችልም ያለውን የእንግሊዝኛ ትርጉም ላቅርርብ። “The prevalence of this contemptuous invective is characteristic of the mentality and attitude of the natives who imagine themselves to be infinitely superior to the white race.”

ትርክቱ ሰፊ ተቀባይነትና ተከታዮች እንዲኖሩት በማሰብ፤ ኢትዮጵያን በአገር ውስጥ የእርስ በእርስ ግጭቶች እንድትበከል፤ ሰላምን እርጋታ እንዳይኖርባት፤ ጥገኛ፤ ድሃና ኋላ ቀር ሆና እንድትቆይ በማጤን የነገድ (የዘውግ) ልዩነቶች፤ የማንነት ጥያቄዎች እንዲያብቡ፤ “ራስን በራስ የማስተዳደር መብት መከበር አለበት (The right to self-determination,” including cessation) ጥልቀትና ስፋት እንዲኖራቸው ምክንያቶችን አቀረበ።

አውሮፓዊያን አፍሪካን ተቀራምተው እንዴት “ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ይከበር” ለማለት ደፈረ? ምክንያቱም፤ ጥቁሮች ራሳቸውን ለማስተዳደር ስለማይችሉ እኛ በበላይነት እየመራን እናሰለጥናቸዋለን ማለቱ ነው። ምክንያታዊ ለማድርግ፤ የዘውግ ልሂቃን እንዲያብቡና እንዲጋሩት ለማድረግ እንደሚከተለው አቀረበው።

“The numerous peoples and tribes who inhabit the territory of the Ethiopian state, and which differ in race, language, culture and religion from the ruling minority of the Abyssinians proper, would long ago have thrown off the Abyssinian yoke if they had been given the right of self-determination. Instead, they are being forcibly kept cut off from European influences and from the advantages that progressive colonization could confer upon the country. The final aim of (Abyssinian) policy of antagonism to the white race, in co-operation with Japan, is nothing less than to act as the champions of all the colored peoples of Africa…ኢትዮጵያ በዘር፤ በቋንቋ፤ በባህል፤ በኃይማኖት የተለያየች አገር ናት፤ የምትገዛው በአናሳው ዘውግ በሃበሻው ነው” ብሏል። ይህ አናሳ ዘውግ ማነው?

መልሱ አማራ (ሃበሻ) የሚባለው ሕዝብ ነው። ይህንን የተሳሳተና አደገኛ ትርክት ውርስና ቅርስ አድርገው የሚመሩበት የአገር ውስጥና የውጭ ኃይሎች መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብና ኢትዮጵያን ለአደጋ አጋልጠዋታል።

ክፍል ሶስትን ይመልከቱ

April 8, 2021

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop

Don't Miss

GaGrnkDXQAAq4mF 1

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም
aklog birara 1

ተስፋ የሰጠውና እመርታዊ የሆነው የአማራ ፋኖ እንቅስቃሴ ምን መሰናክል ገጠመው? እኛስ በጋራ ምን ማድረግ አለብን? 

አክሎግ ቢራራ (ዶር)  የአማራ ፋኖ ለአማራ ሕዝብ ህልውና እንቅስቃሴና ትግል