June 18, 2020
27 mins read

“በዴሞክራሲ ሥም ኢትዮጵያዊነትን  ለማጥፋት ና ባንዳነትን ለመገንባት የሚጥሩትን ኢትዮጵያዊው በቸልታ አያያቸውም። ” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“አሥከአለፉት የቅርብ ሩቅ ዘመናት ድረሥ እንደፖለቲካውና  እንደኢኮኖሚው ሁሉ፣ባህሉንም አሥገድዶ  ነበር ፣አሸናፊ እንደ አብሾ የሚግተው።ለምሳሌ ግራኝ ማሐመድ ክርሥቲያኑን በሰይፍ እየቆረጠ እንዳአሰለመ ሁሉ፣ዓፄ ዮሐንሥም እሥላሙን  በሰይፍ እየቆረጡ ነበር፣ክርሥቲያን ያደረጉት።

‘ልበ አንበሣ ‘ በመባል የሚታወቀው፣የእንግሊዝ ንጉሥ ‘ሪቻርድም’ በሠይፍ ነበር፣የአውሮጳን አህዛብ ፣በግድ የክርሥትናን ባህል የጋተው።

ማርኪሲስቶችም ከሰይፍ አልፈው  ፣በወህኒና በጥየት ነው፣ባህላቸውን ለህዝብ ያጠጡት።

የዛሬ ዘመኑ ጥምቀት፣ግን፣በሰይፍ ፋንታ፣ብዙ ካሮትና፣ትንሽ መራራ ኩርኩም፣ብዙ  ከረሜላና ትንሽ መራራ ቁንጥጫ ይበዛበታል።…

በየትኛውም የትግል መሥመር፣ከውሥጥም ሆነ ከውጪ፣በኢትዮጵያ ባህል ጥቃት የሚሰነዘረውም ለአንድ ዓላማ ብቻ ነው።በዴሞክራሲ ሥም ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋትና ባንዳነትን ለመገንባት።”

የዓለም ሎሬት፣ባለቅኔ፣የቋንቋ ተመራማሪ፣ ደራሲ እና ፀሐፊ ተውኔት  ፣ክቡር ፀጋዬ ገ/መድህን ቀዌሣ

ጦቢያ ቅፅ 5 ቁጥር 11(1990 ዓ/ም)

ሰውኛ ሃሳብ መልካም ነው።ሰው ሰለ ሌላው ሰው ማውራት ያለበት ሰው መሆኑን ተገንዝቦ ከሆነ የሰውኛ ሃሳብ ደሃ አይሆንም።የሰውኛ ሃሳብ ደሃ ላለመሆን ሰውነትን ለሥጋ ሳያደሉ በእውነትና ሥለእውነት  መገንዘብ  ፣ተገንዝቦም ፣ሰው መሆንን ሳይቀባቡና ቆዳና ቋንቋን ሳያዋድዱ መቀበልን ይጠይቃል። ሰው ሆኖ፣እንደሰውና ለሰው ሲሉ መኖርንም የምንማረው ከነዚህ ሰዎች ነው። ።(ከነ ፀጋዬ ገ/መድህን ቀዌሣ ና ከመሣሠሉት)

በዛሬ ጊዜ ሥንቶቻችን ነን፣ሰለሰው ብለን የምንኖረው?ሥንቶቻችን ነን ከራሥ በላይ ነፋሥ የማንለው?ሥንቶቻችን ነን፣በራሳቸው እግር የቆሙትን ፣በተደገፍነው ከዘራ ምክን ያት የምንጠላቸው እና እንዲወድቁ ተባብረን የምንገፈትራቸው።ያውም በእያጓዊ ሴራ በጭብል ተሸፍነን።

ብዙዎቻችን  ያለ ከዘራ እና ጭምብል ታይተን አናቅም ።ያለ ጭምብል ብንታይ ኖሮ ይህቺ ዓለም እንዲህ በሣንካ እና በሰቆቃ አትሞላም ነበር።በጭብላችን ተሸሽገን  በራሳቸው ዕውቀት እና ችሎታ የሚተማመኑትን፣ጭንብል  አልባ ሰዎችን ተባብረን እናወድማቸዋለን።

በማንኛውም የመንግሥት ተቋም  ውሥጥ በጭምብላቸው ምክንያት፣ለተራው ሠራተኛ ፈፅሞ ግልፅ ያልሆኑ እግር አልባዎች፣የሐሰት ወሬ በመፈብረክ ፣የሌቦች፣እና የዘራፊዎ ች  ድርጊት እንዳይጋለጥ ሌት ተቀን የሚሰሩ፣ ሰው መሳይ በሸንጎዎች፣  አውዳሚዎች አሉ። እነዚህ አውዳሚ፣ ጭምብላሞች ፣ባለ ጭራዎች ናቸው።ከሰው ተፈጥሮ  ውጪ የማይታይ  ጭራ አብቅለው ያንን ጭራ በመቁላት ሀገርን ሀብት ለዘራፊዎች በማቀበል፣ሀገረን አውዳሚ በሆነ  ዘረፋ ውሥጥ፣  ተባባሪ የሚሆኑ።

ሁሌም ሀገርን ሲያከሥሩ የምናያቸው እነዚህ እግር አልባ የዘረፋ ተባባሪዎች ናቸው  ።እነዚህ ህሊና ቢሶች ናቸው በማንኪያ የሚሰጣቸውን  የሙሥና ምግባቸውን ብቻ በማየት ፣ የበላዮቻቸው  በጭልፋ ሲዝቁ፣እግረ ቢሥ በመሆን ፣ህጋዊ ሽፋን በመሥጠት ለዘራፊዎች በሽፋንነት  የሚያገለግሉ ። የሚልከሰከሱ ።የሚለቃቅሙ።…

ይህቺ ሀገር በዴሞክራሲ ሥም፣ያውም አብዮት ተጨምሮበት በእግረ ቢሶች አጋዥነት ፤ በለቃቃሚዎች እርዳታ፣እድገቷ ቁልቁሉ እንዲሆን ዛሬም፣ከሆዳቸውና ከግል ምቾታቸው በሥተቀር ፣ ለህዝብና ለታሪክ ደንታ በሌላቸው የገመድ ጉተታወ  ተጠናክሮ ቀጥሏል።በአንድ በኩል ሀግርን ለማግዘፍ አንድ ወገን ሲፍጨረጨር፣ሌላው ሀገርን ይቦጠቡጣል። ለቃቃሚውም ለትራፊው ሲል ከዘራፊው ጎን ቆሞ ፣ሽንጡን ገትሮ ይከራከርለታል። ይህቺ ሀገር ለሃጫቸውን በጭምብል በሸፈኑ ተላላኪ ሹመኞች፣ካድሬዎችና አክ-ቲ-ቪ -ሥቶች  ሰላሞ እየተናጋ ነው።

ይህ የአክ-ቲ-ቪ-ሥቶች ሠላምን የማደፍረሥና ሀገርን የማፍረስ ተግባር እንዲቀጥልም፣ በአንዳንድ የመንግሥት ተቋማት ልጨኞችና እውቀት የዘለቃቸው ፣በራሳቸው ችሎታ የሚተማመኑ እየተገፉ ፣የዝርፍያ ተባባሪዎች እየነገሱ ፣ተጨማሪ የዝርፊያ በር እየተከፈተላቸው እንደሆነ ይሥተዋላል።ይህ የቁልቁለት ጉዞ   ሊቆም ይገባል እላለሁ ።

ይህን የቁልቁለት ጉዞ ለማሥቆም የሚፍጨረጨሩ ቢኖሩም በተቀነባበረ ዘዴ ሲጠሉ እና ከሥራቸው ሲገለሉ ይሥተዋላል። የሚጠሉት እና የሚገለሉትም  የድርጅቱን ዋና ድክመት አጉልተው በማሳየታቸው እና ለሌብነት ፣ባለመተባበራቸው ነው።

በአንዳንድ የመንግሥት  ድርጅቶች እኮ ፣አቅሙ ቢኖራቸው፣ ለጫት ሱሥ ሲሉ ድርጅትን  ከመሸጥ የማይመለሱ ናቸው በከፍተኛ ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ።እነዚህ ፣በምርቃና ምላሥ ፕሮፖጋንዳቸው የማይቻል፣ እና በሐሰተኛ ሪፖርት አፃፃፍ የተካኑ ሰዎች፣ በነቀዘ ተቋም ውሥጥ እሥከሚኒሥቴር መሥሪያቤት ድረሥ ተሠሚነት ቢኖራቸው አይገርመኝም።    ይሁን እንጂ በተጨባጭ ለሌብነት ያልተመቻመቸ የበታች ሠራተኛ ጠላት ከመሆና ቸውም በላይ አንድን ተቋም እና የማምረቻ ድርጅት ቀባሪዎች መሆናቸው የሚያከራክር አይሆንም።

በውሳኔ ሰጪነት ላይ እነዚህን ነቀዞች በማሥቀመጥ አትራፊ መሆን የሚችል ምንም አይነት ተቋም አይኖርም። ከዚህ አጠቃላይ የሀገር ችግር አንፃርደግሞ፣ መንግሥትለራሱ ተቋማት ሁሉ፣ ልዩ የሠራ ቅጥር ውልና  መመሪያ እንዲሁም አዲሥ የዲሥፕሊን ህግ ማውጣት  የሚያሥፈልገው ይመሥለኛል።ከዚህ አንፃር ሀገራችን ገና ብዙ ህዝብና ሀገር የሚጠቀሙበት  ለውጥ እንደሚያሥ ፈልጋትም አሥባለሁ።

“ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ብልፅግናዋን ባልተራዘመ ጋዜ፣ እውን ለማድረግ የሚያሥችል፣ ለውጥ ያሥፈልጋታል።” ሥል፣ለውጡ   ፈርጀ ብዙ መሆኑ ቢታወቅም ፣ በቅድሚያ መንግሥት ተቋማቱን በጥልቀት በመፈተሽ፣ተገቢውን ማሥተካከያ በማድረግ፣የአሠራር ዝርክርክነትን በማሶገድ፣ በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ ተቋም መገንባት ይጠበቅ በታል።የሰው ኃይል አደረጃጀቱም ተቋማቱን በሚያስወድሥ መልኩ  በአጭር ጊዜ የሚገነባበትን ዘዴ መቀየሥ ይጠበቅበታል።

“ለመርህ፣ለጥብቅ ሥነ -ሥርዓት ፣ተገዢ የሆኑ ፣በዕውቀታቸውና በቹሎታቸው የሚተማመኑ  ፣ ለሆድ እና በሆድ የማይገዙ፣ለመብላት የማይኖሩ ፣ህሊና ያላቸው በሌሎች ድጋፍ የማይንቀሳቀሱ በራሳቸው እግር የሚራመዱ፣ የእንሥሣ  ባህሪ ና  ምግባር የሌላቸው ፣እንዲሁም ሰው መሆናቸውን በውል የተገነዘቡ ፣በእያንዳንዱ ክልል የመንግሥት ተቋም ውሥጥ በኃላፊነት እሥካልተቀመጡ እና ተቋማቱን በራሳቸው ባህሪ በአዲሥ መልክ እሥካልገነቡ ጊዜ ድረሥ ፣በዚች ሀገር ላይ በሰዎች እኩልነት እና እኩል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ እውነተኛ ሀገራዊ ዴሞክራሲ ና ፍትህ አይነግሥም።ለገርም አታድግም። “ብዬም አምናለሁ። ።

የጅብ ቡድኖች እዛና እዚህ ተቋቁመው ሁልጋዜ እንብላ የሚሉ ከሆነ እንዴት ሀገር ልታድግ ትችላለች?ሀገር የምታድገው የሰው ጅቦች የማይመሯት ሀገር ሥትሆን ብቻና ብቻ ነው።ሀገር የምትለማው ሰው መሆናቸውን የተገነዘቡ ና ሰውን በጎ ነገር ለማሥተማር የሚችል የግል ሥብእና ያላቸው፣ ሌብነትን የሚጠየፉ፣ለህዝብ ብልፅግና እና ለመልካም ሥማቸው የሚጨነቁ፣ በብቃታቸው የማይታሙ፣በሰው እኩልነት የሚያምኑ ግለሰቦች፣ በመንግሥት ዋና ፣ዋና ተቋማት ኃላፊ ሲሆኑ ብቻ ነው።

ሰው ለጅ በሙሉ፣ እኩል እንደሆነ፤ሰው ገና ሲፈጠር ፣በአፈጣጠሩ፣ከአይኑ ብሌን ፣ከቆዳው ቀለም እና ከእጁ አሻራ በሥተቀር  አንዱ ከአንዱ ፣በአካሉ አፈጣጠር እንደማይለይ  ሣይንሥ ያረጋግጣል ።ሰው ገና ሲፈጠር ፣ያለቋንቋ፣ያለባህል ፣የለዘር፣ያለሀገር፣ያለመንግሥት መሆኑም ይታወቃል።

ዛሬ የምናሥተውለው የሰው ሥርዓት ፣ባህል ና ኃይማኖት ሁሉ፣ ሰው ከተፈጠረ በኋላ ነው የተፈጠረው።ኢትዮጵያዊያንም የጠቅላላችን ጎሣዎች ድምር የሆነ  ቱባ ባህል፣ወግ ሥርዓት ወዘተ።አለን። ለዚህም ነው ፣ የባለቅኔው የታላቁ የዓለም ሎሬት፣የፀጋዬ ገ/መድህን ቀዌሳን ምጡቅ  ምልከታን፣የፅሑፌ  መግቢያ ያደረኩት።

በእውነት ላይ የተመሠረተ፣ ከሌብነት እና ከከንቱነት የራቀ፣ በኢትዮጵያዊያን አኩሪ ባህል ላይ የሚገነባ አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለሀገራችን እንደሚያሥፈልጋት ፣ከእንቅልፉ የነቃው ይህ ተውልድ ያምናል።

ገና ያልባነነ ጥቂት ተውልድ ቢኖርም ያልባነነው ከጥልቅ ግንዛቤ እጥረት መሆኑን እረዳለሁ። ጥልቅ ግንዛቤ ዛሬ ባይኖረውም ነገ ይኖረዋል ብዬም አሥባለሁ። ጥቂት የማይባለውን የሀገሬ ሰው፣ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳይኖረውና ሀገራዊ ፍቅሩ እንዲሸረሸር ያደረገውም  ብልጭልጩ፣ “አርቴፊሻሉ” የምዕራብዊያኑ የኑሮ ዘይቤ በተለያየ መንገድ ወደ አእምሮው ሰርፆ በመግባት ህሊናውን ሥለተቆጣ ጠረው ነው ።ብዬም አምናለሁ።

የእኛን መልካም ና ሌላውን ዓለም የሚያሥተምር ቱባ ባህል ወደ ጎን ገፍተን ፣ ምእራቡ ዓለም፣የበለፀገበትን ጠንካራ የሥራ ዲሳፕሊን ሳይሆን መናኛ ባህሉን፣ሸቀጡን እና የእሱን ከንቱነት  አምላኪ ሆነን እንድንቀር  ጥቂት የማይባሉ ምሁራኖቻችን ፣በማጥመድ በጥቅምም በመያዝ ፣ የምእራብ ዲፕሎማቶች አደንዝዘዎቸው በዕውቀት የኮሰመነው ዜጋ ከእነርሱ ድንዛዜ እንዲኮርጅ አድርገዋል።…

አንዳአንድ ምሁራን፣ ሀገርን እና ህዝብን ለማገልገል ኃላፊነት ተሰጥቷቸው፣ ሰው መሆናቸውን በመዘንጋት ለታሪክ እና ለሀገር ብልፅግና ካልተጨነቁ ፤ እዛና እዚህ ሥልጣንን መከታ በማድረግ ሰውን ከሰው የሚያጋጩ ከሆነ ፣ሳይታወቃቸው በምእራቡ የቅንጦት ኑሮ ህሊናቸውን ካጡ ሀገር እየደኸየች መሄዶ እርግጥ ይሆናል ።

ይህ እውነት ነው። ይህንን እውነት የዛሬ  ባላሥልጣና ቶቻችንን እና የብዙሃኑን  አርሶ እና አርብቶ አደር እንዲሁም የሌላውን ጥሮ፣ግሮ ኗሪ   ኑሯ ማሥተያየት ብቻ በቂ ነው።

ከዚህ እውነት አንፃር፣  ሁሉም በለሥልጣን በተቆጣጠረው  የቴሌቪዢን መሥኮት የሚነገረውን ደጋግሞ በማሠብ ቢናገር መልካም ነው።  ነገ ይህንን ድሎትና ምቾት የሚያሣጣ ቁጣ ሣይመጣበት በፊት አንደበቱን ቢገራ መልካም ይመሥለኛል።እሥከመቼ ነው፣ኑሯችንን የሚያውቀውን ህዝብ በቴሌቪዥን መሥኮት ለመሸወድ የሐሰት ተርክት የምንፈጥረው??…

ከዚህ የቴሌቪዥን እውነት አኳያ፣ሥለ ተግራይ ህዝብ ደንታ የሌለውን፣ በማን አህሎኝነት በሞት ውሥጥም ምርጫ አካሂዳለሁ ያለውን፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን እንደምሳሌ መጥቀሥ ይቻላል ።

በቅድሚያ  የትግራይ ህዝብ ሥል፣ትግራይ ብለው ሰዎች ሥም ባወጡለት አካባቢ የሚኖር የሰው ስብስብ ነው። የትግራይ ሰው ሥል ደግሞ፣ ቀደም ሲል፣ ሰዎች ትግራይ ብለው በሰየሙት የኢትዮጵያ አሥተዳደራዊ ክልል የሚኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ፤ ማለቴ እንደሆነ እንድትገነዘቡልኝ እፈልጋለሁ።

የሌላውም የኢትዮጵያ ክልል ነዋሪ ወይም  ዜጋ በዚህ አግባብ ነው፣ሰው ከመሆን አኳያ መታየት ያለበት። የሚል እምነት አለኝ።

አውሮጳውያኑ በዝባዦች ለብዝበዛ እንዲያመቻቸው ፣ትላንት ባልሰለጠነው ዘመን የሸረቡልንን በቋንቋ የመከፋፈል ሴራ ፣ ዛሬ ጥቂት በሥልጣን አማካኝነት፣የማይገባቸውን ጥቅም፣ የሚያግበሰብሱ  ሆዳሞች ፣  ከተቀመጡበት የመበዝበዣ የሥልጣን ወንበር ላለምውረድ እና ፣ ዳግም ተመልሰው፣ በአዛኝ  መሣይ ቅቤ አንጓችነት እያላዘኑ፣  ሥልጣንን በህዝብ ሥም  ለመያዝ   ፣ “ቋንቋ ና ባህልህ አደጋ ላይ ሊወድቅ ነው …ከሃምሳ ዓመት በፊት የነበሩ፣ጨካኝ፣መሣፍንት እና መኳንንት እንሆ ዛሬ ፣መቃብር ፈንቅለው፣ከሙታን በመነሳት ሊገዙህ ነው።”በማለት የቅጥፈት ትርክት በመፍጠር  ፣ትርክቱንም በውሸት ፕሮፖጋንዳ በማጀብ ና  በማሥጮኽ …ህዝቡን፣ “ተነሥ!ታጠቅ!ተዋጋ!” ቢሉትም፣ሰው መሆኑን የሚገነዘበው ህዝብ በ’ጄ አላላቸውም።

በቋንቋው እንዳይናገር፣እንደይማር፣የየዕለት ሥራውን እንዳይሰራ፣እንዲሁም መንግሥታዊ አገልግሎቱ በራሱ ቋንቋ እንዳይሆን የሚሻ ኃይል እንደሌለ አሣምሮ በማወቁ ለጥሪያቸው ጆሮ ዳባ ልበሥ ነው ፤ ያላቸው።ይሁን እንጂ በእንጀራ አሥገዳጅነት  ፣ሌላ አማራጭ አጥቶ ነፍጥ ፣ታጥቆ የትዕዛዛቸው ፈፃሚ በሆነው ኃይል፣ እናገለግለዋለን የሚሉትን ህዝብ ሳይቀር ፣ እያሥፈራሩት እንደሆነ ይታወቃል።

በ ኢ/ፌ/ሪ የትግራይ ክልል መንግሥት ምክር ቤት ፣የህዝብን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ ፣በመወሰን ፣ዴሞክራሲያዊ ባልሆነ፣የህግ የበላይነት በሌለው፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይሁንታን ባላገኘ እና ተዓማኒ ባልሆነ ምርጫ ፣ለአምሥት ዓመት የሚቆይ ክልላዊ መንግሥት አቋቁማለሁ እያለ ነው።የክልሉ ምክር ቤት ይህንን  ውሣኔ የወሰነው በማንአህሎኝነት እንደሆነ የታወቃል።

በማንህሎኝነት፣”ከእኔ በላይ ነፋሥ ነው፣ማንአባቱ ይከለክለኛል?!ማን ወንድ ያሥቆመኛል !?” በማለት ከህግ በላይ ሆኖ ነው። በአንድ ሀገር ውሥጥ ምርጫን ለማካሄድ፣የምርጫ ቦርድ እንደሚያሥፈልግ እያወቀ፣ ልዩ ልዩ ምርጫ ነክ ተግባራት ማለትም፣ህዝቡ የሚመርጣቸው የፓለቲካ ፓርቲዎች ቅሥቀሳ፣በየአዳራሹ እና በየገበሬው ቀዬ፣እንደሚያሥፈልግና ግልፅ፣ፍትሃዊ፣ተአማኒ እና በገለልተኛ ታዛቢ የተረጋገጠ ምርጫ ማከናወን እንደሚገባ እየታወቀ፣የሀገሪቱን ምርጫ ቦርድ እንደሌለ በመቁጠር፣  “በራሴ ፣ለራሴ ምርጫ አካሂዳለሁ ።ብሎ እንደ አንድ ሉአላዊ መንግሥት  መወሰኑ፣ ለትግራይ ህዝብ ህይወትና ለዴሞክራሲያዊ መብቱ ደንታ ቢሥ መሆንኑ ያመለክታል።

ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ደንታ ቢሥ ከመሆንም ባሻገር፣ ” ራሴ  የውድድሩን ሜዳ መርጬ ፣ራሴ ብቼዬን ሮጬ ፣ ራሴ አሸንፌ ፣ራሴ የድል አክሊሉን ፣በራሴ ላይ በማድረግ አሸናፊነቴን አውጃለሁ።ምን ታመጣላችሁ !! “ማለትም ነው። ይህ ዓፄ በጉልበቱነትም ነው።

ይህንን ዓፄ በጉልበቱነት ደግሞ የትግራይ ህዝብ በዝምታ አያልፈውም።ትላንት ዛሬ አይደለምና ማንም፣ማንንም አይናችሁን ጨፍኑ እና ላሞኛችሁ ማለት ከቶም አይችልም። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፑብሊክ ህገመንግሥትም ይህንን ኢ-ህጋዊ አካሄድ አይፈቅድም።

1ኛ/ ህገመንግሥቱ በአንቀፅ 102 (1) ” በፌዴራልና በክልል የምርጫ ክልሎች ነፃና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኝነት እንዲያካሂድ ከማንኛውም ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል። ” እያለ ያለምርጫ ቦርድ እውቅና ህዝብን ለኮሮና አጋልጬ ምርጫ አካሂዳለሁ በማለት በመወሰኑ

2ኛ/ የኢትዮጵያ መንግሥት ፣በኮቪድ 19  አሥገዳጅነት የአሥቸኳይ ጋዜ አዋጅ በማወጁ ፣በዚህ አዋጅ አግባብ መሠረት በህገመንግሥቱ አንቀፅ 93 /4(ሀ)  “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ጊዜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣቸው ደንቦች መሰረት የሀገርን ሰላምና ሕልውና ፣ የሕዝብን ደህንነት ፣ ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥልጣን ይኖረዋል። ”

4(ለ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣን በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሰረታዊ የፖለቲካና የዴሞክራሲ መብቶች ን  ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘው ደረጃ ፣ እስከ ማገድ ሊደርስ የሚችል ነው።” ተብሎ የተጠቀሰው ተግባ ራዊ ይሆናልና!

ይህንን ህገ መንግሥታዊ ክልከላና አሥገዳጅነት የክልሉ ባለሥልጣኖች በንቀት ገፍተው  ፣በማንአህሎኝነት በህዝቡ ላይ በምርጫ ሥም፣ሞት ማወጃቸውን ከቀጠሉ ፣ በእርግጥም ኢትዮጵያን ለማተራመሥ እና የዋህ ህዝቦቿን እርስ በእርሳቸው ለማጫረስ በእቅድና በሥልት ለሚቀሳቀሱ ፀረ -ኢትዮጵያ ኃይሎች በባንዳነት ለማገልገል ቆርጠው ተነሥተዋል እና የትግራይ ህዝብ ከቶም በዝምታ አያልፍቸውም።እሥቲ፣  ያንን ኩሩው የትግራይ ህዝብ ያሠመረበትን የነፃነትያ የእኩልነቱ ማሳያን ቀይ መሥመር በመጣሥ ፣በመሣሪያ እያሥገደዱ ፣ ያለአንዳች ነፃ ምርጫ፣ያለአንዳች የመራጮች ምዝገባ፣ያለአንዳች ምርጫ  አሥፈፃሚ ፣ያለ አንዳች  ነፃ እና ገለልተኛ ታዛቢ ፣የለአንዳች ተቃዋሚ ፓርቲ የአደባባይ ቅሥቀሣ ፣ተዓማኒ ያልሆነ ምርጫ በጉልበታችን እናካሄዳለን ብለው ይነሱ ???

በበኩሌ በዚህ ወቅት፣ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ ወከባ መፍጠር ለሥልጣን እና ሥልጣን ለሚያሥገኘው ብዝበዛ ሲሉ አቦራ ማሥነሳት፣በግልፅ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጎን መሠለፍ ነው።ብዬ አምናለሁ።ትክክለኛ ዴሞክራቶች ከሆኑ ምን አሥቸኮላቸው?ነገም ሌላ ቀን ነው።በጊዜው ለመመረጥ ይደርሳሉ።ግን አላማቸው ምርጫ አይደለም። ዓላማቸው ሀገሪቱን ትርምስ ውሥጥ በመክተት ፣እንድትገነጣጠል ማድረግ ነው።ይህ ከሆነ ሃሳባቸው  “ባንዳ” የሚለው ሥም በትክክል ይገልፃቸዋል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop