
ተአማራ አካል አንጀት ተንጠልጥሎ እንደ ትል፣
ቆሻሻ እየሳበ የሚቋጥር መግል፣
ትርፍ አንጀት ብአዴን ገላውን የሚገል፡፡
ምግብ ውሀ ምጎ ምጥጥ አርጎ ደምን፣
ተሰውነት ወስዶ የሚቀልብ ጀርምን፣
የከሃዲ ቁንጩ ትርፍ አንጀት ብአዴን፡፡
ታናሽ ፍጡር ሆኖ ሆዱ ዘርጠጥ ያለው፣
ደንዳኔ ደልሎ አይን ምድር ሲያጎርሰው፣
በከርሱ ተገዝቶ እናቱን አጥፊ ነው፡፡
በመግል ነፍርቆ አብጦ ሲፈነዳ፣
በሰራ አካላት ውስጥ በታኝ ባክቴርያ፣
ብአዴን ትርፍ እንጀት የአማራ ዘር መጥፊያ፡፡
ተውሳክን ጎትቶ ተቤቱ ሲያስገባው፣
አብሮ እንደሚጠፋ ፍጹም የማይገባው፣
ትርፍ አንጀት ብአዴን ጭንቅላቱ ቅል ነው፡፡
ኢህዴን ብአዴን ብልጥግና እሚሉት፣
ሦስት ተውላጠ ሥም ለአማራ ትርፍ አንጀት፡፡
ሳጥናኤል አማራን ሊፈትን ሲቃጣው፣
ተእንግዴህ ልጅ እትብት ብአዴንን ሰራው፣
ትርፍ አንጀት አድርጎ በታምራት ላከው፡፡
ልክ እንደ ይሁዳ ዲናርም አሳየው፣
ወላጅ ዘመድህን ሕዝብህን ካድ አለው፡፡
ትርፍ አንጀት ብአዴን ህሊና የነሳው፣
ሰይጣን ያዘዘውን አንድ ባንድ ፈጠመው፣
ለጀርም ድልድይ ሆኖ የአማራን ዘር ፈጀው፡፡
ብአዴን ተይሁዳ እጅግ የሚከፋው፣
ፀጸት የማይገባው ድንጋይ መሆኑ ነው፡፡
ወልደው የማይጥሉት እሬሳ ሆኖበት፣
ተቸገረ አማራ በባዴን ትርፍ አንጀት፡፡
ተአምስት ዘመን ባንዳም እጅጉን የከፋ፣
ትርፍ አንጀት ብአዴን የአማራ በሽታ፣
ሲረገም የሚኖር ዓለም እስክጠፋ፡፡
ጣልያን በመርዝ በመድፍ ፍንክች ያላረገው፣
ትርፍ አንጀት ብአዴን አማራን አደማው፡፡
ተሽሽ ተጣብቆ እንደ በሬ መዥገር፣
አላሳርስ አለ አርበኛ ወቶ አደር፡፡
አማራ ቢፈወስ በቀዶ ጥገና፣
አርባ አመት ታጠቃው ትርፍ አንጀት በሽታ፣
ሁለት ጀምበር አይጠልቅ አጥቂን ድል ሲነሳ፡፡
በላይነህ አባተ
Abatebelai@yahoo.com
ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ ስምንት ዓ.ም.