ወገን ከወገን – ደም የሚያፋስስ፤
ህዝብ የሚያባላ – የሚያጫርስ፤
አምባ ገነን አሳሪ – ገዳይ ገራፊ፤
የሰብዓዊ መብት – ገፋፊ ፤
አገር_ ! እየዘረፈ – የሚያዘርፍ፤
ህዝብ በርሃብ – የሚያረግፍ፤
ጊዜው ናፈቀኝ – የማይበት፤
ተወግዶ የአምባ ገነን ሥርዓት፤
በአገሬ ! – ተወልጄ ባደኩባት ::
ጊዜ ሰጠኝ – ብሎ የሚጀነን፤
ውስተጠ ቀፎ – አምባነን፤
ያንን_ ግረፈው !
እሱን_ እሰረው !
ይህን_ ግደለው !
እነዚያን_ አሳዷቸው !
እነዚህን_ ግፏቸው !
እነሱን_ እሰሯቸው !
ብሎ የሚያዝ – የሌለበት፤
ዘበኛ_ ! ጠባቂ ያልቆመበት፤
ናፈቀኝ የማይበት – የተዘጋ ወህኒ ቤት ::
እነዚህ የእኛ ናቸው – አትንኳቸው !
እነዚያን ግፏቸው – አሳዷቸው !
እነሱን እርስ በርስ – አባሏቸው
እነዚህን ወህኒ ቤት – ክተቷቸው፤
ብሎ የሚያዝ – የሌለበት፤
ፍትህ ነግሣ – ታሳሪ የሌለበት፤
ቁልፉ ተወርውሮ – ክፍቱን የቀረ ወህኒ ቤት፤
ወህኒ ቤት ተዘግቶ – ሲሆን ት/ ቤት፤
ጊዜው ናፈቀኝ – የማይበት !!
በአገሬ_! በኢትዮጵያ መሬት ::
ሰብዓዊ መብታቸው ተገፎ፤ በአምባ ገነኑ የአብይ አህመድ ሥርዓት፤ በወህኔ ቤት ለሚሰቃዩ፤ የህሊና እስረኞች ወገኖቻችን፤ በማስታወሻነት የተቋጨች ::
ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. (15/07/2026)
ጊዜው ናፈቀኝ – የማይበት፤
የተዘጋ ወህኒ ቤት፤
::