አክሎግ ቢራራ (ዶር)
በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች እረገጣ ጉዳይ እየተባባሰ መሄዱ የሚያከራክር አይደለም። ሆኖም፤ በሌሎች አገሮች፤ ለምሳሌ በጋዛ፤ በዩክሬን፤ በሱዳን፤ በሚያንማር ውዘተ የሚካሄዱት እልቂቶች ዓለም አቀፍ የሜድያ ሽፋን ሲያገኙ የምእራብ ሜድያዎች፤ የምእራብ አገር መንግሥታት ባለሥልጣናት የኢትዮጵያን ብሄር እና እምነት ተኮር እልቂቶች ትኩረት አልሰጡትም። ብዙ ምክንያቶች አሉ፤ አንዱ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ለመስራት አለመቻላቸውና ዘገባዎች በአብዛኛው በአማርኛ ብቻ መሆናቸው ነው። ሌላው የአማራ ልሂቃንና ምሁራን አንድ ወጥ ተቋም ለመመስረትና በአድቮኬሲ ስራ ላይ ተከታታይነት ያለው ስራ አለመስራታቸው ነው ብለዋል።
ይህንን ክፍተት በመገንዘብ የGlobal Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) የምስርታ አባልና ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶር አክሎግ ቢራራ ከቦርዱና ከአቶ መስፍን መኮነን ጋር በመመካከር በአሜሪካ ኮንግሬስ የኬነዴ አዳራሽ ተብሎ በሚጠራው የሴናቶር ራሰል ህንጻ May 15, 2026 ጉባኤ ይካሄዳል።
የዚህ ጉባሄ አርስት፤ “በኢትዮጵያ የተከሰተው የሰብአዊ መብቶች ቀውስ ለኢትዮጵያና ለቀጠናው ሰላምና እርጋታ” አደጋ ፈጥሯል የሚል ሲሆን፤ ዋናዎቹ ተናጋሪዎች ፈረንጆች ናችው። ጉባኤው የሚካሄደው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው።
በዚህ ጉባኤ እንዲገኙ የተጋበዙት እንግዳዎች ጫና ፈጣሪዎች እንደሚሆኑ እንስባለን።
ዋናው ተናጋሪ ዶር ግሬጎሪ ስታንቶን፤ የታወቁ የሕግ ባለሞያ፤ ደራሲና የጀኖሳይድ ዎች መስራችና ፕሬዝደንት ናቸው። በተጨማሪ፤ የታወቁት ፎቶ ጆርናሊስት ጀማል ካውንተስ በኢትዮጵያ በአማራ ሕዝብ ላይ የተካሄደውን እልቂት በፎቶግራፍና ቪዲዮ ለአለም ሕዝብ ያቀረቡት ናቸው። ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብ አውዊ መብት ተቋማት፤ አምኔስትሪ ኢንተርናሺናል፤ ለምኬን ኢንስቲቲትና ጀኖሳይ ወች ተጋብዘው በልዩ ልዩ ምክንያት ለመሳተፍ አልቻሉም።
ዶር አክሎግ ቢራራ ይህ ጉባሄ ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገባቸውን ተቋማዊ፤ መዋቅራዊና ተዛማጅ አደጋዎችን መረጃዎችን እየጠቀሱ ያቀርባሉ። ትኩረት የሚያደርጉት በኢትዮጵያ በተከታታይ ለአምሳ አመታታ፤ በተልይ በኢህአዴግ ኦህዴድ ብልጽግና ዘመነ መንግሥት በመካሄድ ላይ ያለውን የሜዘገንን የጦርነት አባዜ፤ እልቂትና ውድመት ለሰላም፤ ለአብሮነትና ለእርጋታ ጸር መሆኑን አስረግጦ ማስረዳአት ላይ እንደሚሆን ነግረውናል። ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ፤ ለምስራቅ አፍሪካና ለመካከለኛው ምስራቅ ሁከት ፈጣሪ ይሆናል ይላሉ።
የኤፓክ ፕሬዝደነት አቶ መስፍን ተገኑ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ምክር ቤት ስለኢትዮጵያ የመብቶች ጥሰት የቀረበውን H.Res.937 – Condemning the Government of Ethiopia for actions that threaten regional stability, violate fundamental human rights, and undermine the strategic interests of the United States in the Horn of Africa ተብሎ የሚጠራው ህግ ሆኖ ከተላለፈ በጦር ወንጀለኞች፤ በሰብአዊ መብት እልቂቶችና በሴቶች ድፍረት ላይ ወንጀል የፈጸሙትን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሕግ የሚያስጠይቅ ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረግ ምክር ቤቱ እንዲያጸድቀው ምክር ያቀርባሉ።
በመጨረሻ፤ መስፍን መኮነን የጉዳዩን አሳሳቢነትና በኢትዮጵያ የብሄር ፌደራሊዝም ተሻሽሎ ወይንም ተለውጦ ሌላ ኢትዮጵያን የሚመጥን ህገ መንግሥት እንዲዘጋጅ ጥሪ ያደርጋሉ።
ጉባኤው ክፍት ሆኖ ሁሉም ተናጋሪዎች በእንግሊዝኛ እንዲያቀርቡና ዘገባው ለመላው የዓለም ሕብዝብ እንዲሰራጭ ጥረት እንደሚደረግ አክሎግ ቢራራ ለጣና ቴሌቢዢን ገልጸዋል። ይህ መል እከት በተደጋጋሚ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ አሳስበዋል።
April 21, 2025