ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም./July 3, 2025
አረመኔው አብይ አህመድ ፋኖን ከመስከረም በፊት አጠፋለሁ ብሎ “ዘመቻ ማዕበል” በሚል ስያሜ በአማራ ህዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፍቷል። እንዳለፉት ዘመቻዎች ሁሉ ወደ ጎጃም ቀጠና ብዛት ያለው ሰራዊት በአራት አቅጣጫ ያስገባ ሲሆን በአራቱም ቀጠናዎች በጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋ እና ጎጃም መጠነ ሰፊ ውጊያ ከፍቷል። ይህ ከመስከረም በፊት ፋኖን አጠፋዋለሁ የሚለው ዘመቻ ከሁለት አመት በፊት በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመው ወረራ እና ሴራ አካል ነው። አማራን አጠፋለሁ ብሎ
በዕቅድ ወረራውን መጀመሩን ድፍን አማራ የሚያውቀው ቢሆንም ከፈረሱ አፍ እንደሚባለው ከፍተኛ የኦሆዴድ/የኦሮሞ ብልፅግና አመራር የነበሩት አቶ ታየ ደንደአ እና ዶክተር ሚልኬሳ ሚዳጋ በጆሯቸው የሰሙትን ታሪካዊ ምስክርነት በተለያዩ ሚዲያወች በመቅረብ መስጠታቸው የሚያረጋግጠው አብይ አህመድ አማራን የማጥፋት ፕሮጀክት ዋና መሪ በመሆን የዘር ማጥፋት(genocide) የፈፀመና እየፈፀመ መሆኑን ነው። አቶ ታየ ደንዳአ “እኔ የታገልሁት ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እኩልነት እና ፍትህ እንዲያገኝ እንጂ አማራን ለማጥፋት አይደለም፣ አማራም እንዲጠፋ አልፈልግም” በማለት ታሪካዊና ሂትለርን ለሚያስንቀው አብይ አህመድ አስደማሚ መልስ ሲሰጡት አብይ አህመድ በወቅቱ እንደደነገጠ ከቃለ ምልልሳቸው ተረድተናል።
እንደዚሁም የሰሜን ዕዝን በሴራ እንዲመታ በማድረግ ትግራይ ላይ የተከፈተውን ጦርነት አብይ አህመድ ራሱ እንዳስጀመረው ብሎም አማራው እንዲጠፋ ሆን ብሎ ሰራዊቱ እንዲያፈገፍግ እያዘዘ የአማራ ህዝብ በህወኃት ወራሪ ኃይል መጠነ ሰፊ ዕልቂትና ውድመት እንዲደርስበት ሆን ብሎ ያደረገ መሆኑን 2,500 ለሚሆኑ የኦሮሞ የፓለቲካ አመራሮች በይፋ በስብሰባ መናገሩን መስክረዋል። ይህን ተግባር የፈፀመው አማራን ለማጥፋት ብቻ ሳይሆን የሰሜን ህዝብ የሚለውን ለማጥፋት ብሎም ለማዳከም እንዲሁም የአማራና የትግራይ ህዝብ የዘላለም ጠላት እንዲሆኑ በማቀድ ሆን ብሎ እንዳደረገው ለተሰብሳቢው አስረግጦ መናገሩን አስረድተዋል። አቶ ታየ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ይህንን የአብይ አህመድን በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመውን እና እየፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለህዝብ ይፋ እንዲሆን በቃለ መጠየቅ ይፋ ማድረጋቸውና ለኢትዮጵያ ህዝብም እንዲደርስ በማድረጋቸው የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አድናቆትና ክብር እየሰጣቸው ይገኛል። ለጨፍጫፊወችም ግዙፍ የሆነውን ወንጀላቸውን በማጋለጥ ከፍትህ እና ከእውነት ጋር በመቆም አርያነታቸውን ያሳዩ ሲሆን ጨፍጫፊውና አረመኔው አብይ አህመድ አቶ ታየ ደንዳአን በድጋሜ ለእስር ስላደረጋቸው ህዝቡ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል።
ዶ/ር ሚልኬሳ ሚዳጋም አቶ ታየ ደንዳአ ይፋ ያደረጓቸውን ምስክርነቶች እውነተኛነት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን አብይ አህመድ በአማራ ህዝብ ላይ ባለው ጥላቻ አማራውን ለማጥፋት ባለው እቅድ በደህንነት መስሪያ ቤቱ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመቶወች የሚቆጠሩ አማሮችና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ምዕመናን በአርሲና በሻሸመኔ እንደተጨፈጨፉ በሚገባ አስረድተዋል። እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የተፈፀሙ ጭፍጭፋወችና ግድያወች በአብይ አህመድና በሺመልስ አብዲሳ ትዕዛዝ የተፈፀሙ መሆናቸውን መስክረዋል። አቶ ጀዋር መሀመድ እና ዶክተር ገዱ አንዳርጋቸውም አብይ አህመድ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የያዘውን እቅድ እና የፈፀማቸውን ወንጀሎች አንድ በአንድ እያጋለጡ ይገኛሉ።
በአሁኑ ሰዓት “ዘመቻ ማዕበል” በሚል ፋኖን እስከ መስከረም አጠፋለሁ በሚል የሚያደርገው ዘመቻ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ብሎም በርሃብ እንዲያልቅ ለማድረግ የታቀደ መሆኑ ግልፅ ነው። የአማራ ገበሬ ድፍን አመት የለፋበትን እርሻ በዘር የሚሸፍንበትን ወቅት በመምረጥ መጠነ ሰፊ ወረራ እያደረገ መሆኑ አብይ አህመድ ምንኛ እኩይ ፍጡር መሆኑን ያረጋግጣል።
አማራ ሲተርት “አንድ ሰኔ የነቀለውን ዘጠኝ ሰኔ አይተክለውም” ይላል። ለንፅፅር ያህል ከዚህ ቀደም የትግሬን እና አማራን ህዝብ ለማጥፋት ባደረገው ጦርነት ወቅት ሰራዊቱን ከትግራይ ወደ አማራ ክልል ያስገባሁት የትግራይ ህዝብ የጥሞና ጊዜ እንዲያገኝ እና እንዲሁም ገበሬው ዘር እንዲዘራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ነው ማለቱን እናስታውሳለን። ይህ የክረምት ወረራ ምን ያህል የተናገረውን የማይኖር ቀጣፊ ብሎም ዘረ-ፈጅ ፍጡር እንደሆነ ይመስክራል።
ፋኖ ከህዝብ አብራክ የወጣ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል መሪ በመሆኑ ፋኖን አጠፋለሁ ማለት የአማራን ህዝብ አጠፋለሁ ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህ የአብይ አህመድ አማራን አጠፋለሁ በሚል የከፈተው ዘመቻ ወይም የቁም ቅዠት ተቀልብሶ