ማንኛውም ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ባለኝ የሚሊተሪ ኃይልና የተወሳሰበ የጦር መሳሪያ ሌላውን አንበረክካለሁ የሚል አርቆ-አሳቢነት የጎደለው የመጋፋትና ሌሎችን አሳንሶ የማየት የውጭ ፖለቲካ የሚያሰከትለው አደጋ!!
ወንድሜ እኮ ነው! አ ይ ከ ብ ደ ኝ ም :: ትርጉም ነቢዩ ተክሌ March 6, 2022 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ታሪክ በጃፖን አገር የሆነ እውነተኛ ክስተት ነው :: ልጁ በጃፓን በጦርነቱ ወቅት : የሞተውን ወንድሙን በጀርባው አዝሎ አብሮት ካለው ወታደር ጋር ረዥም የእግር ጉዞ ያደርግ ነበር:: ወታደሩ ክስተቱን አስተውሎ ልጁን በጉዞው እንዳይዝልበት በማሰብ በቃ “ወንድምህ ሟቷል : ቅብረውና ጉዟችንን እንቀጥል” ብሎ ይጠይቀዋል :: ልጁም መልሶ ወንድሜ እኮ ነው! ለእኔ አይከብደኝም ሲል መለሰለት:: ወታደሩም ልጁ ለወንድሙ ያለውን እውነተኛ ፍቅር ተመልክቶ እንባውን አፈሰሰ።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ምስል በጃፓን አገር የአንድነት ምልክት ሆኖ ይኖራል:: ምንም እንኳንታሪኩ በጃፓን አገር የሆነ ቢሆንም :የዚህ ፎቶ እውነተኛ ታሪክ ለእኛም የወንድማማችነትና የእህታማማችነት እውነተኛ ፍቅር ምልክት ነው! “ወንድምህ ለአንተ አይከብድህም ምክንያቱም ወንድምህ ነውና… እህትህም ለአንተ አትከብድህም እህትህ ናትና:: ከዚህ እውነት ውጭ ተፈጥሮአዊ አይደለም ስለዚህ:- ቢወድቅ አንሳው:: ቢደክም ደግፈው:: ቢቸግረው እርዳው:: ፍትህ ቢነፈግ ስለፍትህ ድምጽ ሁንለት:: እርሱን በመሸከም ድከም:: እርሱን ለመደገፍ ጥረት አድርግ:: ስህተት ቢያደርግ ይቅር በለው:: ቢስት መልሰው ! ሰዎች ጀርባቸውን ቢያዞሩበት አንተ ግን በጅርባህ ተሸከመው :: ለአንተ አይከብድህም :ወንድምህ ነውና :: ይህን በማድረግ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማለህ!! Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story ሰበር የደስታ ዜና 7ግዜ ጠርምሶ የወጣ ጀግና – እንኳንም አተረፈህ Next Story ብልጽግና እና ስርዓታዊ ሽብርተኝነት-ገለታው ዘለቀ
ማንኛውም ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ባለኝ የሚሊተሪ ኃይልና የተወሳሰበ የጦር መሳሪያ ሌላውን አንበረክካለሁ የሚል አርቆ-አሳቢነት የጎደለው የመጋፋትና ሌሎችን አሳንሶ የማየት የውጭ ፖለቲካ የሚያሰከትለው አደጋ!!