በግል ስብዕናዬም፣ እንደሰላማዊ ታጋይም፣ በሃይማኖት ፣ በባህል ተጽዕኖ ውስጥ እንዳለ ሰው በድርድር፣ በንግግር፣ በውይይት፣ በይቅርታ፣ በምህረት … አምናለሁ ። እነዚህ ሁሉ እሴቶቼ ቢሆኑም ግን ለሁሉም ነገር ወግ አለው ባይ ነኝ ። የተመረጠ መንግሥት፣ የሕዝብ ውክልና ያለው ገለመለ የሚባለውን ድስኩር እንዳልሰማ ፈጣሪዬን እየተማፀንኩ፤ አንተ ጥቁር ሕዝብ ሆይ! በተለመደው ሆደ ሰፍነትህ፣ መከራ ባጎመጠው ጫንቃህ ሕወሓትን
#ይቅርታ ለመጠየቅ ተዘጋጅ ። አሁንም የጠየቁትን ለመስጠት እጅህ አይሳሳ¡ ሌላ ምርጫ የለንምና ።