
የጀግንነትና የነጻነት ተምሳሌት አገር ኢትዮጵያ! በየጊዜው ዓለምን የሚያስደምም ጀብዱ የሚፈጽሙ ጀግኖችን መፍጠር መታወቂያዋ ነው። ልጆቿ ለሀገራቸው ህልውና መስዋዕት መክፈልን እንደጽድቅ ይቆጥሩታል። በጠላት መረገጥን አምርረው ይጠየፋሉ። በጠላት ከመገዛት ሕይወታቸውን ቢያጡ ይሻሉ። ይህ በታሪክ ቅብብሎሽ የታየ ሃቅ ነው።
ዛሬም አሸባሪው ትህነግ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር በአማራና አፋር ክልሎች መጠነ ሰፊ ወረራዎችን መፈጸሙ ያንገበገባቸው በርካቶች ናቸው። ይህንን ወረራ ለመመከት በየጦር ግንባሮቹ የገቡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ድንቅ ጀብዱ እየፈጸሙ ይገኛል።
በጋሸና ግንባር የተሰለፈው ጀግናው ወጣት ታድሶ ኃይሌ ልሳነወርቅ ጀብድ ከፈጸሙ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው። እድሜው በ20ዎቹ መጀመሪያ የሚገኘው ጀግና በመቂት ወረዳ የገረገራ ከተማ ነዋሪ ነው። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትም ወጣቱ ስለሰራው ጀብዱ ጠየቀው። ጀግናው በቁጥብ አንደበቱ ስለተፈጠረው ሁኔታ አጫወተን።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠላትን ከደብረ ዘቢጥ እስከ ኮኪት እና ፍላቂት ሲያባርረው እግሬ አውጭኝ ያለው የሽብር ቡድኑ በጋሸና ግንባር አርቢት ላይ አደገኛ ምሽግ በመሥራት ተቀመጠ። ምሽግ ሰርቶ ዙሪያውን በፈንጅ አጠረ። ወጣት ታድሶና የሰፈር ጓደኞቹ ከመከላከያ ጎን በመሰለፍ መስዋዕትነት ለመክፈል ስምምነት ማድረጋቸውን አይዘነጋውም።
አካባቢህን ጠብቅ
ወደ ግንባር ዝመት
ሠራዊቱን ደግፍ
EBC