
- ወልቃይት እና ራያ ከጦርነቱ በፊት በነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ፣
- በትግራይ የተደረገውን ምርጫ መንግሥት እውቅና እንዲሰ ፣
- በፌደራል መንግሥቱ ተመጣጣኝ የሥልጣን ቦታ እንዲያገኝና በ-2020 በትግራይ የተመረጡት የክልል ተመራጮች በፌደራሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገቡ ከሆነ ፣
- በከፍተኛ የሚኒስቴር ቦታ የሥልጣን መጋራት ከተሰጠን ፣
- ለትግራይ ይሰጥ የነበረውን የአስር ቢሊዮን በጀት ከተለቀቀ ፣
- በመከላከያ ሠራዊት ለደረሰብን ኪሳራ መንግሥት ካሳ የሚሰጠንና የትግራይን ህዝብ ይቅርታ የሚጠይቅ ከሆነ ፣
- በእሥር ላይ የሚገኙ የትግራይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ሌሎችም ከእስር ከተለቀቁ እንዲሁም ካሳ የሚከፈላቸው ከሆነ ፣
- ድርድሩ በትክክል እስኪተገበር ድረስ ዋስትና ሊሆነን ይችል ዘንድ አሁን በያዝነው የአማራ ክልል ለአንድ ዓመት መቆየት የምንችልበት እውቅና ከተሰጠን
- የኢትዮጵያ መንግሥት በህወሓት ላይ የተመሠረተው ክስ እንዲቋረጥ እና ለቀጣዩም በህወሓት ባለሥልጣናት ዘንድ ክስ የማያነሳ ከሆነ ፣
- በሁመራ የተወሰደብን የሰሊጥ መሬት እንዲመለስልንና የተወሰደብን የሰሊጥ ምርት ካሳ የሚከፈለን ከሆነ ፣
- ህወሓት እንደሌላው ክልል ለሠራዊታችን ትጥቅ እንዲፈቀድለት እና አሁን የያዘውንም ትጥቅ እውቅና የሚሰጠን ከሆነና ዓቢይ ሥልጣን የሚለቅ ከሆነ ፣
ባጭሩ የማይታመን ቢመስልም የመደራደሪያ ዋና ዋና ነጥቦች እነዚህ ናቸው ።
ጉዱ ካሳ